YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ይህ በአዲስ አበባ ውስጥ ኮልፌ ቀራንዮ ልዩ ስሙ #ካራቆሬ የሰፈሩ ወጣቶች ከአካባቢው ባለሱቆች እና የታክሲ ተራ አስከባሪዎች ጋር፡በመተባበር ለአካባቢው ነዋሪ የእጅ ማስታጠብ እና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየሰሩ ነው።

- በርቱ 👍👍

@YeneTube @FikerAssefa
የአውሮፓ ህብረት የአውሮፓ መሪዎች አስፈላጊ ያልሆነ ጉዞ ወደ አውሮፓ ህብረት ለ 30 ቀናት አግደውታል ፡:

- CNN
@Yenetube @FikerAssefa
በአፋጣኝ ይተግበር!! የግዜ መቆጣጠሪያ የአሻራ ማሽኖችን የመንግስትም ሆነ የግል መስሪያ ቤቶች መጠቀም ማቆም አለባቸው።
#ሼር
@Yenetube @FikerAssefa
የጀርመኑ ፖለቲከኛ ቻንስለር ዕጩ ፍሬደሪክ ሜርዝ ለኮሮኔቫቫይራል በሽታ እንደተገኘባቸው ቃል አቀባዩ ለሲኤን.ኤን አስታውቀዋል፡፡

Via:-CNN
@Yenetube @Fikerassefa
በረራ ያቆሙ ሀገራት ⬇️

አሜሪካ ፣ አውስትራሊያ ፣ ካምቦዲያ: ካናዳ ፣ ኬፕ ቨርዴ: - ቻይና ፣ ኮሎምቢያ: ቼክ ሪፐብሊክ: ግብፅ ፣ ጀርመን ፣ ሄይቲ: - ሆንግ ኮንግ ፣ ሃንጋሪ: ህንድ: ጃፓን ፣ ማሌዥያ ፣ ሞሮኮ: - ኒው ዚላንድ ፣ ፔሩ: ፊሊፒንስ: ሩሲያ ፣ ሳውዲ አረቢያ ደቡብ ኮሪያ ፣ ስፔን ሲሪላንካ ቦሊቪያ: ታይላንድ: ቱርክ: ቬትናም ፣ ዩክሬን።

@Yenetube @Fikerassefa
በኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ቁጥር 200,000 ማለፉ ተሰምቷል።

- እጃችሁን ለከ 30 - 40 sec በደንብ ታጠቡ

- ባልታጠበ እጃችሁ አይን : አፍንጫ : ጆሮ አትነካኩ

- እነዚህ ከተገበራችሁ የቫይረሱን ስርጭት መግታት እንችላለን።
@Yenetube @Fikerassefa
በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎቶቹን ላልተወሰነ ጊዜ በፖስታ ብቻ እንደሚሰጥ አስታወቀ። በአካል ወደ ፅህፈት ቤቱ የሚያመሩ አስቀድመው በስልክ ቀጠሮ መያዝ እንዳለባቸው አሳስቧል።

Via:- Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
የጣሊያን ፖሊስ የኮሮና ቫይረስ ረድቶት ሲያሳድደው የነበረን የማፊያ የተደራጀ የወንጀል ቡድን መሪ መያዝ ችሏል፡፡

የሎክሪው ድራንጋታ የማፊያ ቡድን መሪ ሴዳር ኮዲ ካለፈው ነሐሴ ጀምሮ በፖሊስ ቢፈለግ ቢታሰስ አልጨበጥ ብሎ ቆየ፡፡

ከስፍራ ስፍራ እየቀያየረ አልያዝ አለ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተቀሰቀሰ ጊዜ የማፊያ አለቃውም ከስፍራ ሰፍራ መዘዋወሩን ትቶ በአንድ ቦታ ለመወሰን ተገደደ፡፡

የኮሮና ቫይረስ መንቀሳቀሻ እንዳሳጣው ፖሊሶች ከተደበቀበት ደርሰው አፈፍ እንዳደረጉት የፃፈው AFP ነው፡፡

#ShegerWerewoch
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት የአዲስ አበባው የፋሲካ ኤክስፓና ባዛር መክፈቻ ለሳምንት ተራዝሟል

ሴንቸሪ ፕሮሞሽን በ29 ሚልየን ብር ጨረታ ያሸነፈበትና በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማእከልና የገበያ ልማት ድርጅት ላይ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና ሲል የነበረበት የፊታችን መጋቢት18 ተከፍቶ እሰከ ፋሲካ ዋዜማ ድረስ ሊካሂድ የነበረው “አዲስ ኤክስፓ 2020” ኤክስፓና ባዛር መክፈቻ ለአንድ ሳምንት መራዘሙን አዘጋጆቹ ለፊደል ፖስት ገልፀዋል።
የሴንቸሪ ፕሮሞሽን ፕሮጀክት ሀላፊ ወይዘሪት እድላዊት ዘውገ ለፊደል ፖስት እንደገለፀችው ኤክስፓው መክፈቻ ማራዘም ያስፈለገበት ምክንያት ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ተመሳሳይ ነገር በመንግስት በመወሰዱ ነው ።
” ባዛርና ኤክስፓ ሰው የሚበዛበት ነው ።የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንዲህ አይነት ነገር ማከናወን ተጋላጭነትን ያመጣል።

እኛም በአሁን ሰአት ይሄን ማድረግ አንፈልግም ።”
”የቫይረሱ ስርጭት ቆሞ ነገሮች መልካም ከሆኑና መንግስት ቀጥሉ ካለን ኤክስፓውን መጋቢት 25 ጀምረን እሰከ ዳግማዊ ትንሳኤ ድረስ እናከናውናለን ።ካልሆነም በየወቅቱ የደረሰንበትን አቋም ለነጋዴውና ለህብረተሰቡ እናሳውቃለን ” ብላለች ።
በብዙ መቶ ሺ ሰዉ ይጎበኘዋል ተብሎ የሚጠበቀው ኤክስፓ 450 የሚጠጉ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

via:- Fidelpost.com
@YeneTube @Fikerassefa
Ethiotelecom ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 444 አጭር የስልክ ቁጥር ይፋ አድርጓል።
@Yenetube @Fikerassefa
ጁቡቲ የመጀመሪያውም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን #ዛሬ ይፋ አድርጋለች። በኮሬና ቫይረስ ተጠቂው የስፔን ዜጋ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ወደ ጁቡቲ ማርች 14 እንደገባም ተገልጷል። ግለሰቡ ክትትል እየተደረገለት ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
እውነት ነው!!
አሁን አቶ የሺንጉስ በለጠ ጋር ድውለን #አረጋግጣናል የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የሚከተለውን ፅሁፍ አንብቡት የምታሟሉ ሄዳችሁ ወሰዱ

እድሜያቸው ከ 48 አመት በላይ ለሆናቸው ጎልማሶችና አቅመ ደካሞች እንዲሁም ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤ ድርጅታችን ከኮረና ቫይረስ በሽታ ጋር በተያያዘ በሐዋሳ በሚገኘው ጊዜው የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች አስመጪና ጅምላ አከፋፋይ:-

1. Face Mask
2. Alchol
3. Examination Glove በነፃ የሚያቀርብ መሆኑን ስንገልፅ በነፃ እንኳን ለመስጠት የማንችል ተገቢና ማስተዋል በበዛበት መንገድ ተደራሽ ለማድረግ ሁላችንም ያለብንን ሀላፊነት በማስታወስ መሆኑን እንገልፃለን።
የደሀ ሀገር መከታውና ተስፋው አምላኩ ነውና ሁላችንም ወደ ፈጣሪያችን መፀለይን ተቀዳሚ ተግባራችን እናድርግ።

ፈጣሪ ሀገራችንን ከክፋ ነገር ሁሉ ይጠብቅልን።
#የሺንጉስ በለጠ

አድራሻ ሐዋሳ ሞቢል ሰፈር የቀድሞ ሸዋበር ሆቴል አጠገብ
ስልክ +2519 13066471/910525153/941414158

#ሼር_እናመሰግናለን!!
ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ተረጋገጠ

ኢትዮጵያዊያኑ እዚያው ጣሊያን ውስጥ በበሽታው ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ያናገራቸው የውጪ ጉዳይ ምንጮች አረጋግጠዋል።

በወርርሽኙ የሞቱት ሁለቱም ሰዎች ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የነበረ ወንድና ሴት ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ የታወቀ ሲሆን አንደኛው ለረጅም ዓመታት ጣሊያን ውስጥ የኖሩ መሆናቸውም ቢቢሲ ለመረዳት ችሏል።

ሁለተኛዋ ሟች መቼ ወደ ጣሊያን እንደሄዱ በትክክል ባይገለጽም ቤተሰብ ለመጎብኘት ወደ ጣሊያን በመሄድ እዚያው የቆዩ እናት እንደሆኑ ታውቋል። ሁለቱም ሟቾች ህመሙ ከታየባቸው በኋላ አስፈላጊውን የህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደቆዩና በመጨረሻም ለህልፈት መብቃታቸው ተገልጿል።

ባለሙያዎች እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ በሽታ በእድሜ በገፉና ሌሎች የቆዩ የጤና ችግሮች ባሉባቸው ሰዎች ላይ እስከ ሞት የሚያደርስ ከባድ ጉዳትን ያስከትላል።

ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው እንዳለፈ የተነገረው ሁለቱ የኢትዮጵያዊያንም ሞት የተፋጠነው ቀደም ባለ የጤና ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሎ ተጠርጥሯል።

Via:- ቢቢሲ አማርኛ
@Yenetube @Fikerassefa
WHO COVID19 ብሎ የሰየመውን አዲሱን አለምን እያመሰ ያለው ቫይረስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይና ቫይረስ በማለት በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
-70 የተማሪ ባሶች ተጨምረዋል

በመዲናዋ የትራስፖርት እጥረት እንዳይፈጠር በሚል 70 ሸገር የተማሪዎች ሰርቪስ ወደ ትራስፖርት ዘርፉ እንዲቀላቀል መደረጉን ቢሮው ለኢትይ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#ኬንያ_ለግብፅ_ደገፈች የሚለው ዜና ውሸት ነው

አምባሳደር መለስ ዓለም የአል-አህራም “ዘገባ ፍፁም ውሸት ነው” በማለት ለአሻም ቲቪ ተናገሩ

አል-አህራም፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ፤ ኬንያ የግብፅን “መልካም” አቋም ትደግፋለች ሲሉ በስልክ ለአብድል ፋታህ አል-ሲሲ ተናግረዋል በማለት የዘገበውን፣ በኬንያ የኢፌዲሪ አምባሳደር መለስ ዓለም ዘገባው ‹ፍፁም ውሸት እና የግብፅ ማደናገሪያ ፕሮፖጋንዳ ነው› ሲሉ ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓም ለአሻም ቲቪ ገልፀዋል፡፡

አል-አህራም ትናነት እንዳወጣው ዘገባ፤ ግብፅ በመግለጫዋ ኬንያታ “የግብፅ አቋም ‹ከቅን ፍላጎት› የመነጨ ነው” ሲሉ ተናግረዋል በማለት ገልጾ ነበር፡፡

አምባሳደር መለስ በተጨማሪም፣ የግብፅ ሚዲያዎች ከቀናት በፊት ጥቂት ግብፃውያን የተሰበሰቡበት ፎቶ በመለጠፍ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግብፅን ደገፉ በሚል የሀሰት ዜና ማሰራጨታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ወደ ኬንያ አቅንተው ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካውያን አለመግባባቶች በአፍሪካውያን መፈታት እንዳለባቸው የሚያምኑበት መሆኑን ያረጋገጡላቸው ሲሆን ይኸውም በፕሬዝዳንቱ የፌስቡክ ገፅ ላይ እንደሚገኝ አምባሳደር መለስ አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ያላትን አቋም ለማስረዳት ወደ ተለያዩ ሀገራት የልዑካን ቡድኖችን ልካለች፡፡ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴም ወደ ኬንያ አቅንተው ነበር፡፡ በንግግራቸው ላይም የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ የአባይን ወንዝ በተመለከተ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ ክፍፍል መኖር አለበት ሲሉ ተናግረው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ከኬንያ በተጨማሪም ወደ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ በመጓዝ ከሀገራቱ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተገናኝተው ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ያላትን አቋም ማስረዳታቸውና ፕሬዝዳንቶቹም ለኢትዮጵያ ያላችውን ድጋፍ መግለጻቸው ይታወቃል።

Via:- Spokeman office
@Yenetube @Fikerassefa
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ቡርኪነፋሶ ላይ ዛሬ የመጀመሪያ ሞተ ተመዝግቧል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሰብ ሰሀራን ላይ ሰው ሲሞት የመጀመሪያ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን የሚከታተል ግብረ ሃይል ተቋቋመ።

@Yenetube @Fikerassefa
#የኮሮና ማከሚያ መድሀኒት

በጃፓን የተመረተው መድሀኒት ለኮሮና ቫይረስ ውጤታማ መድሀኒት ሆኖ አግኝቼዋለሁ ስትል ቻይና ገለጸች፡፡

ዘጋርዲያን በዘገባው እንዳመለከተው አዲስ የጉንፋን ዝርያ ያለውን በሽታ ለማከም ጃፓን የምትጠቀመው መድሀኒት የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለማከም ውጤታማ መሆኑን የቻይና ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ በጃፓን ፋጂ ፊልም የተመረተው “ፋቪፒራቪር” የተሰኘው መድሀኒት በሁዋንና ሼንዜን ከተሞች በ340 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ላይ ተሞክሮ ጥሩ ውጤት መታየቱ ተገልጿል፡፡

የጃፓን ብሄራዊ ቴሌቪዥን NHK የሚኒስትሩን መረጃ ጠቅሶ እንደዘገበው የኮሮና ቫይረስ የነበረባቸው ሰዎች መድሀኒቱ ከተሰጣቸው ከቀናት በኋላ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ታውቋል፡፡

Via:- EBS
@Yenetube @Fikerassefa
የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለሚቀጥሉት 2 ሳምንታት "የዕሁድ አምልኮ ባይኖር" ስትል አሳሰበች።
@Yenetube @Fikerassefa