YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ኬንያ_ለግብፅ_ደገፈች የሚለው ዜና ውሸት ነው

አምባሳደር መለስ ዓለም የአል-አህራም “ዘገባ ፍፁም ውሸት ነው” በማለት ለአሻም ቲቪ ተናገሩ

አል-አህራም፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ፤ ኬንያ የግብፅን “መልካም” አቋም ትደግፋለች ሲሉ በስልክ ለአብድል ፋታህ አል-ሲሲ ተናግረዋል በማለት የዘገበውን፣ በኬንያ የኢፌዲሪ አምባሳደር መለስ ዓለም ዘገባው ‹ፍፁም ውሸት እና የግብፅ ማደናገሪያ ፕሮፖጋንዳ ነው› ሲሉ ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓም ለአሻም ቲቪ ገልፀዋል፡፡

አል-አህራም ትናነት እንዳወጣው ዘገባ፤ ግብፅ በመግለጫዋ ኬንያታ “የግብፅ አቋም ‹ከቅን ፍላጎት› የመነጨ ነው” ሲሉ ተናግረዋል በማለት ገልጾ ነበር፡፡

አምባሳደር መለስ በተጨማሪም፣ የግብፅ ሚዲያዎች ከቀናት በፊት ጥቂት ግብፃውያን የተሰበሰቡበት ፎቶ በመለጠፍ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግብፅን ደገፉ በሚል የሀሰት ዜና ማሰራጨታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ወደ ኬንያ አቅንተው ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካውያን አለመግባባቶች በአፍሪካውያን መፈታት እንዳለባቸው የሚያምኑበት መሆኑን ያረጋገጡላቸው ሲሆን ይኸውም በፕሬዝዳንቱ የፌስቡክ ገፅ ላይ እንደሚገኝ አምባሳደር መለስ አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ያላትን አቋም ለማስረዳት ወደ ተለያዩ ሀገራት የልዑካን ቡድኖችን ልካለች፡፡ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴም ወደ ኬንያ አቅንተው ነበር፡፡ በንግግራቸው ላይም የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ የአባይን ወንዝ በተመለከተ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ ክፍፍል መኖር አለበት ሲሉ ተናግረው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ከኬንያ በተጨማሪም ወደ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ በመጓዝ ከሀገራቱ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተገናኝተው ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ያላትን አቋም ማስረዳታቸውና ፕሬዝዳንቶቹም ለኢትዮጵያ ያላችውን ድጋፍ መግለጻቸው ይታወቃል።

Via:- Spokeman office
@Yenetube @Fikerassefa