YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በ#ሐረር ከተማ እየተስተዋለ ያለው የመጠጥ ውሃ እጦት #የህግ የበላይነት #ባለመከበሩ ምክንያት መሆኑን የሐረሪ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወልደ አብዶሽ ገለጹ፡፡

ሀላፊው በሰጡት መግለጫ በኤረር ወረዳ ቂሌ አካባቢ ላይ የሚገኘው ውሃ ማሰራጫ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መቋረጡን የገለጹ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች #ከ2 አመት በፊት የተከፈለን ካሳ #በቂ አይደለም በማለት አገልግሎቱን በማቋረጣቸው ነው።

በሀሮማያ የሚገኘው የውሃ ማሰራጫም ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል። ከመቋረጡ ቀደም ብሎ ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚውል 10 #ሚሊየን ብር በ5 ቀናት ውስጥ ይከፈለን የሚል ደብዳቤ በሀሮማያ ኢፈባቴ ቀበሌ 01 ሊቀመንበር በኩል እንደደረሳቸው ሀላፊው ገልጸዋል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
በህገ-ወጦች እገታ ውሃ አጥታ የከረመችው #ሐረር የተወሰነ አካባቢዋ ውሃ ማግኘት ጀመረ፡፡

በ5 ቀን ውስጥ 10ሚሊዮን ብር ይከፈለን ያሉ #የሃሮማያ አካባቢ ወጣቶች የውሃ ማጣሪያ ቁልፉን ነጥቀው መውሰዳቸውንና ሞተሮቹንም ማጥፋታቸውን ነግረናችሁ ነበር

የከተማዋ የውሃ ፍሳሽ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወልደ ሀብዶሽ እንደነገሩን በበዛ ጥረት ቁልፉን አግኝተናል ብለዋል፡፡

ከምስራቅ ኦሮሚያ አስተዳደር፣ከአወዳይ ከንቲባ ጽ/ቤትና ከሃሮማያ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በእምቢተኝነታቸው ፀንተው ከነበሩ ወጣቶች ቁልፉን ተረክበናል ብለዋል፡፡

የውሃ ማጣሪያ ጣቢያው የተወሰኑ የመቆጣጠሪያ የኤሌክትሪክ መስመሮች ተቃጥለው አግኝተዋቸዋል፡፡ አንድ ቀን በፈጀ የጥገና ስራ አሁን የሃሮማያ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ ስራ ጀምሯል ብለዋል፡፡

በመሆኑም አንድ ሶስተኛው የሃረር ከተማ አካባቢ ውሃ እያገኘ መሆኑን አቶ ተወልደ ነግረውናል፡፡አጥፊዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ስራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

ሌላው የሃረር የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ህገ-ወጥ የካሳ ጥያቄ ባቀረቡ ቡድኖች የውሃ መስመሩ ተሰብሮ የነበረው ኤረር አካባቢ የሚገኘው ነበር፡፡ ይህ ግን ገና እልባት ያላገኘ መሆኑን ከከተማዋ የውሃና ፍሳሽ ቢሮ ሀላፊ ሰምተናል፡፡
©Sheger Fm 102.1
@yenetube @mycase27
#ሐረር አራተኛ የተባለ ቦታ ጎማዎች እየተቃጠሉ
መንገድዶች ተዘግተዋል ነዋሪዎች ሰልፍ እያደረጉ ይገኛል።
@YeneTube @Fikerassefa
Update #ሐረር_አሁን

ህዝበ ክርስቲያኑ የተዘጋውን መንገድ አስከፍቶ የገብርኤል እና ጊዮርጊስ ታቦቱን አጅቦ እየተጓዘ መሆኑን ከጋዜጠኛ ቆንጂት ተሾመ ተመልክተናል።

ከሰዐታት በፊት ታቦቻቱ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ መንገድ እንደተዘጋባቸው መረጃዎች ደርሶን ነበር።

@YeneTube @Fikerassefa