በህገ-ወጦች እገታ ውሃ አጥታ የከረመችው #ሐረር የተወሰነ አካባቢዋ ውሃ ማግኘት ጀመረ፡፡
በ5 ቀን ውስጥ 10ሚሊዮን ብር ይከፈለን ያሉ #የሃሮማያ አካባቢ ወጣቶች የውሃ ማጣሪያ ቁልፉን ነጥቀው መውሰዳቸውንና ሞተሮቹንም ማጥፋታቸውን ነግረናችሁ ነበር
የከተማዋ የውሃ ፍሳሽ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወልደ ሀብዶሽ እንደነገሩን በበዛ ጥረት ቁልፉን አግኝተናል ብለዋል፡፡
ከምስራቅ ኦሮሚያ አስተዳደር፣ከአወዳይ ከንቲባ ጽ/ቤትና ከሃሮማያ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በእምቢተኝነታቸው ፀንተው ከነበሩ ወጣቶች ቁልፉን ተረክበናል ብለዋል፡፡
የውሃ ማጣሪያ ጣቢያው የተወሰኑ የመቆጣጠሪያ የኤሌክትሪክ መስመሮች ተቃጥለው አግኝተዋቸዋል፡፡ አንድ ቀን በፈጀ የጥገና ስራ አሁን የሃሮማያ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ ስራ ጀምሯል ብለዋል፡፡
በመሆኑም አንድ ሶስተኛው የሃረር ከተማ አካባቢ ውሃ እያገኘ መሆኑን አቶ ተወልደ ነግረውናል፡፡አጥፊዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ስራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡
ሌላው የሃረር የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ህገ-ወጥ የካሳ ጥያቄ ባቀረቡ ቡድኖች የውሃ መስመሩ ተሰብሮ የነበረው ኤረር አካባቢ የሚገኘው ነበር፡፡ ይህ ግን ገና እልባት ያላገኘ መሆኑን ከከተማዋ የውሃና ፍሳሽ ቢሮ ሀላፊ ሰምተናል፡፡
©Sheger Fm 102.1
@yenetube @mycase27