የትግራይ ልማት ማህበር ጉባኤ በውዝግብ ሲቋረጥ ምርጫው እንደገና እንዲካሄድ ታዘዘ!
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ) በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ያካሄደው 12ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በከፍተኛ የአፈጻጸም ችግሮች ምክንያት መጠናቀቁን አስታወቀ።
በተለይም የሥራ አመራር ቦርድ አመራሮችን ለመምረጥ በተደረገው ሂደት ላይ በተፈጠረው አለመግባባት ጉባኤው ያለ ስምምነት በመቋረጡ ባለሥልጣኑ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ አዟል።
ባለሥልጣኑ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ጉባኤው ከመጀመሪያው ጀምሮ ተሳታፊዎችን በመምረጥ ረገድ ጉልህ የሆኑ ችግሮች የታዩበት ሲሆን ይህ ጉዳይ ለትልማ አመራሮች በተደጋጋሚ ቢገለጽም ጉባኤው በዚሁ ችግር ቀጥሏል።የጉባኤው የመጨረሻ አጀንዳ የነበረው የሥራ አመራር ቦርድ ምርጫ ላይ ተሳታፊዎች መካከል መግባባት ሳይፈጠር በመቅረቱ ጉባኤው ያለ ስምምነት የተቋረጠ ሲሆን የተወሰኑ ተሳታፊዎችም ጉባኤውን ጥለው መውጣታቸው ካፒታል ከመግለጫው ተመልክቷል።
ባለሥልጣኑ ይህ ሁኔታ ማህበሩን ወደ መከፋፈል ሊያመራና ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን ጥቅም ሊያስተጓጉል እንደሚችል በመገንዘብ የሥራ አመራር ቦርድ ምርጫው በአስቸኳይ እንዲስተካከልና አስፈላጊ የሆኑ እርማቶች እንዲደረጉ ባለስልጣኑ አሳስቧል።ይህን ተከትሎ ከዚህ ቀደም በተካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዘው የሚከናወኑ ማናቸውም ተግባራት በባለሥልጣኑ ዘንድ እውቅና እንደሌላቸው በግልጽ አስታውቋል።
ባለስልጣኑ:- የትልማ 12ኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አመራር ቦርድ ምርጫ በህግ ፊት እውቅና እንደሌለውና ተቀባይነት እንደሌለው አጽንኦት ሰጥቷል። ከዚህ የቦርድ ምርጫ ጋር ተያይዘው የሚከናወኑ ማንኛውም ተግባራት፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችና ሌሎች ውሳኔዎች በህግ የሚያስጠይቁ እንደሚሆኑም በጥብቅ አስጠንቅቋል።
-Capital
@YeneTube

👍12😁4❤3
በ #ጅማ ዞን በድረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
በ #ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ ሚርጋኖ በሶ ቀበሌ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ በጣለው ከባድ ዝናብ በድረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።
አደጋው እሁድ ሚያዚያ 26 ቀን 2017 በሚርጋኖ ባሶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገሬ ኦጎደማ በተባለ ቦታ ላይ ለሌት 6 ሰዓት በጣለው ዝናብ መከሰቱን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ከባድ ዝናብ እና ኃይለኛ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የሸቤ ሶምቦ ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤቱ አክሎ ገልጿል።
የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ዩሱፍ አባ ማጫ እና የሚርጋኖ በሶ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ምስጋና ለታ ተጎጂዎችን በመጎብኘት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል ተብሏል።
ባሳለፍነው አመት ሀምሌ 15 ቀን በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል #ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት መለፉም አይዘነጋም።
በተመሳሳይ ወቅት በ #ሲዳማ ክልል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ 11 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሽኮ ዞንም የአራት ሶዎች ህይወት በመሬት መንሸራተት አደጋ ማለፉም ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa

👍12😭6❤4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ምቹ ነች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ምቹ ነች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከል እንደመሆኗ በአህጉራዊ ጉዳዮች ግንባር ቀደም ናት ያሉ ሲሆን፤ በዚህም ልዩ የሆነ የንግድ ሥራ ዕድል እና የባሕል ብልጽግናን የምትሰጥ ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በብዙ ትጋት እዚህ የደረሰው የአውሮፕላን ማረፊያ የሚያበረታታ ስለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ዘመናዊ የመሰብሰቢያ ቦታዎች፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ማረፊያዎች እና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ መሠረተ ልማቶች ያሏት ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ምቹ መሆኗን ነው የገለጹት።
ደማቅ የሆነ ባሕል፣ የተለያዩ የምግብ አማራጮች፣ ሙዚቃዎች እና አስደማሚ የተፈጥሮ ውበት ባሉባት ሀገር የዓለም አቀፍ ስብሰባዎች፣ ኮንፈረንሶች እና ኤግዚቢሽኖች (MICE) በሚካሄዱባት መድረሻዎን ያድርጉ ሲሉ ጋብዘዋል።

😁33👍18❤7👎3👀1
በብርቱካን ተመስገን ጉዳይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበሩት ተጠርጣሪ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ
በሽብር ወንጀል ጉዳይ ተጠረጥረው በእስር ላይ የሚገኙ አራት የኢቤኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች፤ ዋስትና በማስያዝ እንዲለቀቁ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።
ሁለት የጣቢያው ሰራተኞችን ጨምሮ 16 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤት አስታውቋል።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

👍14👎3
ህወሓት አደራዳሪዎች “ትጥቅ ፍቱ ከማለት ውጭ ስምምነቱ በጥቅል እንዲፈጸም ያሳዩት ዝግጁነት ውስን ነው” ሲል ተቸ!
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶርያ ስምምነት “አደራዳሪዎች ትጥቅ ፍቱ ከማለት ውጭ ስምምነቱ በፓኬጅ [በጥቅል] እንዲፈጸም ያሳዩት ዝግጁነት ውስን ነው” ሲል ተቸ።
"ብሔራዊ አንድነታችን ሉዓላዊነታችን ለማስጠበቅ" በሚል መሪ ቃል የፓርቲው 1337 የሚሆኑ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል በተባለው እና ከሚያዚያ 23 እሰከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው ስብሰባ ማገባደጃ ባለ 10 የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
አቋሙን ካንጸባረቀባቸው ጉዳዮች አንዱ የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አንዱ ሲሆን፤ “ሙሉ በሙሉ አልተተገበረም” ሲል በመግለጽ ላለመተግበሩም ሶስት ምክንያቶችን አስቀምጧል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራውን የጊዜያዊ አስተዳደሩን “ተቆጣጥሮት የነበረው የፓርቲው አንዱ ቡድንን” በመጀመሪያ ምክንያትነት ያስቀመጠው መግለጫው በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት በኩል ስምምነቱን ለማስፈጸም “ቁርጠኛ አለመሆኑ ነው” ሲል ገልጿል።
ሌላኛው በአቋም መግለጫው የተካተተው ነጥብ ደግሞ የፓርቲው እውቅናን የተመለከተ ሲሆን “እውቅናየ የሚወሰነው በትግራይ ህዝብ ነው ብየ ነው የማምነው” ሲል ገልጿል። በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ህጋዊ ሰውነቱ ወደ ነበረበት እንዲመለስም ጥሪ አቅርቧል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa

👍26😁8👎4
ኢትዮጵያ እና ኢራን በመረጃ ልውወጥ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢራን ፖሊስ ጋር በጋራና በትብብር መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ/ም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
እንደ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ፤ ሁለቱ የፖሊስ ተቋማት የመረጃ ልውወጥ ለማድረግ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ እና በትብብር ለመከላከል፣ በልምድ ልውውጥ እና በአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የኢራን የሕግ አስከባሪ ኃይሎች ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል አህመድ ረዛ ራዳን ናቸው። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመረጃው፤ መግባቢያ ሰነዱ በስምምነቱ መሠረት በየጊዜው ክትትል እየተደረገ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቋል።
በመጋቢት ወር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የዱባይ ፖሊስ የምርመራ ቡድን ኃላፊ ሌ/ኮለኔል አብደላ መሃመድ ጋር በአዲስ አበባ በወንጀል ምርመራ ዙሪያ መወያየታቸው ይታወሳል።
በሁለቱም ሀገራት ተፈላጊ የሆኑ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ስለሚቻልበት ሁኔታም መወያየታቸውንም የፌደራል ፖሊስ በወቅቱ አስታውቋል።
@Yenetube @FikerAssefa

👍37😁19👎3❤2🔥1👀1
በጀርመን መራኄ መንግስትነት ይመርጣሉ ተብለው የሚጠበቁት ፍሪድሬሽ ሜርስ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ አብላጫ ድምጽ ሳያገኙ ቀሩ።
ሜርስ ዛሬ በሀገሪቱ ምክር ቤት ተመርጠው ሥልጣን ይረከባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።ይሁንና ዛሬ ጠዋት የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች በሰጡት ድምጽ እርሳቸው መራኄ መንግሥት እንዲሆኑ የመረጡት 310 የምክር ቤት አባላት ብቻ በመሆናቸው ሜርስ መራኄ መንግስት ለመሆን የሚያስፈልጋቸው 6 የምክርቤት አባላት ድምጽ ጎድሏቸዋል።በዚህም ምክንያት የምክር ቤቱ ስብሰባ ተቋርጧል።
ሜርስ መራኄ መንግሥት ለመሆን ከ630 የጀርመን ምክር ቤት አባላት ቢያንስ የ316ቱን ድምጽ ማግኘት አለባቸው።ምክር ቤቱ ሜርስ ከዛሬ ጀምሮ የጀርመንን መንግሥት እንዲመሩ ከመረጠ ሥልጣኑን ከተሰናባቹ ኦላፍ ሾልስ ይረከባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ አባል የሆኑት ሾልስ ላለፉት ሦስት ዓመታት ገደማ በመራኄ መንግሥትነት አገልግለዋል።
Via DW

👍16❤3
🚀 ትልቅ እድል በLinkedIn! 🚀
የLinkedIn መለያዎን ይከራዩ፡ በየሳምንቱ ተገብሮ ገቢ ያግኙ!
🔑 እንዴት?
LinkedIn መሆን አለበት። 1 አመት እና ከዚያ በላይ መለያው ይኖርበታል።
💰 የገንዘብ አማራጮች:
• 300+ ግንኙነቶች - 13$ በየሳምንቱ
• 500+ ግንኙነቶች - 15$ በየሳምንቱ
• 800+ ግንኙነቶች - 17$ በየሳምንቱ
• 1000+ ግንኙነቶች - 20$ በየሳምንቱ
• 2000+ ግንኙነቶች - 25$ በየሳምንቱ
👉 ፈጣን ክፍያ - በ24 ውስጥ ይክፈሉ።
🔔 መልካም ዕድል!
• 1 ዓመት ዕድሜ ወይም ከዚያ በላይ
• 300+ - 13$ በሳምንት
• 500+ - 15$ በሳምንት
• 800+ - 17$ በሳምንት
• 1000+ - 20$ በሳምንት
• 2000+ - 25$ በሳምንት
🚫 መግለጫ:
መለያዎን ሊከራዩ፣ መለያዎች ሳምንታዊ ገደቦች መድረስ የለበትም።
• ይህ እውነት ነው
• ምንም አደጋ የለም
• ወንጀል የለም።
📱 ቴሌግራם: @rwslimited

👍4❤1
ዜና፡ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ #በትግራይ የተፈናቃይ መጠለያዎች በርሃብ ሳቢያ ስምንት ሰዎች ሞተዋል ተባለ
በተመሳሳይ #በአማራ ክልል የእርዳታ መቋረጥ ችግር እየፈጠረ መሆኑም ተገልጿል
በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ለሚገኙ ነዋሪዎች የሰብአዊ እርዳት መስጠት ከተቋረጠ ወዲህ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተገለጸ።
በትግራይ አክሱም ከተማ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ስምንት ሰዎች በረሃብና በመድሃኒት እጦት መሞታቸውን የምዕራብ ትግራይ ዞን የአክሱም ክላስተር ተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ ካህሳይ አሳየሀኝ አስታውቀዋል።
በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ይሰጥ የነበረ እርዳታ መቀነስና በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መቋረጥ በክልሉ በሚገኙ ተፈናቃዮች ዘንድ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሆነ ተፈናቃዮች ገልጸዋል።
ተፈናቃዮቹ ምግብ የለም፣ የመጠለያ ድንኳኖች ፈርሰዋል፣ የህክምና ባለሙያዎች ከመጠለያዎች ወጥተዋል፤ “ይደረጉ የነበሩ የዱቄት፣ የዘይትና አልባሳት ድጋፎች የሉም” ማለታቸውም ታውቋል።

😭21👍10❤2😁2
የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ
"እርካታ ቤት ኪራይ አይከፍልም" - በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሰልፍ የወጡ የጤና ባለሞያዎች።
የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ሌሎች የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጣቸው በሚሰሩበት ሆስፒታል በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ጀምረዋል።
የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ በተመለከተ የጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ በሰጡት ማብራርያ የአጭር፣ የመካከለኛ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ይዞ ለችግሮች መፍትሔ ለመስጠት በሒደት ላይ እንደሚገኝ ከቀናት በፊት ለሪፖርተር ተናግረዋል።
"በጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች የሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢና ዕውቅና የምንሰጣቸው ናቸው" ብለው ለሪፖርተር የተናገሩት ዶ/ር ተገኔ ከደመወዝ ጭማሪ ጋር በቀጥታ የማይገናኝ ማበረታቻ ወይም (Non Salary Incentives) ለጤና ባለሙያውና ለሠራተኛው ጠቀሜታው የጎላ ነው ተብሎ ተለይቶ እየተሠራበት ያለ አንዱ ፓኬጅ ነው ብለዋል።
Via:- አዩዘሀበሻ

👍40❤3🔥1
የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት ጥሪ ቀረበለት
የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ክርስቲያኖ ጁኒየር በፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች አዳጊዎች ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠርቷል።
የሮናልዶ የበኩር ልጅ፣ የ14 ዓመቱ ክርስቲያኖ ጁኒየር በአሁኑ ሰዓት በሳዑዲ ዓረቢያ ለአል ናስር ክለብ አካዳሚ በመጫወት ላይ ይገኛል።
የፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በዚህ ወር በክሮሽያ በሚካሄደው የቭላትኮ ማሬኮቪች ዓለም አቀፍ ውድድር የሚሳተፍ ሲሆን በውድድሩ ከጃፓን፣ እንግሊዝ እና ግሪክ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

👍48❤8⚡4👎4👀3
“40 በመቶ የሚሆነው የትግራይ ግዛት በወራሪዎች ስር ነው የሚገኘው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ የክልሉን የግዛት ወሰን ማረጋገጥ ነው” - ፕሬዝዳንት ታደሰ
“የትግራይ ክልል 40 በመቶ የሚሆነው ግዛት በወራሪዎች ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው” ሲሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ የክልሉን የግዛት ወሰን ማረጋገጥ እና የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው መመለስ ነው” ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን የገለጹት በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የሆኑትን ጄነስ ሃኒፈልድ ዛሬ ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
ፕሬዝደንት ታደሰ “40 በመቶ የሚሆነው የትግራይ ክልል ግዛት በወራሪዎች ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው፣ ከሁሉም ነገር በፊት እና ከምንም ነገር በላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተልዕኮ በህገመንግስቱ የተከለለውን የክልሉን የግዛት ወሰን ማረጋገጥ እና የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው መመለስ ነው” ሲሉ ለአምባሳደሩ መናገራቸውን ከጽህፈት ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ውይይት “የመጀመሪያው ዙር 75ሺ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ተግባር እስከ መስከረም ይጠናቀቃል፣ ሁለተኛው ዙር ግን ከክልሉ ግዛት መከበር ጎን ለጎን የሚፈጸም ነው” ሲሉ መናገራቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።

👍16👎9❤4😁3
YeneTube
Photo
አስገኘው አሽኮ ሴቶችን በተመለከተ በሰጠው አስተያየት ላይ ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ
እንደሚታወቀው በሀገራችን የሴቶችና የሴት ህፃናት ጥቃት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ፣ አይነቱን እየቀያየረና በአፈፃፀሙም እየረቀቀ የመጣ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ይህንንም ለመከላከል የተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም መላው የህብረተሰብ ክፍል የራሱን አስተዋፅዖ ማድረግ እንዳለበት እሙን ነው። አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ጥቃት ምን ማለት እንደሆነ በቂ ግንዛቤ የሌለው ከመሆኑም በተጨማሪ በአንዳንድ ግለሰቦች የሚሰነዘሩ ሴቶችን የተመለከቱ አስተያየቶች ለጥቃት መባባስ ጉልህ ሚና አላቸው።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰሞኑን በአንድ ታዋቂ ግለሰብ ማለትም በድምፃዊ አስገኘው አሽኮ ሴቶችን በተመከተ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተደረገው ንግግር ሴቶች በአካላዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እየደረሰባቸው ካለው ጥቃት በተጨማሪ በጠቅላላው በመፈረጅ የስነልቦናዊ ጥቃት እንዲደርስባቸው ያደረገ እና ብዙ ሴቶችንም ያስቆጣ ተግባር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ጉዳዩን ብዙ ሰዎች እንዲቀባበሉት እና የበለጠ ሴቶች ላይ እንዲዘባበቱ ያነሳሳም ጭምር ነው።
ድምፃዊው ከዚህ ቀደም "የሀገር ካስማ" በተሰኘው ሴቶችን ለማበረታታት ታልሞ በተሰራ ህብረዝማሬ ላይ በመሳተፍ የሴቶች አጋር መሆኑን በማሳየቱ እንደተቋም እውቅና ሰጥተን የነበረ ሲሆን አሁን ባደረገው ንግግር ግን ሴቶች ላይ የጥላቻ ዘመቻ እንዲከፈት በማድረጉ ማኅበራችን እጅግ ያዘነ መሆኑን ለመግለፅ ይወዳል።
ድምፃዊው በንግግሩ "በፍቅር ያበደች ሴት ካሳየኸኝ የማይሞት ሰው አሳይሀለው" በማለት ሴቶችን ሁሉ በአንድ በመፈረጅ በአጠቃላይ የሴቶችን ስብዕና የሚነካና ሴቶች በህገመንግስቱ የተሰጣቸውን ክብራቸው ተጠብቆ የመኖር መብት የጣሰ አስተያየትን ሰጥቷል። ይህ ንግግሩም በሀገራችን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀፅ 2(2)፣ 4 እና 7ን የጣሰ እና የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያመጣ ተግባር ነው።
በመሆኑም ማኅበራችን ግለሰቡ በተገቢው መልኩ በህግ ተጠያቂ እንዲሆን የሚሰራ መሆኑን እየገለፅን የተፈፀመውን ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን። ዛሬ ላይ ያለተጠያቂነት የምትታለፍ አንዲት ጥላቻ ነገ ላይ በሴቶች ላይ ለሚፈፀም ከባድ ዘመቻ በር ከፋች በመሆኗ ይህንን ንግግር የምታሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያዎችም ይህን ከማድረግ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን።
በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃትን መከላከል የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሀላፊነት ነው።
በሴቶች ላይ የሚፈፀም የጥላቻ ንግግርን አጥብቀን እንቃወማለን!!
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር (ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ)

😁79👍42👎14❤5
ብሄራዊ ባንክ በነገው ዕለት ሌላ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ባንኩ ለነገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 60 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ገልጧል።
ባንኩበየሁለት ሳምንቱ መደበኛ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ማውጣት ከጀመረ ወዲህ፣ የነገው ጨረታ ሦስተኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታው ይኾናል።

👍23😭7❤3