YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
“ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል “ - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለአፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል።

“ የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል “ ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍77👎7😭74👀4😁3
"የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አመራር የነበረው የሾዴ መገደልን ተከትሎ ከቡድኑ ከድተው መንግስትን የተቀላቀሉ የቀድሞ ተዋጊዎች ቤተሰቦች ኢላማ ተደርገናል"- የቤተሰብ አባላት ለመሠረት ሚድያ

(መሠረት ሚድያ)- ሾዴ እየተባለ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (በመንግስት አጠራር ኦነግ ሸኔ) የቀድሞ ከፍተኛ አመራር በመከላከያ ሰራዊት መጋቢት 26, 2017 ዓ/ም መገደሉን ተከትሎ ቀደም ብለው ከቡድኑ ከድተው መንግስትን የተቀላቀሉ የቡድኑ ተዋጊዎች ቤተሰቦች እየተገደሉ እና እየተሰደዱ መሆናቸውን ለሚድያችን ተናግረዋል።

መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "የጃል መሮ ዋና ሰው የነበረው እንዲሁም በታንዛኒያው ድርድር ከጫካ ወጥቶ ታንዛኒያ ዳሬሰላም ድረስ ከመሮ ጋር ተጉዞ የሸኔ ሽብር ቡድን ተደራዳሪ የነበረው ሾዴ በተወሰደበት እርምጃ ተገድሏል" ማለቱ ይታወሳል።

ሾዴ ከታንዛኒያ መልስ የአጠቃላይ የወለጋ ዞኖች አዛዥ ተደርጎ በመሮ ተሹሞ የነበረ መሆኑንም መከላከያ አስታውቆ ነበር።

ይሁንና አመራሩ በምስራቅ ወለጋ ዞን ሃሮ ሊሙ ወረዳ ገንጂ አካባቢ ከኮርማ ወንዝ ወደ ሱጊ በሚወሰደው መንገድ ላይ በሞተር ሳይክል ተደብቆ ሲጓዝ የፀጥታ ኃይሎች ባገኙት መረጃ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እርምጃ እንደተወሰደበት መንግስት አስታውቆ ነበር።

ይህን ተከትሎ ግን በምስራቅ ወለጋ ዞን ሃሮ ሊሙ ወረዳ ጎርባ ጉዲና እና ሱጌ ቀበሌዎች የሚኖሩ እና ከወራት በፊት ከቡድኑ ከድተው መንግስትን የተቀላቀሉ የቀድሞ ተዋጊዎች ቤተሰቦች ኢላማ መደረጋቸውን ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

"ከሾዴ ግድያ በሗላ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ተጠያቂ ያደረገው የራሱን የቀድሞ ታጣቂዎች ነበር፣ እነዚህ ደግሞ ከድተው መንግስትን የተቀላቀሉት ናቸው" ያሉን አንድ የአካባቢው ነዋሪ የእነዚህ የከዱ ታጣቂዎች የትውልድ ቦታዎች ኢላማ እንደሆኑ ተናግረዋል።

"መጋቢት 30, 2017 ዓ/ም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት በሱጌ ቀበሌ የሚገኙ የቀድሞ ታጣቂዎች ቤተሰቦች ላይ ግድያ ፈፅመዋል፣ ሁለት ህፃናትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች በዚህ እለት ብቻ ተገድለዋል" ያሉን አንድ የቤተሰብ አባል ሁለት ሌሎች ጎረቤቶችም ተጨምረው ተረሽነዋል ብለው ስማቸውን ለመሠረት ሚድያ አጋርተዋል (ስሞቻቸው: ዳባ ዘለቀ፣ ናቾ ደሳለኝ፣ አዳም ዘለቀ፣ ድሪባ ተስፋዬ፣ ሱካሬ ገመቹ፣ ቢቂልቱ ዲሪባ፣ ኢፍቱ ዲሪባ፣ ጋመዴ፣ ድሪባ፣ በቀለ ጎንደሬ እና ጆቴ በቀለ)።

ከዚህም በተጨማሪ መጋቢት 29, 2017 ዓ/ም ታጣቂዎቹ ወደ ሌላኛው ለመንግስት እጁን የሰጠ የቀድሞ ታጣቂ የትውልድ ቦታ ወደሆነው ጋርባ ጉዲና ቀበሌ በመግባት አምስት ሰዎችን እና የቤት እንስሳቶቻቸውን ይዘው እንደሄዱ ሌላ የቤተሰብ አባል ለሚድያችን ተናግረዋል።

"በአጠቃላይ የስምንት ቤተሰቦች አባላት በዚህ ድርጊት ከፍተኛ የሞት እና የእገታ ድርጊት ደርሶባቸዋል፣ ድርጊቱን ያመለጡት ወደ ሀሮ ከተማ ሸሽተዋል" በማለት የሆነውን አስረድተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ እድሜያቸው ከ7 እስከ 60ዎቹ የሚደርሱ የአቶ ሂርጶ ቤተሰብ አባላት ወደ ባሪሶ አካባቢ ተወስደው የነበረ ቢሆንም ሁሉም መገደላቸውን ትናንት መስማታቸውን የቤተሰቡ አባል አስረድቶ አሁን ሀዘን ተቀምጠው እንዳሉ ገልጿል።

በዚህ ዙርያ እካሁን በመንግስት አካላትም ሆነ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የተሰጠ መግለጫ የለም።

ምንጭ:- ከመሠረት!
@Yenetube
👍70😭107👀3😁2
በኬንያ ከነገ ጀምሮ ለ1 ወር የሚቆይ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ተደርጓል‼️

የኬንያ ኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለስልጣን (EPRA) ዛሬ እንዳስታወቀው የቤንዚን ዋጋ በሊትር የ1.95 የኬንያ ሽልንግ፣ የናፍጣ ዋጋ በሊትር የ2.20 የኬንያ ሽልንግ እና የኬሮሲን ዋጋ በሊትር የ2.40 የኬንያ ሽልንግ የዋጋ ቅናሽ ተደርጎባቸዋል ብሏል።

ባለስልጣኑ ነዳጅ ከውጪ የሚገባበት ዋጋ በየካቲት እና መጋቢት ወር መቀነሱን የገለፀ ሲሆን ቤንዚን የ4.89%፣ ናፍጣ የ6.45% እና ኬሮሲን የ6.53% የዋጋ ቅናሽ ማድረጋቸውን ገልጿል።

ቤንዚን በሊትር 174.63 ሽልንግ (178.97 ብር)፣ ናፍጣ በሊትር 164.86 ሽልንግ (168.96 ብር) እንደዚሁም ኬሮሲን በሊትር 148.99 ሽልንግ (152.70 ብር) በሆነ ዋጋ በናይሮቢ እንደሚሸጡም ተገልጿል።

ኬንያ በነዳጅ ምርት ላይ የ16% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምትጥል ሲሆን ከላይ የተገለጸው ዋጋም ይህንን አካቶ እንደሆነ ተገልጿል። 

ከወር በፊት ኬንያ የነዳጅ ዋጋን በተመለከት ጭማሪ ሊኖር እንደሚችል ገልፃ  የነበረ ቢሆንም በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከአራት አመታት በኋላ በዝቅተኛው ደረጃ ላይ እንዳለ በመገለፁ ኬንያ የዋጋ ቅናሽ ስለማድረጓ ተገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍91😭127
🌿🌿እንኳን አደረሳችሁ 🌿🌿

በአልን ምክንያት በማድረግ እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ!!!

በ 900,000 ብር ምን ያደርጋሉ❗️

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

እንዲሁም የመኖሪያ አፓርትመንቶችን

📍 ሊሴ ገብረማርያም  ት/ቤት ጀርባ
ሙሉ ለሙሉ ለመኖሪያ ብቻ

ባለ 1 መኝታ
ባለ 2 መኝታ
ባለ 3 መኝታ

ከ66ካሬ - 142ካሬ ለመኖር  ለኢንቨስትመንት ምቹ

⚠️ቅድመ ክፍያ ከ693ሺ ብር ጀምሮ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ እስከ 25% የሚደርስ ቅናሽ

ቴምር ሪልስቴት

ለበለጠ መረጃ 

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍51
Forwarded from YeneTube
ዛራ ሽቶዎች
በተለያዩ ፍሌቨሮች
Red Zara temptation ,Zara golden decade and Zara hypnotic vanilla
Europe standard
Size: 80ml
በብዛት ወይም በችርቻሮ መረከብ ሚፈልግ እናስረክባለን

ዋጋ በችርቻሮ:7000br
በብዛት:6000br

ስልክ: +251919492435 & +251934003462

ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል 👇
https://tttttt.me/+zRyCg_U0QGZmMzY0

ቲክቶክ አካዉንት 👇
www.tiktok.com/@bt_onlineshopping
👍14👎1
#ህወሓት “የአፍሪካ ህብረት ፓኔል በአፋጣኘ ተሰብስቦ በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አተገባበር” ዙሪያ እንዲመክር ጥሪ አቀረበ

#የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ያሉ ሁኔታዎች አሳሳቢ በመሆናቸው #የአፍሪካ ህብረት ፓኔል ውይይት ሊያደርግ ይገባል ሲሉ” የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

ሊቀመንበሩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በአፍሪካ ህብረት የፕሪቶርያ ስምምነት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር ተልዕኮ ኮሚቴ ሃላፊ ሁነው ከተሾሙት ሜጀር ጀነራል ሳማድ አላዴ ትላንት ሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባካሄዱት ውይይት መሆኑን ፓርቲው ባጋራው መረጃ አስታውቋል።

“በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ ውጭ ያሉት ታጣቂዎች ከትግራይ ግዛት እስካሁን አለመውጣታቸውን፣ የተሰደዱ እና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለስ አለመቻላቸውን እንዲሁም የትግራይ ሉዓላዊ መሬቶች በወራሪዎች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ ሲሉ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለተሿሚው መናገራቸውንም አካቷል።

ሊቀመንበሩ ደብረጺዮን “የፖለቲካ ድርድር እስካሁን አለመጀመሩን፣ የስምምነቱ ፈራሚ የሆነው ህወሓት የተሰረዘው ህጋዊ ሰውነቱ አለመመለሱን” ለተሿሚው ማስታወቃቸውን መረጃው አመላክቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍16😁83
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ኮሪዶር ልማት ፕሮጀክት “በአስቸኳይ እንዲቆም” ጠየቀ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ያለ ተገቢ ምክክር፣ ካሳ ወይም ህጋዊ ጥበቃዎች “በግዳጅ ከቤት ማፈናቀል” እየተፈጸመ መሆኑን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት “የኮሪደር ልማት ፕሮጀክትን “በአስቸኳይ እንዲያቆም” ጠየቀ።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ትናንት ሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ/ም ባወጣው ሪፖርት፤ ቢያንስ 872 ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች በ2016 ዓ.ም ህዳር ወር ከቤታቸው መፈናቀላቸውን በምርመራው ማረጋገጡን ገልጿል። ከእነዚህም ውስጥ 254ቱ የቤት ባለቤቶች ሲሆኑ 618 የሚሆኑት ተከራዮች ናቸው ብሏል።

ከሰዎቹ ጋርም በቂ ምክክር አለመደረጉን፣ ማስጠንቀቂያ እንዳልደረሳቸው እና ካሳ እንዳልተሰጣቸው ሪፖርቱ አመላክቷል። 

ሪፓርተን

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7607
👍76😭12👎83😁3👀1
የብሄራዊ ባንክ አዲሱ መመሪያ

ብሔራዊ ባንክ፣ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ቅርንጫፎችን መክፈት የሚፈልጉ ባንኮች ፍቃድ ለማግኘት እንዲያሟሉ የሚጠበቅባቸውን ልዩ ዝቅተኛ መሥፈርቶች የያዘ መመሪያ ሊያወጣ እንደሆነ ሪፖርተር ዘግቧል።


በረቂቅ መመሪያው ከሚካተቱት መሥፈርቶች መካከል፣ ማናቸውም ባንክ የፍቃድ ጥያቄውን ካቀረበበት ቀን አስቀድሞ በነበረው ዓመት ውስጥ ያለው አጠቃላይ ሃብት በዚያው ዓመት ከተመዘገበው አጠቃላይ የባንክ ዘርፍ ሀብት በትንሹ ሁለት በመቶ ድርሻ ሊኖረው ይገባል የሚለው እንደሚገኝበት ዘገባው ጠቅሷል።

በትንሹ 65 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ሀብት መያዝ፣ ሥጋታቸው ለሚያመዝን ብድሮች የተያዘ መጠባበቂያ ካፒታል ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው 8 በመቶ ዝቅተኛ መሥፈርት የ2 በመቶ ብልጫ ያለው እንዲሆን፣ የባንኩ የገንዘብና የገንዘብ አከል ይዞታ ምጣኔ ማመልከቻውን ካስገባበት ጊዜ በፊት ለነበሩ ሦስት ወራት በብሔራዊ ባንክ ከተቀመጠው ዝቅተኛ መሥፈርት በ3 በመቶ ብልጫ ያለው መኾን እንደሚገባውም በመስፈርትነት እንደተካተቱ ዘገባው አመልክቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍151
🚀 ቡስትግራም:ለቲክቶክ 📹 ፣ ኢንስታግራም 📷፣ ፌስቡክ 👍፣ ዩቲዩብ ✈️ እና ቴሌግራም ✈️ በቀላሉ ላይኮች፣ ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።


📹 የቲክቶክ እድገት: ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷 የኢንስታግራም ማሻሻያ: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

👍 የፌስቡክ አገልግሎት: የፔጅዎ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ፖስቶች ላይ ኢንጌጅመንቶች ይጨምሩ።

📹 የዩቲዩብ አገልግሎት: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

OPEN BOOSTGRAM - 🔗 https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
👍51
ህወሓት “የአፍሪካ ህብረት ፓኔል በአፋጣኘ ተሰብስቦ በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አተገባበር” ዙሪያ እንዲመክር ጥሪ አቀረበ!

“የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ያሉ ሁኔታዎች አሳሳቢ በመሆናቸው የአፍሪካ ህብረት ፓኔል ውይይት ሊያደርግ ይገባል ሲሉ” የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

ሊቀመንበሩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በአፍሪካ ህብረት የፕሪቶርያ ስምምነት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር ተልዕኮ ኮሚቴ ሃላፊ ሁነው ከተሾሙት ሜጀር ጀነራል ሳማድ አላዴ ትላንት ሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባካሄዱት ውይይት መሆኑን ፓርቲው ባጋራው መረጃ አስታውቋል።

“በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ ውጭ ያሉት ታጣቂዎች ከትግራይ ግዛት እስካሁን አለመውጣታቸውን፣ የተሰደዱ እና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለስ አለመቻላቸውን እንዲሁም የትግራይ ሉዓላዊ መሬቶች በወራሪዎች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ ሲሉ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለተሿሚው መናገራቸውንም አካቷል።

ሊቀመንበሩ ደብረጺዮን “የፖለቲካ ድርድር እስካሁን አለመጀመሩን፣ የስምምነቱ ፈራሚ የሆነው ህወሓት የተሰረዘው ህጋዊ ሰውነቱ አለመመለሱን” ለተሿሚው ማስታወቃቸውን መረጃው አመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍24😁63🔥1😭1
ጽናጽል ከበሮና መቋሚያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ንብረት ሆኖ ተመዘገበ

"ጸናጽል፣ ከበሮና መቋሚያ ከሌሎች ከ10 በላይ ቅዱሳት መጽሃፍት ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐዕምሮአዊ ንብረት መሆናቸው ተረጋግጦ ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዘግበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና አግኝተዋል"

Via የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት
@Yenetube @Fikerassefa
👍13141😁24🔥2
#ሀረር ከተማ የአለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል መሆኗ ተገለጸ

#ሆንግ_ኮንግ በተካሄደው የአለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን ጉባኤ ሀረር ከተማ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን የሀረሪ ክልል ርዐሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

አቶ ኦርዲን በድሪ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ሀረር ከተማ “የፌደሬሽኑ አባል መሆኗ” ሀረርን ከሌሎች ከተሞች ጋር ለማስተሳሰር እና አብሮ ለመስራት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023 ሀረር ከተማ ከሰሃራ በታች ካሉ ከተሞች የመጀመሪያዋ የዓለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት አባል ከተማ ሆና መመዝገቧ ይታወሳል፡፡

እንዲሁም ከተማዋ የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስን ጨምሮ በተባበሩት መንግስት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የተመዘገቡ ዓለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ ከተማ መሆኗ ይታወቃል፡፡

በተጨማሪም ከተማዋ ዜጎች በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የሚኖሩባት ከተማ በሚል ዩኔስኮ እውቅና ተሰጥቷቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍24😁96🔥1
የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌 
#ምርቶቻችንን ከ :-
🥣 ሸዋ ሾፒንግ 
🥣 በሽ ገበያ
🥣 ባምቢስ(ልዊስ)
🥣 ሎሚያድ
🥣 ጋራ ማርት
🥣 ዴይሊ ሚኒማርት
🥣 ጋራድ ሱፐርማርኬት
እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል። 

🥣 መልካም በዓል   / 2017 ዓ.ም 🥣
#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
📲 0911 664775 / 0911 872827
👍81
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በ #ሩዋንዳ እያደረጉ ነው

#ኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ ከሚያዚያ 5 ቀን ጀምሮ የአራት ቀን የስራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ ተዘገበ።

ጉብኝቱ ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር እያደረጉ ያሉትን ጥረት ተከትሎ የተካሄደ ነው።  የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ መበጋቢት ወር  በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተፈራርመዋል።

እንደ ዘኒው ታይምስ ዘገባ፤ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ሰኞ ዕለት፤ ኪሚሁሩራ በሚገኘው የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት  ዋና መስሪያ ቤት ከጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ይህንንም ተከትሎ የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት በሰጠው መግለጫ፣ ጉብኝቱ "የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብርን” ለማስፋት "ቁልፍ ዕድል" መሆኑን በመግለጽ ውይይቶቹ "በመከላከያና በሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች  አዲስ የትብብር መስኮች" ላይ ያተኮሩ ናቸው ብሏል።

ፌልድ ማርሻል ብርሃኑ  የኪጋሊ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሙዚየምን እንደሚጎበኙ ዘኒው ታይምስ ዘግቧል። የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ በመጋቢት ወር ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት ልዑካቸው በ #ቢሾፍቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም በወቅቱም ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በወታደራዊ አቅም ግንባታ ስልጠና፣ በተሞክሮ ልውውጥ፣ ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና በሌሎችም ተያያዥነት ባላቸው ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁40👍196👎2🔥2
ለ150 ሺህ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በበየነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል

ለ150ሺህ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ፈተናን በበየነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።

በዘንድሮው ዓመት 150ሺህ ተማሪዎች በበየነ መረብ ለመፈተን ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ 3 ሺህ 222 ትምህርት ቤቶች የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጡ ሲሆን ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 936 ሺህ 624 ተማሪዎች መካከል 416 ሺህ 284 ተማሪዎች በ48 ሺህ 242 መምህራን ማጠናከሪያ ትምህርት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በ2016 ዓ.ም ምንም ተማሪ ከለሰለፉ ትምህርት ቤቶች መካከል 700 ትምህርት ቤቶች ተለይተው የአንድ ዓመት ሙሉ ድጋፍ በተለያዩ ዘርፎች እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።

ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ 294 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 783 ርዕሰ መምህራን፣ 19ሺህ 566 መምህራንና 3ሺህ 628 የአስተዳደር ሰራተኞች በአጠቃላይ 23ሺህ 977 የትምህርት ማህበረሰብ በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል።

በ2016 ዓም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገውንና ውጤት የተገኘበትን የማጠናከሪያ ትምህርት በስፋት ለመስጠት የንቅናቄ ሰነድ በማዘጋጀት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

በ2016 ዓም 674 ሺህ 814 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲው መግቢያ ፈተና ወስደዋል። ከዚህ 29ሺህ 727 ተፈታኞች በተመረጡ ቦታዎች በበየነ መረብ መፈተናቸው ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍24👎6😁21🔥1
የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአስተማሪዎች የ17 ወራት ውዝፍ ደምወዝ እንዲከፈል ወሰነ

የትግራይ ክልል አስተማሪዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያልተከፈላቸው ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ለማድረግ ጉዳያቸውን ፍርድ ቤት ወስደው እንደነበር ይታወሳል። ከክልሉ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ጉዳዩን ተከሳሾቹ የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ የፋይናንስ ቢሮና ጊዝያዊ አስተዳደሩ በሌሉበት ሲከታተል የቆየው የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሚያዝያ ሰባት ቀን ውሳኔ መስጠቱን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ በውሳኔውም ተከሳሾች የአስተማሪዎችን ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፍሉ በመወሰን የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ ወስኗል። የፍርድ ሂደቱ 1ኛ ተከሳሽ የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ 2ኛ ተከሳሽ የትግራይ ፋይናንስ ቢሮ፣ 3ኛ ተከሳሽ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደርና 4ኛ ተከሳሽ የገንዘብ ሚኒስቴር ባልተገኙበት የተደረገ ነዉ።

@Yenetube @Fikerassefa
👍46👀3
በእስር ላይ የሚገኙት ቲክቶከር ጆን ዳንኤል እና ናዮ( ዪዲዲያ) ዛሬ ሚያዝያ 7 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበራቸው የናዮ የመውለጃ ጊዜዋ መድረሱን ተከትሎ ልጄን ለመውለድ ጋንዲ ሆስፒታል ይፈቀድልኝ ብላ መጠየቃን የተሰማ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ባለችበት እስር ቤት (ቃሊት እስርቤት) እንድትወልድ ፍርድ ቤት ወስኗል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭132👍49😁204👎2