YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ቢሾፍቱ

#የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከጋሞ ብሔረሰብ የመጡ አባቶችና ወጣቶች #ቢሸፍቱ ደረሱ። #የኦሮሞ አባ ጋዳዎችም እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀብለዋቸዋል። የኢሬቻ በዓል የክረምቱ ወራት አልፎ የበጋው ወራት በመጀመሩ ለአምላክ #ምስጋና የሚቀርብበት በዓል በመሆኑ የሁላችንም በዓል ነው እንኳንም የኛን በዓል #በዓላቸሁ አድርጋችሁ ለማክበር በመምጣታችሁ እናመሰግናለን ብለዋል።

📌ቀን ላይ የተላከ መልክት ነበር

©MOHAMMED NURE ENDRIES

@YeneTube @Fikerassefa
#ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ደመራ አልተደመረም!!

በቢሾፍቱ (በደብረ ዘይት) ከተማ የተዘጋጀው ደመራ ሳይበራ ፕሮግራሙ ተዘግቷል። መንስዔውም የቅድስት ኪዳነምህረት ካህናት ወደ ዳመራው በተደመረበት አደባባይ ቤ/ክ የምትጠቀመውን ሰንደቅ አላማ ለምን ይዛችሁ መጣቹህ በማለት በተለያዩ አካላት #ከበሩ ሊመለሱ ችለዋል።

በዚህም ምክንያት ካህናቱ በሩ ላይ ብዙ ሰዓት ከቆሙ በዋላ ሊመለሱ ችለዋል። ይህንንም የሰሙ ወጣቱ አባቶች ሣይገኙ ደመራውን አናበራም በማለት ደመራውን ሣያበሩ በጸሎት ፕሮግራሙ ሊዘጋ ችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፌደራል ፓሊስ ከሀገሪቱ ባንዲራ ውጪ ይዞ መገኘት እንደማይቻል ትላንት ያስታወቀ ሲሆን ዛሬ መልሶ የቤተክርስቲያን የራሷን አርማ እና ሎጎ መጠቀም እንደምትችል ማስታወቁ ይታወሳል።

Via:- #Mike_YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በ #ሩዋንዳ እያደረጉ ነው

#ኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ ከሚያዚያ 5 ቀን ጀምሮ የአራት ቀን የስራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ ተዘገበ።

ጉብኝቱ ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር እያደረጉ ያሉትን ጥረት ተከትሎ የተካሄደ ነው።  የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ መበጋቢት ወር  በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተፈራርመዋል።

እንደ ዘኒው ታይምስ ዘገባ፤ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ሰኞ ዕለት፤ ኪሚሁሩራ በሚገኘው የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት  ዋና መስሪያ ቤት ከጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ይህንንም ተከትሎ የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት በሰጠው መግለጫ፣ ጉብኝቱ "የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብርን” ለማስፋት "ቁልፍ ዕድል" መሆኑን በመግለጽ ውይይቶቹ "በመከላከያና በሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች  አዲስ የትብብር መስኮች" ላይ ያተኮሩ ናቸው ብሏል።

ፌልድ ማርሻል ብርሃኑ  የኪጋሊ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሙዚየምን እንደሚጎበኙ ዘኒው ታይምስ ዘግቧል። የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ በመጋቢት ወር ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት ልዑካቸው በ #ቢሾፍቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም በወቅቱም ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በወታደራዊ አቅም ግንባታ ስልጠና፣ በተሞክሮ ልውውጥ፣ ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና በሌሎችም ተያያዥነት ባላቸው ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁40👍196👎2🔥2