የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እስካሁን 200 ያህል አባላቶቼ ታሰረቡኝ ሲል አማረረ።
በኦሮምያ ክልል የሚንቀሳቀሱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በአንዳንድ ዞኖች ጽ/ቤታቸዉ በመዘጋቱ የፓርቲያቸዉ ሕልዉና አደጋ ላይ መዉደቁን አስታዉቀዋል። የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና የፓርቲ አባላት እስራት ከአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በፊትም ነበረ ሲሉ ተናግረዋል።በተለይ በወረዳ የሚገኙ ጽ/ቤቶቻችን ተዘግተዉብናል ያሉት ዶ/ር መረራ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የታሰሩ አባላቶቻችን ጉዳይ ይጣራልን ብለን ደብዳቤ አስገብተናል ብለዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃለ አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው የኦነግ ዘጠኝ የሥራ አስፈፃሚ አባልት በመታሰራቸዉ፤ ፓርቲዉ በሙሉ አቅሙ እየተንቀሳቀሰ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።
#DW
@YeneTube @FikerAssefa1

የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን የነፃ ዝውውር ማስፈፀሚያ መመሪያ ይፋ አደረገ፡፡
የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝ በመከሰቱ ተማሪዎች በነፃ እንዲዛወሩ የተወሰነውን ውሳኔ ተክትሎ የወጣው መመሪያ ለሁሉም የክልልና የከተማ አስተዳደሮች መላኩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በመመሪያው እንደተገለፀው የነፃ ዝውውር የሚደረግላቸው በ2012ዓ.ም የ1ኛ ወሰነ ትምህርታቸውን ተከታትለው የወሰዱና ውጤታቸው በሮስተር የተመዘገበ መሆኑ የተረጋገጠላቸው
እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ የማታ ተማሪዎች የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት ፈተና የወሰዱ ከሆነ ወደ ቀጣዩ ክፍል የሚዛወሩ ይሆናል በሁለተኛ ደረጃ ከ 9-12ኛ ክፍል የሚማሩ የማታ ተማሪዎች ደግሞ አንድን ክፍል ለማጠናቀቅ ሦስት ሴሚስተር የሚጠበቅባቸው በመሆኑ የመጀመሪያውን ተርም ማጠናቀቃቸው ከተረጋገጠ በአዲሱ የትምህርት ዘመን በጀመሩት ክፍል ወደ ሦስተኛ ተርም እንዲሸጋገሩ ተደርጎ የማካካሻ ስራ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
የተማሪ ሪፖርት ካርድን በተመለከተ የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ውጤታቸውን መመዘገብና በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ዓምድ ላይ በኮቪድ 19 ወረርሽን ምክንያት ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ወደ ቀጣዩ ክፍል በነፃ ተዛውሯል/ራለች የሚል ተጽፎበት ለተማሪዎች መደረስ እንዳለበት ተገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደም ከክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት ከ8ኛ እና 12 ክፍል በስተቀር ሁሉም ተማሪዎች በነፃ ወደ ቀጣይ ክፍል እንዲዛወሩ ተደርጎ የማካካሻ ትምህርት እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

YeneTube
በሊባኖስ ቤሩት ዋናው ወደብ ዛሬ በደረሰ ከፍተኛ ፍንዳታ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተገለፀ። በተጨማሪም በርካታ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፣ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ይኑሩ አይኑሩ የታወቀ ነገር የለም። የፍንዳታው ምክንያት ምን እንደሆነ የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም ፣ ከርችት ዴፖ የተነሳ ሳይሆን እንዳልቀረ ብሉምበርግ የሀገሪቱን ማዕከላዊ ቴሌቪዥን ጠቅሶ ዘግቧል። @YeneTube @FikerAssefa1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update
በሊባኖስ ቤይሩት በደረሰው ፍንዳታ እስከአሁኗ ሰዐት ድረስ 63 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ3000 የሚበልጡ ሰዎች መጎዳታቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa1
በሊባኖስ ቤይሩት በደረሰው ፍንዳታ እስከአሁኗ ሰዐት ድረስ 63 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ3000 የሚበልጡ ሰዎች መጎዳታቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa1
#update
በትናንትናው ዕለት በሊባኖስ ቤይሩት የደረሰው ፍንዳታ ምክንያት በወደቡ አቅራቢያ በሚገኝ መጋዘን ሲደረግ የነበረ የብየዳ ስራ ነው ተብሏል።የብየዳ ስራው ሲከናወን በተፈጠረው እሳት 2750 ቶን ከሚጠጋ አሞኒያ ናይትሬት (የተሰኘው በአፈር ማዳበሪያና ቦምቦች ውስጥ የሚገኝ ተቀጣጣይነት ባህርይ ያለው ቁስ) ጋር በመያያዙ ፍንዳታው እንደተከሰተ ሮይተርስ ዘግቧል።እስካሁን በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 78 የደረሰ ሲሆን፣ 4000 ያህል ሰዎች ተጎድተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa

በኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ ባለው አንድ ሳምንት ከሰሞኑ እየጣለ ያለው ዝናብ አሁንም በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ትንበያና ምርምር ማዕከል (ICPAC) አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
በአዲስ አበባ ልዩ የመሬት ኦዲትና ምዝገባ እንደሚጀመር ምክትል ከንቲባው አስታወቁ!
በ2013 ዓ.ም. ዓብይ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ዋናው በከተማዋ የመሬት ይዞታ ላይ ልዩ ኦዲት ማካሄድና የመሬት ምዝገባ ማከናወን እንደሚሆን፣ የአዲስ ከበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ይፋ አደረጉ።ም/ል ከንቲባው ይህንን ይፋ ያደረጉት ከሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ሰባተኛ ዓመት ሦስተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው።የከተማ አስተዳደሩ ትልቅ ሀብት መሬት እንደሆነ የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፣ በሚከናወነው የመሬት ኦዲት ከዚህ ቀደም ያላግባብ የተወሰዱና ለረዥም ጊዜ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ይዞታዎች እንዲመለሱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
በሚደረገው የመሬት ኦዲትና ምዝገባ ተለይተው ለከተማ አስተዳደሩ እንዲመለሱ የሚደረጉት ይዞታዎች፣ ለሌላ ልማት እንደሚውሉ አስታወቀዋል።በኦዲት እንዲመለሱ የሚደረጉት ይዞታዎች፣ በተለይም የከተማዋ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል ጥቅም ላይ እንዲውሉ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አስረድተዋል።
‹‹የጋራ መኖሪያ ቤት ለማግኘት ተመዝግበው ለበርካታ ዓመታት እየተጠባበቁ የሚገኙ ነዋሪዎች፣በማኅበር ተደራጅተው የራሳቸውን የጋራ መኖሪያ ሕንፃ እንዲገነቡ ይደረጋል፤›› ብለዋል።በአሁኑ ወቅትም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን የመኖርያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ 125 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን የተናገሩት ም/ል ከንቲባው፣እየተገነቡ ከሚገኙት ቤቶች መካከል 96 ሺሕ የሚሆኑት በ28/80 የቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ሥር የተያዙ ሲሆን፣ቀሪዎቹ ሁለት ሺሕ ቤቶች ደግሞ በ40/60 የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ሥር የተያዙ መሆናቸውን አስረድተዋል።
Read more👇👇👇
https://telegra.ph/-08-05-219

#Update ፖሊስ የፍርድ ቤት ውሳኔን አልቀበልም አለ! የፌደራል የመጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት የኢዜማ ስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑትን ሒሩት ክፍሌን በዋስ እንዲፈቱ የወሰነውን ፖሊስ እንደማይቀበለው አስታወቀ። Via Addis Maleda @YeneTube @FikerAssefa
የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
ከሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓ·ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት ሂሩት ትላንት ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ·ም የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ ፖሊስ አልፈፅምም ብሎ ሂሩትን በእስር ያቆያቸው ሲሆን ዛሬ የስር ፍርድ ቤት ያስከበረላቸውን ዋስትና ይግባኝ ለማለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ያቀርባቸዋል።
Via Ethzema

የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ እየሞላ በመምጣቱ ውሃ በየደረጃው ለመልቀቅ የሚያስችል የሙከራ ስራ መከናወኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል፡፡
ከግድቡ የሚለቀቀው ዉሃ ወደፊት በታችኛው ተፋስስ ላይ ጎርፍ እንዳይከሰት ለመቆጣጠር እና ውሃውን በተመጠነ መልኩ በመልቀቅ በክረምቱ መጨረሻ ላይ ግድቡ ሙሉ እንዲሆን ለማድረግ በማስፈለጉ እንደሆነ የጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃብታሙ ሰሙ ገልፀዋል፡፡ውሃ ከግድቡ በየደረጃው እንዲለቀቅ መደረጉ በተፋሰሱ ውስጥ የጎርፍ መቆጣጠር ስራ ለማከናወን እንደሚያግዝም ጠቁመዋል፡፡ግድብ የመጣውን ጎርፍ ሁሉ እንደመጣ ላለመልቀቅና የተመጠነ የውሃ ፍሰት እንዲኖር ለማድረግም በየጊዜው እየተቆጣጠሩ መልቀቅ ክረምቱ ሲጠነክር ሊከሰት የሚችለውን ጎርፍ ለመቆጣጠር እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡
እንደ አቶ ሃብታሙ ገለፃ ግድቡ መያዝ ከሚችለው 15 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 12 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የያዘ ሲሆን በሴኮንድ በአማካኝ 800 ሜትር ኪዩብ ውሃ ለመልቀቅ እቅድ ተይዟል፡፡ግድቡ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ከባህር ጠለል በላይ 882 ሜትር ላይ በመድረስ ከፍተኛ ውሃ መያዝ የቻለ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ከዚህ መጠን ጋር ተመሳሳይ ውሃ መያዙን ተናግረዋል፡፡ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከሦስት ወር አስቀድሞ ከባህር ጠለል በላይ 892 ሜትር ላይ በመድረስ ሊሞላ እንደሚችል ያመለክታል፡፡ውሃው ከአሁኑ ካልተለቀቀ ነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ሙሉ በሙሉ ሊሞላ እንደሚችልም ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
#AMN

በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ 32ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ!
በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በተለያዩ ወረዳዎች 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸዉን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ማስተባባሪያ ጽህፈት ቤት ገለፀ።በአፋር ክልል ክረምቱን ተከትሎ እየጣለ ባለው ዝናብ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በ6 ወረዳዎች 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን በፅህፈት ቤቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲን ገልፀዋል።ዳይሬክተሩ እንዳሉት በክልሉ በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ የሚገኙ 7 ወረዳዎች ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት ተጋላጭ ናቸው።ይህን ችግር ለመቅረፍ የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልሉ መንግስት አካላት ጋር በመቀናጀት የጎርፍ መከላከል ስራዎች ሲያከናውን ቢቆይም የዘንድሮው ክረምት ጠንከር ያለ በመሆኑ በ6 ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ አጋጥሟል።
ጎርፉን ተከትሎ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ግምቱ በመጣራት ላይ የሚገኝ ሰብልና እንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።እስከ አሁን ድረስ በአይሳኢታ ወረዳ በጎርጉም ሁለት ቀበሌዎች ለሚገኙ ከ1 ሺህ100 በላይ ሰዎች የፌዴራል መንግስት በሄሊኮፕተር ምግብ የማቅረብ ስራዎች በማከናወን ላይ ነው።ከተፈናቃዮች መካከል 17 ሺህ 450 ሰዎች በአይሳኢታ ወረዳ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች ናቸው።በተለይም ካለፈው እሁድ ጀምሮ በወረዳው ኮሎዱራና ገለአሊ ቀበሌዎች የአዋሽ ወንዝ ሰብሮ ወደ ቀበሌዎቹ በመግባጋቱ 1ሺህ 126 ሰዎች በውሃ ተከበው ይገኛሉ ብለዋል።
ለጊዜው ክልሉ የምግብና ምግብ-ነክ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ የህይወት አድን እርዳታ ለማቅረብ እየሞከረ ቢሆንም ከችግሩ ስፋትና አሳሳቢነት አንፃር የፌዴራል መንግስት እገዛ መጠየቁን አቶ አይዳሂስ ተናግረዋል።በመሆኑም ከሰላም ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው የፌዴራል አካላት ጋር በመተባባር ከዛሬ ጀምሮ በሄሊኮፕተር አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት ስራዎችን ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል።በውሃ የተከበቡት ሰዎች በሔሊኮፕተርና በሞተር ጀልባ በማውጣት ወደ ሌላ አካባቢዎች ለማስፈር የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም ከዳይሬክተሩ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል።በአፋር ክልል በታችኛውና መካከለኛው አዋሽ 63 ሺህ ሰዎች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ሲሆኑ 44 ሺህ ሰዎች በመፈናቀል ስጋት ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።
#ENA

#ችሎት
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳ እና ሌሎች 2 ሰራተኞች በሶስት ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ መስጠቱን ጠበቃቸው አቶ ከዲር ቡሎንን ጠቅሶ የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ከሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓ·ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት ሂሩት ትላንት ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ·ም የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ ፖሊስ አልፈፅምም ብሎ ሂሩትን…
#ችሎት
የፖሊስን የይግባኝ አቤቱታ የሰማው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ትላንት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝን ሳይፈጸም ተጠርጣሪዎችን በእስር አቆይቶ ይግባኝ መጠየቁ ወንጀል ነው ሲል ለፖሊስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
Via ETHzema

በቤይሩት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ጉዳት እየተጣራ ነው – ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
በሊባኖስ መዲና ቤይሩት፤ ትላንት ማክሰኞ በደረሰው ከፍተኛ ፍንዳታ ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደተጎዱ በመጣራት ላይ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ፍንዳታው በደረሰበት አቅራቢያ ባለው የመኖሪያ ሰፈር፤ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ያመለከቱት በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ምን ያህሉ በአደጋው እንደተጎዱ ለማወቅ መቸገራቸውን ገልጸዋል።ቤይሩትን ባናወጠው ከፍተኛ ፍንዳታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር መቶ መድረሱን የሊባኖስ ቀይ መስቀል ማህበር አስታውቋል።በአደጋው የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ አራት ሺህ ማሻቀቡንም የማህበሩ ሃላፊ ዛሬ ጠዋት ይፋ አድርገዋል።በርካታ ኢትዮጵያውያን በቤት ሰራተኝነት እና በሌሎችም ስራዎች በተሰማሩባት የቤይሩት ከተማ፤ በኢትዮጵያውያን ላይ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ እስካሁን በቁጥር የተጠናቀረ መረጃ አልወጣም።
Via Ethiopia Insider

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፤ በጆምባ ሁሴን መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው 6 ተከሳሾች፤ በ4 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ዛሬ ማዘዙን ጠበቃቸው ገልጸዋል።ፖሊስ በዛሬው ችሎት ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ቢጠይቅም ችሎቱ ውድቅ ማድረጉንም ተናግተዋል። በዋስትና ከእስር እንዲወጡ በፍርድ ቤት የተወሰናላቸው፤ ጆምባ ሁሴን፣ ኢብሳ ጅማ፣ መሐመድ ጅማ፣ ኢብራሂም አብዱልጀሊል፣ ኪያር መሐመድ እና አለማየሁ ገለታ የተባሉ ተጠርጣሪዎች እንደሆኑ ጠበቃቸው አቶ ከዲር ቡሎ ዘርዝረዋል።

በአየር ሁኔታ ምክንያት አውሮፕላኖች በጅቡቲ እና ድሬዳዋ ለማረፍ ተገደዱ!
ትላንት ሐምሌ 28 እና ዛሬ የሚታየው ጭጋጋማ አየር ወደ ቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ለማረፍ ይመጡ የነበሩ የተወሰኑ አውሮፕላኖች ላይ እንቅፋት በመፍጠሩ አቅጣጫቸውን በመቀየር ወደ ጅቡቲ እና ድሬዳዋ ለማረፍ መገደዳቸው ተሰማ፡፡ምንጮች እንዳሉት ከጅቡቲ ጋር የአየር ማረፊያዋን በአማራጭ አየር ማረፊያነት ለመጠቀም ባለው ስምምነት መሰረት አንዳንድ ገቢ በረራዎች በመዳረሻቸው ቦሌ ማረፍ ባለመቻላቸው ወደ ጎረቤቲቱ አገር እንዲሁም ድሬዳዋ እንዳረፉ ጠቅሰዋል፡፡የነበረው ተለዋዋጭ የአየር ሁኔታ የተወሰኑ አውሮፕላኖች አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ማስገደዱን ያስታወቁት ምንጮች አብዘኞቹ የትላንት በረራዎች ማምሻውን እና ዛሬ ማለዳ ካረፉባቸው ቦታ ወደ መዳረሻቸው ተመልሰዋል ብለዋል፡፡ትላንት አየር መንገዱ የአየር ፀባዩ እክል ለተፈጠረ የበረራ መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቆ ሌሎች አማራጭ ማረፊያዎች እንደሚጠቀም አስታውቆ ነበር፡፡
#Capital

በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ ማስክ ሳያደርጉ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን በመለየት ፍርድ ቤት ማቅረብ ሊጀምር መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ ለኮቪድ 19 የሚያደርገው ጥንቃቄ ላይ መዘናጋት በመታየቱ ጠንከር ያለ ቁጥጥር ጀምሪያለሁ ብሏል፡፡በኮሚሽኑ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ እንዳሉት በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ ቢሆንም በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታየው መዘናጋት ግን ዋጋ ያስከፍለናልና ይህ ከመሆኑ ሰዎች በቂ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እየሰራን ነው ብሏል፡፡የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ተብለው የተቀመጡትን በተለይ ማስክ አድረገው የማይንቀሳቀሱ ሰዎችን በመመዝገብ ተደጋጋሚ የሆኑትን በመከታተል በአስቸኳይ አዋጁ የተቀመጠውን ቅጣት እንደሚጣልባቸውም ነው ዋና ኢንስፔክተሩ የተናገሩት፡፡
ከዚህ ቀደም ማስክ ሳያደርጉ የሚንቃቀሱ ሰዎችን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንዲታሰሩ ይደረግ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ ሰዎችን ማሰር ስለማይቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ አዋጁን በተደጋጋሚ በሚጥሱት ላይ ግን እርምጃ ለመወስድ አሰራሩ መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገጉ የመብት እገዳዎችን፣ እርምጃዎችን፣ የተሰጠ መመሪያ ወይም ትዕዛዝን ሆን ብሎ የጣሰ ማንኛውም ሰው እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺህ ብር እስከ ሁለት መቶ ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ እንደሚችል በአዋጁ መቀመጡ አይዘነጋም።
Via Ethio FM

ግብፅ በግድቡ ዙሪያ በቅርቡ የተጀመረውን ድርድር ለጊዜው ጥላ የመውጣት ሀሳብ እንዳላት ገለፀች!
ግብፅ በግድቡ ዙሪያ በቅርቡ የተጀመረውን ድርድር ለጊዜው ጥላ የመውጣት ሀሳብ እንዳላት ገልፃለች። ይህን ለማድረግ ያሰበችው በግድቡ አሞላል ሂደት በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን የድርድር ሀሳብ መጀመሪያ የውስጥ ምክክር ላድርግበት በሚል ነው የተባለ ሲሆን የግብፅ የውሃ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያ ያቀረበችው አዲስ የመደራደሪያ ረቂቅ ሀሳብ ህግና መመሪያን ያከበረ አይደለም ሲል ገልፅዋል፡፡
ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ በኩል የቀረበው ምክረ ሀሳብ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችል ህጋዊ መሰረት ይጎድለዋል የሚል ቅሬታ አሰምቷል፡፡ በግድቡ ዙሪያ አንድ አቋም የሌላት ሱዳን በበኩሏ የግድቡ የደህንት ጉዳይ ያሳስበኛል የሚል ሀሳብ ማንሳት ጀምራለች ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት በተካሄደው ስብሰባ የተደረሰበትን ስምምት የሚጥስ ሀሳብ ቀርቧል የሚል ምክኒያት በማቅረብ ግብፅና ሱዳን ለጊዜው የአሁኑ ውይይት እንዲቆም ፍላጎት እንዳላቸው አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
Via Addis Zeybe

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 459 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 319 የላቦራቶሪ ምርመራ 459 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 336 ደርሷል።በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 358 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 8 ሺህ 598 ሆኗል።በዛሬው ዕለት የ13 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 356 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት 185 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ይገኛሉ፤ 11 ሺህ 380 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር እንደሆነ ተገልጿል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 459 ሺህ 746 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሂሩት ክፍሌ በ6 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈቱ።ፖሊስ ዋስትናውን በመቃወም ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢልም፤ ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
#የችሎት_ውሎ
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፤ ዛሬ ችሎት ፊት በቀረቡት፣ በሐምዛ ቦረና እና በ8 የጃዋር መሐመድ ጠባቂዎች የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ሐምሌ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃቸው አቶ ምስጋኑ ሙለታ ገልጸዋል::
Via:- Ethiopia insider

በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ትላንት በደረሰው ከፍተኛ ፍንዳታ የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa