አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ቀጥጥር ስር ውለዋል‼️
ፖሊስ አቶ ተስፋዬ ኡርጌን በተጨማሪነት በሰብዓዊ #መብት_ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
መርማሪ ፖሊስ የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ አቶ ተስፋዬ ኡርጌን በተጨማሪነት በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል #ችሎት ቀርበዋል።
መርማሪ ፖሊስም የቀድሞውን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ በተጨማሪነት በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
አቶ ተስፋዬ የደህንነት መምሪያ ሀላፊ ሆነው ሲሰሩ ሰዎችን በሽብር ተጠርጥራችኋል በሚል በስውር እስር ቤት በማሰርና በማሰቃየት፥ እርቃናቸውን በካቴና አስረው ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በማቆየት፣ ግለሰቦችን ባልተገባ መልኩ ለሽብር መልምለው ወደ ኤርትራ በመላክ እንደጠረጠራቸው ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።
ከዚህ ባለፈም በሽብር ከተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ገንዘብ በመቀበል እና በሀዋላ ከተጠርጣሪዎች ላይ ህገ ወጥ ገንዘብ በመቀበል በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁም ብሏል መርማሪ ፖሊስ።
ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅም 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
አቶ ተስፋዬ በሰጡት ምላሽ እርሳቸው የተጠረጠሩበት ጉዳይ በግልጽና በተናጠል እንዳልቀረበ በመግለጽ፥ እርሳቸውን ለመያዝ በቂና ዝርዝር ጉዳይ አለመኖሩን አስረድተዋል።
በተጨማሪም ሀብት የመፍጠር ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሃብት ማፍራታቸውንና ለአራት ወራት ፍርድ ቤት እየተመላለሱ መሆኑን በመጥቀስ፥ ሃብት ከማፍራት ጋር ተያይዞ ሀምሌ 5 ቀን 2010 ዓ.ም ቤታቸው መበርበሩንና ምርመራው በወቅቱ ማለቅ ነበረበት ብለዋል።
አሁን ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜም ሊሰጥ አይገባም በማለት ተቃውመዋል።
ችሎቱም አቶ ተስፋዬ በተጨማሪነት የተጠረጠሩበት ወንጀል በተብራራ መልኩ እንዲቀርብና ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀን በመፍቀድ ለህዳር 24 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ምንጭ:- ፋና ብሮድካስቲንግ
@YeneTube @Fikerassefa

#ችሎት
ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ አብዲ መሀመድ የክስ መዝገብ እንዲሻሻል ብይን ሰጠ።
በእነ አቶ አብዲ መሀመድ የክስ መዝገብ የአቶ አብዲ መሀመድ እና ዘምዘም ሀሰን ክስ እንዲሻሻል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ብይን ሰጠ፡፡የሌሎቹን ተከሳሾች መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው ችሎቱ፤ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ተቀብሏል፡፡ ተከሳሾቹ ድርጊቱን አልፈጸምንም ሲሉ ክደው በመከራከራቸው አቃቤ ህግ ምስክሮቹ እንዲሰሙለት አመልክቷል፡፡ ፍርድቤቱ ባለፈው ሳምንት መቃወሚያ ባስገቡ ተከሳሾች ጉዳይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፤ የችሎቱ አንድ ዳኛ በእክል ምክንያት በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ብይኑን ለመስጠት ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
-Walta
@YeneTube @FikerAssefa

በነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መስማት ጀመረ፡፡
በነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ዛሬ ረፋድ ላይ የሁለት ምስክሮችን ቃል ተቀብሏል፡፡በክስ መዝገቡ የተከሰሱ 48 ተጠርጣሪዎች ናቸው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት፡፡ ዛሬ መቅረብ ከነበረባቸው 17 ምስክሮች የቀረቡት ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ ተጨማሪ ምስክሮችን ቃል ለመስማት ፍርድ ቤቱ ለነገ ነሐሴ 22/2011 ዓ.ም 3፡00 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡የተጠርጣሪ ጠበቆች ሁሉም ምስክሮች ተሟልተው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ ይህ ባለመሆኑ ደንበኞቻቸው እየተጉላሉ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡ ቀሪዎቹ ምስክሮች የማይቀርቡ ከሆነም ቃላቸውን የሰጡትን ምስክሮች ፍርድ ቤቱ ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ እንደሚገባው ነው ጠበቆቹ የጠየቁት፡፡
ምንጭ: አብመድ

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳ እና ሌሎች 2 ሰራተኞች በሶስት ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ መስጠቱን ጠበቃቸው አቶ ከዲር ቡሎንን ጠቅሶ የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።
@YeneTube @FikerAssefa1

YeneTube
የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ከሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓ·ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት ሂሩት ትላንት ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ·ም የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ ፖሊስ አልፈፅምም ብሎ ሂሩትን…
#ችሎት
የፖሊስን የይግባኝ አቤቱታ የሰማው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ትላንት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝን ሳይፈጸም ተጠርጣሪዎችን በእስር አቆይቶ ይግባኝ መጠየቁ ወንጀል ነው ሲል ለፖሊስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
Via ETHzema

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፤ በጆምባ ሁሴን መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው 6 ተከሳሾች፤ በ4 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ዛሬ ማዘዙን ጠበቃቸው ገልጸዋል።ፖሊስ በዛሬው ችሎት ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ቢጠይቅም ችሎቱ ውድቅ ማድረጉንም ተናግተዋል። በዋስትና ከእስር እንዲወጡ በፍርድ ቤት የተወሰናላቸው፤ ጆምባ ሁሴን፣ ኢብሳ ጅማ፣ መሐመድ ጅማ፣ ኢብራሂም አብዱልጀሊል፣ ኪያር መሐመድ እና አለማየሁ ገለታ የተባሉ ተጠርጣሪዎች እንደሆኑ ጠበቃቸው አቶ ከዲር ቡሎ ዘርዝረዋል።
Via Ethiopia Insider