YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአፍሪካ ህብረት የሚመራውና ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይቀጥላል!

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለ11 ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ከሁለት ሳምንታት በፊት እ.አ.አ ሐምሌ 13/2020 የተቋረጠው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ከሳምንት በፊት ሊቀጥል የነበረ ቢሆንም በሱዳን በኩል በቀረበው ለአንድ ሳምንት የይዘግይልኝ ጥያቄ መሠረት ለአንድ ሳምንት ዘግይቷል፡፡ ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ለቀጣዩ አንድ ሳምንት ድርድሩ ይቀጥላል፡፡የዚህ ሳምንቱ ድርድር ቀደም ሲል ከተካሄደው የ11 ቀናቱ ድርድር በኋላ ለመሪዎች በቀረበው ሰነድ መሠረት መሪዎቹ ባስቀመጠጡት አቅጣጫ የሚቀጥል ሲሆን ኢትዮጵያ እንደ ከዚህ ቀደሙ ፍትሓዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ ድርድሩን ለመቋጨት ትሠራለች፡፡

#MoWIEE
@YeneTube @FikerAssefa1