YeneTube
120K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#COVID-2019_update

የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከስድሳ ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1367 ደርሷል።

Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዳሴው ግድብ ድርድር አቅጣጫውን በመሳት ትኩረቱን የውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ ማድረጉን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል፡፡ ሱዳን አቋሟን ቀይራ እንደ አሜሪካ እና ዐለም ባንክ አጋርነቷን ለግብጽ እንዳደረገች ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ተናግረዋል፡፡ ወደ አደራዳሪነት የተቀየሩት አሜሪካ እና ዐለም ባንክ ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ ነው፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው ዋና መንገድ ዛሬ ከቀትር በኋላ በመተማ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተዘግቶ ውሏል። መንገዱ የተዘጋው በትናንትናው ዕለት "የሱዳን ወታደሮች/ታጣቂዎች" በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶችን ዘርፍ ወስደዋል ከተባለ በኋላ መሆኑን ሰምተናል።

@YeneTube @Fikerassefa
የጭልጋ ወረዳ ፍ/ቤት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ አይከል ከተማ መግቢያ አካባቢ የከባድ መኪና አሽከርካሪ እና ረዳት ላይ ዕገታ ፈጽመዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ5 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጡ ወሰነ።

ምንጭ:Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ሶማሊያ ለጋዜጠኞች እጅግ አደገኛ ሀገር ተባለች!

በሶማሊያ ሐሳብን የመግለጥ እና የፕሬስ ነጻነት ማነቆ መደረጉ ከዕለት ዕለት እየጠበቀ ነው ሲል የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪው ዓለም አቀፉ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስጋቱን ገለጠ። ፕሬዚደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ሥልጣን ከያዙበት ካለፉት ሦስት ዓመታት አንስቶ ኹኔታው በሶማሊያ እጅግ መበላሸቱን ዓለም አቀፉ ድርጅት በዘገባው አትቷል።

በሶማሊያ የሚገኙ ጋዜጠኞች ከፍተኛ ጫና ይደረግባቸዋል፤ የቦንብ ጥቃት ሰለባ ይኾናሉ፣ ይደበደባሉ፣ ጥቃት እና እስር ይገጥማቸዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ተናግሯል። በሶማሊያ ኹኔታዎች ለጋዜጠኞች እጅግ አደገኛ መኾናቸው ተባብሷል ሲል ዓለም አቀፍ ድርጅቱ ስጋት እንዳደረበትም የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ጋዜጠኞች ላይ ጥቃት የሚሰነዘረው በአልሸባብ ታጣቂዎች እንዲሁም በመንግሥት ወታደሮች መኾኑም ተገልጧል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አስጠነቀቀ

ከተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ውጭ የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስጠነቀቀ።

የመገናኛ ብዙሃን የምርጫ ዘገባ ተደራሽነትና ሚና ላይ ቦርዱ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ነው።
በአሁኑ ወቅት ፓርቲዎች ህጉ ከሚፈቅደው ውጭ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸውን በተመለከተ የውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄ አንስተዋል።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ቦርዱ በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የመጨረሻ የምርጫ ሰሌዳ በማውጣት እንደሚያሳውቅ ገልጸው፣ ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ህግ የማስከበር ስራው ወደ ተግባር ይቀየራል ብለዋል፡፡

የምርጫ ሰሌዳው የመጨረሻ ቀን ከተቆረጠ በኋላ "እንደ እስከ ዛሬው ተቻችለን የምናልፈው ጉዳይ ሳይሆን እርምጃ የምንወሰድበት ነው" ሲሉም ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ምክክሩ በሚዲያና የመራጮች ትምህርት፣ የሚዲያ ሚና በመራጮች ትምህርት የውጭ ተሞክሮ፣ ምርጫ ቦርድና በመራጮች ትምህርት ዙሪያ ያለው ዝግጅት እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ ስነ ምግባርና አሰራርን ለመደንገግ በወጣ መመሪያ ላይ እንሚያተኩር ተገልጿል።
ኢዜአ እንደዘገበው የምርጫ ቦርዱ ባወጣው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት 'የምረጡኝ ዘመቻ' ጊዜ ከሚያዚያ 27 እስከነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ነው።

ምንጭ፡-ዋልታ
@Yenetube @FikerAssefa
#Tepii University ላለፉት 2 ሳምንታት የመማር ማስተማር ክንውኑን አቋርጦ የቆየው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የካቲት 9/2012 ወደ መደበኛ ስራው እንደሚመለስ አስታወቀ።
@YeneTube @Fikerassefa
ቻይና የኮሮና ቫረስ ስርጭትን ከመቆጣጠር አንጻር ለውጥ እያሳየች አለመሆኑን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ እንዳለው የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለው ከቻይና ውጪ ባሉ ሃገራት አይደለም፡፡ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበበት በጃፓን መርከብ ላይ ሲሆን 44 ጉዳዮች ተመዝግበዋል፤ይህም በቫይረሱ የተጠረጠሩትን ቁጥር ወደ 218 አሳድጎታል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳው በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የሚከሰት ሞትን መቀነስ ላይ ለውጥ የለም፡፡በሁቤይ ግዛት ብቻ እስከ ትናንት ድረስ 242 ሰዎች ሞተዋል፡፡በግዛቲቱ ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸውን ያስታወሱት በአለም የጤና ድርጅት ድንገተኛ የጤና ጉዳዮች ፕሮግራም ሃላፊ ማይክ ራዬን፤ ይህ የወረርሽኑ ስርጭት ላይ ተፈላጊ ለውጥ መምጣቱን አያመላክትም ብለዋል፡፡

ከቻይና ውጪ ሁለት ሞቶች የተመዘገቡ ሲሆን በ24 ሃገራት 447 በቫይረሱ መጠርጠራቸው ሪፖርት መደረጉንም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ጃፓን አንዲት የ80 አመት ዜጋዋ በቫይረሱ መሞታቸውን ትናንት አስታውቃለች፡፡አሜሪካ ደግሞ ወረርሽኑ በሰሜን ኮሪያ ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋት እንዳላት ገልጻ፤ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችና አሜሪካ እርዳታ እንዲያደርጉ እንደምታመቻች ማስታወሱን ቢቢሲን ጠቅሶ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ለቤተክርስትያን መስሪያ የሚውል የግንባታ ቦታ ጥያቄዋ መልስ ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለፁት ዛሬ ምሽት በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ተወካዮች ጋር በአቡዳቢ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፃ ቤተክርስትያኗ ለብዙ አመታት ስታቀርበው የነበረው ይህ ጥያቄ አሁን ላይ ምላሽ አግኝቷል።የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች መንግስት እና በሀገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰሩት ሰፊ ስራ ውጤቱ መምጣቱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱን አካላት አመስግነዋል፤ በሌሎች እምነቶች የሚነሱ መሠል ጥያቄዎችም በጊዜያቸው መልስ እንደሚያገኙ ጨምረው ገልፀዋል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይህንን ጥያቄ ለሶስት አስርት አመታት ያህል ስታቀርብ መቆየቷን መረጃዎች ያመለክታሉ።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ አዲሱን አርማውን ይፋ አደረገ!

የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።ቦርዱም አዲሱን አርማውን በዚህ ወቅት ይፋ አድርጓል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአገር አቀፍ ምርጫ የግዜ ሰሌዳ ፀድቆ በዛሬው ጉባኤ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#ምርጫ2012
#Election2020
@YeneTube @FikerAssefa
የመራጮች ምዝገባ ከሚጀመርበት ቀን ጀምሮ ክፍት የሚሆን አዲስ የሚዲያ ማእከል በቦርዱ ይቋቋማል፡፡ በቦርዱ የሚዘጋቸው ይህ ዴስክ እስከ ምርጫው ውጤት ድረስ ፈጣን መረጃዎችን ያደርሳል፤ እንደ ሶሊያና ሸመልስ ገለፃ፡፡

#ምርጫ2012
#Election2020

Via አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩ የመረጃ እና የመገናኛ መሳሪያዎች ተያዙ!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩ የመረጃ እና የመገናኛ መሳሪያዎች መያዙን አስታወቀ።የተያዙት የቴሌኮም ማጭበርበር ለማከናወን የሚያስችሉ 6 መሳሪያዎች (Sim box) መያዙንም ነው የገለፀው።በዚህም ከ68 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን በኤጀንሲው የሴኩሪቲ ክሊራንስ አገልግሎት ማዕከል ኃላፊ አቶ መስፍን ሙሉነህ ገልጸዋል።ባለፉት 6 ወራት ከቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች በተጨማሪ ለስለላ አገልግሎት የሚውሉ 60 ካሜራዎችን ሀገር ውስጥ ከመግባታቸው በፊት መያዛቸውን አቶ መስፍን አስታውቀዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲስ አበባና በተወሰኑ ክልሎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትራፊክ አስተዳደር ስርዓት እንደሚዘረጋ ተነገረ፡፡ይህ የተነገረው የቀድሞው የተቋሙ ሚንስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ለአዲሱ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በተቋሙ እየተከወኑ ስላሉ ስራዎች ሪፖርት ሲያቀርቡ ነው፡፡በሪፖርታቸውም ሀገር አቀፍ የቪዲዮ ኮንፈረንስ እና የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችን ጨምሮ የኒኩሊየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የተሄደውን ርቀት አሳይተዋል ተብሏል፡፡ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለተለያዩ አገልግሎቶች ለመጠቀም የተጀመረው ፕሮጀክትም በሪፖርቱ መካተቱን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠቅሶ የዘገበው ሸገር ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትየጵያ ንግድ ባንክ የ2019 የግሎባል ቢዝነስ አውት ሉክ ሽልማት አሸናፊ ሆነ።

የዘርፉን ሽልማት በማሸነፍም ከደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ ባንኮች በመቀጠል በአፍሪካ ሶስተኛው ባንክ መሆን ችሏል።

ባንኩ በ77 ዓመታት ጉዞው ዓለም ዓቀፍ ሽልማት ሲያሸንፍ የመጀመሪያው መሆኑንም አስታውቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የካቲት 6፣ 2012 ከሰዓት በ8፡00 (በአካባቢው የሰዓት አቆጣጠር በ9፡00) ሰዓት ዱባይ ወደሚገኘው ሸባብ አላሕሊ ስቴዲየም በማቅናት በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ ልዩ ልዩ ሀገራት ከሚኖሩ 15,000 ያህል ኢትዮጵያውያን ጋር ምክክር ያደርጋሉ።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም. በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ሚዲያዎች ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ ነቢያት በዛሬው መግለጫቸው በ33ኛው መደበኛው የመሪዎች ስብሰባ እና 36ኛው መደበኛው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የአገራችን ያንፀባረቀችውን አቋም እና የተገኙ ውጤቶች፣ አገራችን ከሌሎች አገሮች ጋር ስላካሄደቻቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች፣ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፖምፔዮ የሚቀጥለው ሳምንት የኢትዮጵያ ጉብኝትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇👇👇
https://telegra.ph/PressRelease-02-14
የ75 ዓመቱ ሰው ሊጥ ሰርቆ ታሰረ!

[አዲስ ዘመን ጋዜጣ እሁድ መጋቢት 26 ቀን 1963 ዓ.ም]

አስር ጊዜ የሌብነት ወንጀል ፈጽሞ የዘጠኝ አመት ተኩል ቅጣት ከተቀበለ በኋላ የተቦካ ሊጥ ከነባሊው ሰርቋል በመባል የተከሰሰው ሰው የፈጸመው ወንጀል በህግ ማስረጃ ስለተረጋገጠበት በአንድ አመት ከስድስት ወር እስራት እንዲቀጣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው አርብ ፈረደ፡፡አቶ ንጋቱ ፋንታ የተባለው ተከሳሽ የሚኖረው በአዲስ አበባ ከተማ የካ ሚካኤል አካባቢ ሲሆን ሌብነትን የዘወትር ሙያው በማድረግ የሰውን ቤት በሌሊት እየሰበረ ልዩ ልዩ የእቤት እቃዎችን በተደጋጋሚ ጊዜ ሰርቆ እንደነበር ፍርድ ቤቱ በቀረበለት ማስረጃ መሰረት ለማረጋገጥ መቻሉን ገልጿል፡፡የ75 ዓመቱ ሽማግሌ የተቦካውን ሊጥ ከነባሊው በሰረቀበት ዕለት ሁለት የቡና ሲኒና አንድ የስፌት አገልግልም ጨምሮ መውሰዱን ራሱ ለፍርድ ቤቱ በሰጠው ቃል አረጋግጧል፡፡

ተከሳሹ በየጊዜው በፍርድ ቤት የተወሰነበትን ቅጣት ተራምዶ የተደጋገመ ወንጀል መፈጸሙን ፍርድ ቤቱ ጠቅሶ፤ ከገሰጸው በኋላ የተከሳሹ ዕድሜ የገፋ ስለሆነ ቅጣቱን አሻሽሎለት በአንድ አመት ተኩል እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። እንዲሁም ከተከሳሹ ጋር የወንጀል ግብረ አበር ሆኗል በመባል የተከሰሰው ደበበ ጫላ ከዚህ ቀደም የሌባ ተቀባይ መሆኑ ቢረጋገጥም በአሁኑ ጊዜ የፈጽመው ወንጀል ከዚሁ ጋር ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ በአንድ አመት እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባሎቼና ደጋፊዎቼ በጅምላ እየታሰሩብኝ ነው አለ፡፡

እስሩ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ፖሊስ እንደሆነም ግንባሩ ዛሬ በፅህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እወቁልኝ ብሏል፡፡እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስም በኦሮሚያ ክልል 7 ዞኖች እና 26 ከተሞች 350 አባሎቹ፣ ደጋፊዎቹና ሌሎች ወጣቶች መታሰራቸውን በመግለጫው አክሏል፡፡ከእነዚህ ውስጥ የ174ቱ ስም ደርሶኛል ሲልም ዘርዝሯቸዋል፡፡

የምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ህጋዊ መሰረት በሌለው እና ቀነገደብ ባልተቀመጠለት ኮማንድ ፖስት እየተዳደሩ ይገኛሉም ብሏል፡፡የአካባቢዎቹ በኮማንድ ፖስት መተዳደር ነዋሪዎቹን ለግድያ፣ ዝርፊያ፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ወንጀሎች አጋልጧቸዋል ሲልም አክሏል።በምዕራብና ቄለም ወለጋ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ከተቋረጡ ከ1 ወር ተኩል በላይ እንደሆነ የግንባሩ ባለስልጣናት በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ አጠቃላይ ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት የነገሮች መክፋት አሳስቦኛል ሲልም ኦነግ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡መንግስት ለችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደግሞ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ያሉ የመብት ጥሰቶችን አጣርቶ መረጃውን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

Via ሸገር ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከየትኛውም አካል ተጽዕኖ ቢኖርም ብሄራዊ ጥቅሟን ያላሰጠበቀ ስምምነት እንደማትፈርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ረፋዱን በሰጡት መግለጫ ፣ በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በህዳሴ ግድብ ላይ እየተደረጉ ስላለው ውይይት አብራርተዋል። ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ሲያደርጉት የነበረውን ድርድርና የረቂቅ የስምምነት ሰነድ ዝግጅት ሳይቋጭ መጠናቀቁ ይታወቃል። በድርድሩ ሱዳን የአቋም ለውጥ አድርጋ ከግብጽ ጋር መወገኗን እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ለግብጽ መወገናቸውን አሁን ላይ ጉዳዩ “4 ለ 1” ሆኗል የሚሉና በዚህም ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ እንደሆነ በመግለጽ የኢትዮጵያ አቋም ምን እንደሆነ ከጋዜጠኞች ጥያቄ ተነስቷል።

በዚህም ቃል አቀባዩ አቶ ነቢያት በሰጡት ምላሽ፤ በግድቡ ዙሪያ ከየትኛውም አካል ተጽዕኖ ቢኖር ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን አሳልፋ እንደማትሰጥና መርህ ላይ የተመሰረተ ጥቅሟን ያስጠበቀ ድርድር እንደምታራምድ አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን አሳልፋ እንደማትሰጥ ነው አጽኖኦት የሰጡት።

በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጋጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት በዚህኛውም ዙር ሳይቋጭ ትናንት ማማምሻውን መጠናቀቁ ይታወሳል።የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በዚህ ሳምንት የሶስቱ አገሮች የህግ ባለሙያዎች የደረሱበትን ረቂቅ ስምምነት ዝግጅት በኢትዮጵያ በኩል ለመገምገም ወደ ስፍራው ማቅናታቸውም እንዲሁ፡፡

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa