YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከሕንድ የመጡ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የነጻ ህክምና ሊሰጡ ነው።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ሕንዳዊያን ሐኪሞች ከኢትይጵያዊያን ሐኪሞች ጋር በመሆን ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የቀዶ ጥገና ህክምና ይሰጣሉ።ሕክምናው ከየካቲት 9 አስከ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በሁሉም የህክምና ዘርፎች አገልግሎት እንደሚሰጡ ሆስፒታሉ አስታውቋል።በመሆኑም የቀደ ጥገና ህክምና የምትፈልጉ ዜጎች ከፊታችን ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ መጥታችሁ መታከም ትችላላችሁ ተብላችኋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል!

እንደሚታወቀው የገቢዎች ሚኒስቴር በአዲሱ ኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጁ ዙሪያ በተለያዩ ወቅት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተከታታይ ውይይት አካሂዷል፡፡ ከውይይቱም የተገኙ ግብአቶችን በመጠቀም አስፈላጊው ማሻሻያዎች አድርጓል፡፡በተጨማሪም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ ማድረግ ያለባቸውን ቅድመ ዝግጅትና በአጠቃላይ በአዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ውይይት አድርኋል፡፡በውይይቱም የኤክሳይስ ታክስ ምንነትና ታሪካዊ ዳራ፣ ኤክሳይስ ታክስ የሚጣልባቸው እቃዎችና አገልግሎት ባህሪያት፣ ኤክሳይስ ታክስ የሚጣልበትና የማሻሻያው ምክንያት፣ የረቂቅ አዋጁ ዋና ዋና ገጽታዎች እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከአምራቾች ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ ደርሷል፡፡ስለሆነም አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

Via Ministry of Revenue
@YeneTube @FikerAssefa
ዕጣ የወጣባቸውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማከፋፈል የፌደራል መንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ እንደሆነ ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ቤቶቹ በኦሮሚያ ክልል መሬት ላይ ነው የተሠሩ በሚል ተቃውሞ ማስተላለፉ መጓተቱ ይታወሳል፡፡ ከዕደለኞች እስካሁን አቤቱታ እንዳልቀረበላቸው የከተማው አስተዳደር ቤቶች ልማት ሃላፊ ተናግረዋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
#COVID-2019_update

የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከአርባ አራት ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1114 ደርሷል።

Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
የብልጽግና ፓርቲ አመራር የሆኑት ታዬ ደንደአ በቢሸፍቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ብርና ሌሎች ንብረቶች ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው ገለጹ። ታዬ ዘረፋው ያጋጠማቸው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቢሾፍቱ በሄዱበት ወቅት ቢን ኢንተርናሽናል በተባለ ሆቴል ምሳ ለመመገብ መኪናቸውን አቁመው በገቡበት ጊዜ “የመኪናቸው በር በማስተር ቁልፍ ተከፍቶ” እንደተሰረቀባቸው ተናግረዋል።

ምንጭ:ቢቢሲ አማርኛ/አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ሰላሳ ዓመታት ከተረፈ-ምርቶች በሚወጣ መጥፎ ጠረን አካባቢን እና ህብረተሰብን ሲያውክ ኖሯል የተባለው የአዲስ አበባ ቄራዎች ድረጅት እና አንድ ሌላ መንግስታዊ ተቋም በአንድ የሕግ ባለሞያ መከሰሳቸውን ተነገረ፡፡ ከሳሹ የሕግ ባለሞያ የሕዝብን በጤናማ አካባቢ የመኖር መብት ለማስከበር በግላቸው በመንግስታዊ ተቋማቱ ላይ የከፈቱት ክስ በሰለጠነው ዓለም የተለመደ ቢሆንም ፤ለሀገራችን ግን አዲስ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ከምባታ ጠንባሮ ዞን በጠምባሮ ወረዳ እስከአሁን መነሻው ያልታወቀ እሳት 30 የሳር ቤቶችን ማቃጠሉን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አብረሃም ቲርካሶ የእሳት አደጋው ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በወረዳ ዱርጊ፥ ሲገዞ፥ ለዘንባራ እና ሆዶ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ መከሰቱን አመልክተዋል።

እስካሁን መነሻው በውል ያልታወቀው የእሳት አደጋ በቀበሌዎቹ የሚገኙ 200 ሰዎችን ያለመጠለያ ከማስቀረቱም በላይ በሰብል እና በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን ነው የፖሊስ አዛዡ ለዶቼ ቨለ የገለጹት።የእሳቱ መንስዔ እስከአሁን በግልጽ ባይታወቅም የአካባቢው ኅብረተሰብ ግን በተከታታይ ከሰማይ እየወረደ የሚገኝና ምናልባትም የፈጣሪ ቁጣ ሊሆን ይችላል እያለ እንደሚገኝ ፖሊስ አመልክቷል።

እንዲያም ሆኖ የሰው እጅ ካለበት በሚል ፖሊስ አደረኩ ባለው ማጣራት እስከአሁን በድርጊቱ ተጠርጣሪ የሆነ ሰውም አለመገኘቱን ኮማንደር አብረሃም አክለው ተናግረዋል። ፖሊስም ለማጣራት የሚያደርገው ክትትልና ምርመራው አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ኮሞሮስ ለቻይና የ100 ዩሮ ድጋፍ አደረገች።

ትንሿ ኮሞሮስ የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት ያቅሟን ያህል መለገሷን RT አስነብቧል።

የኮሞሮስ የ100 ዩሮ እርዳታ በርካቶችን ያስገረመ ሲሆን መረዳዳት ከትንሹ ይጀምራል የሚባለው ለካ እውነት ነው በሚል ዜናው የእለቱ የደግነት ጥግ ተብሎ ተዘግቧል።

ምንጭ:- RT/Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
በተለያየ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገብተው በሕገወጥ መንገድ በሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ መሆኑን የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጅብ ጀማል በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በተለያየ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሕጋዊ ሳይሆኑ በሕገወጥ መንገድ በአገሪቱ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች ወደ ኤጀንሲው መጥተው ሕጋዊ መስመር የማይይዙ ከሆነ ለአገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል እርምጃ ይወሰዳል።እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በተለያዩ ምክንያት በቪዛ ወደ አገር ውስጥ ከገቡ የውጭ አገር ዜጎች መካከል አንዳንዶቹ የቆይታ ጊዜያቸውን ያሳለፉ ሲሆን፤ አንድ የውጭ ዜጋ የቆይታ ጊዜው አልፎ ከሕግ ውጭ ከተቀመጠ ድርጊቱ በሕግ የሚያስቀጣ በመሆኑ በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎችን ወደ ሕግ ሥርዓት ለማስገባት ከሰኔ 2011 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ወደ ኤጀንሲው በመምጣት እንዲመዘገቡ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ማስታወቂያ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በአጣዬና አካባቢው ግጭት ጋር ተያይዞ ክስ የተመሰረተባቸው 38 ግለሰቦች የክስ መቃወምያቸውን አቀረቡ

ከመጋቢት 24 እስከ 29 2011 ዓም በሰሜን ሸዋ ዞን እና በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮምያ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ውስጥ በተለይም በከሚሴ ፣ በአጣዬ ፣ ማጀቴ ቆሬ ሜዳ እና አጎራባች ወረዳዎች በተነሳ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ እና ንብረት መውደሙ የሚታወስ ነው፡፡

ይህንን ተከትሎም ምርመራ ሲያደርግ የቆየው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ2011 ዓም ማገባደጃ ሀምሌ ወር ላይ ደሴ በሚገኘው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍረድ ቤት በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል ያላቸውን 38 ግለሰቦች ከሷል፡፡

ሆኖም ተከሳሾች ጉዳያቸው በአዲስ አባ ማለትም በፌደራል ፍርድ ቤት እንዲታይላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ክርክር ሲደረግበት ቆይቷል፡፡

ይህንን የመወሰን ስልጣን ያለው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ጉዳያቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍረድ ቤት እንዲታይ በወሰነው መሰረት አራቱ የክስ መዝገቦች በድጋሜ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ እና 20ኛ ወንጀል ችሎቶች ተከፍተው መተያት ጀምረዋል፡፡
አቃቤ ህግ በክሱ በድምሩ የ80 ሰው ህይወት ያለፈ ስለመሆኑ እና በርታ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ስለመኖራቸው አካቷል፡፡
በተጨማሪም 1 ቤተክርስቲያን የተቃጠለ መሆኑን እና ይህም ግምቱ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን ሌሎች የወደሙ የአካባቢው ንብረቶችም እንደነበሩ ጨምሮ ገልፅዋል።

በአራት መዝገብ ተከፋፍለው እና በተለያየ ቀጠሮ እየታዩ ያሉት ተከሳሾቹም በበኩላቸው በክሱ የተዘረዘረው የወንጀል ዝርዝር የተጠቀሱባቸውን የህግ ድንጋጌ የሚያሟሉ አይደሉም ሲሉ የመጀመርያ ደረጃ መቃወምያቸውን አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም የስነ ስርአት ህጉ በሚያዘው መሰረት የወንጀል ተሳትፎ ድረሻ ተሟልቶ አልቀረበም ሲሉ ተቃውመዋል፡፡

አቃቤ ህግ በመቃወምያዎቹ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ትእዛዝ የተሰጠ ሲሆን ችሎቶቹ ከየካቲት 24 ጀምሮ በመቃወምያ ክርክሩ ላይ በሚኖሩ ተከታታይ ቀጠሮዎች ብይን ለመስጠት ቀጥረዋል፡፡

Via:- Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
አንጋፋው አርቲስት ጀምበሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

በመድረክ ትወና ከ40 ዓመታት በላይ ያገለገሉት አንጋፋው አርቲስት ጀምበሬ በላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።አርቲስቱ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1949 እስከ 1953 ዓ.ም በቀድሞዉ የሀገር ፍቅር ማህበር በአሁኑ የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በመድረክ ትወና አገልግለዋል።እንዲሁም ከ1953 እስከ 1988 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በመድረክ ትወና ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አርቲስት ጀምበሬ ከተወኑባቸዉ ሥራዎች መካካል የአዛውንቶች ክበብ፣ ኦቴሎ፣ የከተማዉ ባላገር፣ ሐምሌት፣ የዋናው ተቆጣጣሪ፣ የእጮኛዉ ሚዜ፣ የልብ ፅጌሬዳ፣ 1 ዓመት ከ1 ቀን፣ የፌዝ ዶክተር፣ የእግር እሳት፣ የሚስጢር ዘብ እና የድል አጥቢያ ጥቂቶቹ ናቸው።
በተጨማሪም የዘመቻው ጥሪ፣ አመል አለብኝ፣ ግራ የገባው ግራ፣ ያልተከፈለው እዳ የተሰኙ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ መተወናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።አርቲስት ጀምበሬ በላይ በ1933 ዓ.ም በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር የተወለዱ ሲሆን፣ የሁለት ሴት እና የአራት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ8 ሺሕ በላይ አዲስ ተመራቂዎችን ሊቀጥር ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በሚገኙ ከማእከላት እስከ ወረዳ ባሉ ክፍት የሥራ ቦታዎች 8 ሺሕ 100 አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን በመቅጠር ሂደት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።በ2010 እና 2011 ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከ56 በላይ በሚሆኑ የትምህርት መስኮች የተመረቁ የአዲስ አበባ ወጣቶች እንዲወዳደሩ ጥሪ ቀርቦ፣ የበለጠ ብቁ የሆኑትን ለመለየት በተሰጠ ፈተና 8 ሺሕ 100 የተሻለ ውጤት ያላቸውን ተፈታኞች በመለየት የሥራ ቅጥር በመከናወን ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በጅማ ዞን ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፣ በጅማ እና በአጋሮ ከተሞች በርካታ ህዝብ የተሳተፈባቸው የድጋፍ ሰልፎች በመደረግ ላይ ይገኛሉ።

@YeneTube @Fikerassefa
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድጋፍ ሠልፍ እና የኦፌኮ ሕዝባዊ ስብሰባ መከልከል በጅማ

በትናንትናው (3/6/2012) ዕለት በጅማና አጋሮ ከተሞች 'ለብልጽግና እንሩጥ' በሚል መሪ ቃል በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል የተባለ የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ።
የሠልፉ አላማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን መደገፍ እንደሆነ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

https://telegra.ph/JJimma-02-13
ለተቃጠሉት የሞጣ መስጊዶች ግንባታ እና ንብረት ለወደመባቸው ዜጎች ማቋቋሚያ 209 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ!

ለተቃጠሉት የሞጣ መስጊዶች መልሶ ግንባታ እና ንብረት ለወደመባቸው ዜጎች ማቋቋሚያ የሚውል ከ209 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዛሬ አስታውቋል።ከጥር 22 ቀን 2012 ጀምሮ በተካሄደው የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከተጠቀሰው ጥሬ ገንዘብ በተጨማሪ ከ700 ሺህ ብር በላይ በዓይነት መሰብሰቡንም ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ጠቁሟል።ከህዝበ ሙስሊሙ ባለፈ ህዝበ ክርስቲያኑም በድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ መሳተፉን የገለፁት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በውጭ ሀገራት የተሰበሰበ ተጨማሪ ገንዘብ መኖሩን የጠቀሰው ምክር ቤቱ ይህም እስከ የካቲት 24 ቀን 2012 ድረስ ገቢ እንዲደረግም ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።በድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ 200 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ከእቅድ በላይ መሰብሰብ መቻሉም ተገልጿል።በዚሁ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ መጠናቀቁንም ምክር ቤቱ ጨምሮ አስታውቋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬቶች አቀኑ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሦስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬቶች አቅንተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በሚኖራቸው ቆይታ ከመካከለኛው ምሥራቅ ከተውጣጡ 15 ሺህ ገደማ ኢትዮጵያውያን ጋር በአቡዳቢ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የተወካዮች ምክር ቤት የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ!

የተወካዮች ምክር ቤት፣ በአስቸኳይ ስብሰባውም የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል። ኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ 1186/2012 በ4 ተቃውሞ እና በ7 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።ቋሚ ኮሚቴው በስራ ላይ ያለው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ለረጅም ጊዜ በስራ ላይ የቆየ በመሆኑ እና የማምረቻ ወጪን መሰረት አድርጎ የሚሰላ በመሆኑ ግልፅነት የሚጎድለው መሆኑን አንስቷል።

ይህን ለማስቀረትም አዲሱ አዋጅ በመሸጫ ዋጋ ላይ እንዲሰላ በማድረግ ለከፋይ እና አስከፋዩ ግልፅነት የሚፈጥር መሆኑን አመላክቷል።በሲጋራ ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በፓኬት በዋጋው 30 በመቶ እንዲሁም በፍሬ 5 ብር የነበረው በኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያው ተጨምሮ 8 ብር እንዲሆን መደረጉንም ተገልጿል።በረቂቅ አዋጁ የታሸገ ውሃ ላይ ተጥሎ የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ ከ15 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል።

ምንጭ:ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሞገስ ታደሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረው ሞገስ ታደሰ ባጋጠመው የጤና እክል ሕክምና ላይ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ሞገስ ታደሰ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ከ'C' ቡድን ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን፣ ለሲዳማ ቡና፣ ለአዳማ ከተማ፣ ለኤሌክትሪክ እና ለወልድያ ክለቦች ተጫውቷል።በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከታዳጊ ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ በመጫዋት ሀገራዊ ኃላፊነቱን ተወጥቷል።

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በ23 ተቃውሞ፣ በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ።

@YeneTube @Fikerassefa
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ልዝርዝር ምርመራ ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ መርቶታል።

Via HoPR
@YeneTube @FikerAssefa