ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መደምደሚያ
ችግሩ ምንድን ነው? የተፈታች ሴት አታግቡ ነው እንዴ? ከመነሻው ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ በነብዩ”ﷺ” ቀዳማይ ባለቤት ባርያ ሆኖ ሳለ ነብያችን”ﷺ” ነጻ በማውጣት በእርሱ ላይ የለገሱለት ሰው እንጂ መቼስ ልጃቸው ነውና? ሲቀጥል የዒዳህ ጊዜያቸውን ጨርሰው ተፋተው የለ እንዴ? ወይስ በራሳችሁ ባይብይ እግዚአብሔር ለገዛ ነብዩ የሰው ሚስቶች ስለሰጠው አለማንበባችሁ ነው? እግዚአብሔር ለነብዩ ዳዊት የጌታውን የሳዖልን ሚስቶች በብብቱ ሰጥቶታል፤ በሰፈሩት ቁና መሰፈር”double standard” ይሉሃል እንደዚህ ነው፦
2ኛ ሳሙኤል 12፥8 የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ *የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ*፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።

ነብዩ ዳዊት ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ ገሎ ሚስቱንም ለራሱ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስዷል፦
2ኛ ሳሙኤል 12፥9 አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ ኬጢያዊውን *ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል*፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።

በጣም የሚያሳዝነው እርሱ ባጠፋው ጥፋት ሚስቶቹ በዓይኑ ፊት ተወስደዋል፤ ከቤርሳቤህ የተወለድ ህጻን ያለ ወንጀሉ እንዲቀሰፍ ተደርጓል፦
2ኛ ሳሙኤል 12፥11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ *ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ*፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።
2ኛ ሳሙኤል 12፥14-15 ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች ታላቅ የስድብ ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ *የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል* አለው። ናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔርም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችውን ሕፃን ቀሠፈ፥ እጅግም ታምሞ ነበር።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እውን ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ማርቆስ 13:32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።

መንደርደሪያ
*ልጅ* የሚለው የግሪኩ ቃል ሁዎስ Υἱός ሲሆን ወልድ ማለት ነው፣ ወልድ የተባለው ኢየሱስ ከሆነ ኢየሱስ ቀንና ሰዓቱን አያውቅም ማለት ነው፣ አይ በሰውነቱ እንዳይባል እውቀት የስጋ ሳይሆን የዓይምሮ ባህርይ ነው፣ ጥቅሱ *ከአብ በቀር* በማለት ይዘጋዋል፣ *በቀር* ደግሞ ተውሳ-ከግስ ስለሆነ ያ እውቀት የአብ ብቻ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣ *አባት* የሚለው የግሪኩ ቃል ፓተር Πατήρ ሲሆን አብ ማለት ነው፣ ይህን ጥቅስ ለመንደርደሪያ ያክል በዚህ ከተረዳን ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ያልሆነበትን የተለያየ ሙግት እንመለከታለን፦

ሙግት አንድ
ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ቢሆን ኖሮ ከሌላ ህላዌ እውቀት ይማራልን?
ዮሐ 8:28 አባቴም *እንዳስተማረኝ* እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ።
ዮሐ.7:15-16 አይሁድም። ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። *ትምህርቴስ* ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤
ዕብራውያን 5:8 ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን *ተማረ*፤

ሙግት ሁለት
ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ቢሆን ኖሮ በጥበብ ያድግ ነበርን? የጥበብና የማስተዋል፥ የእውቀት መንፈስ ያርፍበታልን?
ሉቃስ 2:52 ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።
ኢሳይያስ 11:2 የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።

ሙግት ሶስት
ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ብሎ ይናገር ነበርን?
ማርቆስ 11:13 ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም።

ይህን የስነ-አመክንዮ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ባደረገ መልኩ ከተረዳን ወዲህ ከተቆላበት ወደ ተጋፈበት ጉዳይ እንገባለን፣ ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው ብለው የተነሱባቸውን ጥቅሶች እንመልከት፦

ጥቅስ አንድ
ዮሐ 21:17 ጴጥሮስ አዘነና። ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤

ይህ ጥቅስ የተጻፈበት ሙሉውን ምዕራፍ የዮሐንስ ወንጌል ክፍል እንዳልሆነ የአዲስ ኪዳን ምሁራን ይስማማሉ፣ ዮሐንስ ወንጌሉ የሚጠናቀቀው ዮሐ 20:31 ላይ ነው የሚል መረጃ አላቸው፣ ነገር ግን ይህ ሙግት በጥራዝ ጠለቅ ጥናት ካልታየ በስተቀር በጥራዝ ነጠቅ ጥናት ከባድ ስለሆነ የመጣው ጥቅስ ባሉበት ደረጃ መመለሱ ብልህነት ነው፣ ሁሉን ታውቃለህ ማለት አጠቃላይ ታውቃለህ ማለት ነውን? መልሱ አዎ ከሆነ አማንያንም ሁሉን አዋቂዎች ናቸው፦
1ዮሐ.2:20 እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ *ሁሉንም ታውቃላችሁ*።
*ሁሉ* የሚለው ቃል በአንጻራዊ ደረጃ ለአማንያን እንደተጠቀመበት ሁሉ ለኢየሱስም በዚህ ሂሳብ ነው የሚታየው፣ ምክንያቱም ኢየሱስ የማያውቀው ነገር ስላለ።
ጥቅስ ሁለት
ማቴዎስ 9:4 ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?

ኢየሱስ ሁሉ አዋቂ ካልሆነ በልባቸው ክፉ ማሰባቸውን በምን አወቀ? ይህ ቆንጆ ጥያቄ ነው፣ ኢየሱስ በልባቸው ያለውን ያወቀው የእውቀት መንፈስ ስላረፈበት ያወቀው በመንፈስ ቅዱስ ነው፦
ማርቆስ 2:8 ወዲያውም ኢየሱስ በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ *በመንፈስ* አውቆ እንዲህ አላቸው፦ በልባችሁ ይህን ስለ ምን ታስባላችሁ?
ሉቃስ 4:1 ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ከዮርዳኖስ ተመለሰ፥ በመንፈስም ወደ ምድረ በዳ ተመርቶ፥ አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ።
ኢሳይያስ 11:2 የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።

ምን ኢየሱስ ብቻ ጴጥሮስም ሐናንያና ሰጲራ የደበቁትን ነገር አውቆ ነበር፦ ሃዋርያት ስራ 5:1-10 ጴጥሮስ ያወቀው በመንፈስ ነው ከተባለ ጴጥሮስ ላይ ያረፈው መንፈስ አይደል እንዴ ኢየሱስ ላይ ያረፈው?

መደምደሚያ
3:79 ለማንም ሰዉ አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠዉና ከዚያም ለሰዎች ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሆኑ ሊል አይገባዉም፤
72:26-27 እርሱ ሩቁን ሚስጢር ዐዋቂ ነው፣ በሚስጢሩ ላይ አንድንም አያሳውቅም። ከመልክተኛ ለወደደው ቢሆን እንጅ ለሌላ አይገልጽም ፤

አላህ አንድ ነብይ ሲያስነሳ እውቀትን፣ ጥበብን፣ መጽሐፍናና ነብይነትን ይሰጠዋል፣ በዚህም የሩቅ ሚስጥራትን ያውቃል እንጂ በራሱ ሁሉን አዋቂ አይደለም፣ አንድ ነብይ ከሰው በላይ የሆነ እውቀት እንዳለው ከአይሁዳውያን መረዳት ይቻላል፦
ሉቃስ 7:39 የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ። ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥
ዮሐንስ 4:17-19 ሴቲቱ መልሳ። ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ፦ ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት። ሴቲቱ። ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ።

እውነት ነው ኢየሱስ ነብይ ነው፣ ሰዎች የማያውቁት ነገር ያቅ ነበር፦
ማርቆስ 6:4 ኢየሱስም። ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።
ማቴዎስ 21:11 ሕዝቡም።፡- ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው አሉ።
ሉቃ24:19 በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤
ዮሐ 9:17 አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ደግሞ አሉት። እርሱም። ነቢይ ነው አለ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የመልእክተኛ ቃል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

81:19 እርሱ ቁርአን “የተከበረ መልክተኛ ቃል” ነው إِنَّهُۥ لَقَوْلُ رَسُولٍۢ كَرِيمٍۢ ።

እዚህ ጋር ሁለት ቁልፍ ቃላት መመልከቱ ይህ ጥቅስ ጭራሽ ቁርአን የአላህ ቃል መሆኑን ያጠናክራል፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ እንየው፦

ነጥብ አንድ
“መልክተኛ”
“ረሱል” رِسَالَة የሚለው ቃል “ተላላኪ” ከሆነ የግድ “ሙርሲል” مُرْسِل ላኪ መኖር አለበት፣ “መልክተኛው” እዚህ ጋር የተባለው ጂብሪል”አ.ሰ.” ነው፤ ላኪው ደግሞ አላህ ነው፣ በላኪና በመልክተኛ መካከል ደግም “ሪሳላ” رِسَالَ “መልእክት” ያስፈልጋል፣ መልእክቱ ደግሞ “ቁርአን” ነው፣ መልእክት የላኪ ቃል እንጂ የተላኪ ቃል አይደለም።

ነጥብ ሁለት
“ቃል”
“ቀውል” قَوْل የሚለው “ቁል” قُلْ “በል” ከሚል ትዕዛዛዊ ግስ የመጣ ነው፤ “ቀውል” ለሙራሲል የምንጠቀምበት ነው፤ “ሙራሲል” مراسل ማለት “አስተላላፊ”reporter” ሲሆን ቀውል ጅብሪል ከአላህ አስተላልፊ ሆኖ የሚያስተላልፈውን ቃል ያመለክታል፣ ነገር ግን “ከላም” كَلَٰم ለሙአለፍ የምንጠቀምበት ነው፤ “ሙአለፍ” مؤلف ማለት “አመንጪ”author” ማለት ነው፤ የቁርአን አመንጪ ላኪው አላህ ነው፤ በእርግጥም ቁርአን በጂብሪል መልእክተኛነት የተላለፈ የአምላካችን የአላህ ቃል ነው፦
9፥6 ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ “”የአላህን ቃል”” ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ وَإِنْ أَحَدٌۭ مِّنَ ٱلْمُشْرِكِينَ ٱسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَٰمَ ٱللَّهِ ፡፡

በሱረቱ አት-ተክዊር 81፥19 ላይ ያለው አውድ ላይ የተጠቀሰው መልእክተኛ ጂብሪል ስለመሆኑ የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለቤት ዘንድ ባለሟል የሆነ እና በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ ታማኝ የሆነ መልክተኛ መባሉ ነው፦
81፥20-21 የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለቤት ዘንድ ባለሟል የሆነ፤ በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ “ታማኝ” የሆነ መልክተኛ ቃል ነው።

“ታማኝ” መባሉ ከላኪው ከአላህ መልእክቱን በማድረስ አደራውን የሚያሟላ ከሆነ መልእክቱ ምንጩ የላኪው ነው፤ ነገር ግን ሌላ ጥቅስ ላይ ደግሞ ነብያችን ለማመልከት የተከበረ መልክተኛ ተብለዋል፦
69:40 እርሱ ቁርአን የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው።

በዚህ አንቀፅ ላይ የተከበረ መልክተኛ የተባሉት ነብያችን ስለመሆናቸው አውዱ ያሳየናል፦
69:41 እርሱም የባለ-ቅኔ ቃል አይደለም ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ። የጠንቋይም ቃል አይደለም ጥቂቱን ብቻ ታስታዉሳላችሁ።
በወቅቱ የነበሩት ተቺዎች ነብያችንን ባለ-ቅኔ እና ጠንቋይም ናቸው የሚል ትችት ስለተጠቀሙ አላህ ይህ ከንቱ ትችል ለማስተባበል ይህንን ቃል ተናገረ፤ “ቃል” የተባለው ማስተላለፍን ባይሆን ኖሮ ቃል በአንድ ጊዜ እንዴት የሁለት ማንነቶች ቃል ይሆን ነበር? እንግዲህ ነብያችን መልእክተኛ ከሆኑ አላህ ላኪ ከሆነ መልእክቱ ደግሞ ቁርአን ነው ማለት ነው፤ መልክተኛ በመልክቱ ላይ ያለው ድርሻ ማድረስ ብቻ ነው፦
5:67 አንተ መልክተኛ رِسَالَة ሆይ! ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን አድርስ፤ ባታደሪስ መልክቱን رِسَالَ አላደረስክም፤

አላህ፦ “እኔ አስጠንቃቂው ነኝ” በል ሲላቸው ነቢያችን፦ “እኔ አስጠንቃቂው ነኝ” ሲሉ የሚተላለፍ ቃል ይሆናል፦
22:49 ፦ “እላንተ ስዎች ሆይ እኔ ለናንተ ግልጽ አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ” *በላቸው*።
15:89 *በልም* «እኔ ማለቱ አስጠንቃቂው እኔ ነኝ፡፡»

ለምሳሌ ገብርኤል ተልኮ የተናገረው የምስራች የአምላክ ንግግር ሆኖ ሳለ ነገር ግን ያንን የምስራች ወደ ራሱ በማስጠጋት “ቃሌ” ማለቱ አስተላላፊነትን እንጂ አመንጪነትን አያሳይም ከተባለ ከላይ ያለውንም ሙግት በዚህ ቀመርና ስሌት መረዳት ይቻላል፦
ሉቃስ 1፥19-20 መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ *እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር*፤ እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን *ቃሌን* ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም፡ አለው።

ሌላው “ቶራህ” תּוֹרָה ማለት “ሕግ” ማለት ነው፤ ይህ ሕግ ምንጩ ፈጣሪ ነው፤ የፈጣሪ ሕግ ነው፦
ዘጸአት 16፥4 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ *”በሕጌ”* ይሄዱ ወይም አይሄዱ እንደሆነ እኔ እንድፈትናቸው፥ እነሆ ከሰማይ እንጀራን አዘንብላችኋለሁ፤

ነገር ግን ይህ የአምላክ ሕግ የሙሴ ሕግ ተብሏል፦
ሚልክያስ 4፥4 ለእስራኤል ሁሉ *”ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን “የሙሴን ሕግ” አስቡ”*።

ፈጣሪ በሙሴ በኩል ለእስራኤል ሁሉ ያዘዘው ሥርዓትንና ፍርድን ወደ ሙሴ በማስጠጋት የሙሴን ሕግ ስላለው እውን ቃሉ የሙሴ ነው ማለት ነውን? አይ ቃል አቀባይ ስለሆነ የሙሴ ሕግ ተባለ ከሆነ መልሱ እንግዲውስ ከላይ ያለውን የነብያችንን እና የጂብሪልን በዚህ ሒሳብና ስሌት ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የማይታየው አምላክ
https://youtu.be/PrdKEl6x9R8

በኡስታዝ ወሒድ ዑመር


ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ የዳዋ ተደራሽነትን ያስፉ።
የኃጢአት ስርየት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥135 ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱ እና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት *ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለም*፡፡ በስሕተት በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት ተደግሳለች፡፡ وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ

“ኃጢአት” የሚለው ቃል በቁርአን “ዘንብ” ذَنب “ኢሥም” إِثْم “ኸጢዓ” خَطِيٓـَٔة “ጁናህ” جُنَاح “አጅረሙ” أَجْرَمُ ሲሆን ትርጉሙ አበሳ፣ አመፅ፣ አለመታዘዝ፤ ወንጀል፣ ጥፋት ተብሎ የተቀመጠው ነው። ይህም አላህ አድርግ ያለንን አለማደረግ አታድርግ ያለንን ማድረግ ያመለክታል።
"ከፋራ" كَفَّارة‎ የሚለው ቃል "ከፈረ" كَفَّرَ ማለትም "ሸፈነ" "አስተሰረየ" "አበሰ" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን "ማበስ" "መሸፈን" "ስርየት" የሚል ትርጉም አለው፤ ኀጢአቶችን የሚያስተሰርይ አምላካችን አላህ ብቻ ነው፦
3፥135 ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱ እና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት *ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለም*፡፡ በስሕተት በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት ተደግሳለች፡፡ وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ

አምላካችን አላህ ኃጢአታችንን የሚያስተሰርየው ንስሃ ስንገባ፣ ስናምን፣ እርሱን ስንፈራና መልካም ሥራ ስንሰራ ነው፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እንይ፦

ነጥብ አንድ
"ተውበት"
አምላካችን አላህ አት-ተዋብ" التَّوَّاب ማለትም ከባሮቹ "ንስሃን ወይም ፀፀትን የሚቀበል" ነው፤ ባሮቹ ደግሞ ወደ እርሱ “ተውበት” تَوْبَة ማለትም “ንስሃ” ሲገቡ "ተዋቢን" تَّوَّابِين ማለትም "በንስሃ ተመላሾች" ይባላሉ፤ ንስሃ ኃጢአቶቻችን ያስተሰርያል፦
39፥53 በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ *አላህ ኃጢኣቶችን በሙሉ ይምራልና*፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
39፥54 *ቅጣቱም ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትርረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ*፡፡ ለእርሱም ታዘዙ፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

አላህ ንስሃ ለገባ ሁሉ ኃጢኣቶችን በሙሉ ይምራል፤ ቅጣቱ የሚፈጸምበት የትንሳኤ ቀን ከመምጣቱ በፊት፦ "ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ" ተመለሱ የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ንስሃ የምትጠቅመው ሞት በመጣበት ጊዜ፦ "እኔ አሁን ተጸጸትኩ" ለሚል እና ለነዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው ለሚሞቱ አይደለችም፦
4፥18 *ጸጸትንም መቀበል ለእነዚያ ኀጢአቶችን ለሚሠሩ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ «እኔ አሁን ተጸጸትኩ» ለሚልና ለነዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው ለሚሞቱ አይደለችም*፡፡ እነዚያ ለእነሱ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል፡፡ وَلَيْسَتِ التَّوْبَةُ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ حَتَّىٰ إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ إِنِّي تُبْتُ الْآنَ وَلَا الَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمْ كُفَّارٌ ۚ أُولَـٰئِكَ أَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

ተውበት ሦስት ሸርጦች አሉት፤ እነርሱም፦ የሰራነውን ኀጢኣት መተው፣ መጸጸት እና ላንሰራው ቆራጥነት ናቸው፤ ይህ ንስሃ ንጹሕ የኾነችን ጸጸት ነች፦
66፥8 እናንተ ያመናችሁ ሆይ!
*ንጹሕ የኾነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፡፡ ጌታችሁ ከእናንተ ኀጢኣቶቻችሁን ሊሰርይላችሁ* ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ሊያስገባችሁ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا تُوبُوا إِلَى اللَّهِ تَوْبَةً نَّصُوحًا عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَن يُكَفِّرَ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيُدْخِلَكُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ يَوْمَ لَا يُخْزِي اللَّهُ النَّبِيَّ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ
ነጥብ ሁለት
"ኢማን"
አምላካችን አላህ "አል-ሙእሚን" المُؤْمِن ማለትም ለባሮቹ "ታማኝ" ነው፤ ባሮቹ ደግሞ በእርሱ ላይ “ኢማን” إِيمَٰن ማለትም "እምነት" ሲኖራቸው "ሙእሚን” مُؤْمِن ማለትም "አማኝ" ይባላሉ፤ እምነት ኃጢአቶቻችን ያስተሰርያል፦
48፥2 እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَآمَنُوا بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَهُوَ الْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۙ كَفَّرَ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَأَصْلَحَ بَالَهُمْ
5፥65 የመጽሐፉም ባለቤቶች *ባመኑ እና ከክህደትም በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ባገባናቸው ነበር*፡፡ وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَكَفَّرْنَا عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأَدْخَلْنَاهُمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ

“ዐቂዳህ” عقيدة‎ የሚለው ቃል “ዐቀደ” عَقَدَ ማለትም “ቋጠረ” ወይንም “ዐቅድ” عَقد ማለትም “መቋጠር” ከሚል ቃል የተመዘዘ ነው፤ ለምሳሌ “የተቋጠሩ” ለሚለው ቃል “ዑቀድ” عُقَد ሲሆን ይህ ቃል “ዐቀደ” عَقَدَ ከሚለው ቃል የረባ ነው፦
113፥4 “በየተቋጠሩ” ክሮች ላይ ተፊዎች ከኾኑት ደጋሚ ሴቶችም ክፋት፡፡ وَمِن شَرِّ ٱلنَّفَّٰثَٰتِ فِى ٱلْعُقَدِ

ስለዚህ “ዐቂዳህ” ማለት አንድ ነገር በደንብ መቋጠር ወይም እንዳይላላ ማጥበቅ ማለት ነው፤ ለምሳሌ የጋብቻ ቃል-ኪዳን “ዑቅደቱ-ኒካህ” ተብሎ ይጠራል፤ “ላ-ኢላሀ ኢለሏህ” እምነትም በአንድ ሙስሊም ልብ ውስጥ በጠነከረ መልኩ መያዝ ስላለበት “ከሊመቱል-ዐቂዳህ” ተብሎ ይጠራል፤ አንድ ሰው እኔን፡- ዐቂዳህ ምንድነው? ብሎ ቢጠይቀኝ፤ ትርጉሙ፡- በልብህ አምነህ የያዝከውና የቋጠርከው ምንድነው? ማለቱ ነው፤ አንድ አማኝ በልቡ ቋጥሮ ያስቀመጠው ዕውቀት “ኢማን” ይባላል፤ በግሪክ “ዶግማ” δόγμα ይባላል፤ ትርጉሙ “አንቀፀ-እምነት”doctrine” ማለት ነው። ኢማን ማለት በልብ የምናምነው፣ በምላስ የምንመሰክረው እና በድርጊት የምንገልፀው ነው፤ የኢማን አስኳሉ “ከሊመቱል-ዐቂዳህ” ማለትም “ላ-ኢላሀ ኢለሏህ” ነው፥ ይህ ከሊመቱል-ዐቂዳህ በቁርአን “ጠንካራን ዘለበት” ይባላል፦
2:256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ *በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ لَآ إِكْرَاهَ فِى ٱلدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ ٱلرُّشْدُ مِنَ ٱلْغَىِّ ۚ فَمَن يَكْفُرْ بِٱلطَّٰغُوتِ وَيُؤْمِنۢ بِٱللَّهِ فَقَدِ ٱسْتَمْسَكَ بِٱلْعُرْوَةِ ٱلْوُثْقَىٰ لَا ٱنفِصَامَ لَهَا ۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
ነጥብ ሦስት
"ተቅዋ"
“ተቅዋ” تَقْوَى ማለት “አላህ መፍራት” ማለት ሲሆን ያ አላህ የሚፈራ ማንነት “ሙተቂን” مُتَّقِين ይባላል፤ አምላካችን አላህ የሁሉም ነገር ፈጣሪ ነው፤ የሚፈራው አንዳች ማንነት ሆነ ምንነት የለም፤ እራሱም፦ “እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ” በማለት ይናገራል፦
23:52 ይህችም አንድ መንገድ ስትኾን ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ *እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ* ፡፡ وَإِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱتَّقُونِ

ወደ ነብያትም ወሕይ ሲያወርድላቸው፦ “ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም ፍሩኝም” ማለትን ነው፦
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከመንፈስ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል፤ አስጠንቅቁ፤ *እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም ፍሩኝም* ማለትን አሳታውቁ በማለት ያወርዳል። يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ

አላህን መፍራት ኃጢአቶቻችን ያስተሰርያል፦
65፥5 ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ ወደእናንተ አወረደው፡፡ *አላህንም የሚፈራ ሰው ኀጢኣቶቹን ከእርሱ ይሰርይለታል*፡፡ ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል፡፡ ذَٰلِكَ أَمْرُ اللَّهِ أَنزَلَهُ إِلَيْكُمْ ۚ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يُكَفِّرْ عَنْهُ سَيِّئَاتِهِ وَيُعْظِمْ لَهُ أَجْرًا
8፥29 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያን ብርሃን ያደርግላችኋል፡፡ ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከእናንተ ላይ ያብስላችኋል*፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن تَتَّقُوا اللَّهَ يَجْعَل لَّكُمْ فُرْقَانًا وَيُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ

ነጥብ አራት
"መልካም ሥራ"
“ዐሚሉስ ሷሊሓት” عَمِلُوا الصَّالِحَات ማለትም “መልካም ሥራ” ማለት ነው፤ “ኢሕሣን” إِحْسَٰن “መዋብ” “ማማር” “መልካም” “በጎ” “ጥሩ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ “ሐሠን” حَسَن ማለት “መልካም” “ውብ” ማለት ሲሆን “ሑሥን” حُسْن ማለት ደግሞ “የተዋበ” “መልካም” “ያማረ” ማለት ነው፤ አንድ ሰው በኢሕሣን ደግሞ “ሙሕሢን” ይባላል፤ “ሙሕሢን” مُحْسِن ማለት “ጥሩ ሠሪዎች” “መልካም ሠሪዎች” “በጎ ሠሪዎች” ማለት ነው፤ የዲን መዋቢያውና ማሳመሪያው “መልካም ሥራ” ነው፤ መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስተሰርያሉ፦
11፥114 ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፡፡ *መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና*፡፡ ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው፡፡ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ طَرَفَيِ النَّهَارِ وَزُلَفًا مِّنَ اللَّيْلِ ۚ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ۚ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ
29፥7 እነዚያም ያመኑ፤ *መልካሞችንም የሠሩ መጥፎዎቹን ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ ላይ እናብስላቸዋለን*፡፡ በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَنُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَحْسَنَ الَّذِي كَانُوا يَعْمَلُونَ

አበይት ኀጢአቶችን የሚያስተሰርየው ተውበት ብቻ ነው፤ ነገር ግን ንኡሳን ኀጢአቶች የሚያስተሰርየው መልካም ሥራዎች ናቸው፦
4፥31 *ከእርሱ ከተከለከላችሁት ታላላቆቹን ኀጢአቶች ብትርቁ ትናንሾቹን ኀጢአቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን*፡፡ የተከበረንም ስፍራ ገነትን እናገባችኋለን፡፡ إِن تَجْتَنِبُوا كَبَائِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُم مُّدْخَلًا كَرِيمًا
53፥32 *እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው*፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ الَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ إِلَّا اللَّمَمَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ وَاسِعُ الْمَغْفِرَةِ ۚ

አል-ዐመሉ ሷሊሕ ሶላት፣ ጾም፣ ዘካ፣ ሰደቃ፣ ሀጅ የመሳሰሉት ናቸው፤ ለምሳሌ ሰደቃ ኃጢአቶቻችን ያስተሰርያል፦
2፥271 *ምጽዋቶችን ብትገልጹ እርሷ ምንኛ መልካም ናት፡፡ ብትደብቋትና ለድኾች ብትሰጧትም እርሱ ለናንተ በላጭ ነው፡፡ ከኃጢአቶቻችሁም ከእናንተ ያብሳል*፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ إِن تُبْدُوا الصَّدَقَاتِ فَنِعِمَّا هِيَ ۖ وَإِن تُخْفُوهَا وَتُؤْتُوهَا الْفُقَرَاءَ فَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۚ وَيُكَفِّرُ عَنكُم مِّن سَيِّئَاتِكُمْ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዙል-ቀርነይን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥83 “ከዙል-ቀርነይንም” ذِى ٱلْقَرْنَيْنِ ይጠይቁሃል፡፡ «በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን አነባለሁ፤» በላቸው፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَن ذِى ٱلْقَرْنَيْنِ ۖ قُلْ سَأَتْلُوا۟ عَلَيْكُم مِّنْهُ ذِكْرًا

መግቢያ
“ገይብ” ማለት ከስሜት ሕዋሳት ባሻገር ያለ የሩቅ ነገር ነው፤ “ገይብ” በሶስት ይከፈላል፤ እርሱም፡-
አንደኛ “ገይቡል ማዲ” ሲሆን ያለፈ ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ከዚህ በፊት አላፊ የሆነ ነገር ነው፤
ሁለተኛው “ገይቡል ሙስተቅበል” ሲሆን መጪው ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ገና ያልተፈጸመ ወደፊት የሚሆን ነው፤
ሶስተኛው “ገይቡል ሙዷሪዕ” ሲሆን እየተፈጸመ ያለ ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ በአሁኑ ሰዓት ቀጣይነት ያለው ነገር ነው። ይህንን ከተረዳን ወደ አንቀፁ መግባት እንችላለን፦
18፥83 “ከዙል-ቀርነይንም” ذِى ٱلْقَرْنَيْنِ ይጠይቁሃል፡፡ «በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን አነባለሁ፤» በላቸው፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَن ذِى ٱلْقَرْنَيْنِ ۖ قُلْ سَأَتْلُوا۟ عَلَيْكُم مِّنْهُ ذِكْرًا

ሰዎቹ ለመጠየቅ ማሰባቸውን አላህ አውቆ ለነብያችን አንቀፁ ላይ ስለ ዙል-ቀርነይን ከመጠየቃቸው በፊት አላህ ቀድሞ “ይጠይቁሃል” ማለቱ “ገይቡል ሙዷሪዕ” ሲሆን ስለ አላህ ስለ ዙል-ቀርነይን መናገሩ ደግሞ “ገይቡል ማዲ” ነው፤ አላህ ስለ ቀርነይን የሚነግረን አስፈላጊውን ብቻ መሆኑን ለማመልከት “ሚን-ሁ” مِنْهُ “ከ-እርሱ” በማለት ጥቂት ትረካ መሆኑን ነግሮናል፤ ሙሉ ለሙሉ ትረካ ቢሆን ኖሮ የሚጀምረው “ሚን-ሁ” ሳይሆን “አን-ሁ” عَنْهُ “ስለ-እርሱ” ነበር፤ ስለዚህ ስለ ዙል-ቀርነይን የተነገረን ትረካ አላህ የሩቅ ነገር አዋቂ መሆኑና ነብያችን የአላህ ነብይ ለመሆናቸው ማስረጃ ለማቆም ነው፤ ይህን እሳቤ ይዘን ስለ ዙል-ቀርነይን ያለውን ምልከታ ነጥብ በነጥብ ማየት እንችላለን፦

ነጥብ አንድ
“ዙል-ቀርነይንም”
“ቀርን” قَرْن ማለት እንደየ አውዱ ትርጉሙ ይለያያል፤ “ቀርን” ማለት አንደኛ “ሱር” صُّور “ቀንድ” ማለት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ “ደህር” دَّهْر “ዘመን” ማለትን ነው፦
6፥6 ከበፊታቸው ከክፍለ “ዘመናት” قَرْنٍۢ ሕዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንን አላዩምን ለእናንተ ያላስመቸነውን ለእነርሱ በምድር ውስጥ አስመቸናቸው፡፡

“ዙል-ቀርነይንም” ذِى ٱلْقَرْنَيْن ማለት በሁለት ክፍለ-ዘመናት ሁለት መንግሥት የነበሩት ንጉሥ ነው፤ መዲና ላይ ስለ ዙል-ቀርነይንም ጠያቂዎቹ የመጽሐፉ ሰዎች ማለትም ይሁዲዋች ከራሳቸው ዳራ ተነስተው ነው፤ አስጠያቂዎቹ ደግሞ የመካ ከሃድያን ናቸው፤ ይህ ንጉሥ ማን ነበረ ለሚለው የተለያየ አመለካከት አለ፤ ተፍሲሩል ጀላለይን ሰሒህ የሆነ ሪዋያ ሳይኖር እርሱ የግሪኩ ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ነው ይላል፤ በታሪክ ደግሞ የግሪኩ ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ደግሞ ሙሽሪክ እንጂ ሙዑሚን አልነበረም፤ አንዳንዶች የቻይናው ኮንፊሺየስ ነው፤ ሌሎች ደግሞ የየመኑ ንጉሥ ነው የሚሉም አልታጡም፤ የዘመናችን ሙፈሲሪን ደግሞ የሜዶኑና የፋርሱ ንጉሥ ታላቁ ቂሮስ ነው ይላሉ፤ እስቲ የሚቀጥለውን ነጥብ እንይ፦
ነጥብ ሁለት
“አይሁዳውያን”
የዘመናችን ሙፈሲሪን ደግሞ የሜዶኑና የፋርሱ ንጉሥ ታላቁ ቂሮስ ብለው የሚያሰምሩበት ከአይሁዳውያን ዳራ ማለትም እስራኢሊያት ተነስተው ነው፤ በአይሁዳዊያን መለኮታዊ ቅሪት ላይ ሁለት ቀንዶች ስላሉት ንጉሥ “ሉው-ቀራናዪም” በሚል ያውቁታል፤ “ሉው-ቀራናዪም” וְל֣וֹ קְרָנָ֑יִם ማለት “ሁለት ቀንዶች ያሉት” ማለት ነው፤ ይህም በዳንኤል ትንቢት ተነግሮ ነበር፦
ዳንኤል 8፥3-4 ዓይኔን አንሥቼ አየሁ፤ እነሆም፥ “ሁለት ቀንዶች የነበሩት” וְל֣וֹ קְרָנָ֑יִם አንድ አውራ በግ በወንዙ ፊት ቆሞ ነበር፥ ሁለቱም ቀንዶቹ ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ አንዱ ግን ከሁለተኛው ከፍ ያለ ነበረ፥ ታላቁም ወደ ኋላው ወጥቶ ነበር።
አውራውም በግ ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜንም ወደ ደቡብም በቀንዱ ሲጐሽም አየሁ፤ አራዊትም ሁሉ ይቋቋሙት ዘንድ አልቻሉም፥ ከእጁም የሚያድን አልነበረም፤ እንደ ፈቃዱም አደረገ፥ ራሱንም ታላቅ አደረገ።

“መለክ” מֶ֫לֶך ማለት “መንግሥት ወይም ንጉሥ” ማለት ሲሆን ሁለትዮሽ”dual” ሲሆን ደግሞ “መልኬ” מֶ֫לֶך ይሆናል፤ “ቀንድ” የመውጊያ ሃይል ነው፤ የሁለቱ ቀንዶች ትርጉም ሁለት መንግሥታት ናቸው፤ እነርሱም የሜዶንና የፋርስ “መንግሥታት ናቸው፦
ዳንኤል 8፥20 ባየኸው በአውራው በግ ላይ የነበሩ ሁለቱ ቀንዶች እነርሱ የሜዶንና የፋርስ “መንግሥታት” מַלְכֵ֖י ናቸው። ”

ነጥብ ሶስት
“ታሪክ”
በታሪክ የሜዶንና የፋርስ መንግሥታት የቆየው ለሁለት ክፍለ-ዘመናት ከ 539 B.C. እስከ 331 B.C. ነው፤ ይህም ንጉሥ ሁለቱ ግዛቱ ምስራቅንና ምዕራብን ያካልላል፤ ሸኽ ሙሐመድ ኢብኑ መሱድ በተፍሲሩ እንደዘገበው ሰዎች የሙዑሚን አሚር አሊን”ረ.አ.” ስለ ዙል-ቀርነይንም ሲጠይቁት፤ “እርሱ የአላህ ባሪያ ነው፤ ስሙም አያሽ ነው” ብሏል።
ከዚህ የምንረዳው ዙል-ቀርነይንም የአላህ ባሪያ እንጂ ሙሽሪክ አይደለም፤ ከኢስራኢሊያት የተገኘው ሪዋያ ታላቁ ቂሮስ ከመወለዱ ከ200 ዓመት በፊት ትንቢት የተነገረት ባሪያ ነው፦
ኢሳይያስ 45፥1-3 እግዚአብሔር *ለቀባሁት*፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት *ለቂሮስ* እንዲህ ይላል። *በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ*፤ በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ *በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ*።

አላህ የበለጠውን ያውቃል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የኢየሱስ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአዕምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው፡፡ هَذَا بَلَاغٌ لِلنَّاسِ وَلِيُنْذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ ” سورة إبراهيم

መግቢያ
ቁርኣን ከወረደበት ምክንያት አንዱ የአዕምሮ ባለቤቶችም አላህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት ነው፦
14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአዕምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው፡፡ هَذَا بَلَاغٌ لِلنَّاسِ وَلِيُنْذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ ” سورة إبراهيم

ነገር ግን ይህንን አንድ አምላክ አንዴ በማንነት ሶስት ነው፣ አንዴ ሰው ሆነ፣ አንዴ ለሰው ኀጢአት ሞተ እያሉ በነውርና በጎዶሎ ባህርይ ያሻርኩታል፤ ይህ አንድ አምላክ በመለኮታዊ ቅሪት ሲናገር እንዲህ ይላል፦
ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥
ኢሳይያስ 44:6 ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።

አንዱ አምላክ እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም እያለን ተመልሰው “ሰውም አምላክ ነህ” ማለት እኛ ፍጡራን፦ ፈጣሪን “ስለ አንተ ከአንተ ይልቅ እኛ እናውቅልሃለን” እያልነው ነው፤ ነገር ግን ኢየሱስ በአንዱ አምላክ እና በሰዎች መካከል መካከለኛ ሆኖ ከአምላክ ሰምቶ የሚናገር ሰው ነው፤ በድንቆች በምልክቶችም ከአንዱ አምላክ ዘንድ ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው ነበረ፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 አንድ አምላክ Θεοῦ አለና፥ በአምላክ Θεοῦ እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም *ሰው* የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ Θεοῦ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤
የሐዋርያት ሥራ 2:22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላክ Θεοῦ በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከአምላክ Θεοῦ ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤

እንግዲህ ኢየሱስ ሰው ከሆነ እና አንዱ አምላክ የላከው ከሆነ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት የተለያዩ ማንነት እና ምንነት ናቸው ማለት ነው፤ ኢየሱስ የሚያመልከው የራሱ አምላክ አለው፦

ነጥብ አንድ
“አምላኬ”
“አምላኬ” ማለት “የእኔ” አምላክ ማለት ነው፤ “አምላኬ” በሚል የመጀመሪያ መደብ “እኔ” የሚል አገናዛቢ ተውላጠ ስም አለ፤ “የእኔ አምላክ”my God” የሚለው የኢየሱስ ሙሉ እኔነት አምላክ አለው፦
ማቴዎስ 27:46 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፡- ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፡- የእኔ አምላክ የእኔ አምላክ ፥ አንተ እኔን ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። “”My God, my God, why have you forsaken me””.
ዮሐንስ 20:17 ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ “አምላኬ” እና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።

በተለይ ኢየሱስ አንዱን አምላክ “አንተ” እራሱን ደግሞ “እኔ” በማለት “አምላኬ” ማለቱ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት ህልውናዎች መሆናቸው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ “ተውከኝ” ስላለም በተወው ባለቤት እና በተተው ተሳቢ መካከል “ተውከኝ” የሚል ተሻጋሪ ግስ”transitive verb” መኖሩ ኢየሱስን ከአምላኩ ይለየዋል፤ በተጨማሪም “ወደ” የሚለው መስተዋድድ*preposition* መጠቀሙ በሁለት ማንነት መካከል ለመለየት የሚመጣ ነው፣ ኢየሱስ ማርያምን *ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ* ማለቱ ወንድሞቹና ማርያም የተለያየ ማንነት እንዳላቸው እንደሚያሳይ ሁሉ “ወደ አምላኬ አርጋለው” ማለቱ አምላኩና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ህላዌዎች መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ኢየሱስ ካረገም በኃላ አብን አምላኬ ይላል፦
ራእይ 3፥2፤ ሥራህን #በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።
ራእይ 3፥12 ድል የነሣው #በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ #የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ #ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።

ነጥብ ሁለት
“አምላካችን”
ኢየሱስ “ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካችሁ” አለ እንጂ “ወደ አምላካችን” ስላላለ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ አምላክ የሆነበትና ለሃዋርያት አምላክ የሆነበት መደብ ይለያያል ይላሉ፤ ይህ ውሃ የማያነሳ ሙግት ነው፤ አንደኛ ይህ አነጋገር የተለመደ ነው፦
ዘፍጥረት 43፥23 እርሱም አላቸው፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ *አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ* በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁስ ደርሶኛል።

“አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ” ስለተባለ አንዱ አምላክ ለአባታቸው ለያእቆብ እና ለልጆቹ አምላክነቱ ይለያያልን? ሁለተኛ ኢየሱስ “አምላካችን” በሚል አንደኛ መደብ ብዜት ተናግሯል፦
ኢሳይያስ61:1-2 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት “”አምላካችንም”” የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ ልኮኛል፤
ማርቆስ 12:29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ “”አምላካችን”” አንድ ጌታ ነው፥
ነጥብ ሶስት
“አምላክህ”
መዝሙረኛ እግዚአብሔር ለኢየሱስ አምላክ መሆኑን ለማሳየት ” አምላክህ” በማለት በሁለተኛ መደብ ተናግሯል፦
መዝሙር 45:7 ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር “አምላክህ” የደስታ ዘይትን ቀባህ።
ዕብራውያን 1:9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር “አምላክህ” ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ።

ለኢየሱስ ባለንጀሮቹ ሲቀቡ የነበሩት ነብያት ናቸው፤ ክርስቶስ ማለት “የተቀባ” ማለት ሲሆን አምላኩ እግዚአብሔር ኢየሱስን የደስታ ዘይት በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ቀብቶታል፤ ቀቢው አንዱ አምላክ ከሆነ ተቀቢው ሰው ብቻ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 10:38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤

ነጥብ አራት
“አምላኩ”
ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ለማሳየት “አምላኩ” በማለት በሶስተኛ መደብ ተናግረዋል፦
ራእይ 1:6 መንግሥትም “”ለአምላኩ”” እና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥
ሚክያስ 5:4፤ እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል “”በአምላኩ”” በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፤ እነርሱም ይኖራሉ፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።

በተጨማሪም “የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ” በማለት ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ተናግረዋል፦
ኤፌሶን 1:17 የክብር አባት የጌታችን “”የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ”” እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።
2ኛ ቆሮንጦስ1:3 የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
2ኛ ቆሮንጦስ 11:31 ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል።

መደምደሚያ
ኢየሱስ በንግግሩ እራሱን ሁለተኛው የአንዱ አምላክ አባል አድርጎ አስተምሮ አያውቅም። ከዚያ ይልቅ እራሱ ከአንዱ አምላክ ውጪ ያደርግ ነበር፦
ማርቆስ 10:18 ኢየሱስም። ስለ ምን ቸር እኔን ትለኛለህ? ከአንዱ አምላክ በቀር ቸር ማንም የለም።Why callest you me good? there is none good but one, that is , God.
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘላለም ህይወት ናት። (1980 አዲስ ትርጉም)
ዮሐንስ 14:1 ልባችሁ አይታወክ፤ በአምላክ Θεοῦ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
ዮሐ7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ*myself አይደለም፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከአምላክ Θεοῦ ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ*myself የምናገር ብሆን ያውቃል።

አንዳንድ ቂሎች “ኢየሱስ አምላክ አለው ግን ለስጋው ነው” ይሉናል፤ ስጋው ፍጡር እና የራሱ ማንነት ከሆነ በስጋው የሚያመልከው አምላክ ካለው ኢየሱስ አምላኪም ተመላኪም ከሆነ ሁለት አይሆንም ወይ? ሲቀጥል “ስጋ” ብቻውን “እኔ” ይላል ወይ? የሰው ሁለተንተና መንፈሱ፣ ነፍሱ እና ስጋው ናቸው፦
1ኛ ተሰሎንቄ 5:23 የሰላምም አምላክ ራሱ “”ሁለንተናችሁን”” ይቀድስ፤ “መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም፣ ፣ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።”

ኢየሱስ የራሱ መንፈስ ካለው፣ የራሱን መንፈስ ለአንዱ አምላክ ከሰጠ የራሱ መንፈስ ከአንዱ አምላክ ይለያል፦
ዮሐንስ13:21 ኢየሱስ ይህን ብሎ “በመንፈሱ” ታወከ መስክሮም።
ሉቃስ 23:46 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ “መንፈሴን” በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ “መንፈሱን” ሰጠ። NIV

አንዱ አምላክ ደግሞ የመንፈስ ሁሉ አምላክ ከሆነ አንዱ አምላክ የኢየሱስ ሁለንተና አምላክ ነው፦
ዘኊልቅ 16:22 እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው። አምላክ ሆይ፥ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ አምላክ(the God of the spirits of all flesh,)፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን? አሉ።
ዘኊልቅ 27:16፤17፤ የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በፊታቸው የሚወጣውን በፊታቸውም የሚገባውን የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ (the God of the spirits of all flesh) እግዚአብሔር በማኅበሩ ላይ ይሹመው።

ስለዚህ አንዱ ኣምላክ አምላክነቱ ለመንፈሱም ጭምር ከሆነ እና ባይብል ላይ 17 ቦታ ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ከተገለፀ እውነትም ኢየሱስ አምላኪ ፍጡር ነው፤ በእውነት ሊመለክ የሚገባው የኢየሱስ አምላክ ብቻ ነው። አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥67 *አንተ መልክተኛ ሆይ! ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን አድርስ፡፡ ባትሠራም መልእክቱን አላደረስክም*፡፡ يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ۖ وَإِن لَّمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُ ۚ

አምላካችን አላህ “ሙርሲል” مُرْسِل ማለትም "ላኪ" ነው፤ ነብያችን"ﷺ" ደግሞ “ረሱል” رِسَالَة ማለትም “መልክተኛው” ናቸው፤ እንዲሁ ቁርኣን የአላህ “ሪሳላ” رِسَالَ ማለትም "መልእክት” ነው።
የመልእክቱ "ሙአለፍ” مؤلف ማለትም “አመንጪ”author” አምላካችን አላህ ሲሆን፤ ነብያችን"ﷺ" ደግሞ የመልእክቱ “ሙራሲል” مراسل ማለት “አስተላላፊ”reporter” ናቸው፤ አምላካችን አላህ ለነብያችን"ﷺ"፦ “ቁል” قُلْ ማለትም “በል” በሚል ትዕዛዛዊ ግስ ያዛቸዋል፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
13፥30 እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደኾነችው ሕዝብ እነርሱ በአልረሕማን የሚክዱ ሲኾኑ ያንን *ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ፡፡ «እርሱ አልረሕማን ጌታዬ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ፡፡ መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው» በላቸው*፡፡ كَذَٰلِكَ أَرْسَلْنَاكَ فِي أُمَّةٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهَا أُمَمٌ لِّتَتْلُوَ عَلَيْهِمُ الَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَهُمْ يَكْفُرُونَ بِالرَّحْمَـٰنِ ۚ قُلْ هُوَ رَبِّي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ مَتَابِ

ሚችነሪዎች ነብያችንን"ﷺ" በትእዛዝ "በል" የሚለው ማን ነው? ብለው ለማወዛገብ ይጠይቃሉ፤ "ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ" የሚለው ሃይለ-ቃል ቁርኣንን አውራጅና ነብያችንን"ﷺ" ላኪው አላህ እራሱ "በል" ማለቱን እንረዳለን፤ በመቀጠል እዛው አንቀጽ ላይ “ቁል” قُلْ ብሎ መናገሩ በራሱ "በል" የሚለው ማንነት አላህ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ በተጨማሪም "በልን" ወደ ነብያችን"ﷺ" የሚጥለው እራሱ እንደሆነ ይናገራል፦
73፥5 *እኛ በአንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለንና*፡፡ إِنَّا سَنُلْقِي عَلَيْكَ قَوْلًا ثَقِيلًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቃል" ለሚለው የተቀመው ቃላት “ቀውል” قَوْل ሲሆን “ቁል” قُلْ ከሚል ትዕዛዛዊ ግስ የመጣ ነው፤ ስለዚህ "በል" እያለ የሚያስነብባቸው እራሱ አላህ ነው፦
3፥58 *ይህ ከተዓምራቶችና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ ሲኾን በአንተ ላይ እናነበዋለን*፡፡ ذَٰلِكَ نَتْلُوهُ عَلَيْكَ مِنَ الْآيَاتِ وَالذِّكْرِ الْحَكِيمِ
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
75፥18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*፡፡ فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ
"ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ "በል" እያለ የሚያስነብባቸው እራሱ ስለሆነ ከራሱ ወደ እርሳቸው የተወረደውን "አንብብ" ይላቸዋል፦
18፥27 *ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّك
29፥45 *ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَاب
29፥51 *እኛ መጽሐፉን በእነርሱ ላይ የሚነበብ ኾኖ በአንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን?* በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታ እና ግሳጼ አለበት፡፡ أَوَلَمْ يَكْفِهِمْ أَنَّا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَرَحْمَةً وَذِكْرَىٰ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

አላህ ቁርኣንን ለሰዎችም ሁሉ የሚነበብ ሆኖ በእርሳቸው ላይ ማውረዱ "በል" ለማለቱ ማስረጃ ነው፤ በተጨማሪም በሁለተኛ መደብ "አንተ ነቢዩ ሆይ" "አንተ መልክተኛ ሆይ" በማለት እያናገረ መሆኑን "ላክንህ" በሚል ሃይለ-ቃል ይናገራል፦
4፥79 *ለሰዎችም ሁሉ መልክተኛ ኾነህ ላክንህ*፡፡ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا
33፥45 *አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪ እና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا
5፥67 *አንተ መልክተኛ ሆይ! ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን አድርስ፡፡ ባትሠራም መልእክቱን አላደረስክም*፡፡ يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ۖ وَإِن لَّمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُ ۚ

"ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን አድርስ" የሚለውን አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ይህንም የተወረደው "ሪሳላ" መሆኑን ለማመልከት "ባትሠራም መልእክቱን አላደረስክም" በማለት መልእክቱ ቁርኣን መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ እንዴ? እውነቱ ቢጠፋባችሁስ ህሊናችሁ ጠፋባችሁ እንዴ? አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፤ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የእግዚአብሔር ባህርያት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

እግዚአብሔር ክፉን መንፈስን፣ የስሕተትን አሠራር፣ ጨለማን እና ክሳትን እንደሚልክ ባይብል ይናገራል፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
መዝሙር 105፥28 *ጨለማን ላከ* ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።
መዝሙር 106፥15 የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን *ክሳትን ላከ*።

ይሄ ክፉም መንፈስ እንደ ኡቃቤ ከእግዚአብሔር ዘንድ እየተላከ ሳኦልን አሠቃየው፦
1ኛ ሳሙኤል 16፥14 የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ *ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው*።
1ኛ ሳሙኤል 18፥10 በነጋውም ሳኦልን *ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው*፥

ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር ሹራ እያደረገ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል፦
1ኛ ነገሥት 22 20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል*፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።

እግዚአብሔር ሰዎች የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ይሰጣል፦
የሐዋርያት ሥራ 7፥42 እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ *የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው*፥

እግዚአብሔር ሰዎች በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ *እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥26 ስለዚህ *እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን *እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፦
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፦
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።
ባይብል ላይ ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ኃይሉ ይገልጥበት ዘንድ እና ስሙ በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ነው፦
ዘጸአት 9፥16 ነገር ግን *ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ*።
ሮሜ 9፥17 መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና።

“ቃሻህ” קָשָׁה ማለት “ማደንደን” ማለት ሲሆን እግዚአብሔር ፈርዖን የእስራኤል ልጆችን እንዳይለቅ እና ሙሴን እንዳይሰማ የፈርዖንን ልብ አደንድኖታል፦
ዘጸአት 7፥3 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ אַקְשֶׁ֖ה * ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።
ዘጸአት 14፥4 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ וְחִזַּקְתִּ֣י * ፥ እርሱም ያባርራቸዋል፤
ዘጸአት 9፥12 እግዚአብሔርም *የፈርዖንን ልብ አደነደነ וַיְחַזֵּ֤ק *፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም።
ዘጸአት 14፥8 እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ *የፈርዖንን ልብ አደነደነ* וַיְחַזֵּ֣ק ፥

እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ልብን ስላደነደነው የፈርዖን ልብ ደነደነ፦
ዘጸአት 7፥13 *እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ የፈርዖን ልብ ደነደነ וַיֶּחֱזַק֙:*፥ አልሰማቸውምም።
ዘጸአት 7፥14 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ *የፈርዖን ልብ ደነደነ*፥ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ።
ዘጸአት 9፥7 ፈርዖንም ላከ፥ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። *የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ*፥ ሕዝቡንም አልለቀቀም።

እውን ፈርዖን ተጠያቂ ነውን? ልቡንስ ካደነደነው ህዝቤን ልቀቅ ብሎ ሙሴና አሮንን መላክ ለምን አስፈለገ? ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ ብሎ ፈርዖንን መውቀስ ለምንችአስፈለገ? በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን መንፈሱን አደንድኖታል፦
ዘዳግም 2፥30 የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ *እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና*፥ ልቡንም አጽንቶታልና።

ለነገሩ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፦
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፦
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።

ነቢዩም ቢታለል ያንን ነቢይ ያታለለው እግዚአብሔር ነው ይላል፤ ሕዝቅኤልን፣ ኤርሚያስን እና ኢሳይያስን ያታለለው እርሱ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፦
ሕዝቅኤል 14:9፤ ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ *ያታለልሁ* እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥
ኤርሚያስ 20:7 አቤቱ፥ *አታለልኸኝ* እኔም ተታለልሁ፥
ኤርሚያስ 4:10 እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ። ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ *አታለልህ* አልሁ።
ኢሳይያስ 63:17 አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን “አሳትኸን”? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢየሱስ ሰው ነውና መፀዳጃ ቤት ተቀምጦ ሲያንኳኩበት ምን ይላል?

ሀ. ሰው አለ!
ለ. አምላክ አለ!
ሐ. ዝም!

መልስ ከእናንተ!

የሰው ልጅ የሆነው ኢየሱስ እየበላና እየጠጣ መጥቷል፤ ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ በሌላ መልኩ ከሰውነት ይወገዳል፦
15:17 “ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን”?

ታዲያ በልቶና ጠጥቶ ወደ እዳሪ የሚጥለውና የሚበሰብሰው ሰው፣ የሚተላው ሰው እንዴት ተመልሶ ሙሉ አምላክ ነው እንላለን? እግዚአብሔር አምላክ እኔ ሰው አይደለሁም እያለ?
ኢዮብ 25:6 ይልቁንስ “ብስብስ የሆነ ሰው”፥ “ትልም የሆነ የሰው ልጅ” ምንኛ ያንስ!
ሆሴ.11:9፤ እኔ “አምላክ” ነኝ እንጂ “ሰው” አይደለሁምና፥

ኢየሱስ ሙሉ አምላክ ከሆነው ከእግዚአብሔር ሰምቶ የሚያስተላልፍ ሙሉ ሰው ነው፦
ዮሐ.8:40 ነገር ግን አሁን “ከእግዚእብሔር የሰማሁትን” እውነት “የነገርኋችሁን ሰው” ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።
ሐዋ 2:22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም “ከእግዚአብሔር” ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ “ሰው ነበረ”፤

ኢየሱስ
1. ይራብና ይጠማ ነበር፦
ማቴዎስ 21፥18 በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ #ተራበ
ዮሐንስ 19፥28 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፡— #ተጠማሁ፡ አለ።

2. ይበላና ይጠጣ ነበር፦
ማቴዎስ 11፥19፤ የሰው ልጅ #እየበላና #እየጠጣ መጣ፥

3. ያ ወደ አፍ ያስገባውን በሌላ መልኩ ከሰውነቱ ያስወጣ ነበር፦
ማቴዎስ 15፥17 ወደ አፍ #የሚገባ #ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?

"ወደ አፍ የሚገባ #ሁሉ ወደ እዳሪ ከተጣለ ኢየሱስ የሚበላውና የሚጠጣው ይወገድ ነው።

እነዚህ ሥድስት ሕጎች ማለትም መራብ፣ መጠማት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መሽናት እና መጸዳዳት ናቸው። እነዚህ የተፈጥሮ ሕጎች የሚገዙት አካል ማምለክ ሺርክ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ጥያቄ ለኦርቶዶክሳውያን

ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦
“ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”
ትርጉም፦
“ዳግመኛ #የጌታችን #የክርስቶስ #ስጋ #አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”

የኢየሱስ ስጋ አምላክ ነው ይለናል። ታዲያ ኢየሱስ የሚመገባቸው ምግቦች ከምግብነት ወደ አምላክነት ያድጋሉን? ሰውነቱ ሲከሳስ የከሳው ሰውነት አምላክ ከነበረ አምላክነቱ ይጠፋልን? ደሙ ሲፈስ ያ ደም አምላክ ከነበረ ከምድር ጋር አፈር ሆኗልን? የተገረዘውስ ሸለፈት አምላክ ከነበረ አፈር ሆነ? ኢየሱስ የበላቸው ምግቦች እድለኞች ናቸው ሆድ ውስጥ ገብተው አምላክ ይሆናሉ። ከዚያ በሌላ መልኩ ከሰውነት ሲወገዱ አምላክነታቸውስ ይወገዳልን? ስጋው ፍጡር ነው። ፍጡር አምላክ ነውን?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
የጸሐይ መጥለቂያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

ፀሐይ የፕላኔታችን ስርዓተ-ብርሃን”Solar System” እምብርትና ከህልቆ መሳፍርት ከዋክብት አንዷ የንጋት ኮከብ ስትሆን፣ ቁርአን የምትወጣበትን እና የምትገባበትን የስነ-ምርምር ጥናት ሳያትት ቀድሞ በመናገር ፋና ወጊና ፈር ቀዳጅ ነው፣ ቁርአን ፀሐይ የምትወጣበትንና የምትገባበትን በተለያየ ፈርጅና ደርዝ ያስቀምጠዋል፦

ፈርጅ አንድ
“ምስራቅና “የምዕራብ”
“መሽሪቅ” مَشْرِق የሚለው የአረቢኛው :አሽረቀ” أَشْرَق
َ”አበራ” ወይም “ገለጠ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ገላጭ” ወይም “ምስራቅ” የሚል ፍቺ አለው፣ ይህ ቃል በቁርአን በነጠላ 11 ጊዜ ተወስቷል።
“መግሪብ” مَغْرِب የሚለው ቃል ደግሞ “ገረበ” غَرَبَ “ገባ” ወይም “ተደበቀ” አሊያም “ተሰወረ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ገቢ” ተደባቂ፣ “ምዕራብ” የሚል ፍቺ አለው፣ ይህ ቃል በቁርአን በነጠላ 10 ጊዜ ተወስቷል፤ ፀሐይ ለአይናች የምትጠልቅበትና የምትወጣበት ነገር እኛ ሊገባን በሚችለው መረዳት ከእኛ አንጻር ተነገረን እንጂ ከመነሻው አትገባም አትወጣ፤ የፀሐይን መውጣትና መግባት ሰው ቤቱ ገባና ወጣ ስንል ቤቱ ቃሚ ሰውዬው ተንቀሳቃሽ በሚል ሂሳብ አንረዳውም፣ የእኛን እይታን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ ምስራቅና ምዕራብ አንጻራዊና ጥቅላዊ ነው፦
73:9 እርሱም “የምስራቅ” الْمَشْرِقِ እና “የምዕራብ” وَالْمَغْرِبِ ጌታ ነው፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ መጠጊያ አድርገህም ያዘው።

ዋቢ የምርምር ጥናት፦
1.Gregory, S. A. (1998). Introductory Astronomy & Astrophysics
2.Phillips, K. J. H. (1995). Guide to the Sun. Cambridge University Press. p. 73.
3.Zirker, J. B. (2002). Journey from the Center of the Sun. Princeton University Press. pp. 15–34

ፈርጅ ሁለት
“ሁለቱ ምሥራቆችና ሁለቱ ምዕራቦችም”
“መሽሪቀይኒ” الْمَشْرِقَيْنِ “የመሽሪቅ ሙተና”dual” ሲሆን ፀሐይ በበጋ ጊዜ በሰሜን ንፍቀ-ክበብ”north pole” ስትወጣ በክረምት ጊዜ ደግሞ በደቡብ ንፍቀ-ክበብ”south pole” መውጣቷን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
“መግሪበይኒ” الْمَغْرِبَيْنِ የመግሪብ ሙተና”dual” ሲሆን ፀሐይ በበጋ ጊዜ በሰሜን ንፍቀ-ክበብ”north pole” ስትገባ በክረምት ጊዜ ደግሞ በደቡብ ንፍቀ-ክበብ”south pole” ትገባለች፣ ይህንን ቁርአን ያስተነተነው በአንጻራዊና በተናጥሎአዊ ነው፦
55:17 “የሁለቱ ምሥራቆች” الْمَشْرِقَيْنِ ጌታ፤ “የሁለቱ ምዕራቦችም” الْمَغْرِبَيْنِ ጌታ ነው።