ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጥያቄ ለኦርቶዶክሳውያን

ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦
“ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”
ትርጉም፦
“ዳግመኛ #የጌታችን #የክርስቶስ #ስጋ #አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”

የኢየሱስ ስጋ አምላክ ነው ይለናል። ታዲያ ኢየሱስ የሚመገባቸው ምግቦች ከምግብነት ወደ አምላክነት ያድጋሉን? ሰውነቱ ሲከሳስ የከሳው ሰውነት አምላክ ከነበረ አምላክነቱ ይጠፋልን? ደሙ ሲፈስ ያ ደም አምላክ ከነበረ ከምድር ጋር አፈር ሆኗልን? የተገረዘውስ ሸለፈት አምላክ ከነበረ አፈር ሆነ? ኢየሱስ የበላቸው ምግቦች እድለኞች ናቸው ሆድ ውስጥ ገብተው አምላክ ይሆናሉ። ከዚያ በሌላ መልኩ ከሰውነት ሲወገዱ አምላክነታቸውስ ይወገዳልን? ስጋው ፍጡር ነው። ፍጡር አምላክ ነውን?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom