ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ያህዌህ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

የሥላሴ አማንያን ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም። መዝሙር ላይ "ያህዌህ ዐረገ" ስለሚል ያ ያረገው ያህዌህ ኢየሱስ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፦
መዝሙር 47፥5 አምላክ በእልልታ፥ *"ያህዌህ በመለከት ድምፅ ዐረገ*"። (KJV) God is *"gone up"* with a shout, the LORD with the sound of a trumpet.

"ዐረገ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ዓላህ" עָלָ֣ה ሲሆን "ወጣ" ወይም "ከፍ አለ"gone up" ማለት ነው። ወደ ሰማየ ሰማያት አብ ወጥቷል፦
መዝሙር 68፥33 በምሥራቅ በኩል *"ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለያህዌህ ዘምሩ"*፤ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።
መዝሙር 68፥4 *"ወደ ሰማያት ለወጣም መንገድ አድርጉ፤ ስሙ “ያህ” בְּיָ֥הּ ነው"*፥
(KJV) Sing unto God, sing praises to his name: extol him that rideth upon the heavens by his name JAH, and rejoice before him.

ያህ የያህዌህ ምጻረ-ቃል ነው። በእነዚህ ጥቅስ መሰረት ወደ ሰማይ የወጣው ማን ነው? ያህዌህ! ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ ስሙ ማን ነው? ያህዌህ! የልጁ ስምስ ማን ነው? ኢየሱስ፦
ምሳሌ 30፥4 ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው?

በዚህ ጥቅስ መሰረት የልጁ ባለቤት ወደ ሰማይ ወጣ የተባለው አብ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ወጣ የተባለው አብ ነው። አይ አይደለም! ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ኢየሱስ! ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ ስሙ ማን ነው? ኢየሱስ! የልጁ ስምስ ማን ነው? ኢየሱስ! ያስኬዳልን? አየሱስ የአብና የወልድ ስም ነውን? ኢየሱስ ልጅ አለውን? የኢየሱስ ልጅ የሚባል ኢየሱስ አለን? ቅሉ ግን የወጣው ያህዌህ አብ ሲሆን የልጁ ስም ኢየሱስ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ወጣ የተባለው በመዝሙር ላይ አብ ነው። ያህዌህ አብ ይወርዳል፦
ዘፍጥረት 46፥4 እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ *"እወርዳለሁ"*፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል።
ዘጸአት 19፥18 *ያህዌህም በእሳት ስለ ወረደበት"* የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤
ዘኍልቍ 11፥17 *እኔም እወርዳለሁ*፥ በዚያም እነጋገርሃለሁ፥

የወረደው እንደሚወጣ ከላይ አይተናል። ያህዌህ መውረድ መውጣት ብቻ ሳይሆን ክንፉና ላባ አለው ይበራል፦
መዝሙር 91፥4 *በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም* በታች ትተማመናለህ።
2ኛ ሳሙኤል 22፥11 በኪሩብም ላይ ተቀምጦ *"በረረ"*፤
መዝሙር 18፥10 በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ *"በረረ"*፥

ስለዚህ "ዐረገ" "ወጣ" "ወረደ" "በረረ" ስለአብ ነው የሚናገረው። ለመሆኑ ያህዌህ አንድ ነው። ያ አንዱ ያህዌህ ዐረገ ሲባል ኢየሱስን ካመለከተ ይህ አንዱ ያህዌው አምላኩ ማን ነው? ምክንያቱም ዐራጊው ማንነት የሚያርገው ወደ እግዚአብሔር አምላኩ ነው፤ ዐርጎም የሚቀመጠው በእግዚአብሔርም ቀኝ ነው፦
ማርቆስ 16፥19 ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ *ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ*።
ዮሐንስ 17፥11 *”እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ”*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ”* ብለሽ ንገሪአቸው፥ አላት።

ልብ አድርጉ ኢየሱስ እራሱን በመጀመሪያ መደብ “እኔ” እያለ እግዚአብሔር ደግሞ በሁለተኛ መደብ “አንተ” እያለ በጸሎት ሲናነጋግረው ተመልከቱ፤ ዓራጊው ኢየሱስ ሲሆን ከሚያርግበት ከእግዚአብሔር ማንነት ለመለየት “ወደ” የሚል መስተዋድድ ተጠቅሟል፤ “ወደ አምላኬ ዓርጋለሁ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “አምላኬ” ማለቱ የሚያርገው ማንነት አምላክ አለው። እግዚአብሔር ከሆነ ወደ እግዚአብሔር የሚያርገው እግዚአብሔር አምላክ አለውን? አዎ! ብሎ ማመን ምን አይነት ድራማና ቁማር ነው? ኢየሱስ ያያረገው በአካል እንጂ በመለከት አይደለም። ሲቀጥል "ያህዌህ ወጣ" ትንቢት ሳይሆን አላፊ ግስ ነው፥ ትንቢት ነው ከተባለ ወደ ሰማይ የወጣ ኤልያስ ያህዌህ ነውን? ምክንያቱም ኤልያስም ወደ ሰማይ ወጣ ስለሚል፦
2 ነገሥት 2፥11 *"ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ"*።

ስለዚህ ያህዌህ ወጣ የሚለውን ትንቢት ነው ብሎ መሞገት ውኃ የማይቋጥርና የማያነሳ ስሁት ሙግት ነው።
"አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያህዌህ አይደለም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ሥላሴአውያን መዝሙር ላይ "ያህዌህ ይመጣል" ስለሚል ያ የሚመጣው ያህዌህ ኢየሱስ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፦
መዝሙር 50፥2-3 ከክብሩ ውበት ከጽዮን *"ያህዌህ ግልጥ ሆኖ ይመጣል"*። *"አምላካችን ይመጣል"* ዝምም አይልም፤

ያህዌህ ለፍርድ እንደሚመጣ ብዙ የብሉያት አናቅጽ ይናገራሉ፦
መዝሙር 96፥13 ይመጣልና፤ *በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል"*።
1ኛ ዜና መዋዕል 16፥33 *"በምድር ሊፈርድ ይመጣልና"*፥
መዝሙር 98፥8 ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፤ ተራሮች ደስ ይበላቸው፥ *"በምድር ሊፈርድ ይመጣልና"*።
ኢሳይያስ 66፥15 እነሆ *"ያህዌህ መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል"*፥

ያህዌህ ለፍርድ እንደሚመጣ በእነዚህ ጥቅሶች ካየን ዘንዳ ይህ ያህዌህ አብ እንደሆነ በሰከነ እና በሰላ አእምሮ ማየት ይቻላል፦
ዳንኤል 7፥22 *በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ"*፥

"በዘመናት የሸመገለው" መጥቶ ፍርድን ለልዑል ቅዱሳን እንደሚሰጥ ይናገራል። "በዘመናት የሸመገለው" እዛው ዐውድ ላይ ለሰው ልጅ ግዛትና ክብር መንግሥትም እንደሰጠው ይናገራል፦
ዳንኤል 7፥13-14 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ *"የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ"*፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ *"ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው"*።

በዘመናት የሸመገለው አባት አብ ከሆነ የሰው ልጅ የተባለው ወልድ ነው ካላችሁ፥ ወልድ ወደ አብ ደርሶ ግዛትና ክብር መንግሥትም ከተሰጠው እንግዲያውስ "በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ" የተባለው አብ ነው። አብ ለፍርድ ይመጣል ማለት ነው። "በዘመናት የሸመገለው" ለመፍረድ በዙፋኑ ይቀመጣል፦
ዳንኤል 7፥9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ *"በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ"*፤

ልጁን የላከው የወይን አትክልት ጌታ አብ ሲመጣ ክፉዎችን በክፉ ያጠፋል፦
ማቴዎስ 21፥33 ሌላ ምሳሌ ስሙ። *"የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ"*፤
ማቴዎስ 21፥37 በኋላ ግን፦ *"ልጄንስ ያፍሩታል፡ ብሎ ልጁን ላከባቸው"*።
ማቴዎስ 21፥40 እንግዲህ *የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ"* በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል? እነርሱም፦ *"ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል"*፥ አሉት።

ልብ አድርግ "የወይን አትክልት ጌታ" በሚመጣ ጊዜ እንደተባለ። ራእይ ላይም ያለውና የነበረው የሚመጣው ጌታ አምላክ ከኢየሱስ "እና" በሚል መስተጻምር ተለይቷል፦
ራእይ 1፥4 *"ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም "እና" በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት "እና" ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ"* ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። KJV
Ο Ιωάννης προς τις επτά εκκλησίες στην επαρχία της Ασίας: Χάρη και ειρήνη σε σας από αυτόν που είναι, και ποιος ήταν και ποιος θα έρθει, και από τα επτά πνεύματα πριν από το θρόνο του, και από τον Ιησού Χριστό, ο οποίος είναι ο πιστός μάρτυρας, ο πρωτότοκος εκ των νεκρών, και ο άρχων των βασιλέων της γης.

ጸጋና ሰላም፦
1. ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም
2. ከሰባቱ መናፍስት
3. ከኢየሱስ ክርስቶስ
ለእናንተ ይሁን! ይላል። ልክ ጸጋና ሰላም "ከእግዚአብሔር ከአባታችን እና ከጌታም ከኢየሱስ" ለእናንተ ይሁን! እንደሚል እንደ ጳውሎስ ሰላምታ። በግራንቪል ሻርፕ የግሪክ ሰዋስው አምስተኛው ሕግ "ካይ" και ማለትም "እና" የሚል መስተጻምር እና "አፓ" από ማለትም "ከ" የሚለው መስተዋድድ ተያይዘው የሚመጣውን አብን እና ኢየሱስን ሁለት የተለያዩ ማንነቶች"persons" አድርጎ አስቀምጧቸዋል።
አብ ይመጣል ማለት ቃል በቃል ሳይሆን የእርሱ አላማ መፈጸምንና የእርሱ ክብር መገለጥ ያመለክታል፣ ምክንያቱም አብ ብዙ ጊዜ በብሉይ ኪዳን እንደመጣ ስለሚናገር፦
ዘኍልቍ 23፥3 በለዓምም ባላቅን፦ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ፥ እኔም እሄዳለሁ፤ ምናልባት *"ያህዌህ ሊገናኘኝ ይመጣል"*፤ እርሱም የሚገልጥልኝን እነግርሃለሁ አለው።
ዘፍጥረት 18፥14 በውኑ ለያህዌህ የሚሳነው ነገር አለን? *"የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ አንተ እመለሳለሁ"*፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።

ያህዌህ በዓመቱ ከይስሐቅ ልደት በኃላ መጥቶ ሲመለስ ቃል በቃል ጽንፈ-ዓለሙን ለቆና ትቶ መጣ ማለት እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው። ከላይ የብሉያት እና የአዲሳት አናቅጽ የአብን ለፍርድ መምጣት በዚህ ልክና መልክ ተረዱት። ስለዚህ ያህዌህ ለፍርድ ይመጣል ማለት አብ ሊፈርድ ይመጣል ማለት እንጂ ኢየሱስ ይመጣል ስለተባለ ያህዌህ ነው ማለት በፍጹም አይደለም። በላይ ባለው በመዝሙር 50፥2-3 ጥቅስ መሠረት ኢየሱስ ያህዌህ አይደለም። ኢየሱስ ያህዌህ ነው ብሎ መሞገት ውኃ የማይቋጥርና የማያነሳ ስሁት ሙግት ነው።
"አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሺርክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥48 *"አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا

“ሺርክ” شِرْك የሚለው ቃል “አሽረከ” أَشْرَكَ ማለትም “አጋራ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በአላህ ላይ “ማጋራት” ማለት ነው። ሺርክ ሁለት ነገርን ያቅፋል፥ አንደኛ “ሙሽሪክ” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “ሸሪክ” ነው። በአላህ ላይ የሚጋራው ማንነት “ሙሽሪክ” مُشْرِك ማለትም “አጋሪ” ሲባል በአላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት ደግሞ “ሸሪክ” شَرِيك ማለትም “ተጋሪ” ይባላሉ።
እዚህ ድረስ በቋንቋው ማብራሪያ ከተረዳን ዘንዳ አንድ ሰው በዱኒያ እያለ ማንኛውንም ኀጢያት ሰርቶ ነገር ግን በተውበት ወደ አላህ ቢመለስ ይቅር ይባላል፦
39፥53 በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ *"አላህ ኃጢኣቶችን በሙሉ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና"*፡፡ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
39፥54 *«ቅጣቱም ወደ እናንተ ከመምጣቱ እና ከዚያም የማትረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ"*፡፡ ለእርሱም ታዘዙ፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

"ጀሚዓ" جَمِيعًا ማለት "በሙሉ" ማለት ነው። በሞት አሊያም በትንሳኤ ቀን ቅጣቱ ከመምጣቱ በፊት ወደ ጌታችን በንስሃ ከተመለስን አላህ ማንኛውም ኃጢኣት ይምራል። ለዚህ ናሙና የሚሆነው የእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ በአላህ ላይ ወይፈንን አጋርተው ከዚያም ወደ አላህ በተውበት ሲመለሱ ይቅር መባላቸው ነው፦
7፥152 *"እነዚያ ወይፈኑን አምላክ አድርገው የያዙ ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ በቅርቢቱም ሕይወት ውርደት በእርግጥ ያገኛቸዋል"*፡፡ እንዲሁም ቀጣፊዎችን እንቀጣለን፡፡ إِنَّ الَّذِينَ اتَّخَذُوا الْعِجْلَ سَيَنَالُهُمْ غَضَبٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَذِلَّةٌ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُفْتَرِينَ
7፥153 *"እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው"*፡፡ وَالَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِهَا وَآمَنُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

ዐውዱ ላይ "አለዚነ" الَّذِينَ ማለትም "እነዚያ" በሚለው አንጻራዊ ተውላጠ-ስም በፊት መነሻ ላይ "ወ" وَ የሚል አያያዥ መስተጻምር ይጠቀማል። ይህ የሚያሳየው "እነዚያም" የተባሉት ወይፈኑን አምላክ አድርገው የያዙት ሰዎች መሆናቸውን እንረዳለን ማለት ነው። በተለይ "ከእርሷ" ተብላ የተጠቀሰችው ተውላጠ-ስም ከላይ የተጠቀሰውን የኃጢያት ድርጊት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ከዚያም ድርጊታቸው የተጸጸቱትን አላህ ይቅር ብሏቸዋል፦
4፥153 *"ከዚያም ተዓምራቶች ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡ ከዚያም ይቅር አልን"*፡፡ ሙሳንም ግልጽ ስልጣንን ሰጠነው፡፡ ثُمَّ اتَّخَذُوا الْعِجْلَ مِن بَعْدِ مَا جَاءَتْهُمُ الْبَيِّنَاتُ فَعَفَوْنَا عَن ذَٰلِكَ ۚ وَآتَيْنَا مُوسَىٰ سُلْطَانًا مُّبِينًا

ነገር ግን አንድ ሰው ካጋራ በኋላ ምህረት የሚያገኘው በህይወት ዘመን ቆይታው እንጂ ሞት በመጣበት ጊዜ አሊያም ከኃዲዎች ሆነው ለሚሞቱ አይደለም፦
4፥17 *ጸጸትን መቀበል በአላህ ላይ የሚገባው ለእነዚያ ኀጢአትን በስህተት ለሚሠሩና ከዚያም ከቅርብ ጊዜ ለሚጸጸቱት ብቻ ነው፡፡ እነዚያንም አላህ በእነርሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል"*፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ إِنَّمَا التَّوْبَةُ عَلَى اللَّهِ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِن قَرِيبٍ فَأُولَـٰئِكَ يَتُوبُ اللَّهُ عَلَيْهِمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا
4፥18 *"ጸጸትንም መቀበል ለእነዚያ ኀጢአቶችን ለሚሠሩ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ «እኔ አሁን ተጸጸትኩ» ለሚልና ለነዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው ለሚሞቱ አይደለችም፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል"*፡፡ وَلَيْسَتِ التَّوْبَةُ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ حَتَّىٰ إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ إِنِّي تُبْتُ الْآنَ وَلَا الَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمْ كُفَّارٌ ۚ أُولَـٰئِكَ أَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

"ከዚያም ከቅርብ ጊዜ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። ከኃዲዎች ሆነው የሚሞቱ በትንሳኤ ቀን በሰሩት ነገር ይጸጸታሉ፣ ነገር ግን ምንም አይጠቅማቸውም፦
39፥56 *የካደች ነፍስ፦ «እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስኾን በአላህ በኩል ባጓደልኩት ዋ ጸጸቴ» ማለቷን ለመፍራት፤ أَن تَقُولَ نَفْسٌ يَا حَسْرَتَىٰ عَلَىٰ مَا فَرَّطتُ فِي جَنبِ اللَّهِ وَإِن كُنتُ لَمِنَ السَّاخِرِينَ
39፥57 *ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ፣ ለኔ ወደ ምድረ ዓለም አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎቹ በሆንኩ ማለቷን ለመፍራት أَوْ تَقُولَ لَوْ أَنَّ اللَّهَ هَدَانِي لَكُنتُ مِنَ الْمُتَّقِينَ
39፥58 *"ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ ወደ ምድረ ዓለም አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎቹ በኾንኩ» ማለቷን ለመፍራት መልካሙን ተከተሉ"*፡፡ أَوْ تَقُولَ حِينَ تَرَى الْعَذَابَ لَوْ أَنَّ لِي كَرَّةً فَأَكُونَ مِنَ الْمُحْسِنِينَ
ስለዚህ አንድ ሰው በሞት ጣዕር ላይ አሊያም በሚቀሰቀስበት ቀን በተውበት ቢጸጸት ጸጸቱ ተቀባይነት የለውም። “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ ብሎ ጣዖታትን ውድቅ አድርጎ እና አንዱን አምላክ አላህ በብቸኝነት ያመለከ ሰው ለሠራው መጥፎ ሥራ ተውበት ከገባ አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጥለታል፦
25፥70 *ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَـٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
16፥119 ከዚያም ጌታህ *ለእነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

ነገር ግን “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” ይዘው በሚሠሩት መጥፎ ሥራ ተውበት ካላደረጉ ብጤዋን እንጅ አይመነዱም፤ በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፤ በክፉም ሥራ የመጡ ሰዎች እነዚህ መጥፎዎችን የሠሩ ይሠሩት የነበሩትን እንጅ አይመነዱም፦
27፥90 *በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፡፡ «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጅ አትመነዱም»* ይባላሉ፡፡ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَكُبَّتْ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
29፥4 *ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሊያመልጡን ይጠረጥራሉን?* ያ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ፡፡ أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ أَن يَسْبِقُونَا ۚ سَاءَ مَا يَحْكُمُونَ

አማንያን “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” በመያዛቸው በሠሩት መጥፎ ሥራ ልክ ተቀጥተው አሊያም በነቢያችን”ﷺ” ምልጃ የጀነት ናቸው። የነቢያችን”ﷺ” ምልጃ በትንሳኤ ቀን የሚያገኘው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ላለ ሰው ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏

በአላህ አምልኮ ላይ ሌላ ማንነትን እና ምንነት ያላሻረከ ነገር ግን ዐበይት ወንጀሎችን የሠራ በነቢያችን”ﷺ” ምልጃ ከጀሃነም ቅጣት ነጻ ወጥቶ ወደ ጀነት ይገባል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2622
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”የእኔ ምልጃ ከእኔ ኡማህ ዐበይት ወንጀሎችን ለሰሩ ሰዎች ነው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ شَفَاعَتِي لأَهْلِ الْكَبَائِرِ مِنْ أُمَّتِي
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 155
ዒምራን ኢብኑ ሑሴይን”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጥቂት ሕዝብ ከእሳት ወጥተው ወደ ጀነት በሙሐመድ”ﷺ” ምልጃ ይገባሉ፤ ጀሀነሚዪን ተብለው ይጠራሉ*። حَدَّثَنَا عِمْرَانُ بْنُ حُصَيْن ٍ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ يَخْرُجُ قَوْمٌ مِنَ النَّارِ بِشَفَاعَةِ مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم فَيَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ، يُسَمَّوْنَ الْجَهَنَّمِيِّينَ ‏
በአላህ ላይ ያላሻረከ ለሠራው ማንኛውም ወንጀል ተውበት እስካላደረገ ድረስ ቅጣቱን በጀሃነም ይቀጣል። ቅጣቱ ሲያልቅ ወደ ጀነት ይመለሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 113
አቡ ዘር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጂብሪል ወደ እኔ መጣና፦ "ማንም በአላህ ላይ ሳያጋራ የሞተ ጀነት ይገባል" ብሎ የምስራች ሰጠኝ። እኔም፦ "ቢሰርቅም ዝሙትም ቢሰራ? ብዬ ጠየኩት፥ እርሱም፦ "አዎ ቢሰርቅም ዝሙትም ቢሰራ" አለኝ*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ أَتَانِي جِبْرِيلُ فَبَشَّرَنِي أَنَّهُ مَنْ مَاتَ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‌‏.‏ قُلْتُ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى قَالَ ‏"‏ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 201
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦.... *"ከሰዎች መካከል በሥራቸው ለዘላለም በጀሃነም ሲዘወትሩ ሌሎች ደግሞ ቅጣት ተቀብለው ከጀሃነም ይወጣሉ፣ አላህ የሻው ከጀሃነም ሰዎች መካከል ምህረት ያደርግለታል። ለመላእክትም፦ "እርሱን ብቻ ያመለከውን አውጡ" ብሎ ያዛቸዋል"*። تَخْطَفُ النَّاسَ بِأَعْمَالِهِمْ، فَمِنْهُمْ مَنْ يُوبَقُ بِعَمَلِهِ، وَمِنْهُمْ مَنْ يُخَرْدَلُ ثُمَّ يَنْجُو، حَتَّى إِذَا أَرَادَ اللَّهُ رَحْمَةَ مَنْ أَرَادَ مِنْ أَهْلِ النَّارِ، أَمَرَ اللَّهُ الْمَلاَئِكَةَ أَنْ يُخْرِجُوا مَنْ كَانَ يَعْبُدُ اللَّهَ

"ከሰዎች መካከል ለዘላለም በጀሃነም የሚዘወተሩ" በአላህ ላይ ያጋሩ ናቸው። አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም። ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ቀጥቶ አሊያም በነቢያችን"ﷺ" ሸፋዓ ይምራል። የሚያጋራን ሰው አላህ ገነትን በእርሱ ላይ በእርግጥ እርም አደረገ፤ የአጋሪው መኖሪያውም እሳት ናት፦
4፥48 *"አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا
5:72 *"እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት"*። ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም። إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

አላህ ከሺርክ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
"ወሰነ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን በምድር ውስጥ ያለውን መወሰኑን እንጂ መፍጠሩን አያሳም። "ቀደረ" እና "ኸለቀ" በይዘትም ሆነ በአይነት፥ በመንስኤውም ሆነ በውጤት ሁለት የተለያዩ ለየቅል የሆኑ ቃላትና ትርጉም ናቸው። በየትኛው ቀምርና ስሌት ቀምራችሁን አስልታችሁ፥ በየትኛው መስፈትና ሚዛን ለክታችሁና መዝናችሁ ነው "ወሰነ" የሚለውን "ፈጠረ" ብላችሁ 2+4= 6 ብላችሁ ድምር…
ጥያቄ ቁጥር 45
በስህተት ጥያቄው ሳይገባ ተቆርጧል። እዚህ ሙሉውን እዩት፦

ጥያቄ 45
አላህ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው በስድስት ቀን ወይስ በስምንት ቀን?

በስድስት ቀን፦
57:4 እርሱ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዙፋኑ ላይ የተደላደለ ነው፤

በስምንት ቀን፦
41:9-12 በላቸው፦ እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለርሱም ባላንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው። በርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፤ በርሷም በረከትን አደረገ፤ በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውስጥ፣ ለጠያቂዎች ትክክል ሲሆኑ ወሰነ።…..በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደርጋቸው፤

መልስ
አምላካችን አላህ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ እንደፈጠረ ይናገራል፦
7፥54 *ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው*፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام
50፥38 *ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን*፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

ይህ ጥቅላዊ ገለጻ ሲሆን በተናጥል አስፈላጊ የሆነው አፈጠጠሩ እንዲህ ይገልጻል፦
41፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ *"ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን?"* ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

"ኸለቀ" ማለት "ፈጠረ" ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ቀን እስከ አራተኛው ቀናት ባሉት በአራት ቀናት ውስጥ በምድር ላይ የረጉ ጋራዎችን፣ በውስጧም ምግቦችዋን ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦
42፥10 በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፡፡ በእርሷም በረከትን አደረገ፡፡ *"በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ"*፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ
"ወሰነ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን በምድር ውስጥ ያለውን መወሰኑን እንጂ መፍጠሩን አያሳም። "ቀደረ" እና "ኸለቀ" በይዘትም ሆነ በአይነት፥ በመንስኤውም ሆነ በውጤት ሁለት የተለያዩ ለየቅል የሆኑ ቃላትና ትርጉም ናቸው። በየትኛው ቀምርና ስሌት ቀምራችሁን አስልታችሁ፥ በየትኛው መስፈትና ሚዛን ለክታችሁና መዝናችሁ ነው "ወሰነ" የሚለውን "ፈጠረ" ብላችሁ 2+4= 6 ብላችሁ ድምር ውስጥ የገባችሁት? ዐውዱን ንባቡን"contextual setting" ቀጥለን እንየው፦
42፥11 *"ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ*፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ

“ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَانٌۭ ሲሆን “ጋዝ” ማለት ነው፤ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አላህ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ። “ሱመ” ثُمَّ ማለትም ከዚያም” የሚለው አያያዥ መስተጻምር ተርቲብ ነው፤ “ተርቲብ” ترتيب ማለት “ቅድመ-ተከተል” ማለት ነው፤ ይህ ቅድመ-ተከተል በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ የጊዜ ቅድመ-ተከተል ሲሆን ሁለተኛው የንግግር ቅድመ-ተከተል ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ዓውዱ የንግግር ቅድመ-ተከተል ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ አላህ ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፤ ጭስ የነበረችውን ሰማይ በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 *በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው*፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ *ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ

ቁጥር ሲገኝ 2+4+2= 8 ማለት ዝም ብሎ ቀላል አይደለም። ማን መደመር ውስጥ ግባ አለህ? ምድር በሁለት ቀን ውስጥ መፈጠሩን፣ የነበረው ሰማይ ሰባት ሰማያት በሁለት ቀን ውስጥ መደረጋቸው እና በምድር ውስጥ ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ መወሰኑን ነው የሚናገረው። ሲቀጥል “ፊ” فِي የሚለው መስተዋድድ “ውስጥ” ማለት ሲሆን 1 ቀን በሁለት ውስጥ 2 ቀን በአራት ውስጥ አሉ። ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ወሰነ ማለት እና ምግቦችዋን በአራተኛው ቀናት ወሰነ ማለት የተለያየ ትርጉም ይሰጣል። ስለዚህ 2 ቀናት 4 ቀናት ውስጥ ይካተታሉ። እሩቅ ሳንሄድ ምድር በሁለት ቀኖች ውስጥ ቢፈጠርም ምድር በስድስት ቀናት ውስጥ እንደተፈጠረች ይናገራል፦
7፥54 *ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው*፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام

ይህ የሚያሳየው 2 ቀናት በስድስት ቀናት ውስጥ መኖራቸውን እንጂ እዚህ ጋር 6 ስለሚል 6+2+4+2=14 ብለን የቂል አስተሳሰብ ማሰብ አለሌነት ነው። እኔ በነካ እጄ በሰማይና ምድር አፈጣጠር ዙሪያ እንዲገባቸው አንድ ጥያቄ ከባይብል ልጠይቃቸው፦ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የፈጠረው በመጀመሪያ ቀን ወይስ በስድስት ቀን?

A.በመጀመሪያ ቀን፦
ዘፍጥረት 1፥1-5 *"በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ *"ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን*፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።

B. በስድስት ቀን፦
ዘጸአት 31፥17 *"እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ"*፥
ዘጸአት 20፥11 *እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና"*።

እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የፈጠረው በመጀመርያ ቀን ነው ወይስ በስድስት ቀን? በስድስት ቀናት "ውስጥ" ቢል ኖሮ ምናልባት 1 ቁጥር በስድስት "ውስጥ" ስላለች ችግር አይኖረውም ነበር። ይህ ወፍራም የቤት ሥራ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙተሲል እና ሙሥተቲር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

43፥3 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

“አል በላጋህ” البلاغة ማለት “የንግግር ስልት”rhetoric” ማለት ነው፤ በግሪክ “ሬቶሪኮስ” ῥητορικός ይሉታል። አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ በላጋህ በማድረግ በዐረቢኛ በላጋህ አውርዶታል፦
43፥3 *እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*። إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

በዚህ የንግግር ስልት ውስጥ ሁለት ዋና ዋና እሳቤዎች አሉ፥ አንዱ "ሙተሲል" مُتَّصِل ሲሆን ሁለተኛው "ሙሥተቲር" مُسْتَتِر ነው። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ሙተሲል"
"ሙተሲል" مُتَّصِل ማለት በቃላት፣ በሃረግ እና በዓረፍተ-ነገር ግልጽ ሆኖ የሚመጣ ግስ እና ተውላጠ-ስም ነው። ለምሳሌ አላህ፦ ለነቢያችን"ﷺ" "ቁል" ማለትም "በል" በሚል ትእዛዛዊ ግስ ይናገራል፦
7፥188 *እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስጠንቃቂ እና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው*፡፡ قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ ۚ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

በተጨማሪም ነቢያችን"ﷺ" ያሉትን ነገር "ቃለ" قَالَ ማለትም "አለ" በማለት ለእኛ ይነግረናል፦
25፥30 መልክተኛውም «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት» *አለ*፡፡ وَقَالَ ٱلرَّسُولُ يَٰرَبِّ إِنَّ قَوْمِى ٱتَّخَذُوا۟ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانَ مَهْجُورًۭا

ይህ "ቁል" ወይም "ቃለ" የሚለው ግስ አያያዥ ትረካ ሲሆን በግልጽ ሲመጣ "ሙተሲል" مُتَّصِل ይባላል።
ነጥብ ሁለት
"ሙሥተቲር"
"ሙሥተቲር" مُسْتَتِر ማለት በቃላት፣ በሃረግ እና በዓረፍተ-ነገር ተደብቆ የሚመጣ ግስ እና ተውላጠ-ስም ነው። ለምሳሌ አላህ፦ ለነቢያችን"ﷺ" "ቁል" ማለትም "በል" በሚል ትእዛዛዊ ግስ ተደብቆ እዚህ አንቀጽ ላይ መጥቷል፦
11፥2 *(እንዲህ በላቸው)፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡»* أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

የዐማርኛ የቁርኣን ትርጉም "እንዲህ በላቸው" የሚለው ቃል በቅንፍ ያስቀመጡት "ቁል" የሚለው ስለሌለ እና "ቁል" የሚለው ተደብቆ ስለሚመጣ ነው፤ "ከእርሱ ማለትም ከአላህ የተላክሁ" የሚለው ነቢያችን"ﷺ" እንዲሉት የታዘዙት ቃል እንደሆነ እሙን ነው፦
51፥49 *"ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት ጥንድን ፈጠርን"*፡፡ وَمِن كُلِّ شَيْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
51፥50 *"«ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና» (በላቸው)*፡፡ فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ ۖ إِنِّي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِينٌ

"ፈጠርን" የሚለው አላህ ነው፤ ቀጥሎ "አስጠንቃቂ ነኝ" የሚለውን በውስጠ ታዋቂነት "ቁል" የሚለው ተደብቆ ስለሚመጣ ለሙስተቲር አቻ ትርጉም ስለሌለ የዐማርኛ የቁርኣን ትርጉም "በላቸው" የሚለው ቃል በቅንፍ አስቀምጠውታል።
ነቢያችን”ﷺ” ጂብሪልን “አሁን ከምትጎበኘን በብዛት እኛን ለመጎብኘት ምን ያግድሃል? ሲሉት፤ እርሱም፦ “በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም” ብሎ መለሰ፤ አላህ ይህንን የመለሰውን መልስ በተከበረው ቃሉ ለእኛ እንዲህ ነገረን፦
19፥64 *(ጂብሪል አለ)፦ «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም»* وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُۥ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّۭا
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97 , ሐዲስ 81:
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ጂብሪል ሆይ! አሁን ከምትጎበኘን በብዛት እኛን ለመጎብኘት ምን ያግድሃል? አሉት፤ እርሱም፦ "በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም፤ ከዚያም፦ ጂብሪል አለ፦ “በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም” የሚለው አንቀፅ ከዚያም ወረደ፤ ይህም ለሙሐመድ”ﷺ” መልስ ነው*። حَدَّثَنَا خَلاَّدُ بْنُ يَحْيَى، حَدَّثَنَا عُمَرُ بْنُ ذَرٍّ، سَمِعْتُ أَبِي يُحَدِّثُ، عَنْ سَعِيدِ بْنِ جُبَيْرٍ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ يَا جِبْرِيلُ مَا يَمْنَعُكَ أَنْ تَزُورَنَا أَكْثَرَ مِمَّا تَزُورُنَا ‏”‌‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلاَّ بِأَمْرِ رَبِّكَ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا‏}‏ إِلَى آخِرِ الآيَةِ‏.‏ قَالَ هَذَا كَانَ الْجَوَابَ لِمُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم‏.‏

ጂብሪል መልአክ እንደመሆኑ በል ተብሎ ከሚታዘዘው ውጪ አንድም ቃል አይልም፤ መላእክት አላህ በንግግር አይቀድሙትም፤ እርሱ ያላለውን አይሉም፤ እነርሱም በትእዛዙ ይሠራሉ፦
21፤27 *በንግግር አይቀድሙትም፤ ያላለውን አይሉም፡፡ እነርሱም በትእዛዙ ይሠራሉ*፡፡ لَا يَسْبِقُونَهُۥ بِٱلْقَوْلِ وَهُم بِأَمْرِهِۦ يَعْمَلُونَ

ስለዚህ ከመነሻው በል ብሎ ያለው አላህ ነው፤ ካለም በኃላ “አለ” ብሎ ለእኛ የሚነግረን አላህ ነው። "አለ" የሚለው በሙሥተቲር ከላይ እንደተገለጸው የመጣ ነው። ተመሳሳይ ናሙና እስኪ እንመልከት፦
3፥51 *«አላህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት*፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» (አላቸው)፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

"ቃለ" ወይም "አላቸው" የሚለው ተደብቆ መምጣቱን የምናውቀው በሌላ አንቀጽ ዒሣ፦ "ያዘዝከኝን ቃል" ማለቱ ነው፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ * አላህ ጌታዬን እና ጌታችሁን ነው፥ አምልኩት* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

በተጨማሪ ለምሳሌ አላህ እኛ እንድንል፦ "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" በሉ ይላል፦
1፥6 *ቀጥተኛውን መንገድ ምራን*፡፡ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
“ኢህዲና” اهْدِنَا ማለትም “ምራን” ብዙ ቁጥር ሲሆን ይህ ባለቤት ግስ አማኞችን ያመለክታል፤ ተሳቢው ግስ ደግሞ መሪውን አላህን ያመለክታል፤ ስለዚህ “ቁሉ” قُلُوا የሚለው ሙስተቲር ሆኖ የመጣ ነው። ለምሳሌ በሱረቱል በቀራህ 2፥187 ላይ “ከተበ” كَتَبَ ማለትም “ጻፈ” የሚለውን ወደ ኢንግሊሽ ሲቀየር “He wrote” ነው፣ “He” ደግሞ ወደ ዐረቢኛ “ሁወ” هُوَ ማለትም “እርሱ” ነው፤ “ሁወ” هُوَ የሚለው “ከተበ” كَتَبَ ላይ ሙስተቲር ሆኖ የመጣ ነው፤ በተጨማሪም ነቢያችን”ﷺ” በሐዲስ ላይ ሱረቱል ፋቲሓን የሚለው የአላህ ባሪያ ወደ አላህ መሆኑን በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ነግረውናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4 ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ”ረ.ዐ” እንደተረከው *ነቢዩ”ﷺ” አሉ፦ “የቁርአን እናት ሳያነብ የሰገደ ሰው ሶላቱ ጎዶሎ ነው”* አንድ ሰው ለአቢ ሁረይራ፦ “ከአሰጋጁ በኋላ ብንሆንም እንኳን”? አለው፤ እርሱም አለ፦ “ለራስህ አንብብ ምክንያቱም ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁና፦ *”ኃያሉና የተከበረው አላህ እንዲህ ብሏል፦ “ሶላትን በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፍየዋለሁ እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል*፤ ባሪያው፦ *”ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው” ሲል አላህ፦ “ባሪያዬ አመሰገነኝ” ይላል*፤ ባሪያው፦ *”እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ” ሲል ደግሞ አላህ፦ “ባሪያዬ አሞገሰኝ’ ይላል*፤ ባሪያው፦ *”የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው” ሲል አላህ፦ ባሪያዬ አላቀኝ” ይላል*፤ ባሪያው፦ *”አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን” በሚል ግዜ አላህ፦ “ይህ በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ነው እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል” ይላል*፤ ባሪያው፦ *”ቀጥተኛውን መንገድ ምራን የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” በሚል ግዜ ደግሞ አላህ፦ “ይህ ለባሪያዬ ነው፤ እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል” ይላል*፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ صَلَّى صَلاَةً لَمْ يَقْرَأْ فِيهَا بِأُمِّ الْقُرْآنِ فَهْىَ خِدَاجٌ – ثَلاَثًا – غَيْرُ تَمَامٍ ‏”‏ ‏.‏ فَقِيلَ لأَبِي هُرَيْرَةَ إِنَّا نَكُونُ وَرَاءَ الإِمَامِ ‏.‏ فَقَالَ اقْرَأْ بِهَا فِي نَفْسِكَ فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى قَسَمْتُ الصَّلاَةَ بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي نِصْفَيْنِ وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ فَإِذَا قَالَ الْعَبْدُ ‏{‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى حَمِدَنِي عَبْدِي وَإِذَا قَالَ ‏{‏ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى أَثْنَى عَلَىَّ عَبْدِي ‏.‏ وَإِذَا قَالَ ‏{‏ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ مَجَّدَنِي عَبْدِي – وَقَالَ مَرَّةً فَوَّضَ إِلَىَّ عَبْدِي – فَإِذَا قَالَ ‏{‏ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏.‏ فَإِذَا قَالَ ‏{‏ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ * صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا لِعَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ سُفْيَانُ حَدَّثَنِي بِهِ الْعَلاَءُ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ يَعْقُوبَ دَخَلْتُ عَلَيْهِ وَهُوَ مَرِيضٌ فِي بَيْتِهِ فَسَأَلْتُهُ أَنَا عَنْهُ ‏.‏

አሁን ጉድ የሚፈላው በተመሳሳይ ስሌትና ቀመር ባይብል ላይ መቀመጡን ስናይ ነው። ዓራጊው ኢየሱስ ሆኖ ሳለ ለመቅደላዊት ማርያም፦ "እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ" በዪ አላት፦
ዮሐንስ 20:17 ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። *”እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ”* ብለሽ *”ንገሪአቸው”* አላት።”

መቅደላዊት ማርያም ሄዳ፦ “እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ” ስትል የምታርገዋ መቅደላዊት ማርያም ናትን? አይ “ይላል” በይ ለማለት ተፈልጎ ነው ከሆነ መልሱ፥ "ይላል" የሚለው የት አለ? ስንል በውስጠ ታዋቂነት አለ ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን በዚህ መልክና ልክ ተረዱት። ሕዝቅኤል፦ “እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ” በል ተብሏል፦
ሕዝቅኤል 11፥16 ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ፥ ወደ አገሮችም በትኛቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ፥ በመጡባቸው አገሮች በእነዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ በል።

“እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ” የሚለው ሕዝቅኤል ነውን? አይ አይ “ይላል” በል ለማለት ተፈልጎ ነው ከሆነ መልሱ፥ "ይላል" የሚለው የት አለ? ስንል በውስጠ ታዋቂነት አለ ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ” በላቸው” አለው፦
ዘጸአት 16 ፥11-12 *እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦* የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ፦ ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ *እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ” በላቸው*።

“እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ” የሚለው ሙሴ ነውን? አይ “ይላል” በል ለማለት ተፈልጎ ነው ከሆነ መልሱ፥ "ይላል" የሚለው የት አለ? ስንል በውስጠ ታዋቂነት አለ ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን በዚህ ሒሳብ ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የወላጅ ሐቅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

31፥14 *ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት አዘዝነው*፡፡ መመለሻው ወደ እኔ ነው፡፡ أَنِ اشْكُرْ لِي وَلِوَالِدَيْكَ إِلَيَّ الْمَصِيرُ

የወላጅ ሐቅ በኢሥላም ትልቅ ቦታ አለው፥ ወላጅን ማመስገን፣ ለወላጅ መልካም መሥራት፣ በጎ መዋል፣ መልካም ንግግር መናገር የወላጅ ሃቅ ነው፦
31፥14 *ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት አዘዝነው*፡፡ መመለሻው ወደ እኔ ነው፡፡ أَنِ اشْكُرْ لِي وَلِوَالِدَيْكَ إِلَيَّ الْمَصِيرُ
45፥15 *ሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው*፡፡ وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ إِحْسَانًا
17፥23 ጌታህም እንዲህ ሲል አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ *በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ኡፍ አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው*፡፡ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۚ إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا
6፥151 «ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር በእርሱም ያዘዛችሁን ላንብብላችሁ» በላቸው፡፡ «በእርሱ በአላህ ላይ ምንንም ነገር አታጋሩ፡፡ *ለወላጆችም በጎን ሥራ ሥሩ*፡፡ قُلْ تَعَالَوْا أَتْلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمْ عَلَيْكُمْ ۖ أَلَّا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا
4፥36 *አላህንም አምልኩ፤ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው መልካምን ሥሩ*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

ወላጆችን ችላ ማለት ትልቅ ወንጀል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 47
አቢ በክራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ትላልቅ ወልጀሎችን ልንገራችሁን? እነርሱም፦ "አዎ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" እርሳቸው፦ "በአላህ ላይ ማሻረክ እና ለወላጆች ግዴለሽ መሆን ነው" አሉ"*። عَنْ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ أَبِي بَكْرَةَ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِأَكْبَرِ الْكَبَائِرِ ‏"‌‏.‏ قَالُوا بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ‏.‏ قَالَ ‏"‏ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْن
ነገር ግን ለወላጅም ቢሆን በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች እና ለአላህ መስካሪዎች መሆን አለብን፦
4፥135 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ይህ ቃል የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ሲሆን “ፍትሕ” ማለት ነው፤ ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ ተብሎ እና አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ተብሎ የሚደረግ ነው። ይህ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ፍትሕ ዝንባሌን ከመከተል ነጻ ያወጣል። አላህ ሰውንም በወላጆቹ በመልካም አድራጎትን እንድንወዳጅ ቢያዘንም ነገር ግን ወላጅ ጣዖት አምልክ ቢለን በዚህ ነጥብ በፍጹም እንዳንታዘዛቸው ከልክሎናል፦
31፥15 ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር *"በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው፡፡ "በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው"*፡፡ ወደ እኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡وَإِن جَاهَدَاكَ عَلَىٰ أَن تُشْرِكَ بِي مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا ۖ وَصَاحِبْهُمَا فِي الدُّنْيَا مَعْرُوفًا ۖ وَاتَّبِعْ سَبِيلَ مَنْ أَنَابَ إِلَيَّ ۚ ثُمَّ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
29፥8 *ሰውንም በወላጆቹ መልካም አድራጎትን አዘዝነው፡፡ ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ጣዖት በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው*፡፡ መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ حُسْنًا ۖ وَإِن جَاهَدَاكَ لِتُشْرِكَ بِي مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا ۚ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

"በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። "ተወዳጃቸው" የሚለው ቃል "ሷሒብሁማ" صَاحِبْهُمَا ሲሆን "ሷሒብ" صَىٰحِب ማለትም "ባልደረባ" ከሚለው የስም መደብ የረባ ሲሆን "ባልደረባ ሁናቸው" ማለት ነው። በመልካም ሥራ ባልደረባነት ማለት ወላጅን ማመስገን፣ ለወላጅ መልካም መሥራት፣ በጎ መዋል፣ መልካም ንግግር መናገር እና ጡረታ መጦር ወዘተ ነው። እርሱም ቢሆን በቅርቢቱም ዓለም ጉዳይ ላይ ነው። ግን በተቃራኒው፦ "ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ጣዖት በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው" የሚለውን ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። ይህንን ክህደት ከእምነት አብልጠው ቢወዱ እረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ እረዳት የሚያደርጋቸው እነዚያ እነርሱ በዳዮች ናቸው፦
9፥23 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክህደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነርሱ በዳዮች ናቸው*። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا آبَاءَكُمْ وَإِخْوَانَكُمْ أَوْلِيَاءَ إِنِ اسْتَحَبُّوا الْكُفْرَ عَلَى الْإِيمَانِ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አውሊያ" أَوْلِيَاءَ በብዜት የመጣው "ወሊይ" وَلِىّ ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "ወሊይ" ማለት "እረዳት" ማለት ነው። በመልካም በማዘዝ በመጥፎ በመከልከል ለአማኞች ወሊይ እራሳቸው አማኞች እንጂ ከሃድያን ወላጆች ወሊይ አይደሉም፦
9፥71 *"ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ"*፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَيُطِيعُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَـٰئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ اللَّهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

ይህ ወደ ሺክር የሚያመራ ወዳጅነት በትንሳኤ ቀን፦ "ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ" የሚያስብል ጸጸት ነውና እንጠንቀቅ፦
25፥28 «ዋ ጥፋቴ! *"እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ"*፡፡ يَا وَيْلَتَىٰ لَيْتَنِي لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙሲባህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥30 *"ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት ምክንያት ነው"*፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡ وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

አምላካችን አላህ “አል-ዐሊም” العَلِيم ማለትም “ሁሉን ዐዋቂ" ነው፤ “ዒልም” عِلْم ማለትም “ዕውቀት” ደግሞ የእርሱ ባህርይ ነው፤ አላህ ሁሉን ነገር ያካበበው በዕውቀቱ ነው፦
65፥12 አላህ በነገር ሁሉ ቻይ መሆኑን አላህም *በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ ይህንን አሳወቃችሁ*። أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا

እዚህ አንቀፅ ላይ የምንመለከተው የአላህ "ዕውቀት" እና “ሸይእ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ሁለት ጉዳዮች መሆናቸውን ነው፥ “ዕውቀት” ምንም ነገር ሳይኖር የአላህ ባህርይ ሲሆን “ነገር” ደግሞ “ፍጡር” ነው፥ “ነገር” ደግሞ ጊዜና ቦታ ሁሉ ነው። አምላካችን አላህ ስለ አንድ ነገር ዕውቀት በመጽሐፍ ውስጥ ከሁሉ ነገር መከሰት፣ መደረግ እና መከናወን በፊት መዝግቦቷል፦
50፥4 ከእነርሱ ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ *ዐውቀናል፡፡ እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ*፡፡ قَدْ عَلِمْنَا مَا تَنقُصُ الْأَرْضُ مِنْهُمْ ۖ وَعِندَنَا كِتَابٌ حَفِيظٌ
22፥70 አላህ *በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መኾኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ነው*፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَابٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 54, ሐዲስ 414
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ በመጀመሪያ ምንም ነገር ሳይኖር አላህ ነበረ፤ ከዚያ ዙፋኑን በውሃ ላይ ነበረ፤ *ከዚያ ሁሉን ነገር በመጽሐፍ ጻፈ*፤ ከዚያ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ، وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ، وَكَتَبَ فِي الذِّكْرِ كُلَّ شَىْءٍ، وَخَلَقَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ ‏”‌‏.

“ለውሐል መሕፉዝ” لَوحَ المَّحْفُوظ ማለት “የተጠበቀው ሰሌዳ”preserved tablet” ማለት ሲሆን አላህ በለውሐል መሕፉዝ ላይ ድርጊቱን የከተበው ስለሚያውቀው እንጂ እንዲከናወን አይደለም።
ለምሳሌ ሀራም ነገር ማድረግ ከልክሏል፤ ያንን የከለከለው አንድ ሰው ከማድረጉ በፊት አላህ የከተበው ስለሚያውቀው እንጂ ያ ሰው እንዲያደርገው አይደለም፤ ያ ቢሆንማ አላህ እንዲያደርግ መከልከሉና በማድረጉ መቅጣቱ ትርጉም አይኖረውም ነበር። ስለዚህ አምላካችን አላህ አንድ ክስተት ከመከሰቱ ቢፊት፣ አንድ ድርጊት ከመደረጉ በፊት፣ አንድ ክንውን ከመከናወኑ በፊት ስለሚያውቀው ያንን ዕውቀት በተጠበቀው ሰሌዳ ከትቦታል፦
57፥22 በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ ማንንም አትነካም *ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ*፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي أَنفُسِكُمْ إِلَّا فِي كِتَابٍ مِّن قَبْلِ أَن نَّبْرَأَهَا ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ
"ሙሲባህ" مُّصِيبَة ማለት "መከራ" ማለት ሲሆን ይህ ሙሲባህ ክስተት ሆኖ ከመከሰቱ ቢፊት፣ ድርጊት ሆኖ ከመደረጉ በፊት፣ ክንውን ሆኖ ከመከናወኑ በፊት አላህ ስለዚያ ሙሲባህ ስለሚያውቀው ያንን ዕውቀት በተጠበቀው ሰሌዳ ከትቦታል። ያ ሙሲባህ የሚከሰተው አላህ ስለፈቀደ ነው፦
64፥11 *"መከራም ማንንም አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ"*፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን ለትዕግስት ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَمَن يُؤْمِن بِاللَّهِ يَهْدِ قَلْبَهُ ۚ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

የአላህ ፈቃድ በሁለት መልክ ለፍጡራን ተቀድሯል፤ አንዱ ያለፈቃዳቸው ሲሆን ሁለተኛው በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ላይ ነው። የመጀመሪያው ፍጥረት ሲፈጠር ያለፈቃዱ በአላህ ፈቃድ የተፈጠረ ነው። ሰው በመወለድ፣ በሞት፣ በመተኛት፣ በማስነጠስ ምርጫ የለውም፦
28፥68 *ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ለፍጡራን ምርጫ የላቸውም*፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَة

ለምሳሌ ሞት ሙሲባህ ነው፤ ግን መሞት አያስጠይቅም አያስቀጣም። ሁለተኛው ሙሲባህ ግን በተሰጠው ነጻ ፈቃድና ምርጫ የምናመጣው ስለሆነ ያስጠይቃል፦
21፥23 *ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ፍጥረቶቹ ግን ይጠየቃሉ*፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ
16፥93 *ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ*፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون
102፥8 ከዚያም *ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ*። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ

“ነዒም” نَّعِيمِ ማለት “ጸጋ” ማለት ነው፤ በተሰጠን ነጻ ፈቃድና ምርጫ የምንሰራው መልካም ሥራ ሆነ ክፉ ሥራ ያስጠይቀናል ወይም ያስመነዳናል። ሁሉም ሙሲባህ ሳይሆን በተሰጠን ነጻ ምርጫ ከሙሲባህ የሚነካን እጆቻችን በሠሩት ፈሣድ ነው፦
42፥30 *"ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት ምክንያት ነው"*፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡ وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ
30፥41 *"የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተሰራጨ"*፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡ ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

"ኃጢኣት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ፈሣድ" ሲሆን “ፈሣድ” فَسَاد ማለት “ጥፋት” “ብክለት” “ብልሽት” ማለት ነው፥ ይህንን ድርጊት የሚተገብሩ ግለሰቦች ደግሞ “ሙፍሢድ” مُفْسِد ማለትም “አጥፊ” “አበላሺ” “በካይ” ይባላሉ። ሙሲባህ ሳይሆን "ከ"ሙሲባህ ሰዎችን የሚያገኘው የሰዎች እጆች በሠሩ ፈሣድ ነው። ለምሳሌ በምድሪቱ ላይ ረሃብ ያለው ምግብ ታጥቶ አሊያም ለእህል የሚሆን ተስማሚ የእርሻ ቦታ ታጥቶ ሳይሆን ክፋት፣ ጭካኔ፣ ስግብግብነት፣ ጥላቻ ስላለ ነው። በምድሪቱ ላይ ድህነት ያለው 80% የሚሆነውን የምድራችን ሃብት 20% የሚሆኑ የምድራችም ሃብታሞች በሞኖፓልና በስግብግብነት ስለያዙት ነው።
አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፤ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፥ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ ለሰዎች መልካምን አድርግ፤ በምድርም ውስጥ ፈሣድን አትፈልግ፡፡ አላህ ሙፍሠዲንን አይወድምና፦
28፥77 *"አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፤ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፤ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ ለሰዎች መልካምን አድርግ፤ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና"*። وَابْتَغِ فِيمَا آتَاكَ اللَّهُ الدَّارَ الْآخِرَةَ ۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ الدُّنْيَا ۖ وَأَحْسِن كَمَا أَحْسَنَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ الْفَسَادَ فِي الْأَرْضِ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሦስት መአልትና ሌሊት በመቃብር

ሦስቱ ቀን የሚጀምረው ከመቃብር ነው ብዬ እሞግታለው፥ ምክንያቱም፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥3 ..መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ that he was buried and that he was raised on the third day according to the Scriptures,

ተቀበረ ካለ በኃላ በሦስተኛው ቀን ተነሣ ይለናል። በምድር ልብ ማለትም በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ ይናገራል፦
ማቴዎስ ወንጌል 12፥40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።

ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በመቃብር ያለውን ጊዜ የሚሸፍን መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ መቃብር የገባው ደግሞ በምሽት ነው፦
የማርቆስ ወንጌል 15.42-46 አሁንም """በመሸ ጊዜ""" የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፥ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። ጲላጦስም አሁኑን እንዴት ሞተ ብሎ ተደነቀ፥ የመቶ አለቃውንም ጠርቶ ከሞተ ቆይቶአልን? ብሎ ጠየቀው፤ ከመቶ አለቃውም ተረድቶ በድኑን ለዮሴፍ ሰጠው። በፍታም ገዝቶ አውርዶም በበፍታ ከፈነው ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው፥ በመቃብሩ ደጃፍም ድንጋይ አንከባለለ።

""በመሸ ጊዜ""" የሚለው ሃረግ ይሰመርበት። የአይሁድን በዓል ማየት ይቻላል፥ አይሁድ የሚያከብሩት በዓል ከ 12 ሰአት በኃላ የነገው ነው። ያ በዓል የሚጀመረውም ሌሊቱ ከምሽቱ 12 ነው። ምሽት የሌሊት መጀመሪያ ነው፦
ዘጸአት 12፥18 በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን "በመሸ ጊዜ" ከወሩም እስከ ሀያ አንድ ቀን በመሸ ጊዜ የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።
የማቴዎስ ወንጌል 26፥20 "በመሸም ጊዜ" ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 11፥13 ዳዊትም ጠራው፥ በፊቱም በላና ጠጣ፥ አሰከረውም ነገር ግን "በመሸ ጊዜ" ወጥቶ ከጌታው ባሪያዎች ጋር በምንጣፉ ላይ ተኛ፥
የማርቆስ ወንጌል1፥32 "ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ"፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤

"ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ" የሚለው ይሰመርበት። ምሽት ማለት የፀሐይ መግባት ነው፦
የማርቆስ ወንጌል1፥32 ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤

እንግዲህ ከዚህ ከሰንበት ማለት ከቅዳሜ ዋዜማ ምሽቱ የቅዳሜ ከሆነ ከዚያ ጀምራችሁ ቁጠሩት። ሰኞ ማታ ለማክሰኞ ዋዜማ ላይ ይመጣል። ያ ማለት ሶስት ቀንና ሌሊት አይሞላም። በተረፈ አይሁዳውያን ቀን የሚሉት ሙሉ መአልትና ሌሊት የያዘ እንጂ የተጎማመደ ብድር አይደለም። የተቀበረው የሰንበት ዋዜማ አልቆ ሲመሽ ከሆነ ከዚያ ሌሊት ጀምሮ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ሰኞ ማታ ለማክሰኞ ይሆናል። በሰምንቱ ፊተኛው ቀን እህዱ ጠዋት ከተነሳ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት የተባለው አይሞላም፦
ማርቆስ 16፥2 ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወደ መቃብር መጡ።

ብዙ ክርስቲያኖች የሚቆጥሩት ከተሰቀለበት ነው። ያ ግን ስህተት ነው። የሚቆጠረው በምድር ልብ ውስጥ ማለትም በመቃብር የቆየበት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
አንዱ አምላክ አይሞትም

2 ቆሮንቶስ 5 ፥14 ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤

""አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"" ይላል፤ አንዱ ምን? አንዱ አምላክ? በፍፁም አንዱ አምላክ እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፦
" #እርሱ #ብቻ #የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:16)
" #ብቻውን #አምላክ ለሚሆን #ለማይሞተው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:17)
"17 Now unto the King eternal, #immortal, invisible, the only wise God, [be] honour and glory for ever and ever. Amen."
(1Timothy 1:17)
1 ቆሮንቶስ 8፥4 #ከአንዱም #በቀር #ማንም #አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

አንዱ ምን ታዲያ? በአንዱ አምላክና በሰዎች መካከል ያለ አንዱ ሰው፦
" #አንድ #አምላክ አለና፥ በአምላክና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5)
"5 For [there is] #one #God, and one mediator between God and men, #the #man Christ Jesus;"
(1Timothy 2:5)
" ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና #በአንድ #ሰው #በኢየሱስ #ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 5:15)

አብ አንድ አምላክ ሲሆን የማይሞት ነው። ኢየሱስ አንዱ ሰው ስለ ሁሉ ሞተ። እንደ ጳውሎስ ትምህርት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
የስቅለት ውዝግብ

የአዲስ ኪዳን ምሁር ሄርማን ቻርለስ በ 1890 AD ሲናገሩ፦ 5,800 የሚደርሱ የአዲስ ኪዳን ግሪክ እደ-ክታባት ይገኛሉ፤ እነዚህ እደ-ክታባት እርስ በእርሳቸው የቃላት ሆነ የትርጉም ልዩነት አላቸው፤ ለምሳሌ በሳይናቲከስና በቫቲካነስ እደ-ክታባት መካከል የ 3,036 የቃላትና የትርጉም ልዩነት አላቸው ብለዋል፤ ይህ ልዩነት የመጣው የአዲስ ኪዳን ስረ-መሰረት”orgion” ስለሌለና አሁን ያለት እደ-ክታባት የቅጂዎች ቅጂ ስለሆነ እንደሆነ ምሁራን ይናገራሉ፤ ይህ ልዩነት ጤናማ አለመሆን ብቻ ሳይሆን የክርስትናን ዶግማ ክፉኛ ይፈታተናል፤ ምክንያቱም እነዚህን አራት ወንጌላት ሃዋርያት አለመፃፋቸው ብቻ ሳይሆን በእነርሱ የዳቦ ስም የገለበጡት ፅሁፍም ችግር ስላለበት ነው፤ እስቲ ይህንን ልዩነት ዛሬ በስቅለቱ ዙሪያ ያሉትን ዘገባዎች እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“የቤተ መቅደስም መጋረጃ”
የሉቃስ ዘጋቢ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከተቀደደ በኃላ እንደሆነ ይተርካል፦
ሉቃስ 23፥45-46 “የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ተቀደደ”። ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።

የማቴዎስ ዘገቢ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከመቀደዱ በፊት እንደሆነ ይተርካል፦
ማቴዎስ 27፥ 50-51 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። እነሆም፥ “የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ”፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከተቀደደ በኃላ እንደሆነ የሚተርክልን የሉቃስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከመቀደዱ በፊት እንደሆነ የሚተርክልን የማቴዎስ ዘጋቢ?

ነጥብ ሁለት
“በሰቀሉትም ጊዜ”
ቅድሚያ የአራቱ ወንጌላት ተራኪዎች ጊዜን የሚቆጥሩት በዕብራውያን አቆጣጠር ብቻ መሆኑ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ ነው፤ የሮማውያን አቆጣጠር አንዳንዶች ይጠቀሙ ነበር የሚለው ቅጥፈት የታሪክ፣ የአውድና የባህል ማስረጃ የለውም፤ ይህ ቅጥፈት ግጭትን ለመደበቅ ሆን ብሎ ግምታዊ ነው፤ ለምሳሌ ማርቆስ የዕብራዊያን አቆጣጠሩ ኢየሱስ ተሰቀለ የተባለበት በዕብራውያን 3 ሰአት ነው ይለናል፦
ማርቆስ 15፥25 “”በሰቀሉትም ጊዜ” “”ሦስት ሰዓት”” ነበረ።
ማርቆስ 15፥33 “ስድስት ሰዓትም”” በሆነ ጊዜ፥ እስከ “”ዘጠኝ ሰዓት”” በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
34 “”በዘጠኝ ሰዓትም”” ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤

በዚህ ሁለም ይስማማል፤ ኢየሱስ ተሰቀለ የተባለው ከ ቀኑ ጠዋት 3 ሰአት ነው፤ ከዮሃንስ ዘገባ ጋር ፍጭቱን ከማየታችን በፊት ዮሃንስ የሚጠቀመው የዕብራውያን አቆጣጠር መሆኑን በአፅንኦትና በአንክሮት እንመልከት፦
ዮሐንስ 1፥40 መጥታችሁ እዩ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ “አሥር ሰዓት” ያህል ነበረ።
ዮሐንስ 4፥6 በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ “”ጊዜውም ስድስት ሰዓት”” ያህል ነበረ።

ድካም ያለበት ቀትር ስድስት ሰአት የዕብራውያን አቆጣጠር እንጂ የሮማውያን አቆጣጠር አይደለም፤ ምክንያቱም የሮማውያን ስድስት ሰአት የዕብራውያን ከምሽቱ 12 ሰአት አሊያም ከጎህ 12 ሰአት ነው፤ ይህን ሃቅ ይዘን የዮሃንስ ዘጋቢ ጋር ኢየሱስ ስድስት ሰአት ላይ እንኳን ሊሰቀል ይቅርና ገና ህዝቡ ስቀለው እያሉ ይጮኹ እንደነበር ይተርካል፦
ዮሃንስ 19፥14-15 ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ “ስድስት ሰዓትም” የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም፦ እነሆ ንጉሣችሁ አላቸው። እነርሱ ግን፦ አስወግደው፥ አስወግደው፥ “”ስቀለው”” እያሉ ጮኹ።

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? በሰቀሉት ጊዜ 3 ሰአት ነበረ ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ 6 ሰአት ላይ ገና አልተሰቀለም ብሎ የሚተርከው የዮሃንስ ዘጋቢ?

ነጥብ ሶስት
“ሶስት ቀን”
ኢየሱስ የአላህ ነብይ ነው አይዋሽም፤ መቼም አራቱ ወንጌላት ላይ ያሉት ቃላት አይደለም የኢየሱስ ይቅርና የመጀመሪያዎቹ ፀሃፊያን ያልሆኑ ንግግሮች በእማኝነትና በአስረኝነት ማቅረብ ይቻላል፤ ነገር ግን ነጥባችን እርሱ አይደለም፤ ኢየሱስ ተናገረ ተብሎ የተቀጠፈበት ነገር እርስ በእርሱ ይጋጫል፤ እንደ ማርቆስ ዘጋቢ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በኃላ” የሚለው መስተዋድድ በአራተኛው ቀን አሊያም በአምስተኛው ቀን ሊሆን ይችላል፤ ግን ሶስኛውን ቀን አይጨምርም፦
ማርቆስ 8፥31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ሊነሣ” እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።

የማቴዎ ዘጋቢ ደግሞ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በ” የሚለው መስተዋድድ ሶስተኛውን ቀን ብቻ የሚያመለክት ነው፦
ማቴዎስ 16፥21 ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ “”በሦስተኛውም ቀን” ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ነው ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ነው ብሎ የሚተርከው የማቴዎስ ዘጋቢ?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ኢብሊሥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

“ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፤ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፤ ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፤ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ፤ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

ጂኒዎች የተፈጠሩበት አላማ የፈጠራቸው አላህ እንዲያመልኩ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“ኢብሊሥ” إِبْلِيس በተፈጥሮው ከሰው ወይም ከመልአክ ሳይሆን ከጂን ሲሆን በመጥፎ ባህርይው ደግሞ “ሸይጧን” ነው፤ ለአደም አልሰግድም ብሎ በአላህ ላይ ያመጸው እርሱ ነው፦
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

"ከጂን ነበር" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። አምላካችን አላህ "ለመላእክትም ለአደም ስገዱ" ብቻ ሳይሆን ለኢብሊስም ስገድ ብሎታል፥ ይህንን ማለቱ እዚሁ አንቀጽ ላይ፦ "ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ" በማለት አላህ አዞት እንደነበር ይናገራል፦
አላህ፦ *«ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው"*፡፡ «እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ፡፡ قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ ۖ قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِي مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُ مِن طِينٍ

"ባዘዝኳችሁ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ? ሳይሆን "ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ? አለው፥ "ባዘዝኩህ" የሚለው ሃይለ-ቃል ለአደም ስገድ ብሎ አዞት እንደነበር ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳይል። "ለመላእክትም ብቻ ለአደም ስገዱ" ቢል ኖሮ "ብቻ" የሚለው ገላጭ ቅጽል ስላለ አደም ከመላእክት ነበር ብለን እንደመድም ነበር። ነገር ግን "ለ" የሚለው መስተዋድድ መኖሩ በራሱ ለመላእክት ብቻ የሚለውን አያሲዝም። ለምሳሌ፦
7፥179 ከጂኒም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ *"ለ"እነርሱ ልቦች አሏቸው፥ ግን አይገነዘቡበትም፡፡ "ለ"እነርሱም ዓይኖች አሉዋቸው፥ ግን ዐያዩበትም፡፡ "ለ"እነርሱም ጆሮዎች አሉዋቸው ግን አይሰሙበትም"*፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው። وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُون

"ለሁም ቁሉብ" لَهُمْ قُلُوب "ለሁም አዕዩን" لَهُمْ أَعْيُن "ለሁም አዛን" آذَانٌ የሚሉትን ቁልፍ ቃላት አስምሩበት። "ለ"ዘንጊዎች ልቦች፣ ዓይኖች እና ጆሮዎች አሉዋቸው ማለት ሌላው ልቦች፣ ዓይኖች እና ጆሮዎች የለውም የሚለውን እንደማያሲዝ ሁሉ ለመላእክት ስገዱ ማለቱ ለኢብሊስ ስገድ አለማለቱን አያሲዝም። "ለ" የሚለው መስተዋድድ በመነሻ ቅጥያ መምጣቱ "ብቻ" የሚለውን መደምደሚያ አያስደርስም። ሲቀጥል "ኢብሊስ ብቻ ሲቀር" በሚለው ሃይለ-ቃል ላይ "ሲቀር" የምትለዋን ይዘን ኢብሊስ ከመላእክት ነበር ማለት አሁንም የቁርኣንን ሰዋስው ካለመረዳት የሚመጣ ጥራዝ-ነጠቅ ዕውቀት ነው፦
26፥77 *"«እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር እርሱ ወዳጄ ነው"*፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ
ኢብራሂም፦ "ለእኔ ጠላቶች ናቸው። ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር" ማለቱን አስተውል። "ሲቀር" የሚለውን አፍራሽ ቃል ይዘን ከዓለማቱ ጌታ ውጪ ለኢብራሂም ሁሉም ጠላት ነውን? አማንያን፣ ነቢያት፣ መላእክት፣ እንስሳትስ ጠላት ናቸውን? አይ "በቀር" የሚለው የአላህን ወዳጅ ለመሆን የገባ እንጂ "ሁሉን ጠላት ናቸው ከአላህ በቀር" ማለቱን አያሳይም ከተባለ እንግዲያውስ "በቀር" የሚለው ኢብሊስ ብቻ አለመታዘዙን እንጂ መላእክት ውስጥ መካተቱን አያሳይም።
ከመነሻው መላእክት በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም፦
16፥49 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ *"መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም"*፡፡ وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِن دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ *"እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም"*፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አሉ፡፡ *"አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

መላእክት አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ። ኢብሊስ ግን ከመላእክት ስልላሆነ ኮራ፥ በጌታውም ትእዛዝ አመጸ፦
38፥74 ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ *"ኮራ"*፤ ከከሓዲዎቹም ነበር፡፡ إِلَّا إِبْلِيسَ اسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

ይህንን ሊገባችሁ በሚችለው መልኩ ከራሳችሁ ባይብል ላሳያችሁ፦
ዘፍጥረት 2፥16-18 *"እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና"*። እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።

እግዚአብሔር አደምን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ "አትብላ" ብሎ ሲያዘው ሔዋን አልተፈጠረችም። ነገር ግን ሔዋን "አትብሉ" ብሎናል ብላለች፦
ዘፍጥረት 3፥2 ሴቲቱም ለእባቡ አለችው፦ በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን፤ ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ *"እግዚአብሔር አለ፦ "እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም"*።

"አትብላ" ብሎ ያዘዘው አዳምን ብቻ ሆኖ ሳለ "አትብላ" የሚለውን "አትብሉ" በሚል ስላስቀመጠች ሁለቱንም አዟቸው ነበር ይባላል እንጂ ሔዋን አዳም ናት ይባላልን? ሔዋንን ሲያዛት የሚያሳይ ጥቅስ አለመኖሩ ሔዋንን አለማዘዙን ያሳያልን? በፍጹም! እንግዲያውስ ከላይ ያለውን የቁርኣን አንቀጽ በዚህ ሒሳብ ተረዱት። ኢብሊስ በፍጹም መልአክ አልነበረም።
በተጨማሪም በአሌክሳድሪየስ ኮዴክስ በሚገኘው በሮሙ ክሌመንት ማለትም በቀለሚንጦስ ደግሞ የሰገዱት እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ እንደሆነ ተገልጿል፦
ክሌመንት 1፥41 አራዊት፣ እንስሳት ወፎች *”እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ"* ወደ አዳም ተሰበሰቡ ከፊቱ ቁመው ራሳቸውን አዘነበሉ፤ *ለአዳምም ሰገዱ"*።

ሰይጣን ለአዳም ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ኃብተ ፀጋ ማለትም “ሁሉም ፍጥረት መስገዳቸው” ባየ ጊዜ ከዚያ ሰአት ጀምሮ ቅንአት አደረበት፤ እግዚአብሔር በሰይጣን ላይ የነበረውን የምስጋና ልብስ እና የግርማ ልዕልና አስወገደ፤ ሰይጣን ብሎ ሰየመው፦
ክሌመንት 1፥46 *"ሰይጣን ለአዳም ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ኃብተ ፀጋ ባየ ጊዜ ከዚያ ሰአት ጀምሮ ቅንአት አደረበት"*።
ክሌመንት 1፥47 *"በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በሰይጣን ላይ የነበረውን የምስጋና ልብስ እና የግርማ ልዕልና አስወገደ፤ ሰይጣን ብሎ ሰየመው፤ በእግዚአብሔር ላይ ታብዮአልና፤ በእግዚአብሔር መንገድ አልሄደምና ለራሱ ክብር ወዷልና"*።

በተጨማሪም በመቃብያን ላይ ዲያቢሎስ የወደቀበት ለአደም አልሰግድ በማለቱ እንደሆነ ተገልጿል፦
3ኛ መቃብያን 1፥6 *ለሚዋረድልኝ ለአዳም አልሰግድም በማለቴ እግዚአብሔር ስለአባታቸው ስለአዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥያቄአችን!

የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመርያው ማን ነው? ጉማሬ? ሰማይና ምድር? ወይስ ኢየሱስ?

A. ጉማሬ፦
ኢዮብ 40፥15 *"ከአንተ ጋር የሠራሁትን ጉማሬ እስኪ ተመልከት"*፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
ኢዮብ 40፥19 *"እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት "አውራ" רֵאשִׁ֣ית ነው"*።
English Standard Version
“He is the first of the works of God; let him who made him bring near his sword!

"አውራ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "መጀመሪያ"the first" ተብሎ ከላይ ተቀምጧል። የዕብራይስጡ ላይ ደግሞ "ረሺት" רֵאשִׁ֣ית ሲሆን ይህ "ረሺት" ቃል ለሰማይና ምድር ጅማሬነት አገልግሎት ላይ ውሏል።

B. ሰማይንና ምድር፦
ዘፍጥረት 1፥1 *"በመጀመሪያ" בְּרֵאשִׁ֖ית እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ"*።

"በ" ב ማለት "በ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው። "ረሺት" רֵאשִׁ֣ית ደግሞ "መጀመሪያ" ማለት ነው።

C. ኢየሱስ፦
እዚህ አንቀጽ ላይ ደግሞ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ነው ይለናል፦
ራእይ 3፥14 አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ *”የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ”* የነበረው እንዲህ ይላል፦ the beginning of the creation of God. (English Revised Version)
ግሪኩ፦ ἡ ἀρχὴ τῆς κτίσεως τοῦ θεοῦ:

“የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “መጀመሪያ” ለሚለው የገባው ቃል ልክ እንደ የሙታን መጀመሪያ “አርኬ” ἀρχή መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፦
1 ቆሮንቶስ 15፥20 አሁን ግን *”ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል”*።
ግሪክ፦ Νυνὶ δὲ Χριστὸς ἐγήγερται ἐκ νεκρῶν, ἀπαρχὴ τῶν κεκοιμημένων.

“በኵር” የሚለው የግሪኩ ቃል “አፕ-አርኬ” ἀπαρχὴ ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “አፓ” ἀπό ማለትም “ከ” እና “አርኬ” ἀρχή ማለትም “መጀመሪያ” ነው፤ ላንቀላፉት ሙታን “መጀመሪያ” ነው ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመርያው ማን ነው? ጉማሬ? ሰማይና ምድር? ወይስ ኢየሱስ?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom