ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የፍጡር ስም ኢየሱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
ኢየሱስ” የሚለው ስም ፦ በግሪክ “ኤሱስ” Ἰησοῦ በቀዳማይ እብራይስጥ “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁעַ ፣ በደሃራይ እብራይስጥ “ያሱአ” יֵשׁוּעַ ፣ በአረማይክ “ዔሳዩ” ܝܫܘܥ በቀዳማይ አረቢኛ “ዒሳ” عيسى በደሃራይ አረቢኛ “የሱዐ” يسوع ሲሆን ትርጉሙ “ያህ መድሃኒት ነው” የሚል ፍቺ አለው፤ በተለይ ኢየሱስ ሰዎች ሲጠሩበት የነበረ የሰው ስም መሆኑን ለማሳየት በዕብራይስጥ “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁ֣עַ በግሪክ “ኤሱስ” Ἰησοῦ ተብሎ ለሌሎች ሰዎች አገልግልግሎት ላይ ውሏል፤ ይህንን ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
“ብሉይ ኪዳን”
የግሪክ ሰፕቱጀንት ብሉይ ኪዳን ኢየሱስ የሚለውን ስም “ኤሱስ” Ἰησοῦ ብሎ አቀምጦታል፤ የዕብራይስጡ እደ-ክታባት ደግሞ ያህሹአ יְהוֹשֻׁ֣עַ በሚል አስቀምጦታል፤ የግዕዙ ባይብልም በተመሳሳይ “ኢያሱ” ሳይሆን “ኢየሱስ” እያለ አስቀምጦታል፤ ኢየሱስ የሚለው ስም የፍጡራን ስም መሆኑን የተለያየ ናሙና ማየት ይቻላል፦

1. “የነዌ ልጅ ኢየሱስ
የነዌ ልጅ ኢየሱስን በሙሴ ዘመን ይኖር የነበረ ፍጡር ሰው ነው፤ በአማርኛችን ላይ “ኢያሱ” ብለው ቢሉትም በዕብራይስጡ ግን “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁ֣עַ በግዕዙ “ኢየሱስ” ተብሎ ተቀምጧል፦
ዕብራይስጥ፦
וַיַּעַן יְהוֹשֻׁעַ בִּן-נוּן, מְשָׁרֵת מֹשֶׁה מִבְּחֻרָיו–וַיֹּאמַר: אֲדֹנִי מֹשֶׁה, כְּלָאֵם.
የግዕዝ ቨርዢን፦
ዘኍልቍ 11፥28 ወይቤሎ #ኢየሱስ ዘነዌ ዘይቀውም ቅድሜሁ ለሙሴ ዘውእቱ ኅሩዩ ይቤሎ #እግዚእየ ሙሴ ክልኦሙ ።
ትርጉም፦
“ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ #ኢየሱስ#፦ #ጌታዬ ሙሴ ሆይ፥ ከልክላቸው አለው።”

2. “የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢየሱስ
የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢየሱስ በሐጌ ዘመን ይኖር የነበረ ፍጡር ሰው ነው፤ በአማርኛችን ላይ ኢያሱ ብለው ቢሉትም በዕብራይስጡ ግን “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁ֣עַ በግዕዙ ኢየሱስ ተብሎ ተቀምጧል፦
ሐጌ 1:1 በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል… ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ “ኢያሱ”*ያህሹአ* יְהוֹשֻׁ֣עַ እንዲህ ሲል መጣ።
አንዱ አምላክ አይሞትም

2 ቆሮንቶስ 5 ፥14 ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤

""አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"" ይላል፤ አንዱ ምን? አንዱ አምላክ? በፍፁም አንዱ አምላክ እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፦
" #እርሱ #ብቻ #የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:16)
" #ብቻውን #አምላክ ለሚሆን #ለማይሞተው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:17)
"17 Now unto the King eternal, #immortal, invisible, the only wise God, [be] honour and glory for ever and ever. Amen."
(1Timothy 1:17)
1 ቆሮንቶስ 8፥4 #ከአንዱም #በቀር #ማንም #አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

አንዱ ምን ታዲያ? በአንዱ አምላክና በሰዎች መካከል ያለ አንዱ ሰው፦
" #አንድ #አምላክ አለና፥ በአምላክና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5)
"5 For [there is] #one #God, and one mediator between God and men, #the #man Christ Jesus;"
(1Timothy 2:5)
" ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና #በአንድ #ሰው #በኢየሱስ #ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 5:15)

አብ አንድ አምላክ ሲሆን የማይሞት ነው። ኢየሱስ አንዱ ሰው ስለ ሁሉ ሞተ። እንደ ጳውሎስ ትምህርት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom