መኀደረ ጤና
2.41K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የደም #ግፊት #በሽታ #መነሻ#ምልክትና #መከላከያዎች

የደም ግፊት በሽታ የተለመደ ችግር ሲሆን የደማችን ጉልበት/ሀይል ከአርተሪ (የደም ቧንቧ) ግድግዳ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ ሲሆን የሚከሰት ህመም ነው ይህም እንደ ልብ ህመም አይነት የጤና ችግር ያስከትላል። የደም ግፊት ልባችን በምትረጨው የደም መጠን እና ደም በአርተሪዎቻችን ውስጥ ሲያልፍ የመቋቋም ኃይል ይወሰናል። ብዙ ደም ልባችን በረጨች መጠን አርተሪያችን (ደም መልስ) ይጠባል ከዚያም የደም ግፊታት መጠናችን ይጨምራል ማለት ነው። ምንም አይነት ምላክት ሳይኖረው ለአመታት የደም ግፊት መጠናችን ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ይህም የደም ቧንቧዎቻችንን ይጐዳቸዋል።
ያልተቆጣጠርነው ከፍተኛ የደም ግፊት ለከባድ የጤና ችግር የመጋለጥ እድላችንን ይጨምራል ለዚህም የልብ ድካምና የደም መርጋት ተጠቃሾች ናቸው። የደም ግፊት ከብዙ አመታቶች በፊት የነበረ በሽታ ሲሆን በማንኛውም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ያጠቃል። ከፍተኛ የደም ግፊት በቀላሉ የሚታወቅ በሽታ ሲሆን በሽታው እናዳለብን ካወቅን ሀኪምዎን በማማከር በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል።
የደም ግፊት በሽታ መነሻዎች!
ሁለት አይነት የደም ግፊት በሽታዎች አሉ፦
#1. የመጀመሪያ የደም ግፊት
አብዛኞቻችን አዋቂዎች የደም ግፊት መነሻ ምክንያት አይታወቅም። የዚህ አይነቱ የደም ግፊት የመጀመሪያ ደረጃ ይባላል የሚከሰተውም ቀስ በቀስ ከረጂም አመታት ቆይታ በኃላ ነው።
#2. ሁለተኛ የደም ግፊት
አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ የደም ግፊት ከተች በተጠቀሱት ምክንያቶች ያጋጥማቸዋል። ይህ አይነቱ የደም ግፊት ሁለተኛ ደረጃ የደም ግፊት ይባላል በድንገት የሚከሰት ሲሆን ከመጀመሪያ ደረጃ የደም ግፊት ዓይነት የበለጠ ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ያስከትላል።
የተለያዮ ሁኔታዎች እና መድሃኒቶች ለሁለተኛ ደረጃ የደም ግፊት ያጋልጡናል እነሱም፦
👉የኩላሊት ችግር
👉የአድሬናል ዕጢ እብጠት
👉የታይሮይድ ችግር
👉ጥቃቅን የደም ቧንቧዎች ችግር
👉አንዳንድ መድሃኒቶች
👉በህግ የተከለከሉ መድሃኒቶች (ኮኬይን፣ አምፊታሚን)
👉የአልኮል ሱሰኝነት
👉 የእንቅልፍ ችግር
#የደም #ግፊት #ምልክቶች!
አብዛኛውን ጊዜ የደም ግፊት በሽታ ተጠቂ ሰዎች የደም ግፊት መጠናቸው በአስደንጋጭ ሁኔታ እስከሚጨምር ድረስ ምንም አይነት የበሽታው ምልክት አይታይባቸውም። ጥቂት ሰዎች በመጀመሪያ የበሽታው ደረጃ ላይ ከባድ የራስ ምታት፣ የተምታታ ንግግር እና ከወትሮው የተለየ የአፍንጫ መድማት ያጋጥማቸዋል። እነዚህ ምልክቶች የደም ግፊት መጠናቸው ለህይወታቸው አስጊ እስከሚሆን ድረስ ላይታዮ/ላይከሰቱ ይችላሉ። የደም ግፊት መጠንዎን መለካት እንደማንኛውም የህክምና ቀጠሮ ልንወስደው ይገባል።
ከ18 ዓመታችን ጀምሮ ቢያንስ በ2 ዓመት አንድ ጊዜ እንድንለካ ይመከራል። የደም ግፊትዎን ሲለኩ በሁለቱም ክንድዎ መለካት አለብዎት የደም ግፊት በሽታ ካለብዎት ወይም የልብ ችግር ካለብዎት በተደጋጋሚ መለካት ተገቢ ነው። በተወሰነ የጊዜ ልዮነት የጤና ምርመራ የማያደርጉ ከሆነ በፋርማሲና በተለያዮ ቦታዎች በሚገኙ የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያዎች እንዲለኩ ይመከራል።
የደም ግፊት መከላከያ መንገዶች!
#ጤናማ #የሰውነት #ክብደት
ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከ2-6 እጥፍ በደም ግፊት የመያዝ እድላችንን ይጨምራል።
※ በየጊዜው እንቅስቃሴ መስራት
የሰውነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ከ 20―50% ከማያደርጉት ሰዎች የመያዝ ዕደላቸውን ይቀንሳል። እንቅስቃሴ ሲባል ማራቶን መሮጥ አይጠበቅብንም በየቀኑ የሚደረግ ትንሽ እንቅስቃሴ በቂ ነው።
※ የጨው አጠቃቀማችንን መቀነስ
የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ጨው መጠቀማቸውን ሲያቆሙ የደም ግፊት መጠናቸው ይቀንሳል። ጨው መጠቀም ም ማቆም የደም ግፊት መጠናችን እንደይጨምር ያደርጋል።
※ አልኮል መጠጦችን አለመጠጣት/መቀነስ
ብዛት ያለው አልኮል መጠጣት የደም ግፊታችን እንዲጨምር ያደርጋል። የደም ግፊታችንን ለመቀነስ የሚወስድትን የአልኮል መጠን ገደብ ማስቀመጥ ተገቢ ነው።
※ ጭንቀትን መቀነስ
ጭንቀት የደም ግፊት መጠናችንን እንዲጨምር ያደርገዋል ከጊዜ ቆይታ በኃላ ለደም ግፊት በሽታ መነሻ አንድ ምክንያት ይሆናል።
ሌሎች የምግብ ይዘቶች የደም ግፊት በሽታን ለመከላከል ይረድናል ከነዚህም መካከል፦
※ ፖታሲየም
በፖታሲየም የበለፀጉ ምግቦች በደም ግፊት በሽታ ከመያዝ ይከላከላሉ። ፖታሲየም ከተለያዮ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ከእንሰሳት ተዋጽኦዎች እና ከአሳ እናገኛለን።
※ ካልሲየም
አነስተኛ የካልሲየም መጠን የሚጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎች በደም ግፊት የመያዝ ዕድላቸው ይጨምራል። ካልሲየም ከወተት፣ እርጐና አይብ እናገኝዋለን።
※ ማግኒዚየም
የማግኒዚየም መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ ምግቦች መመገብ የደም ግፊት መጠናችንን ይጨምራል። የጤና ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ተጨማሪ ማግኒዚየም የደም ግፊትን ለመከላከል/ለመቀነስ መውሰድ አይመከርም ከመደበኛ ምግባችን የምናገኝው በቂ ስለሆነ።
※ የአሳ ዘይት
ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የምናገኝው ከአሳ ሲሆን የደም ግፊትን በመከላከል ይረዳናል።
※ ነጭ ሽንኩርት
የደም ግፊት መጠንን እና ኮሌስትሮልን በማስተካከል ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል። የካንሰር በሽታን ይከላከላል።
መልካም ጤንነት!!
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ እንዲሀም ለወዳጆ ሼር ያድርጉ
#እርግዝናን #የመከላከያ #መንገዶችና #እውነታቸው

ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከልና ራስዎን ከአባላዘር በሽታዎች ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀሙ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የእነዚህን መከላከያዎች እውነታዎች አውቆና ተረድቶ ጥቅም ላይ ማዋል እጅግ ጠቀሜታ ይኖረዋል
#በወር #አበባ #ጊዜ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ቢደረግ #እርግዝና (ይከሰት #ይሆን ?
👉የወር አበባን በምታይ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የምታደርግ ሴት የማርገዝ ዕድሏ የቀነሰ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አይከሰትም ለማለት አይቻልም፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የወር አበባ ከማለቁ በፊት እንቁላል ሊፈጠር ስለሚችልና ወይንም ደግሞ የወንድ ዘር በማኅፀን ውስጥ እስከ 3 ቀን ወይንም ከዚያ በላይ የሚቆይበት አጋጣሚ ስለሚኖር ነው፡፡
#ጡት #ማጥባት #እርግዝናን #ይከላከላል ?
👉ጡት ማጥባት የእንቁላል መፈጠርን የሚከላከል ቢሆንም የሚቆይበት ጊዜ ግን ለጥቂት ወራት ብቻ ስለሆነ ሰውነት ወደቀድሞ ሁኔታው በሚመለስ ጊዜ የማርገዝ ዕድልም አብሮ ስለሚመለስ ጡት ማጥባት እርግዝናን የሚከላከልብት ጊዜ ውስን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
#የመጀመሪያ #ጊዜ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ማድረግ #ላልተፈለገ #እርግዝና #ያጋልጣል ?
👉አዎን! ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላልተፈለገ እርግዝና ላያጋላጥ ይችላል ብለው የሚያስቡ አንዳንዶች ያሉ ቢሆንም ይህ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ሕመምና ደም መፍሰስ ሊያጋጥም የሚችል ቢሆንም እርግዝናን ከመከላከል ጋር ግን ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቀቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያዎች #ምን #ያህል #እርግዝናን #ይከላከላሉ ?
👉የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በትክክለኛው መንገድ ከተተገበሩ ከ90% በላይ የሚሆን የመከላከያ አቅም ያላቸው ሲሆን ተአቅቦ ግን ጥርጥር የሌለው አማራጭ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጣሪያ ለመጠቀም በሚታሰብ ጊዜ የትኛውን ዓይነት እንደምንመርጥና አጠቃቀሙን በተመለከተ ሐኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡
#በግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ጊዜ #ሁለት #ኮንዶሞች #ደርቦ #መጠቀም #በእርግጥ #እርግዝናን #የበለጠ #ይከላከላል ?
👉አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሁለት ኮንዶምን ደርቦ በመጠቀም የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ያስባሉ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ሲሆን ይባስ ብሎ በሚፈጠረው ፍጭት (Friction) ምክንያት የኮንዶም መቀደድ በማስከተል ላልተፈለገ እርግዝና ለአባላዘር በሽታ የመጋለጥን ዕድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ሁለት ኮንዶሞችን ደርቦ መጠቅም አይመከርም፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያ #እንክብሎችን #መውሰድ #ወዲያውኑ #እርግዝናን #ይከላከላል?
👉የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች አጠቃቀም እና የሚወሰዱበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ እርግዝናን ለመከላከል ጠቃሚ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን የወር አበባ በመጣ ከመጀመሪያው ቀን እስከ አምስተኛው ቀን ውስጥ መጀመር ወዲውኑ ከአልተፈለገ እርግዝና የሚከላከል ሲሆን፣ ከዚያ ጊዜ ውጭ ከመጀመሩ ግን ወዲያውኑ የመከላከል አቅም ስለማይኖረው ኮንዶምን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡
#ሁሉም #የወሊድ #መቆጣጠሪያዎች #ከአባለዘር #በሽታዎች #ይከላከሉ #ይሆን ?
👉ከወሊድ መቆጣጠሪያዎች ውስጥ ኮንዶምን መጠቀም ብቻ ከአባላዘር በሽታ ራስን መከላከል የሚቻልበት ዋነኛው መንገድ ነው፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያ #እንክብሎች #የሰውነት #ክብደት #ይጨምራሉ ?
👉አንዳንድ ሴቶች የሰውነት ክብደት መጨመርን እንዳስከተለባቸው የሚናገሩ ሲሆን ምክንያቱም የምግብ ፍላጎትን መጨመርን ማስከተሉና ፈሳሽ በሰውነታችን እንዲቀመጥ ማድረጉ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠነኛ የሚባል የሰውነት ክብደት መጨመርን ያስከትላሉ፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያን #መጠቀም #መሃንነትን #ያስከትላል?
👉አያስከትልም! ሆርሞኖችን በውስጣቸው የያዙ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ለረጅም ጊዜ ከተወሰዱ መሃንነትን ያስከትላሉ ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም እነዚህን የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መካንነትን እንደማያስከትሉ ሊያውቁት የሚገባ እውነታ ነው፡፡
#ኮንዶምን #በሌሎች #ቁሳቁሶች #መተካት #ይቻላል?
👉በፍፁም አይቻልም! በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን በሌሎች እንደ ላስቲክ፣ ፈኛ፣እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ተክቶ መጠቀም በፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እና ከአልተፈለገ እርግዝናም ሆነ ከአባላዘር በሽታም በጭራሽ እንደማይከላከል ሊያውቁት ይገባል

#መልካም #ጤና
#የሳንባ #ምች (Pneumonia)

የሳንባ ምች የምንለው በሳንባ ላይ ሚከሰትን ኢንፌክሽን ነው፡፡
#የሳንባ #ምች #እንዴት #ይከሰታል?
👉በባክቴሪያ
👉በቫይረስ
በሽታን የመከላከል አቅማቸው የደከመ ሰዎች ላይ ደግሞ #በፈንገስ ምክንያትም ይከሰታል
አንድ ሰው አየር በሚያስገባ ጊዜ እነዚህን በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ወደ ውስጥ ያስገባል ይህም ወደ ሳንባ በመሄድ ኢንፌክሽን ይፈጥራል
#ለሣንባ #ምች #ተጋላጭነት #የሚዳርጉ #ሁኔታዎች
👉ዕድሜ፦ዕድሜያቸው ከ1 ዓመት በታች የሆኑ እና ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ሰዎች
👉በሽታን የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች
👉በጉንፋን የተጠቁ ሰዎች
👉የአስም ሕመም ተጠቂ የሆኑ ሰዎች
👉ሲጋራን ማጤስ
👉የአልኮል መጠጥን እጅግ ማዘውተር
#የሳንባ #ምች #ሕመም #ምልክቶች
👉አክታ የተቀላቀለ ሳል
👉ትኩሳት
👉ትንፋሽ ማጠር
👉የራስ ምታት
👉ብርድ ብርድ ማለት
👉የደረት ውጋት በሳል ጊዜ የሚብስ የልብ ትርታ መጨመር
👉ላብ ላብ ማለት
👉የሰውነት ድካም
👉የምግብ ፍላጎት መቀነስ
👉ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

#የሳንባ #ምችን #እንዴት #መከላከል #ይቻላል?
👉ሲጋራ ማጤስን ማቆም
👉እጅን በሚገባ መታጠብ
የሳንባ ምችን ሕመምተኞች በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችላቸው ሕክምናዎች፤
👉ፈሳሽ በብዛት መውሰድ
👉ዕረፍት ማድርግ
ትኩሳትን ማስታገሻ በመውሰድ መቆጣጠር
በቫይረስ የሚከሰት የሳንባ ምች በአብዛኛውን ጊዜ በጉንፋን ምልክቶች የሚጀምር ሲሆን #ትኩሳት #ደረቅ ሳል #ራስ ምታት#ቁርጥማት እና #የድካም #ስሜትን ያስከትላል ትንፋሽ ማጠር እና አክታ ከአንድ ቀን በኋላ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
በባክቴሪያ የሚከሰት የሳንባ ምች ከፍተኛ #ትኩሳት #አክታን #የቀላቀለ #ሳል ከፍተኛ #የሰውነት #ማላብ #የልብ ምት መጨመር እና በፍጥነት የሚጨምር የአተነፋፈስ ስርዓት ይኖራቸዋል፡፡
የሣንባ ምች ሕክምና ህመሙን እንዳስከተለው ተህዋስያን ዓይነት፤ እንደ ሕመሙ ክብደት እና ተጨማሪ ሕመም መኖር ሁኔታ ይለያያል፡፡
በሕመሙ የተጠቁ ሰዎች ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ሐኪምን በማማከር ሕክምናውን በመውሰድና በሚገባ በመከታተል ከበሽታው መዳን ይቻላል

#መልካም #ጤና
#ፕሮጄሪያ (Progeria)

በሌላ ስሙ (HGPS) በመባል የሚታወቀው የአንድን ልጅ ሰውነት በፍጥነት እንዲያረጅ የሚያደርገው የዘር ውርስ ነው አብዛኛዎቹ ይሄ በሽታ ያለባቸው ህፃናት ከ 13 ዓመት በላይ በህይወት መቆየት አይችሉም በሽታው ሁለቱም ፆታዎች እና ሁሉንም ዘር እኩል ያጠቃል በዓለም ዙሪያ ከ4 ሚልዮን ሕፃናት ውስጥ አንድ ሰው በዚህ በሽታ ይጠቃል

በሰዉ አፈጣጠር ወቅት በአንድ ትክክለኛ ሴል ውስጥ አንድ ስህተት ያልተለመደ ፕሮቲን እንዲፈጥር ያደርገዋል ሴሎቹም Progerin ተብሎ የሚጠራውን ይህን ፕሮቲን ሲጠቀሙ, በቀላሉ ይበሰብሳሉ. የፕሮጀርያ ሕጻናት በሚኖሩባቸው በርካታ ሴሎች ውስጥ progerin ከእድሚያቸዉ ፈጥነዉ በአስቸኳይ እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል

#ምልክቶቹ
አብዛኞቹ ልጆች በሚወለዱበት ወቅት ጤናማ ይመስላሉ ነገር ግን በመጀመሪያ ዓመታቸዉ ውስጥ የበሽታ ምልክት ማሳየት ይጀምራሉ. Progeria ያለባቸው ሕፃናት እድገታቸዉ በጣም ዉስን ነው እንዲሁም ክብደት አይጨምሩም

#የአካል #አቀማመጣቸውም #የሚከተሉትን #ይመስላል
👉ትልቅ ጭንቅላት
👉ትልልቅ ዓይኖች
👉ትንሽ ዝቅተኛ አገጭ
👉ከጫፉ ቀጠን ያለ ቀጭን አፍንጫ
👉ትላልቅ ጆሮዎች
👉የሰዉነታቸው ደም ስሮች በግልፅ ይታያሉ
👉ያልተለመደ የጥርስ አበቃቀል
👉በሚናገሩበት ወቅት ቀጭንና ከፍተኛ ድምፅ ያወጣሉ
👉ሰውነትታቸዉ የቅባት እና የጡንቻ ማጣት ይኖራቸዋል
👉የፀጉር መርገፍ, የዐይን ሽፈሽፍት እና ቅንድብን ጨምሮ
ከ progeria ጋር የሚኖሩ ህፃናት ቶሎ ነው የሚያረጁት ከ 50 አመት በላይ ሊይዙን ይችላሉ በሚባሉ በሽታዎች ይያዛሉ እንደ #የአጥንት መሳሳት #የደም ስሮች በሽታ #የልብ በሽታ
#የኩላሊት በሽታን ጨምሮ በተለያዩ በሽታዎች ይጠቃሉ የ Progeria ህመም ያለባቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ በልብ ድካም ወይም በኩላሊት በሽታ ይሞታሉ
በዚህ በሽታ የተጠቁ ልጆችን የማሰብ ችሎታ ወይም የአእምሮ እድገታቸዉ አይጎዳም ችግሩ ያለበት ልጅ ከሌሎች ልጆች ይልቅ በቸለያዩ በሽታዎች የመያዝ ዕድሉ ከፍተኛ ነው.

#Progeria #ምርመራ

የበሽታው ምልክቶቹ በደንብ የሚታዩ ስለሆነ በተለመደው የክትትል ወቅት የልጅዎ የህፃናት ሐኪም ሊያያቸው ይችላል.

በ Progeria ህመም የተያዙ የሚመስሉ ልጆችን የተለያዩ ለውጦችን ከተመለከቱ ከርስዎ ከሀፃናት ሀኪም ጋር መነጋገር የተለያዩ አካላዊ ምርመራ ይደረግላቸዋል, የእይታ ብቃታቸዉ የልብ ምታቸውንና የደም ግፊትን ይለኩእና የልጅዎን ቁመት እና ክብደት እኩዮቹ ተመሳሳይ ዕድሜ ጋር ያወዳድራሉ ከዚያ በኋላ የሕፃናት ሐኪምዎ አሳሳቢ ከሆነ በደም ምርመራ አማካኝነት የምርመራውን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ የሕክምና ባለሙያዎችን ሊያናግር ይችላል.

#ሕክምናዎች

አሁን ባለንበት ግዜ ለ Progeria በሽታ መድኃኒት አልተገኘለትም, ነገር ግን ተመራማሪዎች አንዱን
ለየካንሰር ህመም መድሐኒት የሆነውን በመጠቀምFTI (farnesyltransferase inhibitors), የተጎዱ ሕዋሶችን ሊያስተካክሉ ይችላሉ. #መድሃኒቶች ብዙውን ጊዜ የበሽታውን ምልክቶች ሊያዘገዩ ይችላሉ.
#መድሃኒት የልጅዎ ሀኪም መድሃኒቶች ሊያዝዙ ይችላሉ ዝቅተኛ የኮሌስትሮል መጠን እንዲኖር ወይም የደም መፍሰስን ለመከላከል አነስተኛ መጠን ያለዉ በየቀኑ
#አስፕሪን የልብ ሕመምን ለመከላከል ይረዳል. #የእድገት ሆርሞኖች ይሰጣሉ ቁመት እና ክብደት ለመገንባት ይረዳሉ
#የሰውነት እንቅስቃሴ (ቴራፒ) ህመም ለልጅዎ ጠንካራና የማይተጣጠፍ መገጣጠምያ እንዳይኖረዉ ይረዳዋል
#ቀዶ #ጥገና የአንዳንድ ልጆችን የልብ ሕመምን ለማዘግየት ለመቀነስ የልብ ቀዶ ጥገና ይደረግላቸዋል
#በቤት #ውስጥ #የምናደርግላቸዉ በProgeria በሽታ የተያዙ ልጆች የሰዉነታቸዉ የዉሀ መጠን በጣም ስለሚቀንስ ስለሆነም ብዙ #ውሃ #መጠጣት አለባቸው.
#ምግቦችን በሰአቱ እንዲበሉ ማበረታታት
ልጅዎ ንቁ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ማበረታታት

#መልካም #ጤና
#የጀርባ_ሕመምዎን_ለማስታገስ_የሚረዱ #ጠቃሚ_ምክሮች

👉 #አቋምዎን_ያስተካክሉ

የጀርባ ሕመም የሚያሰቃይዎት ከሆነ በመጀመሪያ አቀማመጥዎን እና ከባድ ዕቃን የሚይዙበትን ሁኔታ ያስተካክሉ፡፡ ለብዙ ሰዓት ተቀምጠው የሚሠሩ ከሆነ ለወገብዎ መደገፊያ ማዘጋጀት ይኖርብዎታል፡፡ ከመቀመጫዎ ሲነሱ ቀጥ ብለው መነሳት እና ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በሚያነሱበት ጊዜ ከጉልበትዎ በርከክ ብለው ጀርባዎን ቀጥ በማድረግ መሆን አለበት፡፡
የኤሎክትሮኒክስ ዕቃዎችን የሚጠቀሙበትን ሰዓት ይቀንሱ
በሥራም ሆነ በማኅበራዊ ጉዳይ ምክንያት ለረጅም ሰዓታት ከኮምፒዩተሮችና ሌሎች የኤሎክትሮኒክስ ዕቃዎች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ መወሰን ተገቢ ነው፡፡ አጎንብሰን እና ለረጅም ሰዓት ተቀምጠን የምንጠቀምባቸው ከሆነ የጀርባ ሕመም እና የራስ ምታትን ያስከትላሉ፡፡

👉 #መደበኛ_የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴን #ያድርጉ

የጀርባ ሕመምን ቀላል በሚባል የአካል ማፍታታት እና አንገትን እና ወገብን በማንቀሳቀስ መከላከል ይችላሉ፡፡

👉 #ጭንቀትን_ይቀንሱ

ጭንቀት ለብዙ ዓይነት ሕመሞች እንደ ምክንያት የሚጠቀስ ሲሆን ከጀርባ ሕመም ጋርም ተያያዥነት እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም ለራስዎ ጊዜ በመስጠት እና በመዝናናት ጭንቀትዎን ይቀንሱ፡፡

👉 #የሰውነት_ክብደትዎን_ይቀንሱ

የሰውነትዎ ክብደት መጨመር በተለይም በወገብ አካባቢ ስብ ከተከማቸ የጀርባ ጡንቻዎችን ስለሚጎዳ የጀርባ ሕመም ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ አመጋገብዎን ማስተካከል እና ክብደትዎን መቀነስ የጀርባ ሕመምዎን ይቀንሳል፡፡

👉 #በቂ_ዕረፍት_ያድርጉ

በቂ እረፍት ማድረግ ለሙሉ ጤናማነት ጠቃሚ ነው፡፡ እንቅልፍ በሚተኙ ጊዜ በጎንዎ በኩል መተኛት የጀርባ ሕመምዎን ይቀንሳል፡፡

👉 #በቂ_የፀሐይ_ብርሃን_ያግኙ

የፀሐይ ብርሃን ቢያንስ በቀን ለ10 ደቂቃ መውሰድ ለአጥንትዎ ጠንካራነት እጅግ ጠቃሚ እና ለጀርባ ሕመምዎ አንደኛው መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡

👉 #ሲጋራ_ማጤስን_ያቁሙ

ሲጋራ ማጤስ ወደ ታችኛው የጀርባችን አጥንቶች የሚሄደውን የደም ዝውውር ስለሚቀንስ ለጀርባ ሕመም ይዳርጋል፡፡ ስለዚህም ሲጋራ ማጤስዎን እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡

#መልካም_ጤና