መኀደረ ጤና
2.39K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#እርግዝናን #የመከላከያ #መንገዶችና #እውነታቸው

ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከልና ራስዎን ከአባላዘር በሽታዎች ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀሙ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የእነዚህን መከላከያዎች እውነታዎች አውቆና ተረድቶ ጥቅም ላይ ማዋል እጅግ ጠቀሜታ ይኖረዋል
#በወር #አበባ #ጊዜ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ቢደረግ #እርግዝና (ይከሰት #ይሆን ?
👉የወር አበባን በምታይ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የምታደርግ ሴት የማርገዝ ዕድሏ የቀነሰ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አይከሰትም ለማለት አይቻልም፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የወር አበባ ከማለቁ በፊት እንቁላል ሊፈጠር ስለሚችልና ወይንም ደግሞ የወንድ ዘር በማኅፀን ውስጥ እስከ 3 ቀን ወይንም ከዚያ በላይ የሚቆይበት አጋጣሚ ስለሚኖር ነው፡፡
#ጡት #ማጥባት #እርግዝናን #ይከላከላል ?
👉ጡት ማጥባት የእንቁላል መፈጠርን የሚከላከል ቢሆንም የሚቆይበት ጊዜ ግን ለጥቂት ወራት ብቻ ስለሆነ ሰውነት ወደቀድሞ ሁኔታው በሚመለስ ጊዜ የማርገዝ ዕድልም አብሮ ስለሚመለስ ጡት ማጥባት እርግዝናን የሚከላከልብት ጊዜ ውስን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
#የመጀመሪያ #ጊዜ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ማድረግ #ላልተፈለገ #እርግዝና #ያጋልጣል ?
👉አዎን! ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላልተፈለገ እርግዝና ላያጋላጥ ይችላል ብለው የሚያስቡ አንዳንዶች ያሉ ቢሆንም ይህ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ሕመምና ደም መፍሰስ ሊያጋጥም የሚችል ቢሆንም እርግዝናን ከመከላከል ጋር ግን ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቀቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያዎች #ምን #ያህል #እርግዝናን #ይከላከላሉ ?
👉የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በትክክለኛው መንገድ ከተተገበሩ ከ90% በላይ የሚሆን የመከላከያ አቅም ያላቸው ሲሆን ተአቅቦ ግን ጥርጥር የሌለው አማራጭ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጣሪያ ለመጠቀም በሚታሰብ ጊዜ የትኛውን ዓይነት እንደምንመርጥና አጠቃቀሙን በተመለከተ ሐኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡
#በግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ጊዜ #ሁለት #ኮንዶሞች #ደርቦ #መጠቀም #በእርግጥ #እርግዝናን #የበለጠ #ይከላከላል ?
👉አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሁለት ኮንዶምን ደርቦ በመጠቀም የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ያስባሉ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ሲሆን ይባስ ብሎ በሚፈጠረው ፍጭት (Friction) ምክንያት የኮንዶም መቀደድ በማስከተል ላልተፈለገ እርግዝና ለአባላዘር በሽታ የመጋለጥን ዕድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ሁለት ኮንዶሞችን ደርቦ መጠቅም አይመከርም፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያ #እንክብሎችን #መውሰድ #ወዲያውኑ #እርግዝናን #ይከላከላል?
👉የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች አጠቃቀም እና የሚወሰዱበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ እርግዝናን ለመከላከል ጠቃሚ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን የወር አበባ በመጣ ከመጀመሪያው ቀን እስከ አምስተኛው ቀን ውስጥ መጀመር ወዲውኑ ከአልተፈለገ እርግዝና የሚከላከል ሲሆን፣ ከዚያ ጊዜ ውጭ ከመጀመሩ ግን ወዲያውኑ የመከላከል አቅም ስለማይኖረው ኮንዶምን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡
#ሁሉም #የወሊድ #መቆጣጠሪያዎች #ከአባለዘር #በሽታዎች #ይከላከሉ #ይሆን ?
👉ከወሊድ መቆጣጠሪያዎች ውስጥ ኮንዶምን መጠቀም ብቻ ከአባላዘር በሽታ ራስን መከላከል የሚቻልበት ዋነኛው መንገድ ነው፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያ #እንክብሎች #የሰውነት #ክብደት #ይጨምራሉ ?
👉አንዳንድ ሴቶች የሰውነት ክብደት መጨመርን እንዳስከተለባቸው የሚናገሩ ሲሆን ምክንያቱም የምግብ ፍላጎትን መጨመርን ማስከተሉና ፈሳሽ በሰውነታችን እንዲቀመጥ ማድረጉ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠነኛ የሚባል የሰውነት ክብደት መጨመርን ያስከትላሉ፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያን #መጠቀም #መሃንነትን #ያስከትላል?
👉አያስከትልም! ሆርሞኖችን በውስጣቸው የያዙ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ለረጅም ጊዜ ከተወሰዱ መሃንነትን ያስከትላሉ ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም እነዚህን የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መካንነትን እንደማያስከትሉ ሊያውቁት የሚገባ እውነታ ነው፡፡
#ኮንዶምን #በሌሎች #ቁሳቁሶች #መተካት #ይቻላል?
👉በፍፁም አይቻልም! በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን በሌሎች እንደ ላስቲክ፣ ፈኛ፣እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ተክቶ መጠቀም በፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እና ከአልተፈለገ እርግዝናም ሆነ ከአባላዘር በሽታም በጭራሽ እንደማይከላከል ሊያውቁት ይገባል

#መልካም #ጤና
​​#ሁሉም_ከማህፀን_የሚወጣ_ፈሳሽ #በሽታ_ነው ?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#ከሴት የመራቢያ አካል የሚወጣው ተፈጥሮአዊ ፈሳሽ ከሰውነት ሆርሞን ጋር በተገናኘ ከፍና ዝቅ በማለት በሚሮሩ ለውጦች የሚመጣ ሲሆን በእርግጥ ከሰው ሰው ቢለያይም በአብዛኛው ጊዜ ከ2-5 ml (ከ 2-5 ሚሊ ሊትር) ወይም ከግማሽ እስከ ሙሉ የሻይ ማንኪያ መጠን ሊፈስና ነጭ ወይም ቀለም የሌለው ውሃ መሳይ፤ ወፈር ያለ ንፍጥነት ያለው እና ሽታ የሌለው ነው፡፡
መጠኑ በተለያየ የወር አበባ ኡደት ወቅት ሊለያይ ቢችልም የሚበዛው፦ በእርግዝና ወቅት፤ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት በሚጠቀሙ ጊዜያት፤ ኦቩሌሽን (Ovulation) እንዲሁም የወር አበባ ለመምጣት ባለው 7 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡ የተፈጥረ የማህጸን ፈሳሽ የሽንት ቱቦ እና የማህጸን ኢንፌክሽን ለመከላከል እንዲሁም የመራቢያ አካል መድረቅን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡

👉 #በበሽታው_በምንጠቃ_ጊዜ #የሚያሳዩት_ምልክቶች_ምንድ_ናቸው?

📌 በመራቢያ አካላት አካባቢ ማሳከክ፣ መቅላት፣ ማቃጠል፣ የህመም ስሜት እንዲሁም እብጠት መኖር።
📌 አረፋ ያለው በቀለሙም ቢጫ፣ አረንጓዴ የሚመስል ፈሳሽ መኖር።
📌 ሽታ ያለው ፈሳሽ።
📌 በወር አበባ እንዲሁም በግንኙነት ጊዜ ሽታ መኖር።
📌 ከማህጸን ፈሳሽ ጋር ደም መቀላቀል።
📌 በግንኙነት ጊዜ ህመም መኖር።
📌 የሆድ፤ የማህጸን አካባቢ እንዲሁም የታችኛው ወገብ። ህመም መኖር እንደ ዋና ዋና ምልክቶች ይካተታሉ።

👉 #ለዚህም_በሽታ_ከሚያጋልጡ #ምክንያቶች_መካከል

📌 እድሜ ፡ እድሜ እየጨመረ እና የወር- አበባ መምጣት ሲያቆም የማህጸን ፈሳሽ ሊዛባ፣ ድርቀት እና ማሳከክ ሊኖረ ይችላል፡፡
📌 በወር አባባ ወቅት ለንጽህና መጠበቂያ የሚጠቀሙበትን አቆይቶ መቀየር ማቃጠል፣ ማሳከክ እንዲሁም ማበጥ ከማስከተሉም በተጨማሪ ለኢንፌክሽን መራቢያ ጥሩ መንግድ ይከፍታል።
📌 ሽታ ያለው ሳሙና እና አለርጂ ወይም የማይስማማዎትን ሳሙና መጠቀም ተመሳሳይ ምልክት ያመጣሉ።
📌 ጠባብ እና ላይነን የሆኑ ፓንቶችን መጠቀም ።
📌 ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት እና ከአንድ በላይ የግብረስጋ ግንኙነት ጓደኛ መኖር ይጠቀሱበታል፡፡

👉 #ይህን_በሽታ_ለመከላከል_ምን
#ማድረግ_አለብን?

📌 ሞቅ ባለ ውሀ በየቀኑ መታጠብ።
📌 ሽታ ያላቸውን ሳሙናዎቸ፤ ዋይፐር ወይም ማድረቂያ ሶፍቶችን አለመጠቀም።
📌 የማያጣብቅ እና ጥጥነት ያላቸውን የውስጥ ልብሶች መጠቀም።
📌 ሽንት ቤት ከተጠቀሙ በሆላ በውሀ መታጠብ እና በደረቅ ፎጣ ማድረቅ።

👉 👉 #ከዚህም በተጨማሪ እኚህን ምልክቶች የሚያመጡት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው የሆነው በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ መገለጫ ሰለሆነ ይሄም በሽታ እየባሰ ሲሄድ የማህጸን ኢንፌክሽን ብሎም ማህንነትን ስለሚያመጣ ወደ ሀኪምዎ ሄደው ላለብዎት በሽታ ተገቢውን ምክር ያግኙ።


#መልካም_ ጤና