የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
41 subscribers
89 photos
1 video
Download Telegram
#የጎፋ #ዞን #ነዋሪዎች #በ4ኛው #ዙር #ለሀገር #መከላከያ #ሰራዊታችን #ከ37 #ሚልዮን 981 #ሺህ #ብር #በላይ #በዓይነትና #በገንዘብ #ድጋፍ #ማድረጋቸው #ተገለፀ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ህዳር 03/2014 ዓ.ም ሣውላ:- በጎፋ ዞን አስተዳደር ለጀግናው የሀገር መከታና አሌንታ ለሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በየመዋቅሩ ያሉትን የዞኑን ነዋሪዎች በማስተባበር 37,981,276.75 ብር (ሰላሳ ሰባት ሚልዮን ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰባስ ድስት ብር ከሰባ አምስት ሳንቲም) የፋይናንስ አሰራር መመሪያና ደንብ መሠረት ባደረገ መልኩ መሰብሰቡን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና የሀብት አሰባሳቢ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው አስታወቁ።

በመጀመሪያው፣ በሁለተኛው እና በሦስተኛው ዙር በጎፋ ዞን አስተዳደር ነዋሪዎች 434 ሰንጋዎችን ጨምሮ ከ51 ሚልዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የተለያዩ ድጋፎችን በአይነትና በገንዘብ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ መደረጉን ያስታወሱት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በአተኛው ዙርም ደግሞ 317 ሰጋዋችን፣ 46 በጎችን፣ 32 ፍየሎችን ጨምሮ ከሦስት ቀን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ከወትሮው በተሻለ በነዋሪዎች ከፍተኛ ተሳትፎ፣ ተነሳሽነት እና የሀገር ፍቅር ወኔ ከ37 ሚልዮን 981 ሺህ ብር በላይ በዓይነትና በገንዘብ ለጀግና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ መደረጉን ዶ/ር ጌትነት በጋሻው አክለው ገልፀዋል።

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለፆ በአሁኑ በአራተኛው ዙር በጥሬ ገንዘብ ከተሰበሰበው በተጨማሪ በዓይነት:-
👉 በሬ በቁጥር 317
👉 በግ በቁጥር 46
👉 ፍዬል በቁጥር 32
👉 በሶ 34 ኩ/ል፣
👉 ኩኪስ 3.5 ኩ/ል፣
👉ጤፍ 3 ኩ/ል፣
👉ለውዝ 3 ኩ/ል በድምሩ 47.5ኩ/ል
👉 ወደ ግንባር ለመዝመት የተመዘገቡ የአመራሮች ብዛት 18 መሆናቸውን የሀብት አሰባሳቢ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው አሳውቀዋል።

ዘገባው:- የጎፋ ዞን #መንግስት #ኮሚኒኬሽን #ጉዳዮች #መምሪያ #ነው

ህዳር 03/2014 ዓ.ም
#ሣውላ
👉በአስቸኳይ አዋጁ እዝ የመከነው አሸባሪው ሕወሐት ለአዲስ አበባ ደግሶት የነበረው ታላቅ እልቂትና ውድመት‼️ ሼር..ሼር.. ሼር.ይደረግ‼️

♦️ጁንታው በነዋሪነት ስም አዲስ አበባ የነበረውን በብዙ ሺህ የሚቆጠር አባልና ተባባሪውን በሙሉ ለጥፋት አላማው በሚስጥር በወታደራዊ አወቃቀር አደራጅቶት ነበር‼️

♦️በአዲስ አበባ ከውስጥ ሆነው ድንገተኛ ውጊያ ለመክፈት ተዘጋጅተው የነበሩት የሕወሐት አባላት ደጋፊዎችና ተባባሪዎች ነበሩ ‼️

🔴ተከፋይ የአሜሪካ ሚዲያዎች በአዲስ አበባ ተከባለች መዝሙራቸው አፍረዋል። ደንግጠዋል። አዲስ አበባ መግባት ሳይሆን ወደ ሲኦል ወርደዋል። ህወኃት እነሱ እንደጠበቁት እንኳን አዲስ አበባን ሊቆጣጠር ቀርቶ ከአጋፋሪው ሸኔ ጋር አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ወደ መቃብሩ እየወረደ ነው። አይደለም አዲስ አበባ መግባት መቀሌም መመለስ አይችሉም። በየቦታው እንደ ቅጠል እየረገፋ ቀርተዋል። በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችንና በሕዝባዊ ኃይሎቻችን ክንድ በየገባበት ቦታ እየታደነ እየተለቀመ ከአፈር እየተቀላቀለ ነው‼️

🔴ጁንታው አዲስ አበባ እገባለሁ ብሎ ጡሩንባ ሲነፋ የነበረው ምስጢሩ ምንድነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ከፕሮፓጋንዳው በዘለለ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘውን የሚኖረውን ቁጥሩ ከ500 ሺህ በላይ የሚሆነውን የትግራይ ተወላጅ የሚቃወሙት እንዳሉ ሆነው አብዛኛውን ተወላጅ ወጣት ሴት፣ ወንድ፣ ጎልማሳ፣ ሽማግሌ፣ አሮጊት፣ የመንግስትና የግል ሠራተኛ በሙሉ የ"ሀገረ ትግራይ ምስረታን" እንዲቀበሉ አድርጎ በየቀበሌው፣ በወረዳ፣ ዞንና ክልል በወታደራዊ መዋቅር ደረጃ አደራጅቶ፣ እዝና አመራር ፣የግዳጅ ቀጠና ጭምር ሰጥቶ ጨርሶ እንደነበር የተገኙት መረጃዎች የደሴውን የውስጥ አርበኞች ሴራ በማሳያነት በመግለጽ ይጠቁማሉ።

🔴ይህ አደረጃጀት በመላ ሀገሪቱ ባሉ አነስተኛ፣ መካከለኛ ፣ከፍተኛ ከተሞች በጥብቅ ምስጢርነት የተዘረጋ ሲሆን እያንዳንዱ የሕወሐት አባልና ደጋፊ ተባባሪ የመሰለል መረጃ የማቀበል የሕወሐትን ፕሮፓጋንዳ የማሰራጨት ፣ ሕዝቡ ውስጥ ጭንቀት ግራ መጋባትና ፍርሀት እንዲሰፍን የመስራት ግዴታ ያለበት ከመሆኑም በላይ ይሄንኑ የሚሰሩ የተደራጁ ክፍሎችም አሉት ። በገንዘብ የተገዙ የሌላ ብሔረሰብ አባላትም በብዛት ይገኙበታል። መሰሪው ሕወሐት ለዚሁ የክፋት አላማው ሲል በሰላሙ ቀን ከትግራይ አምጥቶ በተለያየ ጊዜ አዲስ አበባ በተለያዮ ክፍለ ከተሞች ያሰፈረውና የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ያደለውን የትግራይ ተወላጅ በሙሉ በሠራዊት ደረጃ አዘጋጅቶ አዋቅሮ ኃላፊዎችን መድቦ ባላቸው መሣሪያ ሁሉ ተጠቅመው በተሰጣቸው ቀጠናና ግዳጅ በድንገት አዲስ አበባን የጦርነት አውድማ እናደርጋታለን ብለው በሰፊው ተዘጋጅተው ጨርሰው ነበር። አዲስ አበባ ውስጥ የተለያዮ መሣሪያዎችን በየግለሰቦቹ ቤትና በየድርጅታቸውም ቀብረዋል። ከተገኘው ከተመዘገበው ያልተገኘው ይበዛል ነው የሚሉት የመረጃው ምንጮች።

🔴 ይሄን ለመጥፊያው ያዘጋጁለትን የጦር መሣሪያ አነፍንፎ ከያለበት አስሶ ከየጋራዡ፣ ከየሆቴሉ፣ ከየንግድ ቤቱ ፤ ከተከራዩትና በስማቸው ከሚገኘው የእቃ ማከማቻ መጋዘን ማውጣትና መያዝ የአዲስ አበባ ነዋሪ ግዴታ ነው። ሳተላይት ስልኮች በፎቆቻቸው ፣ በሆቴሎቻቸው ፣በመኖሪያ ቤታቸው፣ አዲስ አበባን፣ ሱሉልታን፣ ጫንጮን፣ ዱከምን፣ ደብረዘይትን፣ ሞጆን፣ናዝሬትን፣ ሻሸመኔን፣ አርሲን፣አዋሳን፤ ሰንዳፋን፤ለገጣፎን፣ ሆለታንና ሌሎችም ትናንሽና ትላልቅ ከተሞች ውስጥ አልፎም እነሱ ብቻ መጠቀም በሚችሉባቸው ከሰው ለእይታ በራቁ ጫካዎች ውስጥ ሁሉ እንደሚኖራቸው አትጠራጠር። መረጃ የሚለዋወጡበት ትልቁ መሣሪያ እሱው ነው። ፈልገህ አስሰህ አውጣ። የመረጃና ግንኙነት መረባቸውን በጣጥሰው። ሳትቀደም ቅደም። በመሀል ሀገር ሰዎች ቤትም በዝምድና በወዳጅነት በምስጢር አይጠረጠሩም በሚል ያስቀመጡት እንደሚኖር ይታመናል። ይሄ ሁሉ ለአዲስ አበባ ሕዝብ መጨፍጨፊያ የተዘጋጀ መሆኑን አውቀህ ሳትተኛ ቀን ከለሊት አስስ።እየመነጠርክ አውጣ። እድሉን ካገኘ እንደማይምርህ እወቅ ‼️

🔴አዲስ አበባ ውስጥ በፊት ነባር ነዋሪዎችን በከተማ ልማት ስም እያፈናቀለ ሲበታትን የነበረው ማሕበራዊ ግንኙነታቸውን ከመበጣጠስም አልፎ ብዙ ዘመን አብረው ስለኖሩ ይመክሩብኛል ያሴራሉ መበታተን አለባቸው በሚል ያደረገው የሕወሐት የሴራ ፓለቲካ ነበር። የዚህ ማሳያው በደሴ ረዥም ዘመን የኖሩት የትግራይ ተወላጆች ከውስጥ ሆነው እንዴት ሠራዊታችንን እንደወጉት በግልጽ የታየ ነው። ለአዲስ አበባም የተደገሰው እልቂት ከዚህ ጋር የተያያዘና የሰፋ የከፋ ተመሳሳይ የእልቂት ድግስ ነበር። በየቀበሌው፣ በየወረዳው፣ በየዞኑ ( ክፍለ ከተማው) በወታደራዊ አወቃቀር የተዘጋጀው የአሸባሪው ሕወሐት አባላት መዋቅር በአብዛኛው ሲቪሎችን፣ ወጣቶችን፣ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችን፣ በግል ድርጅት ውስጥ የሚሰሩትን፣ ከመከላከያ የተቀነሱና ከተማ ያሉ ነባር ታጋዮችን፣ በሙሉ የሚያካትት፣ ለሀገረ ትግራይ ምስረታ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ግዳጅ የጣለና ያለልዮነት ያሰለፈ ነው። ንጹሀን ቢኖሩም እጅግ በጣም ጥቂት ነው የሚሆኑት። ንጹሀን አሉበት በሚል ስም በፍጹም መዘናጋት አይገባም። ከመቶ አምስት ፐርሰንት ቢገኙ ነው።

🔴የአሸባሪው ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች ሁሉም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥና ዳርቻ ላይ ከውስጥ ሆነው ድንገተኛ ጦርነት ለመክፈት ሕዝብን ለመጨፍጨፍ ለመዝረፍ በተጠና እቅድ ተዘጋጅተው ነበር። በአዲስ አበባ ነዳጅ ማደያዎችን፣ ሆስፒታሎችን፣ ፓሊስ ጣቢያዎችን፣ ወታደራዊ ካምፓችን፣ በተመሳሳይ ሰአት የማጥቃት እቅድ ነበራቸው። ባንኮችን ይዘርፋሉ። አስቀድመው በስም ዝርዝር የያዟቸውን የመንግስት ደጋፊዎች እያወጡ ይረሽናሉ። ደሴና ኮምቦልቻ ሌሎችም ቦታዎች እንዳደረጉት። የመንግስት ወታደሮች ለመከላከል በሚያደርጉት ውጊያ አሸባሪዎቹ ጦርነቱን የጀመሩት ሕዝብ ውስጥ ስለሆነ ብዙ ሕይወት ያልፋል። ውድመት እልቂት ይፈጠራል። የተደራጀና ያልተደራጀ አንድ ስላልሆነ ድንገት በሚፈጠር ውርክብና ትርምስ በዚህ መልኩ አዲስ አበባን ደም እንደ ዥረት የሚፈስባት የጦር ሜዳ እናደርጋታለን ብለው ወስነው ጨርሰው ነበር። ከፈረንጆቹ ጋር ተማክረው እንወጣለን ሲሉ የነበረው ከፊሎቹም የወጡት አማጺው አዲስ አበባ አካባቢ ደርሷል ሲሉ የነበረውም ይኼንኑ የጥፋት ሚስጢር ነጮቹ ስለሚያውቁ ነበር‼️

🔴 በዚህ የጥፋት እቅዳቸው ወያኔና አባላቱ ደጋፊዎቻቸው ያሏቸውን የግል መኪናዎች ሁሉ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ከየሰፈሩ ነዋሪ የሆነውን አባላትና ደጋፊዎቻቸውን ጭነው በመዘዋወር ተኩስ ይከፍታሉ። ድንገተኛ ጥቃት ይሰነዝራሉ። ከውጭ የመጣ የገባ ኃይል አይደለም። እኛው ውስጥ አብረውን የኖሩ ጎረቤት ፣የስራ ባልደረባ ፣ጋብቻ፣ አበልጅ፣ አብሮን የተማረ፣ የምንላቸው በቅርብ የምናውቃቸው ሰዎች ናቸው ተኩስ ከፍተው ሊፈጁን ተዘጋጅተው የነበሩት። በዚህ መልኩ እልቂት ይነግሳል። ትርምስ ይፈጠራል። የተደራጀና ያልተደራጀ ሕዝብ እኩል አይደለም። በዚህ ትርምስ መሀል ውሀ፣ መብራት፣ ምግብ መጠጥ፣ ሕክምና፣ ገበያ፣ ሱቅ ወዘተ ይጠፋል። አዲስ አበባ ላይ ጁንታው በገንዘብ እየገዛ በምስጢር ያዘጋጀው ያደራጀው ማጅራት መቺና ዱርዬ ሰፊ ዘረፋዎችን ያካሂዳል። ሱቆች ፣መደብሮች፣ ወርቅቤቶች፣ ፋርማሲዎች፣ ጫማና ልብስቤቶች፣ ቡቲክ ፣ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ የግል ድርጅቶች ወዘተ በሙሉ ይዘረፋሉ። ሴቶች በብዛት ይደፈራሉ። መንግስት ለመከላከል በሚያደርገው ጥ
ረት

የተወሰነ የከተማውን ክፍል ይዘው መዋጋት ነበር እቅዳቸው።

🔴ከከተማዋ ስፋት አንጻር የተወሰነ ቦታ ገብተው በሚፈጥሩት ትርምስ ተቀናጅተው ተደራጅተው ገንዘብ እየከፈሉ ያዘጋጇቸው የውጭ ሚዲያዎች ወዲያው በአለም አቀፍ ደረጃ ወያኔ አዲስ አበባን ተቆጣጠረ ብለው ዜና ያሰራጫሉ። በዚህ መልኩ ነበር የተዘጋጁት። ይሄንኑ ለጌቶቻቸው አሳውቀው ኤምባሲዎች ለቀው እንዲወጡ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ወከባና ጫና እንዲበረታ ነበር የታቀደው። አዲስ አበባን ነዋሪዋን ለመበቀል ለመግደል፣ ሀብቷን ንብረቷን ለመዝረፍ ለማውደም ከተማዋን እንዳልነበረች አድርገው በማውደም በማጥፋት ለመበቀል ነበር ያቀዱት። በዚህም ምክንያት ኤምባሲዎቹም ሲወጡ የአፍሪካ ሕብረት ሰላም የለም በሚል ቢሮውን በግድ ወደ ግብጽ ካይሮ እንዲለውጥ ለማስገደድ ነበር ወያኔ አሜሪካ ግብጽና ሱዳን መክረው ዘክረው ሲሰሩ የነበሩት። ሴራቸው ሕልም ሆኖ ከሸፈ‼️

♦️ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ያሉት የጁንታው አባላት ወታደራዊ ልብሶችንና መሣሪያዎችን ከቀበሩበት አውጥተው በመልበስና በመታጠቅ በራሳቸው የግል መኪኖች ሰዎቻቸውን ጭነው እየተኮሱ እየገደሉ እያሸበሩ እየዘረፋ ከተማ በመግባት አዲስ አበባን ከሚያተራምሰው ኃይል ጋር ይገናኛሉ። እነሸኔ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በማድረግ አጋርነታቸውን ያሳያሉ። የዘር ጭፍጨፋ ያካሂዳሉ።የመንግስት ኃይሎች በተወሰነው የከተማ ክፍል ሆነው ሲከላከሉ እነአሜሪካ እንግሊዝና የምእራቡ ሰዎች ለወያኔ እውቅና ሰጥተናል ይላሉ። ተመሳሳይ ስልት ሶርያ ላይ ተጠቅመዋል። ይሄንን አደረጃጀት ወያኔ የዘረጋው በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ አነስተኛና ትላልቅ ከተሞች ነው። መዋቅሩን፣ አደረጃጀቱን፣ የሰው ኃይሉን፣ ኢኮኖሚውን፣ የእዝ ግንኙነቱን ፈጥኖ መበጣጠስ አስፈላጊና ወሳኝ ስለነበር እርምጃ ተወስዷል። አሁንም ብዙ ይቀራል። አሁንም ደግሞ ስማቸውንና ብሔራቸውን ለውጠው ፎርጂድ መታወቂያ እያሰሩ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይሄንን የሚተባበር ወንጀለኛ ወዲያው እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል። አዲስ አበባ ጠንካራ ፍተሻ አለ በሚል በአራቱም የከተማ መውጫዎች ባሉ አነስተኛ ከተሞች ላይ ትኩረት አድርገው ይንቀሳቀሳሉ። ተከታትሎ ማደን ይገባል። ይህ የእነሱ የከተማ ማጥቂያ የውስጥ ኃይልን በመጠቀም ጥቃት የመፈጸም እቅድና ዝግጅት በአለም ታሪክ አዲስ አይደለም። ከሽፎባቸዋል። የቀረውም ይከሽፋል‼️እነዚህ በመደበኛ ውጊያ ውስጥ ያሉ የውጊያ ስልቶች አይደሉም። ኢመደበኛ ቀመሮች ናቸው።

👉ይሄን ሁሉ ለመስማት የሚዘገንን ለአዲስ አበባ ሕዝብና ለውቧ ከተማ የተደገሰልንን ታላቅ የሞት እልቂትና ውድመት በፍጥነት የቀለበሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እዝ ነው‼️ ፈጣን ሀገር አድን እርምጃ ወሰደ‼️ የግንኙነት የድርጅትና የእዝ ሰንሰለታቸውን በጣጠሰው‼️ታላቁ የጥፋት የእልቂት አዲስ አበባን በደም ለማጥለቅለቅ ለማውደም ወያኔ የጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ‼️ አሁንም የሚቀሩ ብዙ ርዝራዦች አሉ። በየዋህነት በአብሮ መኖር በርህራሄ ስም መጠቃቱ መገደሉ ይብቃ‼️ ለራስህ ለቤተሰብህ ስትል አካባቢህን የስራህን ቦታ ነቅተህ ጠብቅ‼️ለራስህ ስትል መረጃ ለመንግስት ስጥ። ይሄን ባታደርግ የምትጠፋው አንተም ቤተሰብህም ናቸው።ሁሉም በአንድነት ቆሞ ተባብሮ የመጣበትን አደጋ መክቶ ይቀልብስ‼️

🔴ጥርስህን ነክሰህ መሪህን ፣ሀገርህን ፣ነጻነትህን ክብርህን ጠብቅ። ወያኔ እድሉን ቢያገኝ እንደ ከብት ያርድሀል። አይንህ እያየ ሚስትህን ልጆችህን ይደፍራል። ሀብትና ንብረትህን እያየህ ይዘርፈዋል። እሳት ለኩሶ ያነደዋል። ምራቁን ይተፋብሀል። ሽንቱን ይሸናብሀል። ወዳጄ ይሄ ሁሉ የአዲስ አበባ እንገባለን ድንፋታ በውስጥ በሚገኙ የጁንታው ድብቅ ሠራዊት ሊካሄድ የነበረው እልቂት የከሸፈው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና በፍጥነት በተወሰደው የማያዳግም እርምጃ ነው‼️ እሰየው አበጀህ ብለናል ‼️
♦️ ምናልባት አብሮህ የኖረው፣ በጋብቻ የተዛመድከው ፣የስራ ባልደረባህ የሆነው በድንገት ተነስቶ ልክ ሰሜን እዝ ላይ እንዳደረጉት በየመንደሩ በየጎረቤቱ ብቅ እያለ ፣ ደብቆና ቀብሮ ያስቀመጠውን ቦምብና መትረየስ እያወጣ፣ ሕጻን ወጣት ሴት አሮጊት እርጉዝ ሴት ሳይል ጥይት ቢያርከፈክፍብህ ፣ ስላልተዘጋጀህ የሚጠብቅህ ሞት ነበር። ያኔ ድፍን ከተማው በጩሀትና በጥይት እሩምታ ይታመሳል። መልምለው ያዘጋጁት ቦዘኔና ነፍሰ ገዳይ ወዲያው ዘረፋ ይጀምራል። መብራት ይጠፋል። ሴቶች ይደፈራሉ። ግድያውን በቆንጨራም በጥይትም በስለትም ያካሂዱታል። በአጭሩ ጁንታው ለአዲስ አበባ የደገሰላት አሰቃቂ ጥፋትና ውድመት ይሄንን ይመስል ነበር። በሰፋ ሁኔታ በቡራዩ ላይ የሞከሩትን ዘግናኝ ጥፋትና ውድመት አዲስ አበባ ላይ ለመድገም ነበር እቅዳቸው። አልሆነም‼️ አይሆንምም‼️መንግስት ቀደማቸው‼️ ሕዝቡም በየሰፈሩ ተደራጅቶ ያለውን ይዞ ነቅቶ ከፓሊስ ጋር ይጠብቃል‼️ ሞኝነት ድሮ ቀረ‼️ ጅብ ከሚበላህ በልተህ ተቀደስ ነው ነገሩ‼️ ተጠንቀቅ። አትዘናጋ‼️ከመሪህ ጎን ጸንተህ ቁም‼️ ሌላ አማራጭ የለህም‼️
🔴ድል ለኢትዮጵያና ለልጆቿ ‼️
🔴ድል ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችንና ለሕዝባዊ ሠራዊቶቻችን‼️
🔴ተነስ፣ታጠቅ፣ዝመት‼️
🔴አሸባሪውን ሕወሐት በተገኘበት ቦታ ሁሉ ደምስስ‼️
ጃተማ አባቢያ
የማትንበረከከዋ ኢትዮጵያ
#በምክትል #ርዕሰ #መስተዳድር #ማዕረግ #የግብርናና #የገጠር #ልማት #ክላስተር #አስተባባሪ እና #የክልሉ #ግብርና #ቢሮ #ኃላፊ #አቶ #ኡስማን #ሱሩር #ለይፋዊ #ስራ #ጉብኝት #ዛሬ #ረፋዱ ላይ #ሳውላ #ገብተዋል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የዞኑ የፊት አመራሮች እና ካቢኔ አባላት ምክትል ዕርሰ መስተዳድሩን ተቀብለዋቸዋል። ምክትል ዕርሰ መስተዳደሩ በጎፋ ዞን ቆይታቸው በግብርናው ዘርፍ የተሰሩ ስራወችን ጎብኝተው በሳውላ ከተማ ለሚገኙ ለዘማች በተሰቦች ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ህዳር/ 26/ 2014ዓ.ም
#ሣውላ
በሀገራችን ላይ የሚፈፀመውን የውጭ ጫና የኢኮኖሚ አሻጠጥርን ለመቋቋም እና የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር የተመራው የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሰራ ኃላፊዎ የልዑካን ቡድን ጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ በዶጫ ዳንባላ ቀበሌ በባለሀብት ኢንቨስተር እየለማ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ እርሻ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ አካሄደዋል።

በጉብኝቱ ወቅት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር እንደገለጹት" በባለሃብቱ እየተከናወኑ የሚገኙ የግብርና ልማት ስራዎች እጅግ አበራታች ናቸው ። ከሰራን መለወጥ እንደምንችል እሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ በፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያ የኢንቨስትመንት ማሳ ላይ ያሉ ተግባራት ማሳያ ናቸው ብለዋል"።

የውጪ ዕርዳታ ሳንጠብቅ በራሳችንም ምርት የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ አርሶአደሮቻችንን በመደገፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሀገር ውስጥ የምግብ ለማሟላት የግብርና ተክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርታማነት ለመጨመር በትኩረት ሊሰራ እንደደሚገባ ጠቁመዋል።

#ህዳር 26/2014ዓ.ም
የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ለዘማች ቤተሰብ ልጆች የትምህርት መርጃ መሳሪያ ድጋፍና ለአቅመ ደካማ አረጋውያን ያሰሩትን መኖሪያ ቤት አስረከቡ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሣውላ:ህዳር 26/2014 ዓ.ም የቢሮው ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ለሚኖሩ የዘማች ቤተሰብ ልጆች የትምህርት መርጃ መሳሪያ ድጋፍ እና በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በቢሮው ሰራተኞች እና የስራ ኃላፊዎች የተጀመረው የአረጋውያን የመኖሪያ ቤት ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአረጋውያኑ የቁልፍ ርክክብ ስነ-ስረአት ተከናውኗል።

የዘማች ቤተብንና አቅመ ደካማ አረጋውያንን ለማበረታትና ደጀንነትን ለመገልፅ የተደረገ ድጋፍ መሆኑም ተጠቁሟል።

ድጋፉ ለ39 የዘማች ቤተሰብ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተበረከተ ሲሆን ለ4 አቅመ ደካማ አረጋውያን ደግሞ ተሰርቶ የተጠናናቀቀ ቤት ርክክብ ነው የተደረገው።

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የግብርናና የገጠር ልማት ዘርፍ አስባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር የዘማች ቤተሰብን መደገፍ ከሁላችን የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል።

የዘማች ቤተሰብ ብቻችሁን አይደላችሁም ያሉት አቶ ኡስማን የጀግኖች ሚስቶችና ልጆች በመሆናችሁ ክብርና ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል ሲሉም የዘማች ቤተሰብን አበረታተዋል።

በምትሰማሩበት የስራ መስክ ሁሉ ውጤታማ እንዲሆኑ እመኛለሁ በማለት አቶ ኡስማን የዘማች ቤተሰብን በማሳሰብ ለዘማች ቤተሰብና የአቅመ ደካማ አረጋውያን የሚደረገው ድጋፍ የሚቀጥል መሆኑን አቶ ኡስማን ጠቁመዋል።

እማማ ሽሎቴ አዛዜ በሳውላ ከተማ ቤት ተሰርቶ ከተሰጣቸው አቅመ ደካማ አረጋውያን መካከል አንዷ ሲሆኑ ልጆቼንና የትዳር አጋሬን በሞት አጥቼ ጧሪ ቀባሪ የሌለኝ ሰው ነበረክሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ልጆቼንና ባለቤቴን በሞት ካጣው በኋላ በቤተ እምነት ስረዳ ነበር ያሉት እማማ ሽሎቴ ቢሮ በሰራልኝ ቤት ደስተኛ ሆኜ እንድኖር አርጋችውልኛል በማለት ለተደረገላቸው ሰብአዊ ድጋፍ መርቀዋል።

የሳውላ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉቀን ጉጃ የግብርና ቢሮ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች ለበረከቱት ሰብአዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

#ህዳር 26/2014ዓ.ም
"ስንዴን በክላስተር የሚያመርቱ አርሶ አደሮች የላቀ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራል" በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሣውላ፡ ህዳር 26/2014 ዓ.ም በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር የተመራው የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሰራ ኃላፊዎ የልዑካን ቡድን ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ የሚገኝውን የስንዴ ክላስተር ማሳ የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡስማን ስሩር በዚህ ወቅት እንደገለጹት "አሁን ካለንበት ነባራዊ ሆኔታ አንጻር አርሳደሩ ከክልል ጀምሮ የሚደረግለትን የግብርና ግብዓት ድጋፍ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይጠበቅበታል። አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በነፃ ገበያ ተወዳድሮ የሚሸጥበት ስርዓት መንግስት ዘርግቷል። በቀጣይም አርሶ አደሩ የላቀ ተጠቃሚ እንደሆኑ ይሰራል ብለዋል"።

የአገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የዘመናዊ ግብርናው ዘርፍ ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ለተሰማሩ ውጤታማ ለሆኑ አርሳደሮች የክልሉ ግብርና ቢሮ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርግም የክልሉ ምክትል ዕርሰ አቶ ኡስማን ሱሩር ተናግረዋል።

የሀገር ውስጥ የምግብ ፍጆታን ለማሟላት የግብርና ተክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርታማነት ለመጨመር በትኩረት ሊሰራ እንደደሚገባ ጠቁመዋል።

የውጪ ዕርዳታ ሳንጠብቅ በራሳችንም ምርት የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ አርሶአደሮቻችንን በመደገፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እርብርብ እንዲያደርጉ የቢሮው ኃላፊ ጥሪ አቅርበዋል።

#ህዳር 26/2014 ዓ.ም
#የጉዞ #ማስታወሻ #ቅኝት #በመሎ #ጋዳ #ወረዳ



ታህሳስ 10/2014 ዓ.ም ሣውላ፡ በጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው የተመራው የልዑካን ቡድን የዞኑን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ፣ የዞኑን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብረሃም ዞራ፣ የዞኑን ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጠንክር ጠንካ ጨምሮ ሌሎችም የዞኑን ካቢኔ አባላትና የስራ ኃላፊዎች አካትቶ ልክ ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ ነበር ወደ መሎ ጋዳ ወረዳ ጉዞውን የጀመረው።


ጠመዝማዛውን አስቸጋሪ ዳገትና ቁልቁለት የበዛበትን የባርዛን፣ የጃውላን እና የዳዳን ቀበሊያት አቋርጠን ኢርጊኖ ወንዝ ስንደርስ የጋዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አበበን ጨምሮ ሌሎች የወረዳው አመራሮች በተገኙበት የእንኳን ደህና መጣችሁ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።


የኢርጊኖ ወንዝ ለዘመናት ለመሎ ጋዳ ህዝብ "እሾማ ወርቅ" ሆኖ ያለጥቅሙ ጉዳቱ አመዝኖ የበርካቶችን ህይወት ቀጥፎ አብዛኛውን የጋዳን ነዋሪ ለፀፀት ዳርጎ ብዙ ተስፋዎች ሲያጨልም ቆይቷል።


በጋዳ ወረዳ፣ በዞን፣ በክልል እና በፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባደረጉት ቅንጅት የጉዳዩን አንገብጋቢነትና በየጊዜው በወንዙ ሙላት የከሰተውን የሞት አደጋ "ለሳሊኒ" አመራሮች በማስረዳት ጊዚያዊ የሰው መሻገሪያ በካቦ ገመድ የተወጠረ ፌሮ ብረት የተረበረበበት ተውረግራጊ ድልድይ በመሰራቱ ለጊዜውም ቢሆን ለህዝቡ እፎይታን ስቷል።


ድልድዩ በዋናነት የሚገነባው በደቡብ ክልል መንገዶች ባለስልጣት በኩል ሲሆን በኮትራክተሩ የአቅም ውስነትና ዳተኝነት፣ የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ክትትልና ቁጥጥር ማነስ ተጨምሮበት እንዲሁም የአካባቢው መልካምድር አቀማመጥ ፈታኝነት የተነሳ ተጀምሮ የወቆመው ኢርግኖ ወንዝ ድልድይ አሁንም ዋነኛ የህዝብ ቅሬታ ምንጭ መሆኑ ወንባ ከተማ ላይ በነበረው የህዝብ ምክክር መድረክ ላይ ተነስቷል።


የኢርጊኖን ወንዝ ተሻግረን ጉዞው ቀጥሎ አሊዛ ቀበሌ ሜላ ንዑስ እንዲሁም የጋዳ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ወንባ ከተማ ስንደርስ በሀገር ሽማግሌዋች እና በነዋሪዎች በድጋሜ የእንኳን ደና መጣቹህ አቀባበል ተደርጎለታል።


በመቀጠልም በወረዳው የህብረተሰብ ተሳትፎ ያለ አንዳች መንግስት በጀት የተከናወኑ የልማት ስራዎች በልዑካን ብድኑ የተጎበኙ ሲሆን የመሎ ጋዳ ወረዳ ህዝብ በዚህ ረገድ ለሌሎች የዞናችን መዋቅሮች ተሞክሮ የሚሆን በአርያነት ሊገለጽ የሚችል ተግባራትን ማከናወናቸው በጉብኝቱ ወቅት ተስተውሏል።


ለአብነት ለመግለጽ ያህል 108 ክፍል ያላቸውን የተለያዩ ሴክተር መስሪያቤቶች በመገንባት፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 5 የመማሪያ ብሎኮችን እና 16 ክፍል ያላቸው የመምህራን መኖሪያ ቤቶችን በህረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብተው አገልግሎት ላይ መሆናቸውን በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተመራው የልዑካን ቡድን ምልከታ አካሄዷል።


ወረዳው አዲስ ከመሆኑ አንፃር በርካታ ውስብስብ የመሰረተ ልማት ችግሮች ውስጥ ሆኖም በአጭር ጊዜ ያስመዘገበው ውጤት አበረታች በመሆኑ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ለህብረተሰቡ ከልብ የመነጨ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።


ከልማት ስራዎች ጉብኝት ጎን ለጎን በአካባቢው የሚመረቱ ምርቶች የውጭ ምንዛሪ ሊያስገኙ የሚችሉ እና ገበያ ተኮር የሆኑ የፍራፍሬ፣ የአትክልት፣ የጥራጥሬ እና የስራስር ለአብነትም (የሙዝ፣ የብርቱካን፣ የአናናስ፣ የቡካዶ፣ የፓፓየ፣ የሎሚ፣ የማንጎ......የኦቾለኒ፣ የሰልጥ፣ የሩዙ፣ የቡና፣ የማሾ፣ የጅንጅብል፣ የኮረራማ...ወዘተ) ምርቶች ተጎብኝተዋል።


ከጉብኝት መልስ የህዝብ ውይይት እና ምክክር መድረክ የቀጠለ ሲሆን ውይይቱን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ፣ የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዞራ እና የመሎ ጋዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አበበ መርተውታል።


በውይይት መድረኩ ከሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች የተሳተፉበት ሲሆን በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃ ውይይቱ ተጀምሮ የልዑካን ቡድኑ በአካባቢው ልማት ጉዳይ ለመምከር ወደ መሎ ጋዳ ወረዳ መምጣቱን አመስግነው ከነዋሪዎች በርካታ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች እንደ መንገድ፣ ድልድይ፣ ውሃና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የመብረት፣ የባንክ፣ የቴሌኮም፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና የጤና ተቋም ግንባታ፣ የማዘጋጃቤታዊ ጥያቄዎች እና ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተዋል።


የመንገዱና የኢርጊኖ ወንዝ ድልድይ ግንባታ መጓተት ህብረተሰቡን እያማረረ ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች የህዝቡ ቅሬታ ዋነኛ ምንጭ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።


በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ በሚመለከታቸው የዞን ካቢኔ አባላት እና በመድረኩ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ህብረተሰቡ መንግስት ያለበትን የበጀት ውስንነት በመረዳት በሚልዮን የሚገመት የገንዘብ፣ የጉልበት እና የአይነት ድጋፍ በማድረግ 108 ክፍል ያላቸው የተለያዩ ቢሮዎች መገንባት በመቻላቸው፣ ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 5 ብሎኮችን እና 16 የመምህራንን መኖሪያ ቤቶችን መገንባት በመቻላችሁ የዞኑ ዋና አስተዳደር ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ለነዋሪዎች ላቅ ያለምስጋናና አክብሮት በመሰጠት ግንባር ቀደም የልማት አርበኛ በመሆናቹህ ኮርተንባችኋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህ መልካም ተግባር ለሌሎች ወረዳዎች ተሞክሮ የሚሆን ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።


በዚህ ወስብስብ ነባራዊ ሆኔታ ውስጥ ሆናችሁ ችግሮች ሳይበግሯችሁ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ያደረጋችሁት የደጀንነት ተግባር ጠንካራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን በተግባር አስመስክራቹሀል ብለዋል።


የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አክለውም የተነሱ ጥያቄዎች ትክክለኛ እና አግባብነት ያላቸው የሚታወቁ መሆኑን ተናግረው የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶት ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አስረድተው የኢርጊኖ ወንዝ ድልድ ግንባታ መጓተትን አስመልክቶ የመጀመሪያው ኮንትራክተር በተያዘለት የጊዜ ገደብ ማከናዎን ባለመቻሉ ምክንያት ክልሉ ውሉን አቋርጦ ለሌላ ተቋራጭ መስጠቱን ተናግረው ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ መልክ እንደሚጀመር ተናግረዋል።


በዝህ በጀት አመት ለጋዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ የሚሆን 250,000 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በጀት የተያዘለት መሆኑን ጠቁመው ለቀጣይ አመት ለግንባታ ማስጀመሪያ የሚሆን 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ እንደሚደረግም ቃል ገብተዋል።


ዞኑ የወረዳውን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚያደርገው ጥረት እንዳለ ሆኖ እነዚህን የህዝብ ፍላጎቶች ከበጀት ውስንነት የተነሳ በተፈለገው ፍጥነት ማስኬድ እንዳልተቻለም ተጠቁሟል።


በመጨረሻም በዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ እና በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብረሃም ዞራ በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።


በመቀጠልም የጋዳ ጤና ጣቢያ ግንባታ ለ12 ተቋርጦ ከነበረበት በአዲስ መልክ ተጀምሮ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረሱን ጉብኝት ተካሄዶ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠቃሏል።

ታህሳስ 10/2014 ዓ.ም
ያልተነገረለት እና ያልተዘፈነለት ጠላቶችን ያቀጠቀጠ የአየር ኃይሉ የኛ ጀግና ኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ ማን ናቸው????


ከጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ በና ሐሙስ ገበያ እስከ አሜሪካን ሳን ፍራንሲስኮ በወፍ በረር የጀግናውን ኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ ታሪክ እናስቃኛቹህ።


ታህሳስ 11/2014 ዓ.ም ሣውላ: በጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው የሚመራው አጠቃላይ የዞኑ አመራር ለቀድሞው የአየር ኃይላችን ጀግና ኮሎኔል ከንፉ ሀብተወልድ እንኳን ደህና መጣህ ደማቅ የጀግና አቀባበል አደረጉ።


ኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ የተወለዱት በ1948 ዓ.ም በአሁኑ የጎፋ ዞን በዛላ ወረዳ በና ሐሙስ ገበያ በሚባል አካባቢ ሲሆን ከ1ኛ-3ኛ ትምርታቸውን እዛው በተወለዱበት ቀያቸው ተከታትለዋል።


በኋላም ከ4ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በተወለዱበት አካባቢ በወቅቱ ትምርት ቤት ስላልነበረ ወደ ቀድሞው ፈለገ ነዋይ ልዕልት ሮማንወርቅ ትምርት ቤት (የአሁኑ ሣውላ ቦትሬ ትምርት ቤት) በመዛወር ትምርታቸውን ተከታትለዋል።


ኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ በትምህርታቸው እጅግ በጣም ጎበዝ ትጉህና ታታሪ ስለነበሩ 8ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ከአውራጃው ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው የተደሰቱት አጎታቸው ፊታውራሪ አባይነህ ፊኖ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በወቅቱ አጎታቸው የፓራላማ አባል ስለነበሩ ወደ ሚኖሩበት አዲስ አበባ ከልጆቻቸው ጋር እንዲማሩ ሁኔታውን አመቻቹላቸው። በዚህን ጊዜ ነበር ለኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ የስኬት መውጫ በር በአጎታቸው አማካኝነት የተከፈተላቸው።


ኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ የ2ኛ ደረጃ ትምርታቸውን በጥሩ ውጤት አጠናቀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በMechanical Engineering ተከታትለው ተመርቀዋል። በመቀጠልም በቀድሞው የኢትዮጵያ የአየር ኃይል የአይሮፕላን በረራ ትምህርት ቤት ገብተው በተዋጊ አብራሪነት በመሰልጠን በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል።


ኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ ከ19 ዓመታቸው ጀምሮ የወጣትነት አፍላ ዕድሜያቸው በሙሉ የሀገራችንን የአየር ክልል እዳይጣስ፣ በህዝቡና በተቋማት ላይ ጉዳት እንዳይደር ከባድ ኃላፊነት ተቀብለው ሀገራቸውን በአራቱም ማዕዘናት ተዘዋውረው ለሕይወታቸው ሣይሳሱ በአውሮፕላን አብራሪነት፣ በአሰልጣኝነት እና ተዋጊነት እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን እንዲሁም የሚችሉትን ሁሉ ለሀገራቸው አበርክተዋል።


ምስጋና ጀግና ለሚወልዱ ለጎፋ እናቶች ይሁንና የጎፋ አባቶች በአደዋና በማይጮ ጦርነት ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው የሀገር አንድነትን አጽንተው አኑረውናል። ለዚህም ምስክር የሚሆን ለታሪክ ማስታወሻነት በመሀል አዲስ አበባ ጎፋ ሰፈር ስያሜ ተሰጥቶታል። በተመሳሳይ የአየር ኃይሉ ጀግና ኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ ከ1960ዎቹ እስከ 1983 ዓ.ም ሀገራችን በሰሜን በኩል ከሻቢያ እና ከወያኔ ጋር ያጋጠማትን መጠነሰፋ ወረራ በመመከት እንዲሁም በምስራቅ በኩል ከሱማሊያ ሰርጎ ገብ የተቃጣባትን ወረራ በብቃት በመመከት አኩሪና ደማቅ ታሪክ የሰራ ያልተነገረለት እና ያልተዘመረለት የሀገር ባለውለታ የቁርጥ ልጅ ነው።


ይህንን የሀገር ባለውለታ የአየር ኃይሉን ጀግና ጨምሮ ሌሎችንም የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ለሀገር ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እና ውለታ በመካድ በ1983 ዓ.ም ህወሓት ሀገሪቱን ስልጣን በአሜሪካን እርዳታ ሲቆጣጠር እዚህን የቀድሞ ባለውለታ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለጡረታ እና ያለደመዝ በትኖ ገሚሱን ገድሎ፣ ገሚሱን አስሮ የተቀሩትን በባዕድ ሀገር እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል።


በባእድ ሀገር ከሚከራተቱ እጅግ ብዙ የሀገር ባለውለታ ጀግኖች ውስጥ ታሪኩና ዝናው ያልተነገረለት የአየር ኃይሉ ጀግና ኮሎኔል ክንፉ ሀብተወልድ አንዱ ነው።


ኮሎኔሉ ምንም እንኳን ኑሮውን በስደት ከተቤተሰቡ በአሜሪካን ሳን ፍራንሲስኮ ቢያደርግም ሀገራችን በጭንቅ ጦር በተወጠረችበት በአሁኑ ወቅት የገጠማትን ውስብስ ችግር ከሚወደው ወገኑ ጋር ለመጋፈጥ በመላው አለም የሚኖሩትን ፍቃደኛ የሆኑ በቁጥር 25 የቀድሞ የሀገሪቱ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በማስተባበር ባላቸው ዕውቀት (በአየር ኃይል፣ በምድር ኃይል እና በባህር ኃይል) ለመገዝና ለመደገፍ ቡድኑን መርቶ ወደ አገር ውስጥ የገባ ሲሆን ይዘውት የመጡትን $40,000 (አርባ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) እና በአንድ አይሮፕላን ሙሉ የተጫኑ ግምታቸው በሚልዮን የሚቆጠር ብር የሚያወጣ የተለያዩ መዳኒቶችን በማምጣት ለሀገር መከላከያ ሚኒስተር አስረክበዋል።


ህውሓት ውለታቸውን እና ድካማቸውን ዘንግቶ በክፉ ጊዜ ከሀገር እንዲሰደዱ ቢያደርጋቸውም እነሱ ቂም ሳይዙ እውነተኛ የሀገር ፍቅር ወኔ ስላስገደዳቸው ሀገራችን የገጠማትን ውስብስብ ችግር በመገንዘብ አቅማቸው የፈቀደውን ለማድረግ በስደት የሚኖሩበትን ቅንጡ ህይወት እና ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ሀገራቸውን ለማገዝና ለመደገፍ መተዋልና ምስጋና ይገባቸዋል።


በመሆኑም ይህንን የሀገር ባለውለታ ለማመስገን በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው የሚመራው አጠቃላይ የዞኑ አመራሮች እና የኮሎኔል ከንፉ ሀብተወልድ ወዳጅ ዘመድ በተገኙበት የስጦታ፣ የዕውቅና እና የምስጋና ሥነስርዓት ተካሄዳል።


#ታህሳስ 11/2014 ዓ.ም

#ዘገባው:- የጎፋ ዞን መንግስት
ኮሚኒኬሽን ነው