የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
40 subscribers
89 photos
1 video
Download Telegram
#የጎፋ #ዞን #ነዋሪዎች #በ4ኛው #ዙር #ለሀገር #መከላከያ #ሰራዊታችን #ከ37 #ሚልዮን 981 #ሺህ #ብር #በላይ #በዓይነትና #በገንዘብ #ድጋፍ #ማድረጋቸው #ተገለፀ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ህዳር 03/2014 ዓ.ም ሣውላ:- በጎፋ ዞን አስተዳደር ለጀግናው የሀገር መከታና አሌንታ ለሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በየመዋቅሩ ያሉትን የዞኑን ነዋሪዎች በማስተባበር 37,981,276.75 ብር (ሰላሳ ሰባት ሚልዮን ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰባስ ድስት ብር ከሰባ አምስት ሳንቲም) የፋይናንስ አሰራር መመሪያና ደንብ መሠረት ባደረገ መልኩ መሰብሰቡን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና የሀብት አሰባሳቢ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው አስታወቁ።

በመጀመሪያው፣ በሁለተኛው እና በሦስተኛው ዙር በጎፋ ዞን አስተዳደር ነዋሪዎች 434 ሰንጋዎችን ጨምሮ ከ51 ሚልዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የተለያዩ ድጋፎችን በአይነትና በገንዘብ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ መደረጉን ያስታወሱት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በአተኛው ዙርም ደግሞ 317 ሰጋዋችን፣ 46 በጎችን፣ 32 ፍየሎችን ጨምሮ ከሦስት ቀን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ከወትሮው በተሻለ በነዋሪዎች ከፍተኛ ተሳትፎ፣ ተነሳሽነት እና የሀገር ፍቅር ወኔ ከ37 ሚልዮን 981 ሺህ ብር በላይ በዓይነትና በገንዘብ ለጀግና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ መደረጉን ዶ/ር ጌትነት በጋሻው አክለው ገልፀዋል።

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለፆ በአሁኑ በአራተኛው ዙር በጥሬ ገንዘብ ከተሰበሰበው በተጨማሪ በዓይነት:-
👉 በሬ በቁጥር 317
👉 በግ በቁጥር 46
👉 ፍዬል በቁጥር 32
👉 በሶ 34 ኩ/ል፣
👉 ኩኪስ 3.5 ኩ/ል፣
👉ጤፍ 3 ኩ/ል፣
👉ለውዝ 3 ኩ/ል በድምሩ 47.5ኩ/ል
👉 ወደ ግንባር ለመዝመት የተመዘገቡ የአመራሮች ብዛት 18 መሆናቸውን የሀብት አሰባሳቢ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው አሳውቀዋል።

ዘገባው:- የጎፋ ዞን #መንግስት #ኮሚኒኬሽን #ጉዳዮች #መምሪያ #ነው

ህዳር 03/2014 ዓ.ም
#ሣውላ