#የጉዞ #ማስታወሻ #ቅኝት #በመሎ #ጋዳ #ወረዳ
➖➖➖➖➖➖➖➖
ታህሳስ 10/2014 ዓ.ም ሣውላ፡ በጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው የተመራው የልዑካን ቡድን የዞኑን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ፣ የዞኑን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብረሃም ዞራ፣ የዞኑን ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጠንክር ጠንካ ጨምሮ ሌሎችም የዞኑን ካቢኔ አባላትና የስራ ኃላፊዎች አካትቶ ልክ ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ ነበር ወደ መሎ ጋዳ ወረዳ ጉዞውን የጀመረው።
ጠመዝማዛውን አስቸጋሪ ዳገትና ቁልቁለት የበዛበትን የባርዛን፣ የጃውላን እና የዳዳን ቀበሊያት አቋርጠን ኢርጊኖ ወንዝ ስንደርስ የጋዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አበበን ጨምሮ ሌሎች የወረዳው አመራሮች በተገኙበት የእንኳን ደህና መጣችሁ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
የኢርጊኖ ወንዝ ለዘመናት ለመሎ ጋዳ ህዝብ "እሾማ ወርቅ" ሆኖ ያለጥቅሙ ጉዳቱ አመዝኖ የበርካቶችን ህይወት ቀጥፎ አብዛኛውን የጋዳን ነዋሪ ለፀፀት ዳርጎ ብዙ ተስፋዎች ሲያጨልም ቆይቷል።
በጋዳ ወረዳ፣ በዞን፣ በክልል እና በፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባደረጉት ቅንጅት የጉዳዩን አንገብጋቢነትና በየጊዜው በወንዙ ሙላት የከሰተውን የሞት አደጋ "ለሳሊኒ" አመራሮች በማስረዳት ጊዚያዊ የሰው መሻገሪያ በካቦ ገመድ የተወጠረ ፌሮ ብረት የተረበረበበት ተውረግራጊ ድልድይ በመሰራቱ ለጊዜውም ቢሆን ለህዝቡ እፎይታን ስቷል።
ድልድዩ በዋናነት የሚገነባው በደቡብ ክልል መንገዶች ባለስልጣት በኩል ሲሆን በኮትራክተሩ የአቅም ውስነትና ዳተኝነት፣ የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ክትትልና ቁጥጥር ማነስ ተጨምሮበት እንዲሁም የአካባቢው መልካምድር አቀማመጥ ፈታኝነት የተነሳ ተጀምሮ የወቆመው ኢርግኖ ወንዝ ድልድይ አሁንም ዋነኛ የህዝብ ቅሬታ ምንጭ መሆኑ ወንባ ከተማ ላይ በነበረው የህዝብ ምክክር መድረክ ላይ ተነስቷል።
የኢርጊኖን ወንዝ ተሻግረን ጉዞው ቀጥሎ አሊዛ ቀበሌ ሜላ ንዑስ እንዲሁም የጋዳ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ወንባ ከተማ ስንደርስ በሀገር ሽማግሌዋች እና በነዋሪዎች በድጋሜ የእንኳን ደና መጣቹህ አቀባበል ተደርጎለታል።
በመቀጠልም በወረዳው የህብረተሰብ ተሳትፎ ያለ አንዳች መንግስት በጀት የተከናወኑ የልማት ስራዎች በልዑካን ብድኑ የተጎበኙ ሲሆን የመሎ ጋዳ ወረዳ ህዝብ በዚህ ረገድ ለሌሎች የዞናችን መዋቅሮች ተሞክሮ የሚሆን በአርያነት ሊገለጽ የሚችል ተግባራትን ማከናወናቸው በጉብኝቱ ወቅት ተስተውሏል።
ለአብነት ለመግለጽ ያህል 108 ክፍል ያላቸውን የተለያዩ ሴክተር መስሪያቤቶች በመገንባት፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 5 የመማሪያ ብሎኮችን እና 16 ክፍል ያላቸው የመምህራን መኖሪያ ቤቶችን በህረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብተው አገልግሎት ላይ መሆናቸውን በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተመራው የልዑካን ቡድን ምልከታ አካሄዷል።
ወረዳው አዲስ ከመሆኑ አንፃር በርካታ ውስብስብ የመሰረተ ልማት ችግሮች ውስጥ ሆኖም በአጭር ጊዜ ያስመዘገበው ውጤት አበረታች በመሆኑ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ለህብረተሰቡ ከልብ የመነጨ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
ከልማት ስራዎች ጉብኝት ጎን ለጎን በአካባቢው የሚመረቱ ምርቶች የውጭ ምንዛሪ ሊያስገኙ የሚችሉ እና ገበያ ተኮር የሆኑ የፍራፍሬ፣ የአትክልት፣ የጥራጥሬ እና የስራስር ለአብነትም (የሙዝ፣ የብርቱካን፣ የአናናስ፣ የቡካዶ፣ የፓፓየ፣ የሎሚ፣ የማንጎ......የኦቾለኒ፣ የሰልጥ፣ የሩዙ፣ የቡና፣ የማሾ፣ የጅንጅብል፣ የኮረራማ...ወዘተ) ምርቶች ተጎብኝተዋል።
ከጉብኝት መልስ የህዝብ ውይይት እና ምክክር መድረክ የቀጠለ ሲሆን ውይይቱን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ፣ የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዞራ እና የመሎ ጋዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አበበ መርተውታል።
በውይይት መድረኩ ከሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች የተሳተፉበት ሲሆን በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃ ውይይቱ ተጀምሮ የልዑካን ቡድኑ በአካባቢው ልማት ጉዳይ ለመምከር ወደ መሎ ጋዳ ወረዳ መምጣቱን አመስግነው ከነዋሪዎች በርካታ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች እንደ መንገድ፣ ድልድይ፣ ውሃና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የመብረት፣ የባንክ፣ የቴሌኮም፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና የጤና ተቋም ግንባታ፣ የማዘጋጃቤታዊ ጥያቄዎች እና ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተዋል።
የመንገዱና የኢርጊኖ ወንዝ ድልድይ ግንባታ መጓተት ህብረተሰቡን እያማረረ ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች የህዝቡ ቅሬታ ዋነኛ ምንጭ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ በሚመለከታቸው የዞን ካቢኔ አባላት እና በመድረኩ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ህብረተሰቡ መንግስት ያለበትን የበጀት ውስንነት በመረዳት በሚልዮን የሚገመት የገንዘብ፣ የጉልበት እና የአይነት ድጋፍ በማድረግ 108 ክፍል ያላቸው የተለያዩ ቢሮዎች መገንባት በመቻላቸው፣ ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 5 ብሎኮችን እና 16 የመምህራንን መኖሪያ ቤቶችን መገንባት በመቻላችሁ የዞኑ ዋና አስተዳደር ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ለነዋሪዎች ላቅ ያለምስጋናና አክብሮት በመሰጠት ግንባር ቀደም የልማት አርበኛ በመሆናቹህ ኮርተንባችኋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህ መልካም ተግባር ለሌሎች ወረዳዎች ተሞክሮ የሚሆን ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በዚህ ወስብስብ ነባራዊ ሆኔታ ውስጥ ሆናችሁ ችግሮች ሳይበግሯችሁ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ያደረጋችሁት የደጀንነት ተግባር ጠንካራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን በተግባር አስመስክራቹሀል ብለዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አክለውም የተነሱ ጥያቄዎች ትክክለኛ እና አግባብነት ያላቸው የሚታወቁ መሆኑን ተናግረው የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶት ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አስረድተው የኢርጊኖ ወንዝ ድልድ ግንባታ መጓተትን አስመልክቶ የመጀመሪያው ኮንትራክተር በተያዘለት የጊዜ ገደብ ማከናዎን ባለመቻሉ ምክንያት ክልሉ ውሉን አቋርጦ ለሌላ ተቋራጭ መስጠቱን ተናግረው ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ መልክ እንደሚጀመር ተናግረዋል።
በዝህ በጀት አመት ለጋዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ የሚሆን 250,000 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በጀት የተያዘለት መሆኑን ጠቁመው ለቀጣይ አመት ለግንባታ ማስጀመሪያ የሚሆን 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ እንደሚደረግም ቃል ገብተዋል።
ዞኑ የወረዳውን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚያደርገው ጥረት እንዳለ ሆኖ እነዚህን የህዝብ ፍላጎቶች ከበጀት ውስንነት የተነሳ በተፈለገው ፍጥነት ማስኬድ እንዳልተቻለም ተጠቁሟል።
በመጨረሻም በዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ እና በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብረሃም ዞራ በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።
በመቀጠልም የጋዳ ጤና ጣቢያ ግንባታ ለ12 ተቋርጦ ከነበረበት በአዲስ መልክ ተጀምሮ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረሱን ጉብኝት ተካሄዶ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠቃሏል።
ታህሳስ 10/2014 ዓ.ም