Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
🔴AFF 2020 🔵
The sixth edition of the Addis Foto Fest open call is now accepting submissions!
We invite photographers, curators, and photography collectives to submit projects that could be exhibited during the next edition of the Addis Foto fest, which will take place in Addis Ababa, Ethiopia on December 3-7, 2020. Submit your work to our online application by visiting the festival website; www.addisfotofest.com
Addis Foto Fest is a biennial international photography festival, which has previously featured exhibitions, portfolio reviews, workshops, conference and an award ceremony. It is also the first and only international photography festival in East Africa. The Addis Foto Fest has been recognized as one of the biggest and leading photography festival in Africa.
For more information contact us
Email: addisfotofest@gmail.com
Phone: +251118681351
Pass on this information for photographers you know and admire.
GOOD LUCK!
#Addisfotofest #Destaforafrica #aff #AFF2020 #dfaplc #Photography #Ethiopia

◍ Episode Ⅰ Vol Ⅰ ◍
#Whataboutthem #weaving #ሽመና
#ግለታሪክ
ቦሻ ቦጋለ እባላለሁ የተወለድኩት በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ጨንቻ ወረዳ ውስጥ ነው። ያደኩት ደግሞ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ነው። የሽመና ሙያን የተማርኩት ከአባቴ ነው። ይሄን ሙያ ከ14 አመቴ እስከአሁን እየሰራሁት ነው የምገኘው። አሁን 25 አመቴ ላይ እገኛለሁ። ምንም እንኳን እንደ አብሮ አደጎቼ የተሻለ ገቢ የሚገኝበት የሙያ ዘርፍ ባይሆንም በምሰራው ስራ ደስተኛ ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን!
ይቀጥላል ...
#The Profile
My name is Bosha Bogale. I was born in Gamo zone Chencha area in the southern region. I was raised in Addis ababa around Shiro meda. My father was the one who thought me weaving skills. I am twenty five years old now. I have been weaving ever since I was fourteen. I am happy to have stayed in this proffession! Even if it is not a job sector you gain a lot of money from as my friends, I am happy by the work I do . Thanks God.
To be Continued
#hashtags
#እነእርሱስ #Whataboutthem #World #Africa #Ethiopia #Addisababa
@Mykeyonthestreet

▪Episode Ⅰ Vol Ⅱ▪
#Whataboutthem #weaving #ሽመና
#ፍሬሀሳብ
.
የሽመና ሙያ ጥንታዊ ሙያ ነው! እኛ ከአባቶቻችን ተምረን ለዚህ አድርሰነዋል እዚህ ሙያ ላይ አስቸጋሪ ነገር ብዬ የማስበው እና እኔንም ሆነ የስራ ባልደረቦቼን ደጋግሞ ተስፋ የሚያስቆርጠን ነገር ማህበረሰቡ ትኩረቱን ለነጋዴ እና ለዲዛይነሮች ብቻ መስጠቱ ነው! እኛ የምንሸምናቸውን ልብሶች ለምትወዷቸው ፣ ለምታከብሯቸው ፣ ለተለየ ቀናቹ እየለበሳቹ ለኛ ግን ለልብሶቹ የምትሰጧቸውን ትንሽ ክብር እንኳን አትሰጡንም...ለምን? እኛ ከሸመናቸው (ከሰራናቸው) ልብሶች አንሰን ነው? እውነት ፈጣሪውን ሳያከብሩ የተፈጠረውን ማክበር ልክነት ነው..?
ይቀጥላል....
.
.
.
#Thecore
.
The traditional weaving profession is an ancient one! We have learnt it from our fathers and they from their forefathers. What makes the job difficult and at times make you hopeless is that the society gives more value to designers and vendors! you love and value the garments we produce. you wear them on special days but you don't give us as much respect as what we produce. why? are we less than what we make?
To be Continued
.
.
#እነእርሱስ #Whataboutthem #World #Africa #Ethiopia #Addisababa #Mykey

▪Episode Ⅰ Vol Ⅲ▪
#Whataboutthem #weaving #ሽመና
#Theconclusion
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሽመና ሙያ ተደብቆ ነው ያለው ብዬ አምናለሁ፥ ለኛም ተገቢውን ነገር እየተደረገ ነው ብዬ አላስብም ፤ ማህበረሰብም ሆነ መንግስት በዚህ በኩል ችላ ብሎናል ከእኛ ላይ ገዝተው ለሚያተርፉት ነጋዴዎች የተመቻቸ ነገር ይደረጋል ። እንደ መፍትሄ ብዬ የማስቀምጠው ነገር ማህበረሰብም ሆነ መንግስትም ለሙያው ተገቢውን እውቅና ቢሰጥና ለምንሰራው ስራ ተገቢውን ክፍያ ብናገኝ የሽመና ሙያን አሁን ካለበት ሁኔታ ማዘመን እኛንም ደግሞ ከሞራል እና ከኢኮኖሚ አንፃር ከፍ ወደአለ ደረጃ የሚያሸጋግረን መፍትሄ ነው ብዬ አስባለሁ።
-አለቀ-
.
.
.
.
I believe currently the profession of weaving is is hidden. I also don't believe that the right things are done for us . The government and the society is reluctant towards us. More opportunities are provided for vendors who put our products on the market and profit from them. What I suggest as a solution is that the government and the society gives recognition the profession deserves.I believe its a way that can create modernized ways of production, boost morale for us raise our status economicaly and this is our history!
-The End-
.
.
.
#እነእርሱስ #Whataboutthem #World #Africa #Ethiopia

ጎዳናው ይገርማል?!
ጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ ~ #በረከት_በላይነህ
#ETHIOPIA | ይገርማል መንገዱ
እግረኛው ይገርማል
፧
ሸራ ጫማ ባ'ይነት
በነጫጭ ካልሲ
በሲኪኒ ሱሪ
ከመምህሩ ጋራ
አይስክሬም ሚልስ
የሀይስኩል ተማሪ
.
ፀባይኛ ወጣት
ጃንቦ ተከልሎ
በምርቃና ሆኖ
ሀሳብ የሚፈትል
አንዲት ሙ......ደኛ እናት
በ'ድሜ ከልጆቼ አንሳለው የምትል
ፒዛውን የሚገምጥ
ጭማቂ የሚመጥ
አራዳ አባወራ
በሚስቱ ትከሻ
በልጆቹ ምላስ
ቅምጥ የሚጣራ
.
አንድ ፍሬ ሴቶች
በተገዛ ቅንድብ
በተገዛ ፀጉር በተገዛ ጥፍር
በውሰት ወዘና የተብለጨለጩ
ማኪያቶ ከበው
ለውስኪ ሚንጫጩ
ጅናም ጅንሳም ወንዶች በሴቶች ጫጫታ የሚቁለጨለጩ
.
ይገርማል ጎዳናው ይገርማል መንገዱ....
.
ድንቡሽቡሽ ህፃናት
በቶም ኤንድ ጄሪ ሱስ
ቀልባቸው የከሳ
በአይፎኑ አጮልቆ
ያንጀሊናን ከንፈር የሚስም ጎረምሳ
.
ቀውጢ ዳያስፖራ
.
የሎቲው የቁምጣው የቲሸርቱ ጥለት የተንዘረፈፈው
አማርኛ ሲሸሽ "what's happen" የጠለፈው
.
ነቄ ብላቴና
.
ከዮፍታዬ ቀዬ
ካ'ዲስ አለማየሁ
ከመዝገቡ መንደር
የአዲስ አ'ባ ጥሪ
በቁምጣ ያበረረው
ከቅኔ ተጣልቶ
ከግዕዝ ተኳርፎ ሎተሪ ሚያዞረው
.
ፀዴ ብላቴና
.
ከባላገር ዘመን
ከጨለማ ዘመን
ወደ ብርሃን ጥግ ተሸጋገርኩ ብሎ
በሸንኮራ ምርኩዝ ከተማ ሚያካልል መቋሚያውን ጥሎ
ነብሱ እየሰለለች
በከተሜነት ወግ ባ'ራዳነት ልምሻ
ሲያዘግም የሚውል
ሊስትሮውን ጭኖ በታቦት ትከሻ
.
ፎቆቹ
.
በመስታወት ቁመት በቆርቆሮ ገፆች
ባ'ልሙኒየም ጥራዝ የተብረቀረቁ
የጌቶቻቸውን እድሜ ሚያሳብቁ
ሁሉም........ ሁሉም......ሁሉም ጥግ ናቸው
ለወደቀ ወገን ይራራል ልባቸው
.
ሁሉም
...... ሁሉም
.
ከዘለለት ጥድፊያ
ከሰርክ ውጣ ውረድ በተረፈች አንጀት
ለወደቀ ወገን ምርኩዝ ማበጃጀት
ሁሉም...... ሁሉም ይችላሉ
ስለ'ግዚአር ላለ ይመፀውታሉ
.
እኔ ግን........ እኔ ግን .........ቆጥራለው
የ'ድሜ ክቡር ጀንበር
በጎዳና ፅልመት ሲዋጥ አስተውላለው
ጡረታ መንገድ ዳር ሲከፈን አያለው
.
ቆጥራለው.....ቆጥራለው
.
ቆጥራለው አዛውንት
በየአቀበቱ በየቁልቁለቱ
ማረፊያ ፍለጋ የሚንከራተቱ
ቆጥራለው አዛውንት ከልጆቻቸው ፊት
የልመና መዝገብ የገለጡ አሮጊት
ቆጥራለው በየመንገዱ ዳር
እርጅና ሙሽራው ለምፅዋት ሲዳር
ቆጥራለው በየሸንተረሩ በየተፋሰሱ
አቀርቅሮ ሲያዘግም እርጅና ሞገሱ
ቆጥራለው በ'ያደባባዩ
የሽማግሌ አይኖች የልጅ ፊት እያዩ
ቆጥራለው በየሰርጣሰርጡ
በልመና ጉልበት ከሞት ሲፋጠጡ
የ'ርጅና መዳፎች እሾህ ሲጨብጡ
.
ቆጥሬ..... ቆጥሬ.......ቆጥሬ
በለማኝ አዛውንት ብዛት ተሳክሬ
የማሰንበቻ ስንቅ ከኪሴ ቆንጥሬ
ያፅድቆቴን ዋጋ በሳንቲም መንዝሬ
ባ'ዛውንት ምርቃት ከሀገር ከቀዬው ትርፌን ሳመሳስል
በጎዳናው ቀለም ፃድቅ መልኬን ስስል
ጎልቶ ሚታየኝ ግን የሚያሳፍር ምስል
በቀላል ጥያቄ የነተበ ምስል
.
ጥያቄ
.
የዲጄ ኳኳታ የደናሽ ጋጋታ
የድራፍት እርካታ ያ'ረቄ ድንፋታ
ባጣበበው መንገድ
እንደምን ይቻካል
ላ'ያት ሳንቲም ሰጥቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለወጣት ሹክሹክታ ለገደል ዝምታ
ላስመሳይ ጫጫታ ላድርባይ እሪታ
በተሰራ መንገድ
እውነት ቀላል ነው ወይ
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለቡቲክ ሰልፈኛ ለካፌ 'ድምተኛ
ለውስኪ ጭሰኛ ለበርገር ምርኮኛ
በተሰራ መንገድ
እንደምን ይቻላል
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
አያት....አያት...አያትነት ማለት
በደማቅ አሻራ የሸመኑት ጥለት
ለተራኪ እድሜ የተሰጠ አንደበት
ባ'ባት በ'ናት ፅናት የማይደክም ጉልበት
በልጅ ልጅ መነፅር የማያረጅ ውበት
በልጅ ልጆች ጥበብ የሚታደስ እውቀት
.....................................የሚታደስ እውነት
አያት ሆኑ ማለት
ድርብ አባትነት
ድርብ እናትነት
.
በተለይ እዚህማ.......
በዚህች አይነት ሀገር
ጎጆዋን ላቆመች
በተጋድሎ ካስማ
ባርበኝነት ማገር
በዚህች አይነት ሀገር
ጥያቄና መልሷን
ባ'ዛን በቅዳሴ በምትሰራ መንደር
በዱአ በፀሎት
በምናኔ ምርኩዝ በከረመች ሰፈር
የአያትነት ዋጋው በልኩ ቢሰፈር
ለሳንቲም ምርቃት ባልተሻማን ነበር!
.
ታሪክ በመዳፉ ስላደላደለው
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጉስ አያት አለው
የልጅ ልጆች ስባት ባያመነምነው
ያያቶቻችን መልክ ሁሌም አንድ አይነት ነው
.
እላለው... እላለው....
.
የልጆች ምፅዋት ያ'ያቶች ልመና
ያ'ባቶች ግርግር በሞላው ጎዳና
መንገዱ አይልቅም
ጎዳናው አያልቅም
ይሰፋል ይረዝማል ይሄዳል ይጓዛል
እግረኛው ሞኝ ነው
ሳንቲሙን ዘርዝሮ
ከወደቁ አዛውንት ምርቃት ይገዛል
.
መንገዱ ያስፈራል
መንገዱ ይጨንቃል
ልጆች ሳቅ ሲያንቃቸው
አያት እምባ ይጨምቃል
መንገዱ ያሰጋል መንገዱ ያረጃል
ከዘናጭ ልጆች ጎን እርዛት ያዘለ አያት ይወለዳል
.
ሰጪ ካለቀሰ ተበዳሪ ስቆ
ጌታ ከለመነ አማኙ 'ግር ወድቆ
ልዑል ከዘመረ ንጉሱ ተዋርዶ
ገፁ ተመሳቅሎ ሽፋኑ ካማረ
ወለሉ ተንቆ ምንጣፍ ከከበረ
ባ'ገርኛ ስሌት ማነው ያልከሰረ?
.
እላለው........እላለው
.
ከየጎዳናው ገፅ ጥያቄ አነሳለው
ጥያቄ እጥላለው
እርጅና ለማምሻው ጎዳናን ካመነ
አያት ከልጅ ልጁ ሳንቲም ከለመነ
ባገርኛ ስሌት ማነው ያልመከነ?
.
በ'ግዚኦታ ዘመን በምዕላ ዘመን
እመንገድ ዳር ወድቆ ትራፊ መለመን
በጥሞና ዘመን የሚያስቡት ማጣት
በማውረሻ እድሜ የሚሰጡት ማጣት
በማልበሻ ዘመን በ'ርዛት መቀጣት
በለጋሽነት ወቅት በማጉረሻ ዘመን
በጥማት መገረፍ በርሀብ መመንመን
ከሆነ እጣችን
ይጠየቅ ትርጉሙ የልጅነታችን
ይፈተሽ መንገዱ የልጅ ልጆቻችን
፧
ግድ የለም እንመን
፧
እንመን
፧
በሰውኛ ስሌት ውጤቱ ሲሰራ
ትውልድ ያደኸያል ያያቶች ኪሳራ
በልጅ ልጆች ዓለም
እንደጉድ ቢደለቅ ቢዘመር ቢዘፈን
አባት ይወራጫል ባ'ያቶች መታፈን
.
አባት ሆይ
.
ለልጆችህ ርዕዮት
ትላንቱን የረሳ ተስፋ ሲደራረት
ህልሜ ነው ይልሀል ያ'ያቶቹ ቅዠት
ከልጅህ አንደበት
ቋንቋ እንደዶፍ ቢዘንብ
ትርጉም ቢንፎለፎል ሺ ቃላት ቢጎርፍም
የልጅ ልጅ አግባቢ ግማሽ ገፅ አይፅፍም
ከልጆችህ ባህር
አሳ የሚያጠግቡ ለአሳ ሚስማሙ
እፅዋት ተክሎች
እንደጉድ ቢራቡ እንደጉድ ቢያብቡ
ገበታው አይሞላም ተቀዷል መረቡ
.
ግድ የለም እንመን........እንመን
.
የስኬት ክብደቱ
የምቾት አይነቱ
የነገ ውበቱ ባሻው ቋት ቢለካ
በምንም ቢሰፈር ባሻው ቃል ቢነገር
ጀግና ልጅ አትወልድም
አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር
.
ከፎቆቹ ጥላ....
ከያስፓልቱ ገላ ሲታተም ድምቀቴ
በመስታወት አጀብ ሲጠገን ጉልበቴ
ይኸው አነበብኩት
አያቶቼ ፊት ላይ ተፅፏል ሽንፈቴ
በመኪና ብዛት
በመስታወት አይነት ሲለካ ፍጥነቴ
በግንብ አጥር መአት
በፎቆች ጋጋታ ሲሰላ ስኬቴ
ይኸው ይታየኛል
አያቴ ገፅ ላይ ተስሏል ውድቀቴ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ተስሏል ሽንፈቴ!
***
@getem
@getem
#jeko

👍3
#ETHIOPIA | የሙያ ሠራተኛ ኖዎት ወይስ ተመርቀው ሥራ እየፈለጉ ነው?!
በየትኛውም የሥራ አይነት ላይ ተሰማርተው መሥራት ፍላጎት ያላቹ እና በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ ላይ የተመረቃችሁ (በቲቪኢቲ፣ በዲፕሎማ፣ በዲግሪ) አዲስ ምሩቅ ወይም የሥራ ልምድ ያለው
* አሁኑኑ ይመዝገቡ *
ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!
Download sira app
Use www.siraet.com
Telegram https://tttttt.me/siraapp

ላምላክህ - ላምላኬ!
#Ethiopia | ዘውድአለም ታደሰ
ጀሊሉ ይዳብስህ - ይበርቱ ክንዶችህ
የማርያም ልጅ ደርሶ - ያቁምህ በእግሮችህ!
እግዜር በሽታህን - ይንቀለው ከገላህ
ፈውስ ያውርድልህ - የታመንከው አላህ!
ያደከመህ ይድከም - ይራገፍ በሽታህ
በገጽህ ላይ ይፍሰስ - ይመለስ ፈገግታህ!
ታሞ ተኛ ሲሉኝ - ላፍታ ተንበርክኬ
እንዲህ ነው የጸለይኩ - ላምላክህ ላምላኬ!!
----------
@getem
@getem
@beckyalexander
#Ethiopia | ዘውድአለም ታደሰ
ጀሊሉ ይዳብስህ - ይበርቱ ክንዶችህ
የማርያም ልጅ ደርሶ - ያቁምህ በእግሮችህ!
እግዜር በሽታህን - ይንቀለው ከገላህ
ፈውስ ያውርድልህ - የታመንከው አላህ!
ያደከመህ ይድከም - ይራገፍ በሽታህ
በገጽህ ላይ ይፍሰስ - ይመለስ ፈገግታህ!
ታሞ ተኛ ሲሉኝ - ላፍታ ተንበርክኬ
እንዲህ ነው የጸለይኩ - ላምላክህ ላምላኬ!!
----------
@getem
@getem
@beckyalexander
❤1🎉1