ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
‹‹ጠ›› እና ‹‹ፀ››
Demeke Kebede

ታገሬ ወጥቼ - ከተማ ገብቼ
ገድ ቀናኝና - ካንቺ ተዋድጄ
አልችል ብል ልለምደው - የከተማን ኑሮ
በአነጋገሬ ላይ - አሰማሽ እሮሮ፤
‹‹ፀሐይ›› አልኩ ብዬ - ‹‹ጠሀይ›› በማለቴ
‹‹ፀጉር›› ልል ፈልጌ - ‹‹ጠጉር›› የሚልን ቃል - ከአፌ በማውጣቴ
ተበሳጨሽና - ቁጣ አዘነብሽብኝ
በ‹‹አድርግ››ና ‹‹አታድርግ›› - ግማሽ ቀን ዋልሽብኝ፤
‹‹ ‹ፀ› ማለት ሲገባህ - ‹ጠ›ን አትጥራ ሁሌ - ዳግም እንዳልሰማ
እንዳታዋርደኝ - እንዳታስፎግረኝ - በነቃ ከተማ
በቃህ አቁም በቃ - ዘወትር ‹ጠ› አትበል
‹ጠሎት›ንም ‹ፀሎት› - ‹ጠሀይ›ን ‹ፀሐይ› በል!››

ትዕዛዝሽን ላከብር - ምን ብጠነቀቅም
‹‹ጠ››ን በ‹‹ፀ›› ተክቼ - ተናግሬ አላውቅም፤
ይህን አየሽና…
‹‹ይቅር እንለያይ - በአንተ አልፈር እኔ
ከብጤህ ተዛመድ - አቻ ሽቷል ጎኔ!››
ብለሽ ተለየሽኝ - ያላንዳች ይሉኝታ
ባላወቅሁት ‹‹ቅጥበት›› - ባልገመትኩት አፍታ፤
ሳስበው አመመኝ…
ሰበብሽ ያበግናል - ያጨሳል፣ ያደብናል
ሰው እንዴት በቋንቋ - ፍቅርን ይመዝናል?

ታዲያ ምኔ ዋዛ - ምኔ ሞኝ ነውና
እኔም በተራዬ - እንተከተክ ጀመር - ‹‹ፀ››ን ተካሁኝና
ይኸው ይኸውና …
‹ፅፍራም› ነሽ፣ ‹ገፃፃ› - ፍቅር የማይገባሽ
‹ፀብ› እንጅ መዋደድ - ‹ፄና› የሚነሳሽ
እስኪ አሁን በሞቴ
ምኑ ነው ‹ፅፋቴ›?
በ‹ፀራራ› ፀሐይ - ‹ወክ› እናድርግ ማለቴ?
‹ፀርሙስ› ሙሉ ቢራ - በቀን ‹መፀፃቴ›?
በ‹ፀፀር› ጎዳና - ‹ፀጅ› ይዤ ‹መውፃቴ›?
ነው ወይስ ኮብልዬ - ከ‹ገፀር› ‹መምፃቴ›?
በያ ንገሪኛ
ምኑ ነው እሚያሳፍር - ይህ የኔ አማርኛ?
እኔ ግን ልንገርሽ?
በ‹ፀበልም› ባልድን - ባይለቀኝም ፍቅርሽ
አብሮ መውፃት መግባት - ሰርክ ካሳፈረሽ
ወይ ካሸማቀቀሽ
ከእኔ ጋር መታየት - ከሰው ካሳነሰሽ
ያውልሸ ጎዳናው - ሂጅ ወደፈለገሽ
‹ቢፄ›የን አላፃም
‹ፀብራራ›ው ‹ገፀሬ› - ‹ፃፃ› አለኝ መሰለሽ!!
@getem
@getem
#jeko
ዛሬ ታላቁ ልብ የተወለደበት ቀን ነዉ
ጥር 6 1811
እኔ አባትህ...
ከዘፍጥረቴ ስጀምር
ከጦቢያዬ አብራክ ስወጣ
ከአፈሯ እሸት ቀምሼ
ከምንጯ ውሃ ስጠጣ
ብትኑን ሰብስቤ ይዤ
የሩቁን ባንድ ጠቅልዬ
"ይማሯል እንደ አካልዬ
ይዋጓል እንደ ገብርዬ"
ብዬ
ዝመናን ጋፋት ላይ ጥጀው
ልብ ላይ እድገትን ስዬ
እኔ አባትህ...
የታጠቅ የጦሩ ጌታ
ላገሩ ተጓዥ አውታታ
እውቀትን አጭቶ ያገባ
በጃኖ በነጩ ኩታ
ለእድገት እሰየሁ እንጂ
ለውድቀት ጦር የማልፈታ
እኔ አባትህ...
ዝንት ዓለም የማስበውን
ከዘመን በፊት ጀምሬው
የእውቀት ብልጭታ ገመዱን
ከዙፊል ውሃ ነክሬው
እውቀት ይበጃል ብየ
ላገር ለወገን ነግሬው
አንድነትን ከፍ ለማድረግ
ትንፋሼን ላገር ገብሬዉ
እኔ አባትህ...
ያባት ያያቴ ታሪክ
መክሰሙ ያንገበገበኝ
የድንቁርና ጋሬጣ
ከእርምጃየ ያልበገረኝ
መድፉን ሰርቼ ያልጠገብኩ
መርከቡም ያላስቸገረኝ
አድምጠኝ ልጄ ልንገርህ
አጤ ቴዎድሮስ እኔ ነኝ
በል ተነስ ቁጭ ካልክበት
መቅረዙን ያዘው በእጆችህ
መማር ነው ትልቅ ብርሓን
ጨለማ ይራቅ ከደጅህ
ካባትህ የወረስከውን
አቀብል ለልጅ ልጆችህ
ውል ሳትይዝ ሙግት ላትገጥም
'ሀ' ሳትል ፊደል ላትጠራ
እውቀትን ታጥቀህ ተነሳ
እሱ ነው ደምቆ የሚያበራ
በታሪክ ትልቁ ዶሴ
ሀገር የሚጠራበት
ካለፉት እየቀሰመ
እውነቱን የሚረዳበት
ዛሬውን አፅንቶ አቁሞ
ነገውን የሚቀርፅበት
ቴዎድሮስ ከሚሉት መቅረዝ
ሶሎሞን ሳህለ
@getem
@getem
#jeko
ላልቅስበት
[ ቴዎድሮስ ካሳሁን_ቴዲ አፍሮ]

በነገር ፍም እሳት እያቃጠላቹ
ለማዘኔ ምክንያት እናንተው ሆናቹ
አታልቅስ አትበሉኝ ከፍቶኝ እያያቹ

ሁሉም እየጫረ እሳት ሲለኩሰው
ሻማ እንኳን ያነባል እንባ አውጥቶ እንደሰው!!
@getem
@getem
#jeko
(በላይ በቀለ ወያ)


በተራበው ጎኔ፣ በተጎዳው ኪሴ
እኔም ሰው ነኝና፣
የከንፈር ወዳጄን ተጠምታብኝ ነበሴ
የጥምቀት ለት ሎሚ፣
ኪሴን በሚጎዳ በሚነርት ዋጋ
ይሁን ብየ ገዛሁ፣
ደረቷን ልመታ የዛችን ውብ ሸጋ።

ሎሚውን በእጄ ያዝኩ
ኮረዳዋን ፈለግኩ
ባ'ይኖቼ አማተርኩ

ከኋላዋ አየኋት...
ፀጉሯ ሹሩባ ነው፣ ፊቷ አይታይም
ኋላዋ ካማረ...
ፊቷ ምንም ይሁን እኔን አይጨንቀኝም

ዳሌዋ... ቢዮንሴን ያስንቃል
በንቅልፍ የቧዘዘን አጣድፎ ያነቃል
ስንት የወጣባትን፣
የኛን ሳተላይት ከቻይና ያመጥቃል (አንጥሮ😂)

ወገቧ... አካበድክ ባትሉኝ
ከቀጭኗ እግሬ ሚወፍር አይመስለኝ

ወይኔ ሹሩባዋ
ለመግለፅም እንኳን አንደበትን ያስራል
በቆሙበት መሬት አፍዞ ያስቀራል።

ወደራሴ መጣሁ...
ልወርውር አልወርውር?
ልወርውር አልወርውር?

ወረወርኩ...
ድምም... እዛው ዳሌዋ ላይ
አሟት ዩን ደስ ብሏት ዞር ብላ ብታይ
የኔ ልብ ደንግጣ ልትበር ወደ ሰማይ

እየሮጠች መጣች፣
እያነፈነፈች ትንፋሿ እስከሚያጥራት
ክፉ አስባ ይሆን ልሩጥ ልጠብቃት?

ደረሰች...
ፊቴ ከመድረሷ፣
አንድ ጊዜ በጥፊ አወላመመችኝ
ወደላይ ወደታች፣
መላ ሰውነቴን በደምብ ቃኘችኝ
ወደግራ ጆሮየ በጣም ተጠጋችኝ

ጊዜው የድንጋይ ነው ሎሚ አታባክን
ኪስህን አሟጠህ፣
በገዛኸው ሎሚ ፈፅሞ አትጨክን
አሁን ሳናቅማማ ቶሎ እንሽጠው
ይሄ ውድ ሎሚ፣
ላ'ዲሱ ጎጇችን ትልቅ መሰረት ነው
ብላ አቀፈችኝ
እሰየው ዘንድሮ ለኔም ተሳካልኝ።

@getem
@getem
#jeko
((ፍትህ ሞተች አሉ))

መቸም አዛኝ የላት
መቸም ወዳጅ የላት
ደረት እየደቃ
ዋይ ዋይ ብሎ ሚያለቅስ፤ እንባ ሚያፈስላት።

ወዳጅ ዘመድ ሲሞት፤ ካንጀት ያለቀሰው
ፍትህ ሞተች ሲባል፤እንባ እንዴት ቸገረው።

ደስየ ደምሌ
@getem
@getem
#jeko
ነግሬሽ ነበረ !
(በላይ በቀለ ወያ)

ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን ያስደምማል
ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል
ነግሬሽ ነበረ፡፡
ሰማይ ሚያህል ጭንሽ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል
ምን ተራራ ቢያህል...
ጡትሽ አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም፡፡
ነግሬሽ ነበረ
የናትነት ስሟ ፣
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ፡፡
ነግሬሽ ነበረ
አትስደበኝ እያልሽ ፣ የነገርኩሽ ሁሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመስላሉ፡፡
@getem
@getem
#jeko
አዎ እኔ ደህና ነኝ
============
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ብቻ ዝም ብሎ እራሴን ያመኛል
የወገኔ ስቃይ፣
አንቅልፍ እየነሳ ይቀሰቅሰኛል!
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ሽብር አናውዞታል የልቤን ከተማ
ሰው በሞተ ቁጠር፣
ደረት እየደቃሁ አበራለሁ ሻማ!
አዎ እኔ ደህናነኝ፣
እብደት ተጠግቶኝ ዝም ብዬ ስቃለሁ
ሀገሬ ቁጭ ብዬ፣
ልክ እንደ ባይተዋር ሀገር ናፍቃለሁ!
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ወገኔ ባልኩት ሰው ዘመኔን ምጉላላ
ሆዴን እየራበው፣
በቀን ሀያ ግዜ መከራ ምበላ!
እናም፣
ሀዘን አሰቃይቶኝ ልቤ እየበገነ
አሁን ያልኩት ነገር ደህንነት ከሆነ
አዎ እኔ ደህና ነኝ!

©እዮብ ዘ ማርያም
@getem
@getem
#jeko
እናፍቅሻለሁ ! !
(በ ሰለሞን ሳህለ)
.
ልንገርሽ አይደለ
ከፍ ካለው ቦታ ከፍ ብዬ ቁሜያለሁ
ሰው ያለ አይመሥለኝም ባንቺ ቆርቤያለሁ
አሁንም አሁንም እናፍቅሻለሁ...
ሥላንቺ ከሆነ፣ ብርቱ ነኝ ኃያል ነኝ!
የሸረኞች ደባ፣ የተፈጥሮ እንቅፋት ችሎ እማያቆመኝ
ሐብሌ አይደለሽም አንገቴ ላይ የዋልሽ
ቀለበቴም ሳትሆኝ ጣቴ ላይ ያኖርኩሽ
ዕድሜ የማይፍቀው ንቅሳቴ አንቺ ነሽ!...
ያንተው ነኝ ብለሽኝ
የራስሽ ነኝ ብዬ...
እንዴት አልናፍቅሽ ናፍቆት አበባዬ?
መናፈቅስ በእርሱ - በእርሱ ያምርበታል፣
ተብሎ እሥከሚወራ
ተብሎ እሥከሚነገር
እናፍቅሻለሁ አንቺ የኔ ፍቅር!...
...
እንኳን ከኔ ጠፍተሽ...እንኳን ከኔ እርቀሽ
አጠገቤም ሆነሽ ትናፍቂኛለሽ...
የመዋደድ ኬላ መድረሻ ደንበሩ
መናፈቅ እኮ ነው የፍቅር ደም ሥሩ
አለሽ ጨረቃ ላይ
አለሽ ፀሐይዋ ላይ
አለሽ ሰማዩ ላይ
የትም አይሻለሁ የኔ ሙሉ ክፋይ
ተራራው አንቺ ነሽ
ባሕር ወንዙ አንቺ ነሽ
አገር ምድሩ አንቺ ነሽ
የትም ቦታ ሆኜ የትም ቦታ ሆነሽ
እናፍቅሻለሁ ትናፍቂኛለሽ...
...
ርዕሰ አንቀጽ ሠበር ዜና አንቺ ነሽ
ትረካዬ አንቺ ነሽ
ገሃድ ሕልሜ አንቺ ነሽ
ልብ ወለዴ አንቺ ነሽ
ቲያትሬ አንቺ ነሽ
ሰኞና ማክሰኞ ሮብ ሐሙሴ ነሽ
ዓርብ ቅዳሜ ነሽ
እለተ ሰንበቴ ሁሌ ምሳለምሽ
ማረፍያዬ እሁድ ነሽ
የትም ቦታ ሆኜ የትም ቦታ ሆነሽ
እናፍቅሻለሁ ትናፍቂኛለሽ ! ! !
@getem
@getem
#jeko
'ከሽፍታ' የተሰረቀች ግጥም
(በረከት በላይነህ)

-----------
ገና!
ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤
ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ።

በዳዴ ዘመኔም፣
በ'ወፌ ቆመችም!'፤
አውዴ ክፉ ነበር ለወሬ አይመችም።

እንደ ሚዳቋ ነፍስ እንደ ነብር ጥፍር፤
ስጋትም- ጭካኔም-ነበር የዕውቀቴ ስር፣
"ተጨቆንኩ!"
"ተበደልኩ!"
"ተረገጥኩ!"
"ተገፋሁ!"
"ተቀማሁ!"።
መሬቱ ጠላቴ፤
ሰማዩ ብሶቴ።

ተስፋ ትዝታዬን ሊያጠፋ ለቃቅሞ፤
ባፈሙዝ ያየኛል ገዳይ ደጅ ቆሞ።

ወዘተ...
በእነዚህ 'ምግቦች' አድጎ ሰውነቴ፤
እኮ እንደምን አይሆን 'ጥርጣሬ' ሀብቴ?
መገርሰስ፣ መደምሰስ፣ ማሳደድ-ውበቴ?
ስለዚህ አይድነቅህ!
ቀርበህ ወደድከኝም፣ ርቀህ ጠላኸኝም፤
ገድዬህ ካላለፍኩ የኖርኩ አይመስለኝም።
@getem
@getem
#jeko
ከእናቴ ያስተረፍኩትን
ደብቄዉ የምኖር
ስስታም ነበርኩኝ
ለእዉነተኛ ፍቅር

መጣሽ
አገኘሁሽ
ከሰሰትኩት ጋራ
የደበኩትንም የናቴን ሰጠሁሽ

ይሄዉ አደራየ
ማተብ ነዉ አጥልቂዉ
የራሱ መልስ አለዉ
ፍቅርን ጠይቂዉ
የኔን ባትችይ እንኳ
የእናቴን ጠብቂዉ

ሶሎሞን ሳህለ
@getem
@getem
#jeko
የውጊያ ስልት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሙሴ በበትሩ
ፈርኦን በጦሩ
ኤርትራ ባሕር ላይ ፣ ጦርነት ጀመሩ፡፡
።።።።
ሙሴ በበትሩ…
ግዙፍ ባህር ከፍሎ ፣ ህዝቡን አሻገረ
ፈርኦን በጦሩ
ከነ ወታደሩ
ባሕር ሰጥሞ ቀረ፡፡
።።፣፣
ውጊያ የማይችል ሕዝብ
ግዙፍ ባሕር ከፍሎ ፣ በተዓምር ሲሻገር
ሌላ የውጊያ ስልት
ቀይሮ ይመጣል ፣ ቢሰምጥም ወታደር፡፡






የተሻገረ ህዝብ
ለቀሪ መንገዱ
አሳ እያጠመደ ፣ ከባህር ሲያወጣ
የፈርኦን ወታደር
ሞቶ ለመዋጋት
በአሳ ገላ ላይ ፣ እሾህ ሆኖ መጣ!!!
።።።።
።።።፣
"አሳን መብላት
እንዳይወጋህ ፣ በብልሃት!"
@getem
@getem
#jeko
1
እየሔዱ መጠበቅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
‹‹እየሄድክ ጠብቀኝ›› - ስትይኝ ሄጃለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ….
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ…
አክሱምን እንዳየሽ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ጠራቢው እኔ ነኝ!
ያለፍኩት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ሰማይ ጠቀስ ሐውልት - የተፈለፈለ፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
አክሱም ሐውልት ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ጥበብ አለ!!
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ላሊበላን አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ፈልፋዩ እኔ ነኝ፤…
ያለፍሁት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ህንፃ ቤተ-መቅደስ ፤ የተፈለፈለ፡፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
በላሊበላ ውስጥ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ፅናት አለ፡፡
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ትክል ድንጋይ አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
የኔው መቃብር ነው!
ውድቀቴም እዛው ነው! ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ባባራ ዘመኑ፤
የራሱን መቃብር - ለመትከል የቻለ፤
መኖር የሚመስል - መሞትም ያይደለ፤
በጢያ ድንጋይ ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ውድቀት አለ፡፡
ከውድቀቴ ኃላ - ባይንሽ የምታዪው፤
ታምር የሚመስል - ታሪክ የምትይው፤
ምልክት የሚሆን - መንገድ ስላልተውኩኝ፤
ከመሞቴ በፊት..
ውድቀቴን፤
ሽንፈቴን፤
ከመቃብሬ ላይ - እንዲህ ብዬ ፃፍሁኝ፡፡
ሩጫዬን ጨረስኩ፤
ሰው ነኝ - ተሸነፍኩ!!!
እናምልሽ ውዴ….
‹‹እየሔድህ ጠብቀኝ›› - ያልሽው ቃል ስህተት
ነው፤
ቃሉም ገብቶሽ እንደው…
መራመድ መሄድ ነው፤
መሮጥም መሄድ ነው፤
መብረርም መሄድ ነው፤
አንቺ እንድትደርሺብኝ …
እኔ እየሞትሁ - እጠብቅሻለው!!!
****************
@getem
@getem
#jeko
ማህሌተ ገንቦ
(በእውቀቱ ስዩም)

"ባጭር ቀረን" ስንል ፣ እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
።።።
ፊታችንን ዐይተው እንደተቸገርን ፣
ካይናችን ላወቁ
"ስለማርያም" ብለን
እስክንለምናቸው ፣ ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
።።።
ወድቀው ለማይጥሉ ፣
ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ
ቺርስ!!!!
።።፣
ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን ፣ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ ስጋ ለበስ ትንግርት ፣ ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
@getem
@getem
#jeko
2
ላንቺ ስል...
(በላይ በቀለ ወያ)


<<እንጀራ እወዳለሁ >> ፥ ስትዪኝ ሰምቼ
አንቺን ደስ እንዲልሽ ፥ አብሲቱን ጠጥቼ
ሞቼልሽ ነበረ ፥ ኩፍታ አብዝቼ😂
ደግሞ እንደገና…
<<ማፍቀር መታደል ነው>> ፥ ስትይ ሰማሁና
አንቺን እረስቼ ፤ ሌላ አፈቀርኩልሽ
ምን ማልሆነው አለ ፥ አንቺን ደስ እንዲልሽ?!😂
።።።
@getem
@getem
#jeko
እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ብትደላም ብትከፋም
ምላስ ናት ለህዝቧ ፣ ከአፋችን አትጠፋም።
።።።
አፍ በሚባል ዋሻ...
ምላስን የሚያህል ፣ ስጋ ተሸክሞ
ስጋ ባለመብላት ፣ ማንስ ያውቃል ፆሞ?!
:::::::::
ፍስክ ምላስሽን ፣ ባፍሽ ተሸክመሽ
ከዋናው የደም ምንጭ ፣ ልቤ ላይ ታትመሽ
ፆመኛ ነኝ ስትይ ፣ ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ወደ ነፍሴ ገዳም ፣ ስትገቢ መንነሽ
ዓለም በቃኝ ስትይ ፣ የኔው ዓለም ሆነሽ
ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
መልካም የፆም ወቅት !!!
(በላይ በቀለ ወያ )
@getem
@getem
#jeko
👍1
አገርና አድዋ!
ወይራና ግራዋ!
(ደመቀ ከበደ - አድዋ ድልድይ፤ አዲስ አበባ)

...

እንደሆነው ቀርቶ - እንዳልሆነው አርገው
ቀጥቅጠው፣ በጥብጠው - ቀይጠው ከጠጡት
ታሪክ ግራዋ ነው - ከትናጋ አይወርድም - አይችሉም ሊውጡት፤
የሆነውን አምነው - ያልሆነውን ትተው
መርገው ሳይሆን ፈልጠው
ጠርበው ሳይሆን ጓጉጠው - ታዛ ካስደገፉት
ታሪክ ወይራ እንጨት ነው
ዘመንና አገርን - ከህዝብ ጎጆ ጋር
ሽህ ዕድሜ ያኖራል - የቤት ምሶሶ ነው - አይችሉም ሊጥሉት፤
አድዋም እንዲያ ነው - ግራዋና ወይራ
ድልና ሽንፈት ነው - ጣፋጭ ከመራራ፡፡

* * * * *

ተቀበል አዝማሪ…

‹‹እንዴው ዘ ራ ፌ ዋ…
ያልተፃፈ አንባቢ - በሞላበት አገር
ታሪክ ያበላሻል - ታሪክን መናገር፤››

ይህንን አዝማሪ…

በል ግጠም ይለዋል - የዚህ ዘመን ግጥም
ከቶ እንዴት ይቀበል - ታሪክ ሳያጣጥም?!
(ከማራራቅ ተምኔት - ከዘር አቡጊዳ
እንደ ህያው ጥበብ - ጥላቻ ሲቀዳ
በል ያለው ጊዜ ነው - የሆነው ባለዕዳ!)

*
* * * *

አዝማሪ ቀጠለ…

‹‹ነይ ነይ ዘ መ ድ ዬ…
እልፎች አንድ ሆነው - በሞቱበት አገር
ይኸው ነውር ሆኗል - ታሪክን መናገር፤››

ይህንን አዝማሪ..
የሄደ፣ የመጣ - ‹‹ታሪክ›› ተናጋሪ - ሀተታ መንዛሪ
ከአገር ታሪክ ላይ - የጎጥ አፅምና - አጥንት ዘርዛሪ
ድንገት አመሻሽ ላይ - ጠጪ እንደደከመ - ሰው እንደዛለ አይቶ
በል ይለው ጀመረ - ከህዝቦች ታሪክ ላይ - ግለሰብ ለይቶ፤

ይህንን እያየሁ
እኔ እንዲህ እላለሁ፤

‹‹ምኔ ነው አድዋ?
ምኔ ነው ሶሎዳ?
ምኔ ነው ምኒልክ?
ምኔ ናት ጣይቱ?
ምኔ ነው አሉላ?
ምኔ ነው ዲነግዴ?
ምኔ ነው ጎበና?
ምኔ ነው ገበየሁ?
ምንድኔስ ነው ባልቻ?
ለሚል ጥያቄያችሁ - በታሪክ ስልቻ
አንድ ነው ምላሹ - ሽህ ጊዜ አንድ ብቻ!!

ምክንያት፤
ግራዋ ነው ሲባል - ቅጠሉ መራራ
በታሪኩ ኮርቶ - ታሪክ ለሚሰራ
አድዋ ባላ ነው - ትልቅ የአገር ወይራ!!

* * * * ***

በል አሁን ተቀበል - በል አዚም አዝማሪ
ታሪክ አይበርዝም - ድሮም ታሪክ ሰሪ፤

‹‹እንዴው ዘ ራ ፌ ዋ…
አድዋና ወይራ - ከፍ ካሉ በአገር፣
ከታሪክ በላይ ነው - ታሪክን መዘከር - ታሪክን መናገር!!››

2008 ዓ.ም
@getem
@getem
#jeko
👍2
ሀገሩን በሙሉ ፥ ጨለማ ሲወርሰው
እድሜ ለአንቺ ፍቅር
መብራት ጠፋ ብዬ ፥ አልጮህም እንደሰው።
ወድሃለሁ ስትይ
ብርሀን ያፈልቃል ፣ ነዝሮት ሰውነቴ
አለም ይታየኛል ፣ እንኳን ጠባብ ቤቴ😂

(በላይ በቀለ ወያ)
@getem
@getem
#jeko
1
አድዋ በሎሬት ጸጋዬ ብዕር##
ዋ! አድዋ
«አድዋ ሩቋ፣ የአድማስ ምሰሶ አለት ጥጓ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳሷ:
አድዋ! በአንቺ ብቻ ህልውና፣
በትዝታሽ ብጽእና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ! አድዋ!
የዘር አጽመ ርስቷ:
የደም ትበያ መቀነቷ
የኩሩ ትውልድ ቅርሷ
የኢትዮጵያዊነት ምስክሯ
አድዋ!
ከሞት የባርነት ስርዓት
በደም ለነጻነት ስለት
አበው የተሰውልሽ ዕለት
አድዋ !
የኩሩ ድል በአንቺ ጽዋ
ታድላ በመዘንበሏ
አጽምሽ በትንሳኤ ነፋስ
ደምሽ በነጻነት ህዋስ ሲቀሰቀስ
ትንሳኤዋ ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ ብርu፣ትር ሲል ጥሪዋ
ድው እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ ዋ!
አድዋ!…»
@getem
@getem
#jeko
👍1
ያባቴ እግሮች ይጥፉኝ እንዴ?!
(አሌክስ አብርሃም)

ኦ ሳንታ ማሪያ ሮማ
እመብርሃን የጥሊያኗ
ወዲያ ማዶ በሩቅ ሁና ወዲህ ነበር የፍቅር አይኗ !
እመብርሃን የትላንቷ
እመብርሃን የአሁኗ

የዲያቢሎስ ደንገጡሮች
ከደብርሽ ስር ሲማከሩ
ልጅሽን እንደሰቀሉ
በልብሱ እጣ እንደጣሉ
ጦቢያንም በቅኝ መስቀል
በክፋት ሊቸነክሩ
እጣ ክፍላቸው አድርገው
ርቃኗን ለዘር ሊያስቀሩ

አለሽ በሮማ ደብር ….ይታየኛል ጉልላቱ
ይታየኛል ከቃየሽ ስር የጎሊያድ ትእቢቱ
ሲግተለተል ሲዥመለመል ሲጎደራ ሰራዊቱ
ግራ ቀኝ …ግራ ቀኝ ….
ጀሌ ሰልፈኛ አለቃው
ደጅሽን የፋሽስት ጫማ …ምኞት ወጥሮት ሲደቃው
ሲንቀዠቀዥ ወደሲኦል ሲሰነቅ የቁም ሰደቃው
ከሚኒሊክ የሳት ደብር ካባ መላ ካባ ውቃው

ኦ ሳንታ ማሪያ ሮማ
ወዲህ በማደሪያ ደብርሽ
ያበሾች ጩኸት ሲሰማ
ሰላም ሲሉ ሲማከሩ
ባገሬው ልሳን በስምሽ
በማምላክ ክተት ሲጠሩ
ለአገራቸው ሰላም ብለው ልጅሽን በምነት ሲጠሩት
እነዚሁ እግሮች ናቸው ከደጅሽ በክብር የቆሙት!
ራ ሳ ቸ ው !
ሃቁንማ አላብይም ሳልንተራስ ከአክናዴ
ሌላ ሌላውን ብረሳ ያባቴ እግሮች ይጥፉኝ እንዴ ?!!

ከኩሬው የሰው ደም ጠልቀው
የጣፉት በሰው ገላ ላይ የሳሉት ብራና ፍቀው

የወኔ ኩራዝ ተለኩሶ ይነበብ ዛሬ ይውጣና
ሃቁንማ አላብይም ሳልንተራስ ከአክናዴ
ሌላ ሌላውን ብረሳ ያባቴ እግሮች ይጥፉኝ እንዴ ?!!
እንዴዴዴዴዴዴዴዴ!

ኦ ሳንታ ማሪያ ሮማ …..
ገደልነው ባሉት ሰውነት
ጨረስነው ባሉት አውደ ሰብ
ተመልከች በባዶ እግሩ ላይ
እንዲህም እውነት ሲከተብ
እንዲህም ሃቅ ሲነበብ !!
ይሄ ነው የ አ ባ ቴ እግር !

እነዚህ ፍርክርክ እግሮች
ያተሙት የታሪክ ዳና
ያኖሩት የእምነት እዳ
በየሜዳ ሸንተረሩ ነፃነትን ሲያፈነዳ
እንቢ ብለው እንቢ አስብለው ባርነትን የረገጡ
እንደዋላ በንፋስ ክንፍ ከተራራ አናት የወጡ

ኦ ሳንታማሪያ ሮማ
እመብርሃን የጥሊያኗ
እመብርሃን የትላንቷ
እመብርሃን የአሁኗ
ያባቴን እግር ተመልከች
ራሱ ነው !!
ሃቁንማ አላብይም ሳልንተራስ ከአክናዴ
ሌላ ሌላውን ብረሳ ያባቴ እግሮች ይጥፉኝ እንዴ !!

በየጢሻ በየሜዳው ስለኔ የተዋደቀ
እንዳልባሌ የፈሰሰ የግፍ ደሙ መች ደረቀ
ቀልድ ነው ዛሬ ማንነት ፌዝ ነው ለኛ ነብስን መክፈል
ወይስ ውስጡ አፅም የለም ያባቴ ቀብር ሲደፈን
ይቆፈራ አገር ምድሩ ይፍረስና ቁልል ክደት
ያኔ ከጫንቃችን በላይ ይሰማናል የደም ክብደት
ይጫነናል ያገር እውነት !

በስምሽ ስለአገሩ ተጠርቶ የተዋደቀ
በደሙ ዝናብ ያገር ዋርካ ....በልጁ ልብ ያፀደቀ
ትንታግ የብረት ዘንጎች
ወድቀውም የሚራመዱ
በረገጡበት ስንዝር መሬት
ቁልል ትእቢት የሚንዱ
በጨለማ ባርነት ላይ ኩራዝ ሁነው የሚነዱ !
ራሳቸው እኒሁ እግሮች !

ወጣት ሁኘ ብዘናጋ ሎሚ ተረከዝ ቢያማልለኝ
ምንም ይማይከልለው በልቤ አንድ እውነት አለኝ
ለአገሬ የሳት ቅጥር አድርገው የተከሏቸው
እናገራሁ ዘላለም እነዚህ ፅኑ እግሮች ናቸው !!
ሃቁንማ አላብይም ሳልንተራስ ከአክናዴ
ሌላ ሌላውን ብረሳ ያባቴ እግሮች ይጥፉኝ እንዴ? !!

እኔ ብክድ በየሜዳው ዳናቸው አሁንም አለ
የገለማ ባርነትን ቃል አውጥቶ እምቢ እያለ !
እ ም ቢ!!

ኦ ሳንታ ማሪያ ሮማ ….
ረግጦሽ የመጣን ጡልብ
የፅናት አክናድ አቅምሰው
ስምሽን እስከሚማፀን
በእምነት ያንበረከኩ
እነዚህ ሸካራ እግሮች ለዘላለም ይባረኩ !!
@getem
@getem
#jeko
ጎዳናው ይገርማል?!

ጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ ~ #በረከት_በላይነህ

#ETHIOPIA | ይገርማል መንገዱ
እግረኛው ይገርማል

ሸራ ጫማ ባ'ይነት
በነጫጭ ካልሲ
በሲኪኒ ሱሪ
ከመምህሩ ጋራ
አይስክሬም ሚልስ
የሀይስኩል ተማሪ
.
ፀባይኛ ወጣት
ጃንቦ ተከልሎ
በምርቃና ሆኖ
ሀሳብ የሚፈትል
አንዲት ሙ......ደኛ እናት
በ'ድሜ ከልጆቼ አንሳለው የምትል
ፒዛውን የሚገምጥ
ጭማቂ የሚመጥ
አራዳ አባወራ
በሚስቱ ትከሻ
በልጆቹ ምላስ
ቅምጥ የሚጣራ
.
አንድ ፍሬ ሴቶች
በተገዛ ቅንድብ
በተገዛ ፀጉር በተገዛ ጥፍር
በውሰት ወዘና የተብለጨለጩ
ማኪያቶ ከበው
ለውስኪ ሚንጫጩ
ጅናም ጅንሳም ወንዶች በሴቶች ጫጫታ የሚቁለጨለጩ
.
ይገርማል ጎዳናው ይገርማል መንገዱ....
.
ድንቡሽቡሽ ህፃናት
በቶም ኤንድ ጄሪ ሱስ
ቀልባቸው የከሳ
በአይፎኑ አጮልቆ
ያንጀሊናን ከንፈር የሚስም ጎረምሳ
.
ቀውጢ ዳያስፖራ
.
የሎቲው የቁምጣው የቲሸርቱ ጥለት የተንዘረፈፈው
አማርኛ ሲሸሽ "what's happen" የጠለፈው
.
ነቄ ብላቴና
.
ከዮፍታዬ ቀዬ
ካ'ዲስ አለማየሁ
ከመዝገቡ መንደር
የአዲስ አ'ባ ጥሪ
በቁምጣ ያበረረው
ከቅኔ ተጣልቶ
ከግዕዝ ተኳርፎ ሎተሪ ሚያዞረው
.
ፀዴ ብላቴና
.
ከባላገር ዘመን
ከጨለማ ዘመን
ወደ ብርሃን ጥግ ተሸጋገርኩ ብሎ
በሸንኮራ ምርኩዝ ከተማ ሚያካልል መቋሚያውን ጥሎ
ነብሱ እየሰለለች
በከተሜነት ወግ ባ'ራዳነት ልምሻ
ሲያዘግም የሚውል
ሊስትሮውን ጭኖ በታቦት ትከሻ
.
ፎቆቹ
.
በመስታወት ቁመት በቆርቆሮ ገፆች
ባ'ልሙኒየም ጥራዝ የተብረቀረቁ
የጌቶቻቸውን እድሜ ሚያሳብቁ
ሁሉም........ ሁሉም......ሁሉም ጥግ ናቸው
ለወደቀ ወገን ይራራል ልባቸው
.
ሁሉም
...... ሁሉም
.
ከዘለለት ጥድፊያ
ከሰርክ ውጣ ውረድ በተረፈች አንጀት
ለወደቀ ወገን ምርኩዝ ማበጃጀት
ሁሉም...... ሁሉም ይችላሉ
ስለ'ግዚአር ላለ ይመፀውታሉ
.
እኔ ግን........ እኔ ግን .........ቆጥራለው
የ'ድሜ ክቡር ጀንበር
በጎዳና ፅልመት ሲዋጥ አስተውላለው
ጡረታ መንገድ ዳር ሲከፈን አያለው
.
ቆጥራለው.....ቆጥራለው
.
ቆጥራለው አዛውንት
በየአቀበቱ በየቁልቁለቱ
ማረፊያ ፍለጋ የሚንከራተቱ
ቆጥራለው አዛውንት ከልጆቻቸው ፊት
የልመና መዝገብ የገለጡ አሮጊት
ቆጥራለው በየመንገዱ ዳር
እርጅና ሙሽራው ለምፅዋት ሲዳር
ቆጥራለው በየሸንተረሩ በየተፋሰሱ
አቀርቅሮ ሲያዘግም እርጅና ሞገሱ
ቆጥራለው በ'ያደባባዩ
የሽማግሌ አይኖች የልጅ ፊት እያዩ
ቆጥራለው በየሰርጣሰርጡ
በልመና ጉልበት ከሞት ሲፋጠጡ
የ'ርጅና መዳፎች እሾህ ሲጨብጡ
.
ቆጥሬ..... ቆጥሬ.......ቆጥሬ
በለማኝ አዛውንት ብዛት ተሳክሬ
የማሰንበቻ ስንቅ ከኪሴ ቆንጥሬ
ያፅድቆቴን ዋጋ በሳንቲም መንዝሬ
ባ'ዛውንት ምርቃት ከሀገር ከቀዬው ትርፌን ሳመሳስል
በጎዳናው ቀለም ፃድቅ መልኬን ስስል
ጎልቶ ሚታየኝ ግን የሚያሳፍር ምስል
በቀላል ጥያቄ የነተበ ምስል
.
ጥያቄ
.
የዲጄ ኳኳታ የደናሽ ጋጋታ
የድራፍት እርካታ ያ'ረቄ ድንፋታ
ባጣበበው መንገድ
እንደምን ይቻካል
ላ'ያት ሳንቲም ሰጥቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለወጣት ሹክሹክታ ለገደል ዝምታ
ላስመሳይ ጫጫታ ላድርባይ እሪታ
በተሰራ መንገድ
እውነት ቀላል ነው ወይ
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለቡቲክ ሰልፈኛ ለካፌ 'ድምተኛ
ለውስኪ ጭሰኛ ለበርገር ምርኮኛ
በተሰራ መንገድ
እንደምን ይቻላል
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
አያት....አያት...አያትነት ማለት
በደማቅ አሻራ የሸመኑት ጥለት
ለተራኪ እድሜ የተሰጠ አንደበት
ባ'ባት በ'ናት ፅናት የማይደክም ጉልበት
በልጅ ልጅ መነፅር የማያረጅ ውበት
በልጅ ልጆች ጥበብ የሚታደስ እውቀት
.....................................የሚታደስ እውነት
አያት ሆኑ ማለት
ድርብ አባትነት
ድርብ እናትነት
.
በተለይ እዚህማ.......
በዚህች አይነት ሀገር
ጎጆዋን ላቆመች
በተጋድሎ ካስማ
ባርበኝነት ማገር
በዚህች አይነት ሀገር
ጥያቄና መልሷን
ባ'ዛን በቅዳሴ በምትሰራ መንደር
በዱአ በፀሎት
በምናኔ ምርኩዝ በከረመች ሰፈር
የአያትነት ዋጋው በልኩ ቢሰፈር
ለሳንቲም ምርቃት ባልተሻማን ነበር!
.
ታሪክ በመዳፉ ስላደላደለው
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጉስ አያት አለው
የልጅ ልጆች ስባት ባያመነምነው
ያያቶቻችን መልክ ሁሌም አንድ አይነት ነው
.
እላለው... እላለው....
.
የልጆች ምፅዋት ያ'ያቶች ልመና
ያ'ባቶች ግርግር በሞላው ጎዳና
መንገዱ አይልቅም
ጎዳናው አያልቅም
ይሰፋል ይረዝማል ይሄዳል ይጓዛል
እግረኛው ሞኝ ነው
ሳንቲሙን ዘርዝሮ
ከወደቁ አዛውንት ምርቃት ይገዛል
.
መንገዱ ያስፈራል
መንገዱ ይጨንቃል
ልጆች ሳቅ ሲያንቃቸው
አያት እምባ ይጨምቃል
መንገዱ ያሰጋል መንገዱ ያረጃል
ከዘናጭ ልጆች ጎን እርዛት ያዘለ አያት ይወለዳል
.
ሰጪ ካለቀሰ ተበዳሪ ስቆ
ጌታ ከለመነ አማኙ 'ግር ወድቆ
ልዑል ከዘመረ ንጉሱ ተዋርዶ
ገፁ ተመሳቅሎ ሽፋኑ ካማረ
ወለሉ ተንቆ ምንጣፍ ከከበረ
ባ'ገርኛ ስሌት ማነው ያልከሰረ?
.
እላለው........እላለው
.
ከየጎዳናው ገፅ ጥያቄ አነሳለው
ጥያቄ እጥላለው
እርጅና ለማምሻው ጎዳናን ካመነ
አያት ከልጅ ልጁ ሳንቲም ከለመነ
ባገርኛ ስሌት ማነው ያልመከነ?
.
በ'ግዚኦታ ዘመን በምዕላ ዘመን
እመንገድ ዳር ወድቆ ትራፊ መለመን
በጥሞና ዘመን የሚያስቡት ማጣት
በማውረሻ እድሜ የሚሰጡት ማጣት
በማልበሻ ዘመን በ'ርዛት መቀጣት
በለጋሽነት ወቅት በማጉረሻ ዘመን
በጥማት መገረፍ በርሀብ መመንመን
ከሆነ እጣችን
ይጠየቅ ትርጉሙ የልጅነታችን
ይፈተሽ መንገዱ የልጅ ልጆቻችን

ግድ የለም እንመን

እንመን

በሰውኛ ስሌት ውጤቱ ሲሰራ
ትውልድ ያደኸያል ያያቶች ኪሳራ
በልጅ ልጆች ዓለም
እንደጉድ ቢደለቅ ቢዘመር ቢዘፈን
አባት ይወራጫል ባ'ያቶች መታፈን
.
አባት ሆይ
.
ለልጆችህ ርዕዮት
ትላንቱን የረሳ ተስፋ ሲደራረት
ህልሜ ነው ይልሀል ያ'ያቶቹ ቅዠት
ከልጅህ አንደበት
ቋንቋ እንደዶፍ ቢዘንብ
ትርጉም ቢንፎለፎል ሺ ቃላት ቢጎርፍም
የልጅ ልጅ አግባቢ ግማሽ ገፅ አይፅፍም
ከልጆችህ ባህር
አሳ የሚያጠግቡ ለአሳ ሚስማሙ
እፅዋት ተክሎች
እንደጉድ ቢራቡ እንደጉድ ቢያብቡ
ገበታው አይሞላም ተቀዷል መረቡ
.
ግድ የለም እንመን........እንመን
.
የስኬት ክብደቱ
የምቾት አይነቱ
የነገ ውበቱ ባሻው ቋት ቢለካ
በምንም ቢሰፈር ባሻው ቃል ቢነገር
ጀግና ልጅ አትወልድም
አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር
.
ከፎቆቹ ጥላ....
ከያስፓልቱ ገላ ሲታተም ድምቀቴ
በመስታወት አጀብ ሲጠገን ጉልበቴ
ይኸው አነበብኩት
አያቶቼ ፊት ላይ ተፅፏል ሽንፈቴ
በመኪና ብዛት
በመስታወት አይነት ሲለካ ፍጥነቴ
በግንብ አጥር መአት
በፎቆች ጋጋታ ሲሰላ ስኬቴ
ይኸው ይታየኛል
አያቴ ገፅ ላይ ተስሏል ውድቀቴ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ተስሏል ሽንፈቴ!
***
@getem
@getem
#jeko
👍3