#የመልስሽ #ጥያቄ#እኔ #ምልሽየእንባችን ገንቦ ~ ሳይሰበር በፊት
ይፈስ ነበር አይደል ~ በሳቃችን ግፊት
የተፈጥሮስ ሂደት ~ እንዲህ ሳይጓደል
ከልብ እየሳቁ ~ ማልቀስ ነበር አይደል ?
#እኮ#እኛ #እኮ #ነንሀዘንን በደስታ _ እያነሳን ልንጥል
ስሜታችን ቆርጠን _ ስሌት ልንቀጥል
በአንድ ወገን ስለነው ~የተፈጥሮን መቀስ
በየተራ ሆኗል ~ መሳቅና ማልቀስ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@getem@getem@getem