ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ጨርሰኝ #አትበዪኝ

እጄ እየመረጠ ~ችሎ እንዳይቀባባሽ
እሳሳልሻለሁ ~ መሳሳት ከገባሽ
እኖራለሁ እንጂ
እያብሰለሰልኩሽ ~ እያሰላሰልኩሽ
ጨርሰኝ አትበዪኝ ~ ገና መች ጀመርኩሽ
መች ጀመርኩሽ ውዴ
መች ደገምኩሽ ሆዴ
ቅኔ ነው መውደዴ
ስውር ነው መንገዴ
ከመልመድሽ በፊት ~ ብሩሽና ሸራ
ከመሆንሽ በፊት ~ የጥበቤ አሻራ
የምናቤ ህላዌሽ
ሞልቶ ሳይሞት በፊት ~ በአካል ሳያበቃ
ባለ አቅም ሳይገዛሽ~ሳይቆጥርሽ እንደ እቃ
ገዢ ፊትሽን አይቶ ~ ዋጋ ሳይናገር
የፍቅሬን ቀይ ባህር ~ ከፍሎ ሳይሻግር
* * *
አይንአዋጅ ሆኖበት ~ በምርጫ ተሳክሮ
በድን ግርግዳው ላይ ~ ሳላይሽ ቸንክሮ
እየደጋገመ ~ ላይ ታች አገላብጦ
ከአቻዎችሽ መሀል ~ ከቢጤሽ አማርጦ
ከቤቱ ሳይሰቅልሽ ~ በሚስማር ቀጥቅጦ
ሳልጀምር ጨርሼሽ
ሞላሁ ብለሽ ሳትሄጅ ~ ሳትሰናበቺ
የኔ ብቻ ሁነሽ
መንፈሴ ውስጥ ኑሪ ~ ለአመታት ሰንብቺ
ሰንብቺ በሀሳቤ ~ ክረሚ በጣሙን
ልቅመስ ላጣጥመው ~የመሸሸግ ጣ‘ሙን
ጨርሰኝ አትበዪኝ ~ መጨረስ ለምኔ
የሞላሁሽ እለት ~ እጎድላለሁ እኔ
#ደሞ
አልቀሽ ሊጀምርሽ
ለሚጠባበቀው ~ ሰልፈኛ በሙሉ
መጨረስ አይችልም ~ ትይኛለሽ አሉ
#ቀላል #እችላለሁ
የአይንሽ አቀማመጥ
ጠፍቶኝ እንዳይመስልሽ~ስሜቴን ምታከክ
አልመጣልህ ብሎኝ
ታክቶኝ እንዳይመስልሽ~የአፍንጫሽ መሰልከክ
ከብዶኝም አይደለም
የአንገትሽን እርዝመት~በቀለም ማጥለቅለቅ
ዞማው ፀጉርሽን
ጥቁር መደብ ሰርቶ ~ ሸራ ላይ መለቅለቅ
መች አጣሁት ውዴ
ግንባርሽን ስዬ ~ ገድሽን ማሳመር
መች ጠፋብኝ ሆዴ
የአይኖችሽ ቆብ ቁጥር~የቅንድብሽ መስመር
የፈገግታሽ ለዛ ~ የደም ደም ግባትሽ
ሰምና ወርቅ ያለው ~ ቅኔታዊ ውበትሽ
#ሁሉም እጄ ላይ ነው
ጀምሬሽ ያቆምኩሽ
መስጥሬ የተውኩሽ
እንዳጠፊብኝ ነው ~ እንዳይወስዱሽ ብዬ
እያሰብኩሽ ምኖር ~ በሀሳቤ ከልዬ
ትንሽ ቀረኝ ብዬ ~ በአፌ ብዋሽሽም
እስከምትጨርሽው ~ ልቤ አይጨርስሽም
#የጨረስኩሽ #ለታ
ከባለቀን ሀብታም ~ የበረታው ክንዱ
ከፍሎ ይነጥቀኛል ~ ይወስድሻል አንዱ
== =||= ==
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@peppac
👍21
#ሁሉም_ቀን!!!!
....
ሁሉም ቀን..!!
ብርሃን እና ፅልመት...
መውደድና መጥላት
መማርና መቅጣት
ናፍቆት እና መርሳት
ማመንና መክዳት
...
መውረድና መውጣት
ሳይደርሱ መመለስ
ደርሶ አለመመለስ
መንገስና መርከስ
መሳቅና ማልቀስ
ጀንበሪቱም ያውናት
ቀን ሁሉ እንዲሁ
ጨረቃም እንዲሁ ናት
ያንቺ አለም የኔ አለም
አንድ ሌት  አንድ መአልት
...
መውረድ እና መውጣት
.....
መቅረት እና መምጣት ።

Ⓒ( Dagnu YE Roman )

@getem
@getem
@paappii
👍1