#ይሄን_ታውቂው_ይሆን
.
ኤፊ ማክ
.
የቤቴን መግቢያ በር ፣
አሽሙረኛ አናፂ ፣ ወዳንቺ አቁሞት
ስትወጪ እንደ ፀሀይ ፣
ስትገቢ እንደጀምበር ፣ አያለሁ ባግራሞት
ታውቂው ግን እኔንጃ ፣
ተፈጥሮሽ ካይን ጋር ፣ እንዳለው ቃለ ውል
በሄድሽበት መንገድ ፣
ላፍታ ያየሽ ሁሉ ፣ አብሮሽ እንደሚውል
እንኳን የዘየርሽው ፣
ያኮረፍሺው ቢኖር ፣ እንዴት ሆኖ ሊሆን
የረገጥሽው አፈር ፣
ፍቅርሽ ለደቆሰው ፣ መዳኒት እንደሆን
ይሄን ታውቂው ይሆን?
ከሳቅሽ ሚቀዳው ፣
ካዘንሽ ሚሸመን ፣ የከተማው አየር
እንኳን የቤታችን ፣
የሰፈሩ ጠረን ፣ ባንቺ እንደሚቀየር
ሰንበት አስቀድሰሽ ፣
የቅድስናሽ ልክ ፣ በሰው አፍ ሲተረክ
እንኳን ጎረቤትሽ ፣
ሀገሬው በሙላ ፣ ባንቺ እንደሚባረክ
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አድባር እንደሚሉሽ ፣
ጥለት ሲዘቀዘቅ ፣ ሀዘን ቤት ሲጠና
አልቃሽ እና አስለቃሽ ፣
ሀዘንተኛ ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚፅናና
ፍቅር እና ክብር ፣
ሰዋዊ ግብረገብ ፣ በጎደላት አለም
ቅንዝረኛ ወጣት ፣
አየኋትኝ ብሎ ፣ እንደ ሚስለመለም
ኑሮሽ ሲስተካከል ፣
የቀበሌው ኗሪ ፣ ባንቺ እንደሚሸለም
ካንድ እራስሽ አልፈሽ ፣
ከስጡኝ ተላልፈሽ ፣ ስተርፊ ለብድር
አንዴ የማይበላ ፣
የድሃው ሰፈር ሰው ፣ ጠግቦ እንደሚያድር።
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አያድርገውና...
ድንገት ወንድ ካየን ፣ እቤትሽ ከትሞ
እኔና መሰሌ ፣
ወር እንደምንተኛ ፣ ጨጓራችን ታሞ
ይሄን ታውቂው ሆን?
አታውቂው ይሆናል ፣ እኔ ግን አውቃለሁ
በጉርብትናዬ...
ወድጄሽ ወድጄሽ ፣ ወድጄሽ አልቃለሁ።
።።።።።
@getem
@getem
@gebriel_19
.
ኤፊ ማክ
.
የቤቴን መግቢያ በር ፣
አሽሙረኛ አናፂ ፣ ወዳንቺ አቁሞት
ስትወጪ እንደ ፀሀይ ፣
ስትገቢ እንደጀምበር ፣ አያለሁ ባግራሞት
ታውቂው ግን እኔንጃ ፣
ተፈጥሮሽ ካይን ጋር ፣ እንዳለው ቃለ ውል
በሄድሽበት መንገድ ፣
ላፍታ ያየሽ ሁሉ ፣ አብሮሽ እንደሚውል
እንኳን የዘየርሽው ፣
ያኮረፍሺው ቢኖር ፣ እንዴት ሆኖ ሊሆን
የረገጥሽው አፈር ፣
ፍቅርሽ ለደቆሰው ፣ መዳኒት እንደሆን
ይሄን ታውቂው ይሆን?
ከሳቅሽ ሚቀዳው ፣
ካዘንሽ ሚሸመን ፣ የከተማው አየር
እንኳን የቤታችን ፣
የሰፈሩ ጠረን ፣ ባንቺ እንደሚቀየር
ሰንበት አስቀድሰሽ ፣
የቅድስናሽ ልክ ፣ በሰው አፍ ሲተረክ
እንኳን ጎረቤትሽ ፣
ሀገሬው በሙላ ፣ ባንቺ እንደሚባረክ
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አድባር እንደሚሉሽ ፣
ጥለት ሲዘቀዘቅ ፣ ሀዘን ቤት ሲጠና
አልቃሽ እና አስለቃሽ ፣
ሀዘንተኛ ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚፅናና
ፍቅር እና ክብር ፣
ሰዋዊ ግብረገብ ፣ በጎደላት አለም
ቅንዝረኛ ወጣት ፣
አየኋትኝ ብሎ ፣ እንደ ሚስለመለም
ኑሮሽ ሲስተካከል ፣
የቀበሌው ኗሪ ፣ ባንቺ እንደሚሸለም
ካንድ እራስሽ አልፈሽ ፣
ከስጡኝ ተላልፈሽ ፣ ስተርፊ ለብድር
አንዴ የማይበላ ፣
የድሃው ሰፈር ሰው ፣ ጠግቦ እንደሚያድር።
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አያድርገውና...
ድንገት ወንድ ካየን ፣ እቤትሽ ከትሞ
እኔና መሰሌ ፣
ወር እንደምንተኛ ፣ ጨጓራችን ታሞ
ይሄን ታውቂው ሆን?
አታውቂው ይሆናል ፣ እኔ ግን አውቃለሁ
በጉርብትናዬ...
ወድጄሽ ወድጄሽ ፣ ወድጄሽ አልቃለሁ።
።።።።።
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1