ከመሸ ለምስጋና ብቅ ብለናል !
🙏
#የቻናላችን ቤተሰቦች የላካቹን በሙሉ በጣም እናመሰግናለን 🙏🙏🙏
እውነት እጅግ ብዙ ብዙ መልክቶች ናቸው የተላከልን የሁላችሁንም መልክቶች ማቅረብ አልቻልንም ለዚህም ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን የላክናቸው ይበቃል ከማለት ነው የላካችሁሉን በሙሉ ግን ትልቅ አክብሮት አለን 🙏!!!
ሁላችሁም ሀሳባቹ በነፃነት ስለገለፃቹልን ደስ ብሎናል እናመሰግናለን !!
#አብዛኞቻችሁ ማለት እችላለሁ ልዩነቶቻችን ትንሽ ናቸው አንድ የሚያደርገን ግን ብዙ እንደሆነ ገብቶኛል ያ ደግሞ አስደስቶኛል እኛ የተለያየ ምርጫዎች ፣ ፍላጎቶች ይኖሩናል ይሄ የሚጠበቅ ነው የሚያስገርምም አይደለም .....
ሁላችንም ኢትዮጵያ በተለያየ ምልከታዎች ልንመለከታት እንችላለን ይሄ ሸጋ ነገር ነው !!መነሻችንም መድረሻችንም ግን እሷ ናት !! ሁላችንም ሀገራችን እንወዳለን የተሻለች እንድትሆን እንፈልጋለን ሀገራችን ብዙ መልካም ነገሮች እንድትሆን እንፈልጋለን አይደል.? ስለዚህ የምንፈልገውን ነገር ከመፈለግ ባሻገር ከኛ የሚጠበቀውን ማንኛውንም መልካም ነገር እናድርግላት ከመንገድ ላይ የሙዝ ልጣጭ (ቆሻሻን ) ማንሳትም ጀምሮ መፈለግ ብቻውን ለውጥ አያመጣምና !!
#በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን !! በሃይል የምወደውን የልቤን ሰው #የነብይ መኮንን ግጥም ጀባ ብያቹ ወደ አልጋዬ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር💚💛❤️ አሜን!!!
------------------------------------------------
///ነብይ መኮንን///
በዚህ ዓመት
ሳንጣላ መታረቂያ
ትንሽ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ብቻ መሰደጃ፡፡
ምንለበት ፤
ለምናልባት ብንተውለት !!
ፍፁም መሆን ስለማንችል
ትንሽ ባዶ እንዋዋል ፣ ከልባችን ደግ በኩል፡፡
ለአንጎላችን መላወሻ
ትንሽ ቦታ እንተውለት
" ምናልባት " የምንልበት፡፡
ልክ እንዳምና ፣ ለዚህ ዓመት
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታሰር ይቅር ማያ
ይቅር ብንል መታሰርያ
ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ፡፡
ጥግ ድረስ የለም ስራ ፣ ጥግ ድረስ የለም ፋታ፡፡
በልባችን ደግ በኩል ፣ እንፈልግ ባዶ ቦታ፡፡
የጳጉሜ ዓይነት ትንሽ ቦታ
ለዘመን መለወጫ !!
((( ደግ ለሚያስቡ ))))💚💛❤️
@balmbaras
@getem

ለምሽታችን
💚
#ዛሬ በወዳጄ በቀረበልኝ ግብዣ ምክንያት መሀል ሸገር አብዮት አደባባይ ላይ #አዲስአበባ ሙዚየም አደይ ሚክስድ አርት ኤግዚቢሽን ታድሜ ነበር .....ሸጋ ሸጋ የሆኑ የሚገራርሙ ሀሳብ ያላቸው ሚክስድ አርት አይቻለሁኝ...በጣም የወደድኳቸውን በስልኬ አስቀምጫለሁኝ አንድ ስዕል ብቻ ሳላነሳው መውጣቴ ቆጭቶኛል !!
ልጆቹ ከዚህም በላይ መስራት እንደሚችሉ ያስታውቃሉ.....ሁሉም ማለት ይቻላል ስለ ስራዎቻቸው ገለፃ ለማድረግ ያላቸው ፍላጎትና ተነሳሽነት የሚያስደስ ነው !!
ስዕል እና ግጥም የጥበብ ቁንጮ ናቸው በትንሽ ነገር ነፍፍፍፍፍፍፍፍ መልእክት ማስተላለፍ የሚችሉ የጥበብ ቁንጮዎች ንግስትና 👑 ንጉስ ናቸው #ለኔ!!
#በመጨረሻም እኔ አይቼ የወደድኳቸውን ሀሳባቸው እይታቸው ወድኩላቸው ስራዎችን ጀባ ልበላቹ እና ልሰናበት!
ሸጋ ምሽት!💚