Henok Birhanu:
#ብቸኝነቴ
:
:
የብቸኝነት ዶፍ በላዬ ዘነበ
አንቺን ካጣ ወዲ መንፈሴም ተራበ
ሰው መግባባት ጠፋቶት ምላሴም ለዘበ
ገላዬ አዘን ጎዳው ፅልመትን ደረበ
ልቤ አላምን ብሎ እውነት ነው እያለ ዐይኔ ዘንድ ቀረበ
ዐይኔም አዎ እውነት ነው ለልቤም ነገረው በእምባ እየታጠበ።
:
:
ይሄኔ ነው እንግዲ አንቺን ለማጣቴ እርግጠኛ የሆንኩት
አብረን እንደማንኖር ውስጤን ያሳመንኩት።
:
:
አብረን እንደማንሄድ ከጎኔ ሸሽጌሽ
አቅፌሽ አቅፈሺኝ ባደባባይ ይዤሽ
እንደማይሆን ገባኝ ካሁን ቧላ በቅቷል
መለያየታችንን ሀገር ሁሉ ሰምቷል
አምላክ እስካልሻረው በማህተም ተመቷል።
:
:
ይሄኔ ነው በቃ
ብቸኝነቴ ዘልቆ ከደምስሬ
ብቸኝነቴ ከእግር እስከ ፀጉሬ
እያወዛወዘኝ ልክ እንደ ባህር ዛፍ
እያመነመነኝ ሲያቀልጠኝ እንደ ጧፍ
እያብረከረከኝ ጉልበት እንዳነሰው
ችግር እንደበላ ሆዴን እያመሰው
እንደ ሁዳድ ቆጥሮ ልቤን እያረሰው
ሽቅብ አስመልክቶ ዐይኔን ያስለቀሰው።
:
:
ታዲያ
ምን ይሆንስ መፍቴ ምን ይሆንስ መላ
ባተሌነት ደርሶ ላባከነው ገላ።
ምን ይሆን ማርከሻ ምን ይሆን መድሀኒት
የትካዜ ሾተል ለሚሸነቁረው ቀንም ሆነ ሌሊት።
:
:
ምንም ነው መልሱ የለም አማራጪ
በትዝታ አለንጋ ከመሸንቆጥ ውጪ።
:
:
በስተመጨረሻም
በዚች አጭር መንገድ በዚች የህይወት ጉዞ
እኔነቴ በፍቅር እልፍ ተወዝውዞ
ብዙ ነገር ታዘብኩ ብዙ ነገር ቃኘው
መለያየት ከሞት እንደሚበልጥ አየው።
#አሜን
@getem
@getem
@getem
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu
#ብቸኝነቴ
:
:
የብቸኝነት ዶፍ በላዬ ዘነበ
አንቺን ካጣ ወዲ መንፈሴም ተራበ
ሰው መግባባት ጠፋቶት ምላሴም ለዘበ
ገላዬ አዘን ጎዳው ፅልመትን ደረበ
ልቤ አላምን ብሎ እውነት ነው እያለ ዐይኔ ዘንድ ቀረበ
ዐይኔም አዎ እውነት ነው ለልቤም ነገረው በእምባ እየታጠበ።
:
:
ይሄኔ ነው እንግዲ አንቺን ለማጣቴ እርግጠኛ የሆንኩት
አብረን እንደማንኖር ውስጤን ያሳመንኩት።
:
:
አብረን እንደማንሄድ ከጎኔ ሸሽጌሽ
አቅፌሽ አቅፈሺኝ ባደባባይ ይዤሽ
እንደማይሆን ገባኝ ካሁን ቧላ በቅቷል
መለያየታችንን ሀገር ሁሉ ሰምቷል
አምላክ እስካልሻረው በማህተም ተመቷል።
:
:
ይሄኔ ነው በቃ
ብቸኝነቴ ዘልቆ ከደምስሬ
ብቸኝነቴ ከእግር እስከ ፀጉሬ
እያወዛወዘኝ ልክ እንደ ባህር ዛፍ
እያመነመነኝ ሲያቀልጠኝ እንደ ጧፍ
እያብረከረከኝ ጉልበት እንዳነሰው
ችግር እንደበላ ሆዴን እያመሰው
እንደ ሁዳድ ቆጥሮ ልቤን እያረሰው
ሽቅብ አስመልክቶ ዐይኔን ያስለቀሰው።
:
:
ታዲያ
ምን ይሆንስ መፍቴ ምን ይሆንስ መላ
ባተሌነት ደርሶ ላባከነው ገላ።
ምን ይሆን ማርከሻ ምን ይሆን መድሀኒት
የትካዜ ሾተል ለሚሸነቁረው ቀንም ሆነ ሌሊት።
:
:
ምንም ነው መልሱ የለም አማራጪ
በትዝታ አለንጋ ከመሸንቆጥ ውጪ።
:
:
በስተመጨረሻም
በዚች አጭር መንገድ በዚች የህይወት ጉዞ
እኔነቴ በፍቅር እልፍ ተወዝውዞ
ብዙ ነገር ታዘብኩ ብዙ ነገር ቃኘው
መለያየት ከሞት እንደሚበልጥ አየው።
#አሜን
@getem
@getem
@getem
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu