ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ለምሽታችን
💚


ዛሬ ከግጥም ውጪ በሆነ ጉዳይ ነው ሀሳብ እንድትሰጡበት ስለፈለኩኝ ነው #በተለይ ሴቶች


ለውብ ቀን!
💚

# እቃወማለሁ !!!
# ሴትን_ከእውቀቷ_ይልቅ_በቁንጅናዋ_መመዘን_ለምትፈልጉ
( በዓለም ለ40ኛ ፣ በሀገራችን ለ32ኛ ጊዜ የሚከበረውን " የዓለም የቱሪዝም ቀን "
ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ባህል ፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከመርሀ ግብሮቹ
መሀል የቁንጅና ውድድር ማካሄድ መሆኑ እጅግ የሚያሳፍር ነው ። ለሴቶች የተሻለ ስፍራን
እሰጣለሁ በሚል መንግሥት ስር ፣ ቢሮው ኪነጥበብን ያህል የለውጥ መሳሪያ በእጁ እያለ
የሴቶችን ቁንጅና ( አካል ) ለቱሪዝም ቁስ አድርጎ ማቅረቡ እጅግ አሳዛኝ ነው ። ዓለም
ሴቶችን በቁንጅና የሚያወዳድርበትና እንደ ሸቀጥ የሚሸጥበት የራሱ ዓላማ ይኖረዋል ።
50% ሚኒስትሮቿንና የርዕሰ ብሔርነት ወንበሯን ለሴቶች እኩልነት የሰጠችው ኢትዮጵያ
የሴት ልጆቿን ገላ አራቁታ ለገበያ ማቅረቧ ግን ጊዜውን የማይዋጅ ክብረ ነክ ድርጊት ነው
። # ከፍልስምና ፬ አሳቢዎች አንዱ # ቡርሐን_አዲስ ስለ ቁንጅና ውድድር ይህን ብሏል ።


# ቴዎድሮስ፦ “የቁንጅና ውድድር” የሚባለው ነገር ከዚህ ጋር ተዛምዶ ነው የሚታየኝ፡፡
ዓለም ሴት ልጅን አሳንሶ ካየባቸው መንገዶች አንዱ የቁንጅና ውድድር ነው፡፡ ሴትን
ከሃሳቧና ከእውቀቷ በላይ በማይወዳደር ቁንጅናዋን መለካት ቀጣይ እርምጃው የወሲብ
ባርነት መስሎ ነው የሚታየኝ፡፡ እነዚህ የቁንጅና ውድድር አዘጋጆች ለሽንፈታቸው
“ውስጣዊና ውጫዊ የሚል ስያሜ ቢሰጡትም በሐሳብ መወዳደርን ከቁንጅና ውስጥ
አውጥቶ መመዘኛ ማድረግ ሲቻል አንድ ላይ የጠቀለሉት “ውስጣዊ ቁንጅና” የሚባለው
የውጫዊው መሸፈኛ ስለሆነ ነው፡፡ የውጪውን ትተህ የአማራን፡ የጋምቤላን፣ የኦሮሞን፣
የትግራይን፣ የደቡብን ሴቶች በአንድ መስፈርት መዳኘት ሴትን ከሰውነት አውርዶ ሸቀጥ
መደርደሪያ ላይ ማስቀመጥ መስሎ ይሰማኛል፡፡ አሁን ስትናገረው ደግሞ አንተ
ከገለፅካቸው ህብረተሰብን ማደንዘዣ መንገዶች አንዱ መደረጉን አስባለሁ፡፡ “የዘር ካርድ”
ላይ ያነሳኸውን በሽፋን የማጥመድ ስልት አያይዘህ ብታይልኝ፡፡

# ቡርሐን ፦ ሁኔታዎቹ በጣም የተያያዙና በጥናት የመጡ ናቸው፡፡ ፍሩይድ “ወሲብ
ባህሪያችንን ይቃኛል” አለ፡፡ ከዚያ በፊት ለነበሩት በሃይማኖትም ሆነ በሞራል ለሚመሩት
ህዝቦች ግን የወሲብ ስሜትህን መቋቋም መቻልህ ነው አንተን ትልቅ የሚያሰኝህ፡፡
በስሜት ላይ የበላይ መሆን ነው ሃያልነት፡፡ ግን “ስሜት ነው የሚገዛን” ብሎ ስነ ልቦናውን
ሲያመጣው፣ ማህበረሰቡ ቁስ ሸማች መሆንና ገንዘብ ዋና ገዥ መሆን አለበት የሚል
አስተሳሰብ ሲዳብር “ሰዎች የእኛ አስተሳሰብ ደጋፊና ተከታይ ብቻ እንዲሆኑ ለማስቻል ምን
ማድረግ አለብን?” ብለው ነው እንደገና ተቀምጠው የመከሩበት፡፡ በቃላትም በሐሳብም
ጨዋታ ነው የተያዘው፡፡

"ዘመናዊነት" (modrnism ) የሚለውን ቃል ራሱ የስልጣኔ ሳይሆን የኢኮኖሚ ቃል ነው።ስልክ እንቀያየር ብለን ሁለታችን ስናወጣ የአንተ ሳምሰንግ በመሆኑና የኔ ጣና ሞባይል
በመሆኑ ብቻ እኮ የኔን ሸሸግ አደርገዋለሁ፤ የኔ የተሻለ ቢሠራም እንኳ:: ከዚያ ውጭ
ለአዕምሮህ፣ ለተፈጥሮህ፣ ለሞራልህ ሳይሆን ለስሜትህ የሚሆኑ እንደነ ቁንጅና ውድድር፣
ሞዴሊንግ፣ ፋሽን የመሳሰሉት የተከሰቱት በዚያ ነው፡፡ ሰዎች በስሜት እንዲመሳሰሉ
ካደረግህ ተመሳሳይ ምርት ብታመርትም ተመሳሳይ ገዥ ታገኛለህ፡፡ ውበት የሚባለው ነገር
እኮ በተፈጥሮ ወይም በእውነት ሳይሆን በፋሽኑ ኢንዱስትሪ እንዲዳኝ ነው የተደረገው፡፡
ነጮቹ “ቅጥነት ነው ቁንጅና” ካሉ ቀጭኗ የተሻለ ዋጋ ታወጣለች፡፡ እሷ የምትለብሰው
የዘመናዊ ፋሽን ምልክት ተደርጐ ስለሚቆጠር ዋጋው ከፍ ያለ ይሆናል፡፡ ግን በእርግጠኝነት
ውበት ማለት ቅጥነት ነው እንዴ? ለማን? “ድንቡሽቡሽነት” ከውበት መለኪያነት ተሰረዘ
ማለት ነው? ማን ነው የኢትዮጵያዊቷ ሴት ውበት ለኪ? በትክክል ካሰብን ግን እያንዳንዱ
ማህበረሰብ የራሱ የሆነ የቁንጅና መለኪያ አለው፡፡ የአንዱ ለሌላው አይሰራም፡፡ እንዴት
አድርገህ ነው በባህል፣ በሐሳብ፣ በአኗኗር ከማይገናኝ ዓለም ላይ ሰብስበህ አንድ የዓለም
ቆንጆ የምትመርጠው?

የሞዴሊንግ ትልቁ ሥራው ሸቀጥ ማሻሻጥ ነው፡፡ እውቀት አይደለም፡፡ ሐሳብ አይደለም፡፡
የሞዴሊንግ ዓለም እየሰፋ ከሄደ ራሳቸው ሴቶቹ ቆንጆ ለመሆን የውበት መጠበቂያ
ምርቶችን በብዛት ይጠቀማሉ፡፡ ቆንጆ የምትላት ሴት መጀመሪያ በተፈጥሮ ማንነቷ
እንዳልተወዳደረች በሂደት ግን የቁንጅና መጠበቂያ ምርቶችና የሜክአፕ ግዞተኛ ትሆናለች፡፡
ያለ ሜክአፕ በፍፁም ከቤት የማትወጣ ትሆናለች፡፡ ሴቶቹ ላይ የማይሠራ ሙከራ
(Experiment) የለም፡፡ የከንፈር ቀለም እኮ ብዙ መቶኛው ቫዝሊን ነው፡፡ ሰባት ብር
የሚሸጠውን ቫዝሊን የሆኑ ኬሚካሎችን ጨማምረህ የከንፈር ቀለም ማድረግ ዋጋውን
ውድ ያደርግልሃል፡፡ የከንፈር ቀለም ዋና ምንጩ ወሲባዊ ስሜት መፍጠር ነው፤ ከንፈርን
ከብልት ጋር ማመሳሰል ነው፡፡ ሰውነትን ይበልጥ እርቃን ማድረግ ነው፡፡

አንዳንድ ማስታወቂያዎችም እንደ ከንፈር ቀለሙ ናቸው፡፡ የምታስተዋውቀው የለስላሳ
መጠጥ ሆኖ የምታሳየው ግን ለወሲብ የቀረበች ሴትን ስሜት ነው፡፡ “ለምን?” ስትል
በትክክል ፋሽን በራሱ ሐሳቡ የሸቀጥ ገበያ ስለሆነ ነው፡፡ ፋሽን አዕምሮን፣ ስነልቦናን
የማውረድ መንፈስም አለው፡፡
ትራክተር ወይም መኪናን በሴት ማስተዋወቅ ትርጉሙ ምን ነው? ሴቷን አይተህ መኪናውን
ታያለህ ለማለት ነው:: እኔ እንደው ሴቶቻችን በጣም ቢያስቡበት የምለው ፆታዊነትን ነው፡፡
በጣም ቢያስቡበት መልካም ነው፡፡ “የፆታ እኩልነት” የሚለውን ትርክት በጣም በጣም
በአፅንኦት ረጋ ብለው ቢያዩት በጐ ነው፡፡ ሴቷ “ወንዱ የሚሠራውን መሥራት አያቅተኝም”
ከሚለው ወጥታ በጨዋ መንገድ “ወንድነት ምንድነው?”፣ “ሴትነት ምንድነው?” የሚለውን
መመርመር በጣም ያስፈልጋል፡፡



የፆታዊነትና የፆታ እኩልነት ትርጓሜ በራሱ ችግር ያለው ነው፡፡ ራሱ ላይ ነው ትልቅ ችግር
የፈጠረው፡፡ ዛሬ ሴትን የምትለካት በእውቀቷ አይደለም፤ በጥበቧ አይደለም፤ በምርምሯ
አይደለም፡፡ የምትለካው በቁንጅናዋ ነው፡፡ አንጀሊና ጁሊና አንጌላ አሜሪካን ቢቀርቡ ለማን
ነው ትኩረት የምትሰጠውና ማንን ነው የምታከብረው? ጥቅል አሳቢነት ላይ አይደለም
ሴቶቹን የምትፈልጋቸው፡፡ እንደውም አሁን አሁንማ የሴት ቦታ የሚመስለን ሸቀጡአካባቢ
ነው፡፡ ስለዚህ ሴትን የምንለካበት መነፀር ራሱ ከስጋነቷ ውጭ ክብር የሰጠ አይደለም፡፡
ግን እውነት ሴት ቦታዋ ይህ ሆኖ ነው እንዴ? ማሰብና መመራመር ሳትችል ቀርታ ነው
እንዴ? ሸቀጥ እንደሆነች ተደጋግሞ ፕሮፓጋንዳ መሠራቱ ያመጣው ውጤት ነው፡፡ ባል
እንዴት አድርጐ ከሚስቱ ሐሳብ ይጠብቃል? ሚስቱ ተውባና ተቀባብታ የወሲብ ማሽን
ሆናለት እንድትኖር ነው የሚፈልገው፡፡ ይህም አስተሳሰብ የGlobal consumer Culture
Society ውስጥ ነው፡፡ አራት ነጥብ፡፡

------------------------------------------------


#በዚህ ሀሳብ ላይ አስተያየት ብትሰጡበት #በተለይ ሴቶች

@getem
@getem
@balmbaras
👍3
ለምሽታችን!
💚


´ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት!

በአንድ የገጠር ከተማ በርካታ ተማሪዎችን ሰብስበው የሚያስቀሩ አንድ ሸይኽ ነብሩ።አንድ ቀን ከነዚህ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ለሸይኹ ገንዘብ እንደሚያስፈልገውና ወደ ከተማ ሄዶ ይህንን ለቀለብ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማፈላለግ እንዳለበት ይነግራቸዋል። #ሼይኹም ለተማሪያቸው ከፈቀዱለትና ስንቅ ካዘጋጁለት በኋላ መንገዱን ይጀምራል። ወደ እሚሄድበት ከተማ ለመድረስም ከመንገድ ያለን በረሀ ማቋረጥ ነበረበት። ይህንንም በረሃ አቋርጦ በሚሄድበት ወቅት አንድ የቆሰለ አሞራ ከመሬት ላይ መብረር የማይችል ሆኖ ይመለከተዋል። ታድያ ይህ ደረሳ በዚህ አሞራ ተፈኩር(ማስተንተን) ማድረግ ይጀምራል።


#በዚህ_በረሀ ውስጥ ምንም የሚቀመስ በሌለበት ይህ አሞራ ምን እየበላ ይሆን!?


#እንዴት_በህይወት መቆየትስ ቻለ!?
በዚህ መልኩ በተፈኩር ውስጥ ሳለ ከወደ ሰማይ ሌላ አሞራ ድንገት ከወደ ሰማይ ዱብ ይላል።


#ይህ_አሞራ የሚበላ ነገር በእግሮቹ አንጠልጥሎ ነበርና ለተጎዳው አሞራ ጥሎለት ሄደ። ያ የተጎዳው አሞራም የተጣለለትን ምግብ መመገብ ይጀምራል።
ተማሪውም በጣም ተገረመ። (መቼስ ፈጣሪ ነፍስን ከሪዝቋ ጋር እንጂ መች በባዶ ፈጠራት እና!) ብቻ ነገሩ እጅግ አስገርሞት እና አስደንቆት የሚሄድበትን በመሰረዝ ወደ ሸይኹ መመለስ ጀመረ። ለመመለሱ ምክንያትም ይህንን የተጎዳ አሞራ በዚህ በረሃ ውስጥ የሚመግብ እና የሚረዝቀው ፈጣሪ እኔንም ይመግበኛል ችግሬን ያስወግድልኛል የሚል ነበር። ወደ ሸይኹም እንደደረሰ የተመለሰበትን ምክንያት ይጠይቁታል።

ተማሪውም ያጋጠመውን ሁሉ ይነግራቸውና ፈጣሪው እሱንም ልክ እንደ አሞራው ሁሉ ከችሮታው እንደሚለግሰው ተስፋ አድርጎ መመለሱን ነገራቸው።

#ሸይኹም- ምነው !? እንደው እንተጎዳውና እርዳታ ፈላጊው አሞራ መሆንን ከመመኘት ለምን እንደ ረጂው እና ምግብን ተሸክሞ እንደተባበረው አሞራ መሆንን አልተመኘህም አሉት ይባላል።
---------------------------------------

#ሁሌም ቢሆን ትብብር እና እርዳታን ፈላጊ ከመሆን አንተው እራስህ ረጂ እና ተባባሪ መሆንን ምረጥ።
ከላይ ያለች እጅ ታች ካለች እጅ በላጭስ አይደለች!


#አሁን ወቅቱ ከመቼውም በላይ ቁጭ ብለን ለመረዳት ወይም ከመንግስት ብቻ መፍትሔ የምንጠብቅበት ጊዜ ላይ አይደለንም ሀገራችንን ፣ ወገኖቻችን ፣ ቤተሰቦቻችን ፣ ወገኖቻችን እንዴት ነው ከዚህ ችግር ልንከላከል የምንችለው ብለን በደንብ የምናስብበትና ወደ ተግባር የምንገባበት ጊዜ ነው....እናም ወንድምና እህቶቼ እቤት ከመቀመጥ በዘለለ ደሞ ማድረግ ስላለብን ነገሮች አስቡልኝ የኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ በየአካባቢው አይደል..? አቅም የሌላቸው የንፅህና ሳኒታይዘር ሆነ ምግብ መግዣ የሌላቸው ብዙ አሉ በየአካባቢያችን ስለዚህ እዚህ ቻናል ወንድሞችና እህቶች የምንችለውን እንርዳቸው ይሄን በሽታ የሚከላከሉበት ማቴሪያል እንርዳቸው ፣ የሚበሉትን ገዝተን እንስጣቸው በአቅማችን #ይሄኔ እኛም ለሀገራችን የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን.....ለምን አንድ ሳሙና አይሆንም ....

#ይሄን የምታነቡ ሰዎች ይሄን እንደምታደርጉ እናንተም የመፍትሔ አካል እንደምትሆኑ እምነት አለኝ🙏🙏🙏

ውብ ምሽት ትሁንላቹ!🙏

@getem
@getem
@Nagayta