ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
🔴🔴 #ሼር_ሼር_ሼር 🔴🔴

❗️ ❗️ #አስቸኳይ_የእርዳታ_ጥሪ ❗️❗️

🔴 ወገንን ለመርዳት ግዴታ የቡና ደጋፊ መሆን የለብንም ✔️
🔴 ሰው መሆን በቂ ነው !!!!

ወጣት #ሀያት_ኑሩ_ሁሴን የ18 አመት ወጣት እና #የኢትዮጵያ_ቡና ደጋፊ ስትሆን በደረሰባት የ ኩላሊት ህመም በሽታ ምክንያት ሁለቱም ኩላሊቶቿ መስራት እንዳቆሙ በ ህክምና ተረጋግጧል ።

#ቅዱስ_ጳውሉስ_ሆስፒታል በሳምንት 3 ጊዜ ዲያሊሲስ (የኩላሊት እጥበት) ይደረግላታል እሱም የምታወጣው ገንዘብ ከ 2250 ብር በላይ ነው ። ይህንንም ብሩም ከባድ ስለሆነ ጔደኞቿ በየቀኑ ትኬት 200 ብር እየሸጡላት ነው እሱም ከተሳካ ይሸጣል ።

እስከ አሁን ድረስ ዲያሊሲስ (የኩላሊት እጥበት) ላይ የቆየች ቢሆንም 7 ወር አልፏታል ግዴታ ንቅለ ተከላ መደረግ አለበት ይህንንም ለማድረግ ገና ፕሮሰስ ላይ ነች ።

ነገር ግን ንቅለ ተከላው ከተደረገ በኋላ የማይቋረጥ መድኃኒት መውሰድ አለባት ታድያ ይህንን ወጪ የሚሸፍን አቅም ስለሌላት በ አቅራቢያዋ ወደ ምንገኘው ወደ እኛ እህት ወንድሞቿ እጇን ለመዘርጋት ግዳጅ ሆኖባታል ።

እናም የእግር ኳስ ቤተሰቦች ስንት እህትና ወንድሞቻችን ወገኖቻችን እርዳታ እየፈለጉ ሰው ሳይደርስላቸው ህይወታቸው አልፏል የዚህችንም ህይወት እንታደገው ዘንድ ሁላችንም የ እህታችን እርዳታ ያስፈልጋታል በፍጥነት ሁላችንም የ እህታችንን ህይወት እንታደግ ።

አድራሻ ☞ #አውቶቢስ_ተራ ወረድ ብሎ ዜድ ዋይ ህንፃ ገባ ብሎ መካነ ሰላም ፊት ለፊት #አያት_ኑር_ሁሴን

ስልክ ቁጥር የ እናቷ -- 0911948682 #ሰአዳ

✔️ የባንክ ቁጥር #ኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ
➡️ 1000230747648 #ሰአዳ_እንድሪስ

#ሼር_በማድረግ_ሀላፊነታችንን_እንወጣ 🙏🙏🙏
ግጥም ብቻ 📘
Photo
የተረት መሠረት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አባቶች እናቶች
በፍቅር ተጋግዘው ፣ ያቆሙልን እውነት
በዘመን ጠልሽቶ...
ለእኛ ለልጆች ፣ ይመስለናል ተረት፡፡
።።።።።።
የኛ ትልቅ ችግር ፣ የኛ ትልቅ ህመም
መሰረት ሳንይዝ.
"የመሰረት" ብሎ ፣" እሺ" እያሉ ማዝገም፡፡
።።።።።።፣
ተረት ተረት
"የመሰረት"
አንድ ሀገር ነበረች
"እሺ"
እምነትን ከፍቅር ፣ ገምዳ ያስተማረች፡፡
"እሺ"
አናም በዚች ሀገር...
ሙስሊሞች በእምነት ፣ መስጅድ ሲገነቡ
ክርስቲያኖች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ምሶሶ ሲያቀርቡ፡፡
"እሺ"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም በዚች ሀገር...
ክርስቲያኖች በምነት ፣ ቤተስኪያን ሲያንፁ
ሙስሊሞች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ጉልላት ሲቀርፁ፡፡
"እሺ"
እናም በዚ መልኩ ፣ ሲኖሩ ሰኖሩ
እንደተዋደዱ እንደተፋቀሩ
እንደተጋገዙ እንደተባበሩ
መሰረት እንድናይ...
አንዋር ከራጉኤል ፣ ተጎራብተው ቀሩ
"እሺ"
"እሺ" ማለት ጥሩ
መሰረት ሳይዙ ...
የመሰረት ብሎ ፣ መኖር ነው ችግሩ!!!
።።።።።
።።።።።
በኮልፌ ጠሮ የሚገኝ የኡስማን በስጅድ እና የስላሴ ቤተ ክርስቲያን ጉርብትና።
#ሼር ለሁሉም!!!

@getem
@getem
@getem
ቀንዲል የጥበብ ምሽታችን አዳዲስ የጥበብ ፊቶችን ይዞ ለእሮብ #ጥቅምት_12 ... ጉርድ ሾላ በሚገኘው #ቶፕ_10 ሆቴል ይደረጋል ።
በዚህ ምሽታችን
ወገኛው አሳዬ ደርቤ
ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ
ገጣሚ ያዴል ትዛዙ
ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ
ገጣሚ እዮብ ዘ ማርያም
ገጣሚ ፍቃዱ ጌታቸው
ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ
ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ
ገጣሚ እሱባለው የኔ ነህ
ባለ ቅኔ በቃሉ ሙሉ
ገጣሚ ልዑል ሀይሌ እና ገጣሚ ሚካኤል አስጨናቂ ስራዎቻቸውን ይዘው የሚቀርቡ ይሆናል ።
አዲስ እና በእለቱ የሚቀርብም ክብር እንግዳ ይኖረናል ።
ምሽታችንን ለማድመቅ ለምትፈልጉ ሁሉ ትኬቱ ከጃፋር መፅሀፍት መደብር ...ይገኛል ....በተጨማሪም ልዑል ሀይሌ (0910630305) ...ሚካኤል አስጨናቂ (0920059005) ላይ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ።
#ሼር ማድረግ እናንተን አይጎዳም እኛን ይጠቅማልና ሼር አድርጉልን
#ለሰላም_የምችለውን_ሁሉ_አደርጋለሁ!

1ሚሊዮን ተከታይ የለኝም። ቢያንስ እያንዳንዳቸው 1000 ጓደኛ ያላቸው እስከ 5000 ጓደኞች ግን አሉኝ።

#ከዛሬ_ጀምሮ_በሃገሬ_ጉዳይ_ዳር_ቁጭ_ብዬ_ተመልካች_ላለመሆን_ቃል_እገባለሁ

እናንተስ?

#ሰላምለኢትዮጲያ
#PeaceForEthiopia

#ሼር #share
#4
ለመንግስት የተፃፈ ደብዳቤ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
መልእክት እንዳናደርስ ፣ በስልክህ አፍ በኩል
ወይ ሜሴጅ እንዳንልክ ፣ ወይ እንዳንመሰኩል
ቁጥርን አናውቅም ፣ እንዳንደውልልህ
ገዳይ ጉዳይ ሲሆን
መልእክት እንዳንተው ፣ የለንም ኢሜልህ
ቢጠበን ቢጨንቀን
ተገቢ ባይሆንም
በኢንተርኔት ዘመን ፣ ደብዳቤ ፃፍንልህ።
።።።
እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
የቀን ጅቦች ሲያልፉ
ከቀን ጅሎች ጋራ ፣ ለሞት ተሰልፈን
"ወያኔ ሌባ" እያልን ፣
እየተገፋፋን ፣ ኪሳችን ተዘርፈን
እኛ አለን በተድላ
በቀን ሶስት ጊዜ
ቁርስ ፣ ምሳና ራት ፣ስጋት ስንበላ
ያንተ ደህንነት ነዉ እኛን ሚያስጨንቀን
ተደመሩ ብለህ ፣ ምታስጨፈልቀን
ትእግስት እያበዛህ ፣ ምታሸማቅቀን
ቀልድ ቁም ነገርህ ፣አመት የሚያስቀን
እንደምነህ አንተ ፣
በፍቅር ስብከትህ ፣ የምታቀልጠው ልብ
ትእግስትህ ረቂቅ ፣ ቁርጠኛነትህ ግልብ
ከንብ መንጋ ወጥተህ ፣ የማትናደፍ ንብ
ጧት ማታ ማትሰለች
ሰላም ፍቅር ብለህ ፣ ፀበኞችን መምከር
ከልምጥምጥች ጋር
ከምትለማመጥ ፣
ከአሸባሪዎች ጋር ፣ ከምትከራከር
ለምን አትቆርጥም?
መቼም ደም ለጠማው ፣ ውሃ አይሰጥም
ጳጳሶች አልቅሰው
ሼሆች እንባ ለብሰው ፣ ህዝብ አይገለፍጥም
አቦ አስፈጀኸን
ሚቀለጥሙንን ፣ ቀልጥም ወይ አስቀልጥም።
።።።።

እንደ ምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልኝ የለውጥ ጎዳና
እየተጠቀምን
እንደ ባህር እንቁ ፣ ሟች እየለቀምን
አለንልህ ሰግተን ፣ አለን ለሞት ታጭተን
እንደምነህ አንተ
ፍቅር ፍቅር እያልክ ፣ ምታስፈነክተን
ትእግሰት እያበዛህ
የህዝብህን ትግስት ፣የምትፈታተን
ፍትህ ስንጠይቅ ፣ መግለጫ ምትሰጠን
አንጥረኛን ለቀህ
እኛን እንደብረት ፣ ምታስቀጠቅጠን
አንተ እንደምን አለህ ፣ እኛ አለን ያለ አድሎ
አንድ ሰው ሲከበብ ፣
ሺህ በመንጋው ሞቶ ፣ ሺህ በመንጋው ቆስሎ
አለን ተደምረን
በሰጠህኸን እድል ፣ ኢትዮጵያን አፍቅረን
የማይመጣን ፍትህ
የማይመጣን ሰላም
የማትመጣ ለውጥን ፣በአንድ ላይ ቀጥረን
"ይመጣሉ" እያልን ፣ እንጠብቃለን
አንተ ግን እንዴት ነህ?
አንተ ደህና ከሆንክ ፣ እኛ ስንሰጋ አለን።

እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልኝ የለውጥ ጎዳና
እየተሰበርን "ሰበር" በሚል ዜና
በዘር በዘር ሆነን ፣ እየተደራጀን
የማይተገበር ፣ ህግ እያዘጋጀን
መንገድ ሲዘጋብን...
እግረ መንገዳችን ፣ ህግጋት ተላልፈን
ከደብዳቢ ጋራ
ደብዳቤ እስክንልክ፣ በደማችን ፅፈን
እየተደበደብን ፣ እኛ አለን በተድላ
እንደምነህልን?
እንደምነህልን ካልንህስ በኋላ?!
እኛ አለን በድሎት
ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም
እኛ የምንልህ
"ጥላቻ የጠማው
ፍቅርን ቢግቱት ፣ ጥሙ ከቶ አይቆርጥም
አቦ አስፈጀኸን
ሚቀለጥሙንን ፣ ቀልጥም ወይ አስቀልጥም!
።።።።
እንደምነህ መንግስት
እኛ አለን በስጋት ፥ አንተን ስንነቅፍ ፣አንተኑ ስንደግፍ
ባይቀርልን እንኳ ፣ ይቀራል ያልነው ግፍ
አለን ተደምረን ፣ አለን ተደናብረን
ሀገር ክንፍ አውጥታ
መብረር እንድትችል ፣ እግራችንን ሰብረን
የአንዲት ኢትዮጵያን
ትንሳኤዋን ልናይ ፣ ነፍሳችን ገብረን
አለን ስናነክስ
አለን ስናለቅስ ፣ መኖር እያማረን ።
።።።
እናም የምንልህ
ለውጥ ነውጥ ይዞ ፣ ከመጣ በኋላ
ጥላቻ እንደ ጥላ
ብለን ነበር ያልፋል
ነገር ግን እያደር ፣ጭራሹን ይገዝፋል።
እርግጥ ነው
እውነት ነው
ካምናና ካቻምና ፣ ስናነፃፅረው
በገፍ እና በግፍ ፣ ግፈኛ ያሰረው
ብዙ ሰው ተፈቷል ፣
ኢትዮጵያ ሚለው ስም ፣ ሺህ ጊዜ ተጠርቷል
በጥቂቱም ቢሆን ፣ ተቀርፏል ጭቆና
የማይሆነው ሳይሆን ፣ የሆነው ሆነና
ለውጥ ነውጥ ሆኖ
ከመጣ በኋላ ፣ ስጋት ተባብሷል
የምናውቀው አይጥ ፣ የአንበሳ ለምድ ለብሷል
ሀገር ሀገር ቢሉም ፣ ዘረኝነት ነግሷል
በዝቷል ማፈናቀል
በዝቷል የመንጋ ፍርድ ፣ ተበራክቷል በቀል
ይቻላል ቀላል ነው
በጠራራ ፀሀይ
ሰው በድንጋይ መውገር ፣ ሰው ዘቅዝቆ መሥቀል።
።።
የለም አስታራቂ ፣ የለንም ይቅር ባይ
ዛሬም ሰው ይሞታል ፣ በቀን ባደባባይ
ዛሬም ቁጭት አለ ፣ በነጠላ ጫፍ ላይ።
።።
አገገምን ስንል
አልተገላገልንም ፣ ህመሙ መርቅዟል
በሶ አትብሉ ብሎ ፣ አበበ አውግዟል
ጫላ ጩቤ ጥሎ ፣ ስናይፐር ይዟል።

እኛ የምንልህ
በተገዳዮች ፊት ፣ ገዳይ ካስታመሙ
በተበዳዮች ላይ ፣ በዳይን ከሾሙ
ምንድነው ይቅርታ
ምንድነው ምህረት
የመደመር ሀሳብ ፣ ምንድነው ትርጉሙ ?
ምንድነው እዚ እዛ ፣ ሰው ሚፈናቀለው
ምንድነው እዛ እዚህ ፣ ሰው የሚገደለው
ሚንዲኖ ፀጢታው ፣ ሚንዲኖ ሁካታው
ምን አይነት ፂድቅ ነው
ቀኝ ጉንጪን መስጠት ፣ ግራ ለሚማታው
ፍቅር ለማይገባው
ስለ ፍቅር ብሎ ፣ መታገስ ምንድነው?
ጊራ ጉንጪን ላለ
ግንባር ቀደሙ መልስ ፣ ጊምባሩን ማለት ነው።
እውነታችንን ነው!!!
።።።።።።።።
እንደምነህ መንግስት ፣ እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን ፣ የፍቅር ጎዳና
ሞት እየደገስን
ተገነቡ ሲባል ፣ እየፈራረስን
ተደመርን ስንል ፣እየተቀነስን
እየተጓተትን ፣ በዘር ጅኒ ጃንካ
ዛሬ አለን በስጋት
ነገ ሚሆነውን ፣ ዋቀዮ ሲቤካ።
።።።
እኛ የምንልህ
ከካቻምና በፊት
የነበረን ገዢ ፣ ካቻምና ወቀስን
አምና ስልጣን ያዝን
የካቻምናዎችን ፣ ደም እያፈሰስን
ዘንድሮ በብልሀት ፣
ስልጣን ሀክ አድርገን ፣ ዙፋኑን ወረስን።
ሰይጣኑ ሳይጠፋ
ስልጣኑን ቢይዙት ፣ መች እኛን ፈወሰን
ደም የጠማው ወንበር
በመደመር ማግስት ፣ ደንብሮ ጨረሰን።
እናም የምንልህ
በፍቅር ሲጠመቅ
አልለቅም ያለውን ፣ ፀብ መጥመቅ ያዋጣል
አንዳንዴም አጋንንት
አጋንንቱን ስቦ ፣ በአጋንንት ይወጣል ።
።።።።።
እንደምነህ መንግስት ፣ ስልጣንህ እንዴት ነው
ፍቂርና ምህረት፣ በእርግጥ ጥሩ ነው
ግን ደሞ ግን ደሞ
ሲበዛ ዪመራል ፣ ኣይደለም ተገቢ
ኢንኳንስ የሀገር ገዢ
ግፍን ለሚያበዛ ፣ አዪራራም ረቢ።
።።
እናም የምንልህ
ተገነባን ሲንል ፣ የሚንደን ቶሎ
ተደመርን ስንል ፣ የሚያጎድለን ጎድሎ
አልጠግብ ላለ አካል
እንባ ደማችንን ፣ ላባችንን መጦ
ለሱ ሰላም ሲባል ፣ ህዝቡን አበጣብጦ
ለመኖር ለሚጥር ፣ ሀገሩን በታትኖ
ሆዱን ለሚያሰፋ ፣ ጥላቻን በትኖ
ፍርድ ካልተሰጠው ፣ ምህረት ምንድኖ
ይቅርታ ምንድኖ
የመደመር ሀሳብ ቲርጉሙ ምንድኖ?
።።።
እናም የምንልህ
እሾህ በእሾህ እንጂ ፣ በእሹሩሩ አይወጣም
ፍቅር ያልገባውን
በሚገባው ቋንቋ ፣ ለምን አትቀጣም?
ከእንግዲህ በኋላ
የጨለመበት ህዝብ
ፀሐይ ለሰረቀው ፣ ሻማ አያዋጣም!!!

በመጨረሻም #ሼር በማድረግ ደብዳቤውን ለመንግስት አድርሱ😁


@getem
@getem
@getem
ብለሽኝ ነበረ

"ጎስቁሎ ቢያገኘው እዳፊው ደርቶ
ጊዜ ይደግፋል ~ ልብሱ ለቀጨመ ላመዳም ቡትቶ"

እኔም እልሻለሁ
ፀዳድቶ ካገኘው ~ ግንባሩ ወርዝቶ
ጊዜ የሚመቸው ~ ለባለጊዜ ነው ፊቱን እጁን አይቶ

እባክሽ ውዴ ሆይ
የቂል ማጽናኛሽን ~ ካመድ ደባልቂና ወደ ጓሮሽ ጣይው
ፋይዳ ቢስ ተረትሽን ~ በጊዜ መስታወት አገላብጠሽ እይው።

✍️አወቀ ካሳው
.............…
#ሼር

@getem
@getem
@getem
እስቲ የገጣሚ ሶሎሞን ሳህለን "ያማል" ወደ ወቅታዊ ጉዳይ እንከርብታት
(በላይ በቀለ ወያ) #ሼር ይደረግ

እና እንደ ነገርኩሽ
ሀገር አሸባሪን
ወታደሮች ቀጥሮ ፣ልክ እንደማስጠበቅ
በቄሮዎች ዱላ ፣ ተመቶ እንደመውደቅ
ሬሳ ሲጎተት ፣ አይቶ እንደመሳቀቅ
ለውጡ "ውጡ" ብሎ ፣ ጎዳና እንደመውደቅ
ስቃይ በበዛባት ፣ በዚች ቧልተኛ ሀገር
ከዚህ የበለጠ ፣ የለም ሚያም ነገር።
ዘረኝነት ያማል
የመንጋ ፍርድ ያማል
ሜንጫ ዱላው ያማል
ምስኪን መግደል ያማል
ጳጳስ ሲያለቅስ ያማል
መስጂድ ማፍረስ ያማል
ካህን ማረድ ያማል
መንገድ መዝጋት ያማል
የማይጎድል ፣ የዘር ጎርፍ ፣ የደም ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ቤተስኪያን ማጋየት ፣ ንብረት ማቃጠሉ
በድንጋይ ተወግሮ ፣ ድሀ መገደሉ
ምን ብዬ ልንገርሽ ፣ ያማል ይሄ ሁሉ!
።።።
እና እንደ ነገርኩሽ
ቄሮ ሚወደውን ፣ ሌላው ካልወደደ
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፣ ሌላ ሀገር ከሄደ
ነገር ተበላሸ ፣
ሀገር ተረበሸ
ጭካኔና በቀል ፣ በግፍ ተወለደ
መንገዱ ተዘጋ ፣ ምስኪኑ ታረደ
ተርፎ ይህን ያየ ፣ጨጓራው ነደደ
አንጀቱ በገነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ተከበብኩኝ ብሎ
አንድ ሰው በቃዠው ፣ ከእንቅልፉ ሳይነቃ
ሁሉም ተቀይሮ ፣ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ!
።።
ፈንካች ተፈንካቹ
ገዳዩና ሟቹ
እብሪቱ ጥጋቡ
ያለምንም ምክንያት ፣ የጠፋበት ግቡ
ከመርፌ ቀዳዳ ፣ አእምሮ መጥበቡ
በቆራጭ ሜንጫ ፊት ፣ እልፍ አንገት መቅረቡ
ውል የሌለው ቅዠት ፣የተኛን መክበቡ
እልፍ አእላፍ በደል ፣ መግለጫን ማጀቡ
ደሞ ለሱ ግጥም ፣እናቱን መግለጫ
ምንብዬ ልንገርሽ ፣
ይሄ ሁሉ ነገር ፣ ያማል እንደ ሜንጫ።
።።።
እና እንደ ነገርኩሽ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ግራ ወይ ቀኝ እግሩ
የሌላ ሀገር ምድርን ፣ ልክ እንደረገጠ
አንዱ መንገድ ዘጊ ፣ ወደኔ አፈጠጠ
ዱላ የጨበጠ ፣ አንድ እጁን ሰንዝሮ
በአንድ እጁ ደግሞ ፣ ድንጋይ ተወራውሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…?? ፣ ደረቱን ወጥሮ!
ምን ልታዘዝ ይላል?
እንዴት መንገደኛ ፣ መንገድ ዘጊን ያዛል?!
ክፍት መንገድ ልዘዝ?
አንዲት ሀገር ልዘዝ?
አንድ ፍቅር ልዘዝ?
አንድ ሰላም ልዘዝ?

@getem
@getem

#getem le hulum
ታርጌት የ ሥዕል ትምህርት ቤት
Target art academy

🔵ከ 10 ዓመት በላይ ሥዕልን በሚገባ የማስተማር ልምድ እና ችሎታ ባላቸው ድንቅ የሆኑ ሠዓሊ መምህራን የምትማሩበት የሥዕል ትምህርት ቤት ።
ሥልጠናዎቹ መሰረታዊ የሥዕል ቋንቋ ግንዛቤን ያካተቱ ሲሆን
ለህፃናት እና ታዳጊዎች
ለሙያ መመዘኛ ተፈታኞች (የሙሉ ጊዜ)
ለ ስነ ጥበባት ት/ቤት መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ
ለ ኪነ ህንፃ ተማሪዎች እና ለመላው ለሥዕል አፍቃሪያን በሙሉ በተመጣኝ የትምህርት ክፍያ ይምጡና የሥዕል ጥበብን ተማሩ።

#አድራሻ: ካሳንቺስ ከ ዮናስ ጨርጨር ስጋ ቤት ዝቅ ብሎ
📞. 0911209246
0911248947
0910559131

#ሼር ሥዕል መማር ለሚፈልጉ ሁሉ
@seiloch
@seiloch
👍1
ሰላም!

የሰላምን ጥቅም ለማወቅ የግድ የጦርነት ቀጠና ውስጥ መሆን አይጠበቅብንም የጦርነት አስከፊነት ለማወቅም የጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ መሆን እኮ አይጠበቅብንም።

ሰላም ማለት የጦርነት አለመኖር ብቻ አይደለም ይልቁንም ጦርነት ሳይኖር በመካከላችን የሚኖሩትን ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን በውይይትና በንግግር ፈተን [በጋራ መኖር ጭምር እንጅ...ዞሮ ዞሮ ግን ሰላም ከጦርነት ይልቅ እጅግ የተሻለ ነገር እንደሆነ አውቃለሁ አምናለሁም።

# ሀገራችን በጣም አስቀያሚ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ገብታለች በሁለቱም ጎራ ያሉት ወንድሞቻችን ናቸው አብረን በልተናል አብረን ሁሉን ነገር ተጋርተናል ዛሬ ግን ሁሉም ጎራ ከፍሎ በዚህ በቆሻሻ ፖለቲካ የሰው ልጅ በሁለቱም በኩል እየረገፈ ነው። እናም እባካቹ እዚህ ቻናል ላይ ያላቹ ቤተሰቦች ከጊዜ ወደጊዜ ጦርነቱ የሁላችንም ቤት ማንኳኳቱ የማይቀር ነው እናም #አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ቻሌንጅ እንጀምር ለጊዜው ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። በቻልነው አቅም ስለ ሰላም እንጩህ......የዘመቻው መምሪያ ቃል "Ubuntu" ይባላል በዚህ ሀሳብ የሚስማማ ሁሉ ይሄን ቃል በመጠቀም ዘመቻውን ይጀምር። #ሼር ይደረግ..!


ናካይታ💚💛❤️ ለሀገራችን!

#እስከዛሬም ዝም በማለቴ ይቅር በሉኝ!🙏

@getem
@getem
@Nagayta