(ለአምባዬ ጌታነህ እና ለጃኖ እንዲሁም ስለሀገር እና ብሔር... ለሚጽፉ መልስ)
#ዓለም_ናት_ሀገሬ
፡
"ኢትዮጵያዊያን ነን
ሁሉም የሚያውቀን በደግነታችን
ወጥ ድንጋይ ቀርጸን ሀውልትን ያቆምን..."
እያልክ አትሸንግለኝ
"የጥቁሮች ኩራት
የጀግና ሕዝብ እናት
ድንግል አፈር ድንግል መሬት..."
ብለህ አታቁስለኝ
"ኢትዮጵያ አንድ ናት
ዘር ብሔር ያልሻራት
በጎሳ በዘር ፡ አንፋሰስ ደም
እንኑር በፍቅር ፡ እንኑር በሰላም"
ብለህ አትንገረኝ
"ኩሽ ብሔር የለውም" እያልክ አትፎግረኝ
፡
በል እንግዲህ ስማኝ...
፡
አምላክ አዳምን ሲፈጥረው
በላብህ ብላ ብሎ ሲያዘው
ኢትዮጵያ ኑር አላለው
እስራኤል ኑር አላለው
"ምድር ታብቅልብህ አሜኬላ
አንተም ጥረህ ግረህ ብላ"
ነበር ያለው።
፡
ስማኝ ወንድሜ ሆይ፡
እንኳን ላስብ ስለዘር ብሔሬ
አልሻም ማውራት ስለሀገሬ
ምን ናትና የምሞተው ለአህጉሬ
የእኔስ 'ዓለም' ናት፡ ርስቴና ክብሬ
ለገነት መግቢያ ፡ ጊዜያዊ መንበሬ።
፡
ክርስቶስን አስብ
ቤተ ልሔም ተወልዶ በናዝሬት ያደገው
በዚያ ስለኖረ 'ኤዥያዊ' ልትል ነው?
ወይስ...
"ኢትዮጵያ ስለመጣ ስለባረካት በስደቱ
የለም ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነው በዜግነቱ"
ልትል ነው?
ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ አይደለም
ኤዥያዊም አይደለም
እሱስ የ'ዓለም' ነው ፡ ስሙም መድኃኔዓለም
፡
ፍጡሩን እናንሳ ፡ የአምላኩን ትተን
አይቴ ብሔሩ ፡ ለሊቁ አንስታይን
አሜሪካ ፡ ወይስ ጀርመን?
ኒው ዮርክ ፡ ወይስ ዋሽንግተን?
ሙኒክ ፡ ወይስ በርሊን?
የለም...
የአንጻራዊነት ፡ ምሥጢርን የፈታው
ሐሳብን ከገሀድ ፡ በአንድ ያዋኃደው
የሀገር አይደለም ፡ የ'ዓለም' ሀብት ነው።
፡
እስቲ አስብ ወንድሜ፡
አንገትህን ወደላይ ፡ ወደሰማይ አቅና
እየመጣ ቢሆን ፡ UFO ከደመና
ምድርን ሊቆጣጠር ፡ ግዛቱን ሊያቀና
ያኔ የአዳም ዘር ፡ ያስባል ወይ ብሔር?
ያስባል ወይ ሀገር ፡ ያስባል ወይ አህጉር?
የለም...
ክፍልፍሏ ዓለም ፡ ትሆናለች መንደር
ሰው ሁሉ ያብራል ፡ እንዲኖር የሰው ዘር
ይፈጠራል ትውልድ ፡ ለ'ዓለም' የሚኖር
፡
ስለዚህ ወንድሜ
መኖርያህ 'ዓለም' ናት ፡ አትስበክ ስለሀገር
የ'ዓለም' ንብረት ነህ ፡ አትጻፍ ስለብሔር
(ከተሳሳትኩ እታረማለሁ 📝ል.ግ.ኢ)
@getem
@getem
@getem
#ዓለም_ናት_ሀገሬ
፡
"ኢትዮጵያዊያን ነን
ሁሉም የሚያውቀን በደግነታችን
ወጥ ድንጋይ ቀርጸን ሀውልትን ያቆምን..."
እያልክ አትሸንግለኝ
"የጥቁሮች ኩራት
የጀግና ሕዝብ እናት
ድንግል አፈር ድንግል መሬት..."
ብለህ አታቁስለኝ
"ኢትዮጵያ አንድ ናት
ዘር ብሔር ያልሻራት
በጎሳ በዘር ፡ አንፋሰስ ደም
እንኑር በፍቅር ፡ እንኑር በሰላም"
ብለህ አትንገረኝ
"ኩሽ ብሔር የለውም" እያልክ አትፎግረኝ
፡
በል እንግዲህ ስማኝ...
፡
አምላክ አዳምን ሲፈጥረው
በላብህ ብላ ብሎ ሲያዘው
ኢትዮጵያ ኑር አላለው
እስራኤል ኑር አላለው
"ምድር ታብቅልብህ አሜኬላ
አንተም ጥረህ ግረህ ብላ"
ነበር ያለው።
፡
ስማኝ ወንድሜ ሆይ፡
እንኳን ላስብ ስለዘር ብሔሬ
አልሻም ማውራት ስለሀገሬ
ምን ናትና የምሞተው ለአህጉሬ
የእኔስ 'ዓለም' ናት፡ ርስቴና ክብሬ
ለገነት መግቢያ ፡ ጊዜያዊ መንበሬ።
፡
ክርስቶስን አስብ
ቤተ ልሔም ተወልዶ በናዝሬት ያደገው
በዚያ ስለኖረ 'ኤዥያዊ' ልትል ነው?
ወይስ...
"ኢትዮጵያ ስለመጣ ስለባረካት በስደቱ
የለም ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነው በዜግነቱ"
ልትል ነው?
ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ አይደለም
ኤዥያዊም አይደለም
እሱስ የ'ዓለም' ነው ፡ ስሙም መድኃኔዓለም
፡
ፍጡሩን እናንሳ ፡ የአምላኩን ትተን
አይቴ ብሔሩ ፡ ለሊቁ አንስታይን
አሜሪካ ፡ ወይስ ጀርመን?
ኒው ዮርክ ፡ ወይስ ዋሽንግተን?
ሙኒክ ፡ ወይስ በርሊን?
የለም...
የአንጻራዊነት ፡ ምሥጢርን የፈታው
ሐሳብን ከገሀድ ፡ በአንድ ያዋኃደው
የሀገር አይደለም ፡ የ'ዓለም' ሀብት ነው።
፡
እስቲ አስብ ወንድሜ፡
አንገትህን ወደላይ ፡ ወደሰማይ አቅና
እየመጣ ቢሆን ፡ UFO ከደመና
ምድርን ሊቆጣጠር ፡ ግዛቱን ሊያቀና
ያኔ የአዳም ዘር ፡ ያስባል ወይ ብሔር?
ያስባል ወይ ሀገር ፡ ያስባል ወይ አህጉር?
የለም...
ክፍልፍሏ ዓለም ፡ ትሆናለች መንደር
ሰው ሁሉ ያብራል ፡ እንዲኖር የሰው ዘር
ይፈጠራል ትውልድ ፡ ለ'ዓለም' የሚኖር
፡
ስለዚህ ወንድሜ
መኖርያህ 'ዓለም' ናት ፡ አትስበክ ስለሀገር
የ'ዓለም' ንብረት ነህ ፡ አትጻፍ ስለብሔር
(ከተሳሳትኩ እታረማለሁ 📝ል.ግ.ኢ)
@getem
@getem
@getem
👍3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጉኖ ዘበናይ በአያ ሙሌ አጠራር
መልካም ልደት ስንዱ አበበ🎂🎂🎂
ዕለተ ፋሲካ
በትንሳዔ ማግስት
ታየች የልጅ ንግስት
ዘነበ ወላ ስለ ስንዱ ሲናገር ብዙ ነገር ሰርታ ብዙ ነገሮች አበርክቶት አድርጋ አንድም ሰው
ሲያመሰግናት ባከመስማቴ ሀዘንተኛ ነኝ ስንዱ ቁጡም ናት ደግም ናት ብቻ ስንዱን
አዎዳታለሁ ይላል።
አንድ ጊዜ አንዱ ፀሀፊ ተስፋ ሲቆርጥ አይታው በቃ ለኔ ፃፊልኝ አለችው እየፃፈ ይሰጣት
ነበር እሷም ጠርዛ ለህትመት እንዲበቃ አድርጋ ሰጠችው ሰውየው በዛው ታዋቂ ሆነ
ምስጋና ሲቀርብ አልታየም። የልፋትን ከፈይ እግዜር ነውና እሷ ግድም የላት።
እንዲህ ጉኖ እንዲህና ከዚህም በላይ ናት በኢትዮጵያ ስነ ፁሁፍ ገልህ ድርሻ አላት። እኔ
ሳውቃት እንደዚሁ ምርጥ ፀሁፍ ስታገኝ እንካ ተመገብ የምትል የጥበብ ንግስት።
ቅኔ
እንዲህም ናት
ብንል……
እንዲያም ናት
ብንላት……
እግዜር የዘረፋት
ስንዱ ቅኔ ናት
መልካም ልደት Senedu Abebe ጉኖ ዘበናይ ስኒትዬ
ስላንቺ መግለፅ ከባድ ነው ባልገልፅሽል ልደትሽን ለማክበር ያህል የኔ ሻሀራዳዝ
በነፍስሽ ስትዘምሪ
በፍቅር አሳምሪ
ጉኖዬ ዘበናይ
የልቤ አሸወይናይ………………
እድሜ እና ጤና ይብዛልሽ ጉኖዋ መልካም ልደት🎂🎂🎂
@getem
@getem
@balmbaras
መልካም ልደት ስንዱ አበበ🎂🎂🎂
ዕለተ ፋሲካ
በትንሳዔ ማግስት
ታየች የልጅ ንግስት
ዘነበ ወላ ስለ ስንዱ ሲናገር ብዙ ነገር ሰርታ ብዙ ነገሮች አበርክቶት አድርጋ አንድም ሰው
ሲያመሰግናት ባከመስማቴ ሀዘንተኛ ነኝ ስንዱ ቁጡም ናት ደግም ናት ብቻ ስንዱን
አዎዳታለሁ ይላል።
አንድ ጊዜ አንዱ ፀሀፊ ተስፋ ሲቆርጥ አይታው በቃ ለኔ ፃፊልኝ አለችው እየፃፈ ይሰጣት
ነበር እሷም ጠርዛ ለህትመት እንዲበቃ አድርጋ ሰጠችው ሰውየው በዛው ታዋቂ ሆነ
ምስጋና ሲቀርብ አልታየም። የልፋትን ከፈይ እግዜር ነውና እሷ ግድም የላት።
እንዲህ ጉኖ እንዲህና ከዚህም በላይ ናት በኢትዮጵያ ስነ ፁሁፍ ገልህ ድርሻ አላት። እኔ
ሳውቃት እንደዚሁ ምርጥ ፀሁፍ ስታገኝ እንካ ተመገብ የምትል የጥበብ ንግስት።
ቅኔ
እንዲህም ናት
ብንል……
እንዲያም ናት
ብንላት……
እግዜር የዘረፋት
ስንዱ ቅኔ ናት
መልካም ልደት Senedu Abebe ጉኖ ዘበናይ ስኒትዬ
ስላንቺ መግለፅ ከባድ ነው ባልገልፅሽል ልደትሽን ለማክበር ያህል የኔ ሻሀራዳዝ
በነፍስሽ ስትዘምሪ
በፍቅር አሳምሪ
ጉኖዬ ዘበናይ
የልቤ አሸወይናይ………………
እድሜ እና ጤና ይብዛልሽ ጉኖዋ መልካም ልደት🎂🎂🎂
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
ጆሮ የጠፋ እለት!!!!!!!
አየሁት ሃገሩን ከቆላ እስከደጋ ፤
ወሬ እየደገሱ ፤
ይህን የኔ አገር ሰው ፤
ሆ ያሉት እንደሆን ፤
እየኮለኮሉት በሰፈር በሪጋ ፤
ልቡ ቡልሃ ነው ፤
ሆ ብሎ ይነሳል፤
ይኸ የሰው ጅረት ይኸ የሰው መንጋ ።
በኒ አደምን ሁሉ ፤
ጀሊሉ ሲኸልቀው፤
አፉን አንድ ሽንቁር ፤
ጆሮን ሁለት ሽንቁር አርጎ ያበጃጀው ፤
ብዙ እንድናዳምጥ ፤
ሙጫ እንድንናገር ፤ እንድንሶብር ነው ።
ባይሆን በኛ ምድር ፤
በምላስ ገበያ ፤
እኔ እኔ ልደስኩር፤
እኔ ብቻ ላውራ ፤
የሚል የአፍ ነጋዴ ሰርክ እየተጋፋ፤
እኔን ስሙኝ እንጅ ፤
ላውራ የሚል እንጅ የሚያደምጠን ጠፋ ።
እንዲህ የሆነ እለት ፤
ጆሮ የጠፋለት በወዲያ በወዲህ ምላስ ሲበረታ ፤
አሊም አያሽረው ፤
ጥይት አይዳኘውም የወሬን በሽታ ፤
ይልቅ እንዳገሬ ፤
እጆቼን ዘርግቼ ፤
ዱኣ ልቀማመጥ ፤
የቀልቤን ልንገረው ለሰማዩ ጌታ፤
በዚያ በኔ ግድም ፤
ከደገር ደባትይ ከየጁ እስከ ገታ ፤
በሙፍቲዎች ኪታብ በወልዮች ቱፍታ ፤
አይቻለሁና ፤
ወሬ የቋጠረው ድሪቶና ጉንጉን በዱኣ ሲፈታ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!!💚
@getem
@getem
@balmbaras
አየሁት ሃገሩን ከቆላ እስከደጋ ፤
ወሬ እየደገሱ ፤
ይህን የኔ አገር ሰው ፤
ሆ ያሉት እንደሆን ፤
እየኮለኮሉት በሰፈር በሪጋ ፤
ልቡ ቡልሃ ነው ፤
ሆ ብሎ ይነሳል፤
ይኸ የሰው ጅረት ይኸ የሰው መንጋ ።
በኒ አደምን ሁሉ ፤
ጀሊሉ ሲኸልቀው፤
አፉን አንድ ሽንቁር ፤
ጆሮን ሁለት ሽንቁር አርጎ ያበጃጀው ፤
ብዙ እንድናዳምጥ ፤
ሙጫ እንድንናገር ፤ እንድንሶብር ነው ።
ባይሆን በኛ ምድር ፤
በምላስ ገበያ ፤
እኔ እኔ ልደስኩር፤
እኔ ብቻ ላውራ ፤
የሚል የአፍ ነጋዴ ሰርክ እየተጋፋ፤
እኔን ስሙኝ እንጅ ፤
ላውራ የሚል እንጅ የሚያደምጠን ጠፋ ።
እንዲህ የሆነ እለት ፤
ጆሮ የጠፋለት በወዲያ በወዲህ ምላስ ሲበረታ ፤
አሊም አያሽረው ፤
ጥይት አይዳኘውም የወሬን በሽታ ፤
ይልቅ እንዳገሬ ፤
እጆቼን ዘርግቼ ፤
ዱኣ ልቀማመጥ ፤
የቀልቤን ልንገረው ለሰማዩ ጌታ፤
በዚያ በኔ ግድም ፤
ከደገር ደባትይ ከየጁ እስከ ገታ ፤
በሙፍቲዎች ኪታብ በወልዮች ቱፍታ ፤
አይቻለሁና ፤
ወሬ የቋጠረው ድሪቶና ጉንጉን በዱኣ ሲፈታ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!!💚
@getem
@getem
@balmbaras
ከዳና እስከ ደገር፤ ከሾንኬ እስከ ገታ ፤
ከየጁ ውድመን፤ ከቃሉ እስከ ተንታ ፤
ሲመረቅ ያደገው፤
በአሊሞቹ ኪታብ በወልዮች ቱፍታ ፤
ደግሞ ሊደርብ ነው ፤
የአስኮላውን ጋቢ የአስኮላውን ኩታ።
ገና ከማለዳው ፤
በደገሮች ዱኣ ፤
እየተመረቀ ያደገው ደረሳ የዱኣው ምስለኔ ፤
እንደለመደበት ፤
ሊመረቅ ነው አሉኝ ደርባባው አበሻ ሸህ ኡመር ቦረኔ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
እንዳ አባባ ሼህ ኡመር ኢድሪስን ያማረ ቅዳሜ ትሁንልን!!!!
@getem
@getem
@balmbaras
ከየጁ ውድመን፤ ከቃሉ እስከ ተንታ ፤
ሲመረቅ ያደገው፤
በአሊሞቹ ኪታብ በወልዮች ቱፍታ ፤
ደግሞ ሊደርብ ነው ፤
የአስኮላውን ጋቢ የአስኮላውን ኩታ።
ገና ከማለዳው ፤
በደገሮች ዱኣ ፤
እየተመረቀ ያደገው ደረሳ የዱኣው ምስለኔ ፤
እንደለመደበት ፤
ሊመረቅ ነው አሉኝ ደርባባው አበሻ ሸህ ኡመር ቦረኔ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
እንዳ አባባ ሼህ ኡመር ኢድሪስን ያማረ ቅዳሜ ትሁንልን!!!!
@getem
@getem
@balmbaras
ደግሞ ተሸለሙ!!!!!
የአበሻው አልሃዝሃር፣ ወሎ ማር ዘነቡ፣
አያወላውልም ፣
ለጦቢያ የሚበቃ፣ ሃቅ ነው ኪታቡ።
አራት አይናዎቹ፣
ሸሆቼ በሙሉ፣
በፊትና ገበያ፣ ሃያት የቀናቸው፣
አይቻለሁ ባይኔ፣
የቁርአን አርበኛ ፣ የእሱ ባሮች ናቸው፣
እንኳን ለማጀቱ፣
ላገር የሚበቃ፣ ኑር የከበባቸው፤
ሃገር ሰርቶ ያድራል፤
ጎጆ ይጠግናል ወልይነታቸው ።
ዛሬም ደጋጎቹ ፤
ደግሞ ተሸለሙ ደግሞ ተሸለሙ ፤
ያበሾቹ ኪታብ ልዩ ነው ሙሃባው ልዩ ነው ቀለሙ ።
እኒያ መሻኢኮች ፤
በራብ አንጀታቸው ፤
ዱኒያን አሸንፈው ከጀሊሉ ዘንዳ ተሻግረው ነበረ ፤
ያ ሁሉ ስራቸው በሙፍቲ ሸህ ኡመር ዛሬ ተሞሸረ ።
ይህ ሁሉ አጃኢበት ፤
ይኸ ሁሉ ደስታ ፤
ዛሬ የተገኘው በነገስታት ፊት ፤
እምባ ፈሶበት ነው በዱኣ በዚክር በቀን በሌሊት ፤
ገለታ ይድረሰው ለአለሙ ጌታ ቢነይት ቢነይት ለማይጎድልበት ።
አሁንም ጓዴ ሆይ ፤
ኧረ ተወኝ ጓዴ፣
ተወኝ ልሂድበት፣
አውቀዋለሁ እኔ፣ የኢልሙን ጎዳና፣
ወዘናው ማርኮኛል ፤
የነ ሙፍቲ መንገድ ያበሾቹ ዳና ፤
ቱፍታ ያወረዛው ፤
የሃያትን ሽቶ ፣ የኢማንን ጥፍጥና፣
ደገር ቦረና ላይ ፤
ዳና ከጀማው ስር፣ ቀምሻለሁና።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
የአበሻው አልሃዝሃር፣ ወሎ ማር ዘነቡ፣
አያወላውልም ፣
ለጦቢያ የሚበቃ፣ ሃቅ ነው ኪታቡ።
አራት አይናዎቹ፣
ሸሆቼ በሙሉ፣
በፊትና ገበያ፣ ሃያት የቀናቸው፣
አይቻለሁ ባይኔ፣
የቁርአን አርበኛ ፣ የእሱ ባሮች ናቸው፣
እንኳን ለማጀቱ፣
ላገር የሚበቃ፣ ኑር የከበባቸው፤
ሃገር ሰርቶ ያድራል፤
ጎጆ ይጠግናል ወልይነታቸው ።
ዛሬም ደጋጎቹ ፤
ደግሞ ተሸለሙ ደግሞ ተሸለሙ ፤
ያበሾቹ ኪታብ ልዩ ነው ሙሃባው ልዩ ነው ቀለሙ ።
እኒያ መሻኢኮች ፤
በራብ አንጀታቸው ፤
ዱኒያን አሸንፈው ከጀሊሉ ዘንዳ ተሻግረው ነበረ ፤
ያ ሁሉ ስራቸው በሙፍቲ ሸህ ኡመር ዛሬ ተሞሸረ ።
ይህ ሁሉ አጃኢበት ፤
ይኸ ሁሉ ደስታ ፤
ዛሬ የተገኘው በነገስታት ፊት ፤
እምባ ፈሶበት ነው በዱኣ በዚክር በቀን በሌሊት ፤
ገለታ ይድረሰው ለአለሙ ጌታ ቢነይት ቢነይት ለማይጎድልበት ።
አሁንም ጓዴ ሆይ ፤
ኧረ ተወኝ ጓዴ፣
ተወኝ ልሂድበት፣
አውቀዋለሁ እኔ፣ የኢልሙን ጎዳና፣
ወዘናው ማርኮኛል ፤
የነ ሙፍቲ መንገድ ያበሾቹ ዳና ፤
ቱፍታ ያወረዛው ፤
የሃያትን ሽቶ ፣ የኢማንን ጥፍጥና፣
ደገር ቦረና ላይ ፤
ዳና ከጀማው ስር፣ ቀምሻለሁና።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
*ምፅውት-ሕመም**(ልዑል ሀይሌ)
.
ሕመም ተ-ው-ሻ-ለ-ሁ
ራስ ከታመመ ሠው፤
ማይማር ገላዬ
ስቃይ እንዲደርሰው፤
በሕመም ያለፈ
ሲሽር ሲጠነክር ዘመናት ታዝቤ፤
ሕመም ተመፀወትኩ
በፈውስ ፍለጋ ብርታትን አስቤ፤
.
(ይኸው ምፅውት ሕመም...)
.
ስቃይን ከስቃይ እየተለካካሁ፤
ሠውነቴን ላውጅ በሕመም ተመካሁ፤
ምንም ብድር ሕመም
ባያም' እንደመፅዋች እንዳበደረው ሰው፤
ላፍታም አያስተኛም
መድኃኒት ፍለጋ እ-የ-ቀ-ሰ-ቀ-ሰ-ው፤
.
(ይኸው ቀሰቀሰኝ...)
.
ከየቅጠሉ ላይ ከየስራስሩ፤
ሕልሞች ይታዩኛል
የኔን ሐኪምነት የሚመሠክሩ፤
.
ልበጥስ ያን ቅጠል
ልንቀለው ያንን ስር፤
ያድነኝ እንደሆን
ከገባሁበት ማጥ ከሠው ሕመም እስር፤
.
ልፈልግ ድኅነቴን
ልፈልግ ድኅነቱን ለመፅዋች ታማሚ፤
ምፅውት ሕመም ያ'ርገኝ መድኃኒት ቀማሚ፤
.
(ይኸው ቅመማዬ...)
.
ሕመም አይጥፋ እንጂ
መድኃኒት አይጠፋም፤
ስቃይ የበዛበት
ፈውስ ያስባል እንጂ ላፍታ አያንቀላፋም፤
.
እኔም የሠው ሕመም
ተመፅውቼ ያደርኩ የጊዜ ታማሚ፤
ፈውሱን ነው 'ምከፍለው
ሕመም ስላ'ረገኝ መድኃኒት ቀማሚ፤
5/11/2011
መቐለ
@getem
@getem
@getem
.
ሕመም ተ-ው-ሻ-ለ-ሁ
ራስ ከታመመ ሠው፤
ማይማር ገላዬ
ስቃይ እንዲደርሰው፤
በሕመም ያለፈ
ሲሽር ሲጠነክር ዘመናት ታዝቤ፤
ሕመም ተመፀወትኩ
በፈውስ ፍለጋ ብርታትን አስቤ፤
.
(ይኸው ምፅውት ሕመም...)
.
ስቃይን ከስቃይ እየተለካካሁ፤
ሠውነቴን ላውጅ በሕመም ተመካሁ፤
ምንም ብድር ሕመም
ባያም' እንደመፅዋች እንዳበደረው ሰው፤
ላፍታም አያስተኛም
መድኃኒት ፍለጋ እ-የ-ቀ-ሰ-ቀ-ሰ-ው፤
.
(ይኸው ቀሰቀሰኝ...)
.
ከየቅጠሉ ላይ ከየስራስሩ፤
ሕልሞች ይታዩኛል
የኔን ሐኪምነት የሚመሠክሩ፤
.
ልበጥስ ያን ቅጠል
ልንቀለው ያንን ስር፤
ያድነኝ እንደሆን
ከገባሁበት ማጥ ከሠው ሕመም እስር፤
.
ልፈልግ ድኅነቴን
ልፈልግ ድኅነቱን ለመፅዋች ታማሚ፤
ምፅውት ሕመም ያ'ርገኝ መድኃኒት ቀማሚ፤
.
(ይኸው ቅመማዬ...)
.
ሕመም አይጥፋ እንጂ
መድኃኒት አይጠፋም፤
ስቃይ የበዛበት
ፈውስ ያስባል እንጂ ላፍታ አያንቀላፋም፤
.
እኔም የሠው ሕመም
ተመፅውቼ ያደርኩ የጊዜ ታማሚ፤
ፈውሱን ነው 'ምከፍለው
ሕመም ስላ'ረገኝ መድኃኒት ቀማሚ፤
5/11/2011
መቐለ
@getem
@getem
@getem
በ ቅርፅ ምሳተፍበት አውደ ርዕይ አቢቹ ራሱ!!! በታላቅ አክብሮት ተጋብዛቸዋል.....!!!
@artbekiyechalal
@artbekiyechalal
@artbekiyechalal
@artbekiyechalal
@artbekiyechalal
@artbekiyechalal
___ትንፋሼ___________
የህይወትን ፈረስ ጋማ ይዤ
ሽቅብ ስጋልብ የልቤን ልጓም ጓምጄ
በገብረ ጉንዳን ተምሳሌት ሌት እና ቀኑን ተግቼ
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል በረሀ ሐሩሩን ፈስሼ
የናይልን ወንዝ ፈር ይዤ
ከባህር ጣዎት ከምስራቅ ነፋስ ታግዬ
ሞክሬ ነበር ልጸና...
ምሰሶ ላቆም ጎጆ ልቀልስ ላቀና
ግን ምን ያደርጋል ደቀቅኩኝ
በቅዝቃዜ ቆርፍጄ በእቶን እንዳለ ጥቂት ስብ
እየተጋጋምኩ ቀለጥኩኝ
መቆም አቃተው ወደቀ መርከቤም ተሰባበረ
ደግፎ የያዘኝ መልዕቅ ተበጣጠሰ ወደቀ
ሽቅብ ጋላቢው ፈረስም ድንገት በርግጎ በረረ
ብቻዬን ሆንኩኝ ተረሳው
ባህሩ ዋጠኝ ሰጠምኩኝ
ላልወጣ ገባው ተዋጥኩኝ
ለዚህ ሁሉ ግን ምክኒያቱ አውሎው አይደለ ነፋሱ
ሰምቶ አይደለም የጦር ድምፅ የኮበለለው ፈረሱ
ከምስራቅ አውሎ የበረታ
ከጦር ድምፅ እጅግ የላቀ
መልዕቅ በጥሶ የጣለ
መርከብ የሰባበረ
ከራሴ ወጥቶ እኔኑ የወጋኝ
የራሴው ትንፋሽ ነበረ
<<<<< ኑዛዜ >>>>>
በዚህች አጭር የህይወት ጎዳና
ላልፍ ሞከርኩኝ ብዙ ፈተና
የዕድሜ ማህበር ባዘጋጀው መብል
ተጎንጭቻለው የመከራን ጠበል
ትንሽ ብትሆንም ብዙ አይቻለው (እንደ እኔ)
በገባኝ ልክ ብዙ አውቄያለው
እናም እናቴ...
በህይወት እያለው በቁሜ ሞቼ
ፅፌልሻለው ይሄን ኑዛዜ
" በራሴ የህይወት ሩጫ ተሸንፌያለው
እስካለው ድረስ ላንቺ እኖራለው።"
ተፃፈ
ግንቦት 06/2011
ሐዋሳ IOT dorm 422
አብርሃም እንዳለ ገዳ
@getem
@getem
@getem
የህይወትን ፈረስ ጋማ ይዤ
ሽቅብ ስጋልብ የልቤን ልጓም ጓምጄ
በገብረ ጉንዳን ተምሳሌት ሌት እና ቀኑን ተግቼ
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል በረሀ ሐሩሩን ፈስሼ
የናይልን ወንዝ ፈር ይዤ
ከባህር ጣዎት ከምስራቅ ነፋስ ታግዬ
ሞክሬ ነበር ልጸና...
ምሰሶ ላቆም ጎጆ ልቀልስ ላቀና
ግን ምን ያደርጋል ደቀቅኩኝ
በቅዝቃዜ ቆርፍጄ በእቶን እንዳለ ጥቂት ስብ
እየተጋጋምኩ ቀለጥኩኝ
መቆም አቃተው ወደቀ መርከቤም ተሰባበረ
ደግፎ የያዘኝ መልዕቅ ተበጣጠሰ ወደቀ
ሽቅብ ጋላቢው ፈረስም ድንገት በርግጎ በረረ
ብቻዬን ሆንኩኝ ተረሳው
ባህሩ ዋጠኝ ሰጠምኩኝ
ላልወጣ ገባው ተዋጥኩኝ
ለዚህ ሁሉ ግን ምክኒያቱ አውሎው አይደለ ነፋሱ
ሰምቶ አይደለም የጦር ድምፅ የኮበለለው ፈረሱ
ከምስራቅ አውሎ የበረታ
ከጦር ድምፅ እጅግ የላቀ
መልዕቅ በጥሶ የጣለ
መርከብ የሰባበረ
ከራሴ ወጥቶ እኔኑ የወጋኝ
የራሴው ትንፋሽ ነበረ
<<<<< ኑዛዜ >>>>>
በዚህች አጭር የህይወት ጎዳና
ላልፍ ሞከርኩኝ ብዙ ፈተና
የዕድሜ ማህበር ባዘጋጀው መብል
ተጎንጭቻለው የመከራን ጠበል
ትንሽ ብትሆንም ብዙ አይቻለው (እንደ እኔ)
በገባኝ ልክ ብዙ አውቄያለው
እናም እናቴ...
በህይወት እያለው በቁሜ ሞቼ
ፅፌልሻለው ይሄን ኑዛዜ
" በራሴ የህይወት ሩጫ ተሸንፌያለው
እስካለው ድረስ ላንቺ እኖራለው።"
ተፃፈ
ግንቦት 06/2011
ሐዋሳ IOT dorm 422
አብርሃም እንዳለ ገዳ
@getem
@getem
@getem
የወደቀዉ ብዕር ገንፍሎ የጣልኩት
ከመሬት አንስቼ ስለሌላ ቸክችክ ብዬ አስገደድኩት
በጊዜ መቆየት እራሱን አሟጦ
ስለሌላ አልፅፍ አለ ብዕርነቱን አጥቶ
ጨምድጄ የጣልኩት ያ ነጭ ወረቀት
የድሮዉን ትቼ አዲስ ልፅፍበት
ብታገል ብለፋ ወይ ፍንክች አላለም
ከኔ ጋር ተኳርፎ ሊያርፍበት አልቻለም
ድሮ የበላነዉ ያ ነጭ እንጀራ
ኩርማን ሆኖ ኖሯል ቆምጣጣ መራራ
ለብዙ ሚበቃዉ አብልቶ አጠጥቶ
ጥንቱን እያሰበ አርጀ ሸብቶ
ትራስ አቅፎ ማደር የለመደዉ ክንዴ
አዲስ ትሁን ብየዉ ልማድህ ልማዴ
አሻፈረኝ አለ አልቻለም ካለሷ
ጠረኗ አልጠፋም ዛሬም ከትራሷ
አሷን የሚሸኙት ደከመኝ ማይሉ
ሌላ ጋራ ለመሄድ
ጠንካሮቹ እግሮቼ ፍፁሙኑ ዛሉ
አይኖቼ ሰሞኑን ፀባይ አዉጥተዋል
በረባ ባልረባው ነፍራቃ ሆነዋል
ለሊቱን በሙሉ አፍጠው ያድራሉ
ጣርያ ጣሪያ እያዩ ደም እየመሰሉ
መሳቅ መፍለቅለቁን ካንቺ የለመዱ
ጥርሶቼ ተደብቀዉ ከየት ወዴት ይምጡ
አንቺ ከሄድሽ በኋላ የመጣው ብዙ ነዉ
ያልሆነውስ የለ ምስጋና ላንቺ ሰዉ
ነገር ግን...
ካንቺ ጋር እያለን አብረን የሚወዱን
አንቺ ስትሄጂ ከኔ ጋር ተጣልተን
መኖሩ ከብዶኛል እንኳን ሌላ ላምን
ስለዚህ የኔ ፍቅር
እባክሽ አስታዉሽኝ የኔ ነበርሽ እኮ
ፍቅራችን ያስታዉስሽ ትዝታዉን ልኮ
✍ልጅ ሞሌ
@getem
@getem
@getem
ከመሬት አንስቼ ስለሌላ ቸክችክ ብዬ አስገደድኩት
በጊዜ መቆየት እራሱን አሟጦ
ስለሌላ አልፅፍ አለ ብዕርነቱን አጥቶ
ጨምድጄ የጣልኩት ያ ነጭ ወረቀት
የድሮዉን ትቼ አዲስ ልፅፍበት
ብታገል ብለፋ ወይ ፍንክች አላለም
ከኔ ጋር ተኳርፎ ሊያርፍበት አልቻለም
ድሮ የበላነዉ ያ ነጭ እንጀራ
ኩርማን ሆኖ ኖሯል ቆምጣጣ መራራ
ለብዙ ሚበቃዉ አብልቶ አጠጥቶ
ጥንቱን እያሰበ አርጀ ሸብቶ
ትራስ አቅፎ ማደር የለመደዉ ክንዴ
አዲስ ትሁን ብየዉ ልማድህ ልማዴ
አሻፈረኝ አለ አልቻለም ካለሷ
ጠረኗ አልጠፋም ዛሬም ከትራሷ
አሷን የሚሸኙት ደከመኝ ማይሉ
ሌላ ጋራ ለመሄድ
ጠንካሮቹ እግሮቼ ፍፁሙኑ ዛሉ
አይኖቼ ሰሞኑን ፀባይ አዉጥተዋል
በረባ ባልረባው ነፍራቃ ሆነዋል
ለሊቱን በሙሉ አፍጠው ያድራሉ
ጣርያ ጣሪያ እያዩ ደም እየመሰሉ
መሳቅ መፍለቅለቁን ካንቺ የለመዱ
ጥርሶቼ ተደብቀዉ ከየት ወዴት ይምጡ
አንቺ ከሄድሽ በኋላ የመጣው ብዙ ነዉ
ያልሆነውስ የለ ምስጋና ላንቺ ሰዉ
ነገር ግን...
ካንቺ ጋር እያለን አብረን የሚወዱን
አንቺ ስትሄጂ ከኔ ጋር ተጣልተን
መኖሩ ከብዶኛል እንኳን ሌላ ላምን
ስለዚህ የኔ ፍቅር
እባክሽ አስታዉሽኝ የኔ ነበርሽ እኮ
ፍቅራችን ያስታዉስሽ ትዝታዉን ልኮ
✍ልጅ ሞሌ
@getem
@getem
@getem
ተሽጦ ያተረፈ
..
አንቺማ
ሰራሁለት እያልሽ ÷ ለፍፈሽ ላገሩ
ከድሮ ዝነጣው
ከድሮ ማማሩ
አፋታሁት ብለሽ ÷ ቸረቸርሽ ጉራሽን
ምን እንደተሰራሽ ÷ አታውቂም ጉድሽን!
.
በእሷ እጅ መዳሰስ ÷ ሾይጣን ጋር መደነስ!
ከ'ሷ ጋር ማስቀደስ ÷ ጠንቋይ ደጃፍ መድረስ
እሷ ላይ መጠምጠም ÷ በአላህ መረገም
ተብሎ እንኳ ባገር
እንደ ቀላል ነገር
ይሁዳ መሆንሽ ÷ አንድም ሰው ሳይጠፋው
በዚያ ውብ ከንፈርሽ
ተስሞ ለመሸጥ ÷ የበዛው ወረፋው
ለምን ይመስልሻል?
አንዳንዱ ባርነት ÷ ከነፃነት ሲሻል
የታሰረ ባርያ ፥ መሲሁን ይሸሻል
…
ባንቺ የተሳመ
እየተቋደሰ ÷ ከእንቡጥሽ ውብ ለዛ
እየተካፈለ ከልዩ መኣዛ
በነገድሽው ማግስት ÷ ይህችን አለም ገዛ !
በይ ጉድሽን ስሚ !
« አለም እንደሆነ
ከንፈር አምላኪ ነው ÷ ለአሻራሽ ይጋፋል
ባንቺ የተሸጠ ÷ አንቺ ላይ ያተርፋል »
..
( ናትናኤል ጌቱ )
@getem
@getem
@paappii
..
አንቺማ
ሰራሁለት እያልሽ ÷ ለፍፈሽ ላገሩ
ከድሮ ዝነጣው
ከድሮ ማማሩ
አፋታሁት ብለሽ ÷ ቸረቸርሽ ጉራሽን
ምን እንደተሰራሽ ÷ አታውቂም ጉድሽን!
.
በእሷ እጅ መዳሰስ ÷ ሾይጣን ጋር መደነስ!
ከ'ሷ ጋር ማስቀደስ ÷ ጠንቋይ ደጃፍ መድረስ
እሷ ላይ መጠምጠም ÷ በአላህ መረገም
ተብሎ እንኳ ባገር
እንደ ቀላል ነገር
ይሁዳ መሆንሽ ÷ አንድም ሰው ሳይጠፋው
በዚያ ውብ ከንፈርሽ
ተስሞ ለመሸጥ ÷ የበዛው ወረፋው
ለምን ይመስልሻል?
አንዳንዱ ባርነት ÷ ከነፃነት ሲሻል
የታሰረ ባርያ ፥ መሲሁን ይሸሻል
…
ባንቺ የተሳመ
እየተቋደሰ ÷ ከእንቡጥሽ ውብ ለዛ
እየተካፈለ ከልዩ መኣዛ
በነገድሽው ማግስት ÷ ይህችን አለም ገዛ !
በይ ጉድሽን ስሚ !
« አለም እንደሆነ
ከንፈር አምላኪ ነው ÷ ለአሻራሽ ይጋፋል
ባንቺ የተሸጠ ÷ አንቺ ላይ ያተርፋል »
..
( ናትናኤል ጌቱ )
@getem
@getem
@paappii
#በምናልባት ~ሰበብ
፡
ካሳደገኝ ልማድ
ከአብሮነት ቀዬ~እራሴን አርቄ
በራሴ አኩኩሉ
በትዝታ ዋሻ ~እራሴን ደብቄ
ለብዙ ዘመናት
ከተሸሸኩበት~ከኖርኩበት ጫካ
ፍንጣቂ ጨረር
ፀሊም ትዝታዬን~ቢመስለኝ ያፈካ
ከደበቀኝ ክህደት
ከመገፋቴ ላይ~መጠገን እያየሁ
በጨረሯ ተስፋ
ወዳልመጣው ዛሬ~ለመሄድ ተመኘሁ፡፡
፡
ኩኩሉ ባይ እኔ
ለማይነጋ ሌሊት ~እኔው ተሸሻጊ
በራሴ አኩኩሉ
እራሴን ደብቄ ~እራሴን ፈላጊ
ታዲያ ከኔ በቀር
ያ'መታት ዋሻዬን~ጫካዬን ሊያሳጣ
በመሸው ቀኔ ላይ
መሻት የፀነሰው~ጨረር ከየት መጣ?
፡
አላውቅም እኔንጃ
ምናልባት ምስጢሩ~ከሆነ ግን ካንቺ
በብርሀን ሙይው
የፍቅር ዋሻዬን ~ጨለማዬን እንቺ፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@getem
፡
ካሳደገኝ ልማድ
ከአብሮነት ቀዬ~እራሴን አርቄ
በራሴ አኩኩሉ
በትዝታ ዋሻ ~እራሴን ደብቄ
ለብዙ ዘመናት
ከተሸሸኩበት~ከኖርኩበት ጫካ
ፍንጣቂ ጨረር
ፀሊም ትዝታዬን~ቢመስለኝ ያፈካ
ከደበቀኝ ክህደት
ከመገፋቴ ላይ~መጠገን እያየሁ
በጨረሯ ተስፋ
ወዳልመጣው ዛሬ~ለመሄድ ተመኘሁ፡፡
፡
ኩኩሉ ባይ እኔ
ለማይነጋ ሌሊት ~እኔው ተሸሻጊ
በራሴ አኩኩሉ
እራሴን ደብቄ ~እራሴን ፈላጊ
ታዲያ ከኔ በቀር
ያ'መታት ዋሻዬን~ጫካዬን ሊያሳጣ
በመሸው ቀኔ ላይ
መሻት የፀነሰው~ጨረር ከየት መጣ?
፡
አላውቅም እኔንጃ
ምናልባት ምስጢሩ~ከሆነ ግን ካንቺ
በብርሀን ሙይው
የፍቅር ዋሻዬን ~ጨለማዬን እንቺ፡፡
((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@getem
እኔ ለተከፋሁ ፥ እኔን ሆድ ለባሰኝ
መኖር ምናባቱ ፥ ህይወት ከንቱ ሚያሰኝ
በሽታ ከያዘኝ....
ሆድ ካገር ይሰፋል? እኔን ይተልቃል?
መኖሬ ቢያከትም ፥ ህላዌ ያበቃል?
.
ዛፉ ክንፍ አብቅሎ ፥ መጥረቢያ ካልሸሸ
ፀሃይ ፅልመት ፈርታ ፥ በጠዋት ካልመሸ
ውልደት ሞትን ጠልቶ ፥ ካልቀረ ጨንግፎ
ስለምን ያቅታል
አንድ ቀን ማሳለፍ ፥ ቅሬታን ታቅፎ?
.
ውሃ ጥም ከውሃ ፥ ጦርሜዳ ሳይወርዱ
ረሃብም እንጀራን ፥ ሳይደቃው በክንዱ
ሳር መረገጥ መሮት ፥ ሳያበቅል ተንኮል
መጀመሪያ ሞት ነው ፥ ለመሞት መቸኮል፡፡
.
ና ልሰርህ ልቤ
ሲሞላ አትብረር ፥ ሲጎል አትሰበር
ሸክሙን እንልመደው ፥ የመኖርን ቀንበር
በውልደት የገባን
በሞት እስክንወጣው ፥ ማሳለፊያውን በር፡፡
.
(መነሻ ሃሳብ- ሩሚ)
@getem
@getem
@paappii
#haileleul_aph
መኖር ምናባቱ ፥ ህይወት ከንቱ ሚያሰኝ
በሽታ ከያዘኝ....
ሆድ ካገር ይሰፋል? እኔን ይተልቃል?
መኖሬ ቢያከትም ፥ ህላዌ ያበቃል?
.
ዛፉ ክንፍ አብቅሎ ፥ መጥረቢያ ካልሸሸ
ፀሃይ ፅልመት ፈርታ ፥ በጠዋት ካልመሸ
ውልደት ሞትን ጠልቶ ፥ ካልቀረ ጨንግፎ
ስለምን ያቅታል
አንድ ቀን ማሳለፍ ፥ ቅሬታን ታቅፎ?
.
ውሃ ጥም ከውሃ ፥ ጦርሜዳ ሳይወርዱ
ረሃብም እንጀራን ፥ ሳይደቃው በክንዱ
ሳር መረገጥ መሮት ፥ ሳያበቅል ተንኮል
መጀመሪያ ሞት ነው ፥ ለመሞት መቸኮል፡፡
.
ና ልሰርህ ልቤ
ሲሞላ አትብረር ፥ ሲጎል አትሰበር
ሸክሙን እንልመደው ፥ የመኖርን ቀንበር
በውልደት የገባን
በሞት እስክንወጣው ፥ ማሳለፊያውን በር፡፡
.
(መነሻ ሃሳብ- ሩሚ)
@getem
@getem
@paappii
#haileleul_aph