ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ለምርቃት ስጦታ ፎቶ ለማሳል

በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ማዘዝ ይቻላል ።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህ እድል እንዳያመልጦ!
@seiloch
@seiloch
ፍቅርሽ እያመሰኝ
እርቀሽ ከደጄ በናፍቆት ስቀጣ
ምን ማረግ ችላለሁ
ካልመጣሽ በስተቀር እኔ እንደው አልመጣ፡፡

በሰማዩ ጋሪ
ባህሩን አልፌ አልሻገር ነገር ወዳለሽበቱ
በሰው ሀገር ሳይሆን
ባ'ገር ነው ሚገለጥ የፍቅር ውበቱ
እባክሽ ነይልኝ
ሁሉንም ተይና ሊበላኝ ነው ቤቱ፡፡

ፍቅር ይዞኛል ከሩቅ ሰው፡፡

(ልብ አልባው ገጣሚ)

@getem
@getem
@getem
1
ያለ ሪፈረንደም
ብሔሬ ይቅደም
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
"ሁሉ የየራሱን ፣ ዘር ማንዘር ያገዝፋል
ሁሉ የብሔሩን ፣ ክብር ይለፈልፋል
ሁሉ ትልቅ ነኝ ሊል ፣ ይኮለታተፋል
እንደሰው የሚያስብ
እንደ ሀገር የሚያስብ ፣ እንዴት አንድ ይጠፋል?"
ብዬ አልጠይቅም
ሰማይና ምድር ፣ ቢደበላለቅም
ሙሉ ትውልድ ቢያልቅም
ብነሳም ብወድቅም
ዘሬን አገዝፋለሁ
ዘር ለገበሬ ነው ፣ ሲሉኝ እስቃለሁ
እውነቱን አውቃለሁ
ብሔር ያፀድቀኛል ፣ ዓለም ቢኮንነኝ
በዘሬ አላፍርም!
ሰው ወይ ኢትዮጵያዊ ፣ ወይ ሁለቱንም ነኝ!

@getem
@getem
@gebriel_19
አቦ በደሴ ሞት
ጦሳ መጋረጃ፤
ሮቢት መዉረጃ፤
ሆጤ ለማርገጃ፤
ስሂን ለደረጃ፤
ጀሜ ለወዳጃ፤
ገራዶ ለሀጃ፤
ኩታበር ለሞጃ፤
መርሆ መፍረጃ፤
ጅብሩክ መነገጃ፤
ሸዋ በር መስገጃ፤
ቢለን መወዳጃ፤
አቦ በደሴ ሞት ፤ነጃ በለን ነጃ፤
ቀየዉ ሰላም ይሁን ፤እምቦሳና ጥጃ፤
እናቲቱ ብርቄ፤ ልጅቱ ከዲጃ፤
የአሊሞቹን አገር ፤እንዳይዉጠዉ ሙጃ፤
ክፍት አላት መሰል፤ የነካትን እንጃ፤
ጀምአዉ ተሰብሰብ ፤እንግባ ወዳጃ፤
ስቃ እንድትበላ፤ የልጆቿን ሆጃ፤
አቦ በጦሳ ሞት ፤ነጃ በላት ነጃ፤
ታዉቅበት የለም ወይ ፤የመዉደድን ነገር ፤የፍቅሩን ደረጃ ፤
አቦ በደሴ ሞት ፤ነጃ በለን ነጃ፡፡

------------------------
ሸጊቷ ቅዳሜ!!!!!

ዘበናይ ቅዳሜ!!!!!!!!!
ሽሙንሙን ፣
ሽሙንሙን፣
ሽቅርቅር፣
ፍንድቅድቅ፣
ፍልቅልቅ በይልኝ፣
ሳቄ ይቀድመኛል፣
ሰማዩ ሲገለጥ፣ አንች ስትመጭልኝ።

((( ጃ ኖ )))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
ሀገሬ ሞተች ወይ ???

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ድሮ!!

እንዲያ ነበር ወጉ !

የመናፈቅ ጥጉ.. .

ጓዝን አንጠልጥለው ፥ ኮብልለው ሲሄዱ

ድንበር አቆራርጠው ፥ ተሰደው ሲነጉዱ

ከሰው ደጃፍ ቆመው...

በርቀት አሻግረው...

በአይን እየማተሩ ፥ ትዝታ 'ሚቸሯት

ሀገር ማለት አድባር ፥ ግዙፍ ተራራ ናት።

እንዲህ እንደዛሬው!

እንዲህ እንደ አሁኑ.. .

እንደ ጊዜው ስሌት

በዘመን ወረቀት ...

ቅኔያትን ቋጥረን ፥ ናፍቆት ሳንዘራበት 

ጉያዋ ስር ታቅፈን...

ናፈቀችን የሚል ፥ ሳንዘፍን  ዘፈን 

ያኔ ... በፊት ... ድሮ

ርቀት ነበረ ...

የተሰዳኝ ለቅሶው ፥ የአፉ እንጉርጉሮ ።

እስቲ ታዘቢልኝ ?!

መልስሽን ላኪልኝ 

ትዉልዱን ምን ነካው ?

ኗሪውን ምን ነካው ?

ባህሩን አሳብሮ ርቆ ሳይጓዝ

ናፈቀችኝ ብሎ እንባ የሚዘራው ?

በይ እስቲ ንገሪኝ? !

መልስሽን አድርሺኝ?

ምን ያለው ጊዜ ነው ?

የወቅት እንጉልፋቶ ፥ የቅራሬ ዘመን 

ሀገር አዘንግቶ ፥ ክልል ያስፈቀረን ?

እስቲ ታዘቢልኝ? !

መልስሽን ላኪልኝ ...

ኢትዮጵያ የሚሏት ፥ ያባቶቼ ሀገር 

ለምን ናፈቀችኝ? 

ጠፍታም እንደሆነ!

ከምድረ ገፅ ሸሽታ ፥ ህላዌዋ ከስሞ 

"ሀገርህ የለችም ፥ እንዲያ እንደ ቀድሞ

ግንዷ ብቻ ቀርቷል ፥ አበባዋ ከስሞ 

ብለሽ አርጂኝና ~ ሀቅታው ሲወጣ 

እኔም ሞተኝ ብዬ.. .እርሜን እንዳወጣ!

ታዝበሽ ንገሪኝ

መልስሽን አድርሺኝ.. .

ሀገሬ ወዴት ናት ??

ናፈኳት!

ናፈኳት!!

ናፈኳት! !!

@getem
@getem
@getem
ጭፍን አማኝ !!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።።

እኔማ...

የሕይወት ስሌቴ ፥ መተንፈሻ በሯ 

የጎጆዬ ደጀን ፥ ምሰሶ ማገሯ 

የግቢዬ ፍካት ፥ አበባና ስሯ 

እሷ ናት እያልሁኝ

እንዲህ እያሰብሁኝ

ስንት ዘመን ቀርጥፌ

ዓመታትን ኖርሁኝ።

ይብላኝ እንጂ ለኔ!

መገን የሷ ፍጥረት

የውበት ሰገነት

ዓይኗ ጠሀይ ሆኖ ፥ በዓለም የሚያበራ

ሽንጧ የሺህ ግምት ፥ ዳሌዋ ተራራ

ተረከዘ ሎሚ ፥ ጣቶቿ አለንጋ

ጡቷ የንጉስ ጦር ፥ ደረት የሚወጋ

እያልሁ ለምፎክር 

መንደር ለማሸብር

በመልክሽ ምጥማጥ ውስጥ

እግሬን ቀብድ አሲዤ

እዛዉ ለምዳክር ።

ልቤን ኸሌማቱ ፥ ከበላይ አኑሬ

ቁረሺ ለምልሽ ፥ ሥጋዬን ደርድሬ

ይብላኝ እንጂ ለኔ!

ሀገሬዉ በስላቅ ፥ እሳት ለገረፈኝ

በከንፈሩ ምፀት 

አልሰማም እያለ ፥ ሀዘኑን ለቸረኝ

ይብላኝ እንጂ ለኔ!

ጣዖቴ ነሽ ብዬ ፥ ሰግጄ ሳልጨርስ

መልክዐ ስምሽን ፥ ቀድሼ ሳልጨርስ

ንፁህ ናት እያልሁኝ ፥  ለማድር ፎክሬ

ጆሮዬን ላሸሸሁ ፥ ከመንደሩ ወሬ።

ይብላኝ እንጂ ለኔ!

በዘመናት ማምሻ ፥ ሀቅ አገኘሁ ብዬ ፥ ስለት ለገበርሁኝ

ከፀሎቴ ማግስት ...

ከሰው ጋር ተኝተሽ ፥ የቀኑ ቅዠቴን ፥ በቁም ለተጋትሁኝ።

@getem
@getem
@getem
👍1
"ደግ አይበረክትም"


©(አበባው መላኩ)

እስከ:ማዕዜኑ
..እስከ፡ማዕዜኑ
አነብር:ውስተ:ልብየ:ትካዘ
ዐሊውየ:ሕገ:ወትዕዛዘ:
ማርያም:ኩነኒ:መናዝዘ።
አቤል: በፀጋ : ርቆ ፣
በየዋህነት:ከመጠቀበት ፣
ቃዬል:በንፍገት:ከብሮ ፣
መቀመቅ:ከወረደበት፣
የዕጓለ መሕያው: ታሪክ ፣
ሲጀመር : የጠቆረበት .
እንውረድ:ብሎት:ወንድሙን ፣
እስትንፋሱን:የነጠቀበት ፣
ኃዘና ፣ ስምዒ:ወብካያ ፣
ለሃገሪትነ:ኢትዮጵያ ።
የሞት:ታሪክ:ሊዘከር
በአዝማናት:ማሀል:ሊነገር
የመጀመሪያው:መልአክ ፣
ታሪኩን:ሲፅፈው:እንደዚህ:ነበር። ....
ክልዔቱ: አኃው: መንገደ:ቀላይ :ወረዱ፣
እኒህ:ሁለት:ወንድሞች:ወደ:አዘቅት:የሄዱ፣
አንደኛው:ሟች:ሊሆን:ገዳይ:ሊሆን:አንዱ፣
አሃዱ:ተመይጠ፣ ወኢተመይጠ አሃዱ ፣
አንደኛው ሲመለስ
ሁለተኛው እዚያው የቀረ፣
ውረድ እንውረድ ያለው
ወንድሙ ገድሎት ነበረ።
ከዚህ የቀን፡ጎደሎ፡ነው ፣
ከዚህ፡ክህደት፡በኋላ፣
ከተራራው፡አናትና፡
ከግርጌ፡በቆመው፡ማሀል፡
መተማመኑ፡የላላ።
የአዳም፡የልጅ፡ልጅ፡ሁሉ
፡ምን፡ቢጀግን፡ምን፡ ቢያቅራራ፣
ምን፡ደግ፡ንግርት፡ቢያስነግር ፣
ምን፡ በማዕረግ፡ቢጠራ ፣
ይገሉኝ፡ይሆን፡እያለ፡ነው ፣
ውረድ፡ሲሉት፡ የሚፈራ ።
እናም፡መውረድ፡ሞቱ፡ነው፡
አንዴ፡ደርቡን፡ ከወጣ ፣
ውረድ፡ሲባል፡በመውረዱ፡ነው ፣
ወንድሙ፡ ሕይወቱን፡ያጣ።
በርግጥ፡ለምን፡ይወርዳል፡
መውረድስ፡ማንን፡ ጠቀመ ?
የወረደውን፡መግደሉ፡ለዘላለሙ፡ካልቆመ !


@getem
@getem
@getem
የግጥሜ ዋና መግቢያ'ና መደምደሚያ
የቃሎቼ እርጋት የሀሳቤ ማስፈርያ
የቤት መምቻ ምቴ የፍቅሬ መግለጫ
የስንኜ ቅኔ የልቤን ውስጥ ማውጫ
አርጌ እንድፅፍሽ ፅፌም እንዳኖርሽ
አብዝተሽ ቅረቢኝ አብዝቼ ልውደድሽ


((ወድጄ እንድፅፍሽ))

@getem
@getem
@getem
.....የባለቅኔ ግራ መጋባት......

የመግጠም ስሜቱ በሀዘን:
በችግር : በስቃይ ጎልብቶ
የፈሰሰ እንባውን በብዕሩ ቀለም:
በጥበብ አስልቶ
መከፋቱን ነቅሶ በቅኔ እሚያሳየው
ሲደሰትም ደግሞ ጃምቦ እማይጨብጠው
ብዕር የሚይዘው
ያ የሚስጥር አባት ጠቢቡ ገጣሚው
ዝምታን የሚመርጥ ግጥምን የማይፅፍ:
ግራ ሲገባው ነው ።

እስጢፋ ተስፋየ

@getem
@getem
@GEBRIEL_19
ዝምታ ነው ፍቅር

የምን አንቺ ሆዬ የምን ባቲ ቅኝት
አምባሰል ለምኔ የትዝታ መአት
አምጡልኝ ክራሬን በወጉ ልደርድር
ጅማቱን ጥላችሁ 'ባንጀቴ ይወጠር
አንደበቴ ዝምበል ቃል እንዳትናገር
ቅኝቱ ልቤ ነዉ የዜማዬ ደም ስር
በዝምታ ላዚም ዝምታ ነው ፍቅር፡፡

ከንጉስ አማኑኤል ብርሃኑ

@getem
@getem
@getem
አንቺ ቅኔ
(ቡሩክ ካሳሁን)

ስላንቺ ለመግጠም ፈልጌ ነበረ
ላንቺ ግጥም መፃፍ ሞክሬ ነበረ
ምን ያደርጋል ታዲያ
የወረቀት ቋጥኝ ፊቴ ተከመረ
የቅዳጅ ገፅ ጋራ
የተጨማደደው የሀሳብ ተራራ
ከግርጌ እስካናቱ
በምርጥ ግጥሞች ቢሆን መገንባቱ
ልፋ ቢለኝ እንጂ ስትፅፍ እድሜህ ይለቅ
እንደ እርሳስ ሲቀረፅ
ኋላ እንዴት ይችላል ቅኔን ግጥም መግለፅ?

@burukassahunc
@getem
@getem
#ትረፊ_ስትለኝ

እራሴን ሳገኛው ከጦጣዎች ተርታ*
ወቅሼህ ነበረ አንተ ታላቅ ጌታ
ታስታውስ እንደሆን
እነሱን ከጎጆ እኔን ደሞ ከዱር
ስለምን ለየኸኝ ሰው ከሚባል ፍጡር
ብዬሀለሁ ያኔ ሳይገባኝ ሰው ማለት
አይገኝም እና ሞት የቀበጡ ዕለት
ትረፊ ስትለኝ ጦጣ አረከኝና
ከሰው ዘር ለየኸኝ ይድረስህ ምስጋና
ከሚታየው ሀጢያት ከዲያብሎስ ስራ
ሰው በረከሰበት ከዚህ አለም ተራ
ለይተህ ያኖርከኝ ሀጢያት እንዳልሰራ
እንኳንም ፈጠርከኝ ጦጣ አደረክና
ትረፊ ስትለኝ
ለዘመናት ሳየው ሰውን አተኩሬ
ያጠራጥረኛል ለአንድም ቀን መኖሬ
በሚሰራው ስራ ሁሌም ተማርሬ
እያፈርኩበት ነው አሁን አሁን እማ
በወንድሙ ደስታ ሲቆስል ሲደማ
የእህቱን ገመና ሲያወጣው በገሀድ ምንም ሳያቅማማ
እጄን ከአፌ አደረኩ ትዝብቴን ላሰማ
አቤት ያንተ ፍጡር ሀጢያቱ የበዛ
ይቅርብኝ ሰው መሆን ጥንቅር ይበል እዛ
ከሰው መጠለያ ውስጡ ሰላም ካጣ
በማይሆን በሚሆን እንዲህ ከተንጣጣ
በጫካ መኖሬም የለብኝም ጣጣ
"የባሰም አለና..." እንዳለው ተረቱ
የሰማዩ ጌታ አንተ ክንደ ብርቱ
ምስጋና ይድረስህ ላረከኝ ጦጢቱ ።
------------------------//------------------------
✍🏽©መቅደስ ተስፋዬ ሞላ
15/11/2016
------------------------//------------------------


@getem
@getem
@getem
1
ተፍጻሜተ ፍቅር

ፍቅሬ መውደድሽን ፡ እንዳላይ በተግባር
የሞተ አለና ፡ ወርዶ ስለፍቅር
ከጽርሐ አርያም ፡ ወደ ምድር
ተገርፎ በጅራፍ ፡ ተወግቶ በሚስማር

(ልሳነ ግእዝ ዘኢትዮጵያ)


@getem
@getem
@gebriel_19
*በጭስ ተደብቄ*
(እውነተኛ ታሪክ)
ገጣሚ 👉ናትናኤል ግዛው 👈

በጭስ ተደብቄ ራሴን ሳቃጥል፣
ለብቻዬን ሆኜ ርቄ ከሰው መሀል፣

ያለፈን ትዝታ ከውስጤ ላወጣ፣
በጭስ ተደበኩኝ ደስታዬ ላይመጣ፣

እለኩሰዋለሁ ደግሜ ደግሜ፣
የሲጋራው ጫፍ በከንፈሬ ስሜ፣
በጭሱ ግርዶሽ ውስጥ እልፍ ተጋድሜ፣
ባይመጤ ትዝታ ክፉኛ ሰጥሜ፣
ባልታየ በሽታ ለማልድን ታምሜ፣

ታሪኬን በሙሉ የምረሳው መስሎኝ፣
የከንፈሬን ወዳጅ ለኩሳታለሁኝ፣

ከጢሱ መሀከል አንቺን ስፈልግሽ፣
ስምሽ ካፌ ውሎ ደግሜ ብጠራሽ፣
የለሽም እናቴ ኸረ ወዴት ገባሽ፣

አይኔ እኮ ተያዘ ሳል ተፈታተነኝ፣
እንደ ልጅነቴ እስቲ አይዞህ በዪኝ፣
እንደ ደጉ ጊዜ ትኩሱን አቅምሺኝ፣

ሀዘኔ ቢከፋ ውስጤን ቢያነድለው፣
በጭስ ተደብቄ ራሴን ቀብራለው፣
በሱስ ተነክሬ ከትላንት ሸሻለው፣

የእናቴ ምትክ ያልኳትንም ፍቅሬን፣
ቀልቧን ሌላ ገዛው ቀረሁ ለብቻዬን፣
ፈጣሪም አበዛው ከመረው ስቃዬን፣

ለማንም ሳልነግር በጭስ ተደብቄ፣
ህመሜ ሳይታይ ብቻዬን ማቅቄ፣

መኖር አያሰኘኝ፣
ነገም አይናፍቀኝ፣
የከንፈሬን ወዳጅ ብቻ ስማለሁኝ፣

እንደ ልጅነቴ ልክ እንደናቴ ጡት፣
ከከንፈሬ ውላ ታድራች ከኔ ጣት፣

ችዬ ላልሄድ ነገር ከትዝታ ርቄ፣
ኖራለሁ ዘመኔን በጭስ ተደብቄ፡፡

@getem
@getem
የአርነት ጥያቄ?!
(ሚካኤል አስጨናቂ)


።።።።።።።።።።።።።።።።
እኔም አንድ ሰሞን !
እንደ ክፉው ሳዖል
እልፍ አንገት ለመቁረጥ
ሰይፍ ይዤ ስሮጥ
በቃላትህ በትር ፥ በድምፅህ ድንፋታ
መሬት ላይ ወድቄ ...
ልቤን አስማረክሁኝ ፥ መንፈሴ ተረታ ።
ከዛ ካህን ፈለግሁ ...
በደሌን ተናዘዝሁ ...
ደግሞም ያንተ ካህን ፥ መጥሀፍ አዋቂ
የስምህ ቀዳሽ ሰው ፥ ቃላትን አርቃቂ
"ሰይፍ እንዳነሳ ፥ ሰይጣን በኔ አድሮ
እልፍ አንገት ለመቁረጥ ፥ እንደቆየ አሲሮ"
ስህተቱን ጠቅሰው
እንደነበር አርገው
ከቃልህ ቀንጭበው
መክረው አስተማሩኝ
ይሄን ባሉኝ ማግስት
እኔም ያንተ ፍጥረት....
ጲላጦስን ሆኜ እጄን እያነፃሁ
ንሰሐዬን ሻርኩኝ ።
አንተም ይሄን ስታይ!
በአርያም ፎክረህ ...
አይደረግም ብለህ.. .
ለምን ? እንዳትለኝ!
.
ሰይጣን በኔ አድሮ ፥ ለሚቀላው አንገት
ለሚያቆየው በደል ...
በኔ ነፍስ ፈንታ ፥ ራሱ ይወንጀል ።
እኔ ምን ተዳዬ ???

@getem
@getem
@getem
ጌታየ አንተ አብጀው ፤
እኔ ቅዋ የለኝ አስቤም አልፈጀው፤
አታየውም እንዴ ፤
ትልቅ ያልነው ሁሉ፤
በዘር ተቦዳዶኖ በደም ስካር አብዶ እያንቦጀቦጀው፤
ደምህ ደሜ ማለት ፤
እንኳን ላገሩ ሰው ለራሱም አልበጀው ፤
የኛን ተወዉና ፤
ጌታየ በእዝነትህ ሃገሩን ፈርጀው ።
አደራ አንተ አብጀው!!!

(( ጃ ኖ ))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
📖📖📖📖📖
የማይሞት ትዝታ

እንዳ'ረም ከልቤ ሞከርሁኝ ልነቅልሽ
እንደአረጀ ልብስ አሰብሁ ልለውጥሽ
እንዳረጀ እቃ ተመኘሁ ልጥልሽ
ቆሻሻ ነሽ ብዬ ከገንዳ ልከትሽ

ብዙ ሞክሬያለሁ ካገሬ ልሰድሽ
ካይኔ እንድትርቂ ከጦቦያ ላስወጣሽ
ከምድር ጫፍ ቦታ ከአድማስ ላደርስሽ

ሰላም ለማግኘትም ፈለግሁኝ ልገድልሽ
በምጠጣው መጠጥ...
ጉበቴን ገድዬ አንቺን እንድገድልሽ
በጫት በሲጃራ...
ሳንባዬን ጨርሼ አንቺን ልጨርስሽ

ግና
ዛሬም እንደድሮ ዛሬም እንደ አምና...
በማደርገው ነገር ሳትወርጂ ከክብርሽ
በልቤ ዙፋን ላይ አለሽ ተቀምጠሽ
አንቺ ተንደላቀሽ እኔን ሰላም ነስተሽ
ደሜ ውስጥ ያለውን ትዝታሽን ጥለሽ

(📝ል.ግ.ኢ)

@getem
@getem
@getem
"ርዕሱን ለአድማጭ"
ርዕሱ ነው
( አምባዬ ጌታነህ )

እኔ የአንቺ ደሐብ-ብኩን ደግ አፍቃሪ፣
ለክብረሽ መግለጫ - ፊደልሽን ቆጣሪ፣
እየተቅለሰለስኩ በልጅሽ ፊት ስኖር፣
ከማዘን በስተቀር ስቄ አላቅም ከምር።
ያም ለዛ ያም ለዛ ሲያጋድል እያየሁ፣
በጊዜ ዳኛ ላይ ፍትህ እየተራብሁ፣
ሁሌ እንዳጉተመተምሁ
'ልጅ አሳድግ ብየ
ካገር እኖር ብየ
ለባሻ ዳርኩለት ሚስቴን 'ህቴ ብየ።'
እንዳለው ገበሬ፣
አለሁኝ እንዳለሁ
ግፍ ሆኖብኝ ክብሬ።

አባት ማጣት ሀዘን - እናት ማጣት ህመም፣
ሆኖ እንደ እግር እሳት እልፍ አመት ቢፈጅም፣
በተበዳይ ልብ ውስጥ ለምፅ እንደሚያሳርፍ ገዳይ አውቆ አያቅም፣
እኔ ያለ ወላጅ መቅረቴ አያመውም።

ሰማይ የግፍ እምባ ሊጥል አቀርዝዟል፣
ጋራ ሸንተረሩ በዝምታ ነግሷል፣
ሜዳ ወንዛ ወንዙ ቅጠሉ ጠንዝሏል፣
እናት ሞቅ አጥልቃ፣
ቁርንጮዋን ታጥቃ፣
ፊቷ ተነጫጭቷል፣
አባት ወደ ማታ ባዘን አጎንብሷል፣
የእኔም የነገ እጣ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።

ለዛሬ ያለምነው ቅዠት ሲሆን ተስፋ፣
አንተ የፍጥረት አምላክ
የምህረት ዝናብህን ባጥል እንኳ አካፋ።
ነፃ በሆነች ምድር ነፃ አውጪዎች ሞልተው ነፃ ህዝብ ጠፋ።
እኒህ ነፃ አውጪዎች
የለውጡ አምበሳዎች
በቀን አስር ጊዜ ' እመኑን 'የሚሉን፣
ከምናየው እውነት የተፃረረውን
' መሲህ ነን ' የሚሉን
ከእመኑን ባሻገር እንድናምን 'ሚሹት ውሸቱ ምን ይሆን፣

ባለሁለት ወንበር ምቾት ካልተሰማኝ፣
የምለውን ሰምቶ ሰርቶ ካልታዘዘኝ
አባወርነቴን ከተፈታተነኝ
የእሱ መኖር ለእኔ ..
መሄጃ መቆሚያ ማረፊያ ካሳጣኝ፣
እንዴት መላ አላስብ፣
እንዴት ሴራ አልሸርብ
የምን እያቀፉ እንደ ልጅ ማባበል፣
ሳለ ብልህ ዘዴ
በመፈንቅለ ስም መሪነትን መግደል።

እንዲህ ነው እንግዲህ የኛ ዘመን ጣጣ፣
የየዋህ እስትንፋስ የንፁህ እድል እጣ።
ያደለው በሰው ልብ እንደተናፈቀ በክብር ይሞታል፣
ያለደለው ደግሞ የራሱን ቁም ሙቶ ሊገድል ይኖራል፣
ምንድን ነው ሰው መሆን ያዘነ ማስመሰል፣
በውስጥ እየሳቁ ለቅሶ ምን ያደርጋል፣
ፍረድ አንተ ጌታ...
የኃጢያት እልፍኜን
ና ደብድብ ጣራዋን
ወየ ኡኡ ብየ ላቅልጠው ዋይታየን
ቅጣኝ ለክህደቴ
አርገው እውነት የምር የውሸት ለቅሶየን።

እናም በኔ ዘመን...
የእውነት ዘውድ ተጭኖ የሚታየው አሁን፣
ቀዳዳን በር አረጎ ሚያይ ልዩነትን
አንድነትን ትቶ የሚስብክ ጥልን።
በአንድ መንጋ ሚሄድ፣
ያለ ሀሳብ ሚነጉድ
ግን
እስከየት ድረስ ነው?
ጎዳናው ሚያዘልቀው
እስከ መቼ ድረስ በጎጥ አንድ መንገድ፣
በንፁሃን ደም ላይ..
ንፁሃንን ከሶ እያሰሩ መሄድ።
ነውስ?
'ውሻ በቀደደው ጅብ ሠፍቶ ይገባል
ፍየል በግ ቢያጣ እንኳ
ቋንጣውን ሸምጥጦ ይሮጣል እንዲባል
ሆነ በቃ እንግዲህ
የዚች አገር እጣ በተራ መበደል?!

ተው
እንተው
በዳይ ከተበዳይ እኩል ፍትህ ካለ ካልሰከነ ነገር፣
ቤትን ካላቆመ
አንደኛው ጭራሮ ሌላው ሆኖ ማገር፣
ምስጥ የበላት ጎጆ ትመስላለች ሀገር።
"
' ? '
በበረሀ ጋመን ጠውልጎ ያልረባው፣ማውጣት የተሳነው የማህፀንሽ ፍሬ፣
ለአርባ አምስት አመታት ንጉሥ ያልወጣብሽ ምን ኀጥያት ሰርተሽ ነው ንገሪኝ ሀገሬ?

ምንዱባን ኢትዮጵያ - ምትለምኝ ሰጥተሽ፣
ጥበብሽ ሳይቆሽሽ
የምታጥቢ ፈተሽ
ሩህሩኋ የኔ
ጥጥ ፈታይዋ እናቴ፣
ምን ልብ ነው ያለሽ
እኔ እየጠላሁሽ
አንቺ ምትሳሽልኝ ንገሪኝ በሞቴ?

' መደምደሚያ '
በአንድ ቋንቋ ዘየ የሰራነው መንደር፣
ምን ብንኩራራበት አይሆነንም ሀገር።
ይብቃን መጋደሉ፣
ይብቃን መላቀሱ፣
መርገምት ነው ይሄ
እንፀልይ ወደ እርሱ።
ደግሞ
ያሻው ቢከፋኝም፣
ያሻ ብቀየምም፣
ወንድምነትክን ግን
ለሰከንድ አልፍቅም
ሲነኩህ ያመኛል ይሰማዋል ጎኔ፣
ይህ ሁሉ ግፍ ይቁም በአንተ በእሷ በእኔ
ልዩነቱ ይብቃን አንድ እንሁን ወገኔ።

ሰኔ 30/2011 ዓ.ም ሌሊት 9:18 አለቀ

@getem
@getem
@getem
ማናለ ሸረኛ ቴሌኮምን 'ሚያክል
ጥሬ-ስጋ ጋብዞ ቢላ ሚከለክል!
በስጦታ ጥቅል
ሁሉን አንበሽብሾ፣ ሲቀበል ምርቃት
ኔቶርኳን በጃ'ዙር
እንዳሻት እንዳትሮጥ፣ እግሮቿን ነጠቃት።

አንካሳዋ ኔቶርክ
ሜዳው እንደዳገት፣ ክብዷት ስታዘግም
ሰበበኛው ፌዝቡክ
ይህን አመኻኝቶ፣ ላመሉ ሲለግም
የሥጦታው እድሜ
ሆኖ ግማሽ ጷግሜ

ሳንጠቀምበት፣ በወግ ሳይፈይደን
ስንለማመጠው፣ ስልክ ላይ ተጥደን
ያገልግሎት ማብቂያው
ሳናውቀው ደረሰ፣ መገባደጃው ሳ'ት
ኧረግ እናንተዬ
ነዉር አይደለም ወይ፣ እያሳዩ መንሳት??!!
ነገሩ ነውንጂ
ብሶት ሚያናግረን፣ በየአደባባዩ
በነጣ ይቅርና
ደሞዝ እየበላም፣ ይኸው ነው ጠባዩ።

ወገኛው( @Dani_pher )

@getem
@getem
@getem
👍1
ስለቴን ልዋጠው

ቅድም የወጋሁት፣ገና ሳይደርቅ ደሙ፣
ሳይድንለት ቁስሉ፤
ሌላውን መርጬ ሳልሰነዝር በፊት ስለቴን ለአካሉ፤
ዛሬ እንኳን አልፎልኝ ምላሴን ከትቼ ጥርሴን ልግጠምና፤
ሰው ሳለወጋ ልዋል አፌን ልዝጋውና።

.....Facha....

@getem
@getem
@getem