ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#በምናልባት ~ሰበብ

ካሳደገኝ ልማድ
ከአብሮነት ቀዬ~እራሴን አርቄ
በራሴ አኩኩሉ
በትዝታ ዋሻ ~እራሴን ደብቄ
ለብዙ ዘመናት
ከተሸሸኩበት~ከኖርኩበት ጫካ
ፍንጣቂ ጨረር
ፀሊም ትዝታዬን~ቢመስለኝ ያፈካ
ከደበቀኝ ክህደት
ከመገፋቴ ላይ~መጠገን እያየሁ
በጨረሯ ተስፋ
ወዳልመጣው ዛሬ~ለመሄድ ተመኘሁ፡፡

ኩኩሉ ባይ እኔ
ለማይነጋ ሌሊት ~እኔው ተሸሻጊ
በራሴ አኩኩሉ
እራሴን ደብቄ ~እራሴን ፈላጊ
ታዲያ ከኔ በቀር
ያ'መታት ዋሻዬን~ጫካዬን ሊያሳጣ
በመሸው ቀኔ ላይ
መሻት የፀነሰው~ጨረር ከየት መጣ?

አላውቅም እኔንጃ
ምናልባት ምስጢሩ~ከሆነ ግን ካንቺ
በብርሀን ሙይው
የፍቅር ዋሻዬን ~ጨለማዬን እንቺ፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))
@getem
@getem
@getem