ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ህሊና

ሰው በሰው ቢከፋ ፡ ሰው በሰው ቢቀና
በአእላፍ ሰራዊት ፡ ንጉሡ ቢጽናና
ስለገንዘብ ብሎ ፡ በአቋራጭ ቢያቀና
እንበለ ሰንበት ሆኖ ፡ ከሰማይ ቢወርድ መና
ዝናም እምቢ ብሎ ፡ ባይቋጥር ዳመና
ሰዉ ቢመጻደቅ ፡ በትናንቱ ዝና
ሰው አላየኝ ብሎ ፡ ቢሰራ ሙስና
ፍርዱ ከተሰጠ ፡ ለሚሞላ ካዝና
ሥነ ፍጥረት ቢጓዝ ፡ በሐሰት ጎዳና
ለእኔስ...
በፍቅር የገዛችኝ ፡ አለችኝ ህሊና
በእውነት የምትመራኝ ፡ አለችኝ ህሊና

(📝ል.ግ.ኢ)

@getem
@getem
@getem