ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
(ለአምባዬ ጌታነህ እና ለጃኖ እንዲሁም ስለሀገር እና ብሔር... ለሚጽፉ መልስ)

#ዓለም_ናት_ሀገሬ

"ኢትዮጵያዊያን ነን
ሁሉም የሚያውቀን በደግነታችን
ወጥ ድንጋይ ቀርጸን ሀውልትን ያቆምን..."
እያልክ አትሸንግለኝ

"የጥቁሮች ኩራት
የጀግና ሕዝብ እናት
ድንግል አፈር ድንግል መሬት..."
ብለህ አታቁስለኝ

"ኢትዮጵያ አንድ ናት
ዘር ብሔር ያልሻራት
በጎሳ በዘር ፡ አንፋሰስ ደም
እንኑር በፍቅር ፡ እንኑር በሰላም"
ብለህ አትንገረኝ

"ኩሽ ብሔር የለውም" እያልክ አትፎግረኝ

በል እንግዲህ ስማኝ...

አምላክ አዳምን ሲፈጥረው
በላብህ ብላ ብሎ ሲያዘው
ኢትዮጵያ ኑር አላለው
እስራኤል ኑር አላለው
"ምድር ታብቅልብህ አሜኬላ
አንተም ጥረህ ግረህ ብላ"
ነበር ያለው።

ስማኝ ወንድሜ ሆይ፡
እንኳን ላስብ ስለዘር ብሔሬ
አልሻም ማውራት ስለሀገሬ
ምን ናትና የምሞተው ለአህጉሬ
የእኔስ 'ዓለም' ናት፡ ርስቴና ክብሬ
ለገነት መግቢያ ፡ ጊዜያዊ መንበሬ።

ክርስቶስን አስብ
ቤተ ልሔም ተወልዶ በናዝሬት ያደገው
በዚያ ስለኖረ 'ኤዥያዊ' ልትል ነው?
ወይስ...
"ኢትዮጵያ ስለመጣ ስለባረካት በስደቱ
የለም ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነው በዜግነቱ"
ልትል ነው?

ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ አይደለም
ኤዥያዊም አይደለም
እሱስ የ'ዓለም' ነው ፡ ስሙም መድኃኔዓለም

ፍጡሩን እናንሳ ፡ የአምላኩን ትተን
አይቴ ብሔሩ ፡ ለሊቁ አንስታይን
አሜሪካ ፡ ወይስ ጀርመን?
ኒው ዮርክ ፡ ወይስ ዋሽንግተን?
ሙኒክ ፡ ወይስ በርሊን?
የለም...
የአንጻራዊነት ፡ ምሥጢርን የፈታው
ሐሳብን ከገሀድ ፡ በአንድ ያዋኃደው
የሀገር አይደለም ፡ የ'ዓለም' ሀብት ነው።

እስቲ አስብ ወንድሜ፡
አንገትህን ወደላይ ፡ ወደሰማይ አቅና
እየመጣ ቢሆን ፡ UFO ከደመና
ምድርን ሊቆጣጠር ፡ ግዛቱን ሊያቀና
ያኔ የአዳም ዘር ፡ ያስባል ወይ ብሔር?
ያስባል ወይ ሀገር ፡ ያስባል ወይ አህጉር?
የለም...
ክፍልፍሏ ዓለም ፡ ትሆናለች መንደር
ሰው ሁሉ ያብራል ፡ እንዲኖር የሰው ዘር
ይፈጠራል ትውልድ ፡ ለ'ዓለም' የሚኖር

ስለዚህ ወንድሜ
መኖርያህ 'ዓለም' ናት ፡ አትስበክ ስለሀገር
የ'ዓለም' ንብረት ነህ ፡ አትጻፍ ስለብሔር

(ከተሳሳትኩ እታረማለሁ 📝ል.ግ.ኢ)

@getem
@getem
@getem
👍3