ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ብኩን አፍቃሪ ፪
(ሚካኤል አስጨናቂ)
.
አንቺን ያጣሁ ጊዜ...
ፀሀይቷ ጠልቃ ምድሩ ያልገለጠ
ጨረቃ ተሠብራ ጎኗ ያገጠጠ
ከዋክብት አብረው የታባህ የሚሉኝ
በከንቱ አጀባቸው አንጓጠው የናቁኝ
መስሎ ይታየኛል።
።።።
አንቺን ያጣሁ ጊዜ...
ቀድማ የጠለቀች ፀሀይ የማትወጣ
ጨረቃ ምታፍረኝ ክበቧን ስታጣ
አንጓጣጭ ከዋክብት ስቀው 'ማያበቁ
በዓይኔ እንባ ማዕበል የሚንቦራጨቁ
መስሎ ይሰማኛል።
።።።
አንቺን ያጣሁ ጊዜ
እኒያ አላዋቂዎች...
ወፈፈ እያሉ ይነክሩኛል ጠበል
መድሀኒት ቀይጠው ያጎርሱኛል ቅጠል
እጣን አጣጢሰው ቄጠማ ጎዝጉዘው
ይለማመናሉ...
ለራሱ የማያውቅ አዋቂ ጋር ሄደው ።
።።።
አይገርምም ዓለሜ?
አይገርምም የኔ ውድ?
.
እነዛ የዋሆች...
አይረዱኝም እንጂ ፥ ደርሰው ቢያውቁኝማ
መድሀኒቴ አንቺ ፥ መምጣትሽን ሳልሰማ
.
በክንድሽ ታቅፌ ከጉያሽ ሳልገባ
ከጡቶችሽ ዋሻ....
እመሀል ዘልቄ ፥ ናፍቆት ሳላነባ
.
በሎጋ ጣቶችሽ ፀጉሬ ሳይዳበስ
በትንፋሽሽ ንዝረት ልቤ ሳትታመስ
ፈገግታሽ ደምቆልኝ ደስታ በኔ ሳይነግስ
.
ፀሊሜ ተገፎ ፀሀይ ሳትወጣ
ጨረቃ ላታፍረኝ በክበብ ሳትመጣ
አንጓጣጭ ከዋክብት ...
መምጣትሽን አይተው አንገት ሳይደፉ
በፀበል አልድንም...
በቅጠል አልሽርም፥ ከንቱ ነው 'ሚለፉ!!

@getem
@getem
@gebriel_19
1
አልረዳህም

ስወድህ ሳፈቅርህ ስንከባከብህ
አልከኝ ችላ ችላ ፍቅሬን ረስተህ
ሲሻህ አምሽተህ አልያም ተከፍተህ
ትመጣለህ ከየትም ፍቅሬን ረሰተህ
አይጠቅምህም ተወው ግራ መጋባቱ
እሰው አፍ መግባቱ ትዳር ማናጋቱ
አንድ ቀን ሲገባህ የእኔና አንተ ነገር
አንድ ቀን ሲሰማህ የእኔና አንተ ፍቅር
ፍቅሬ መልሽ ስትል ፍቅሬ አምጭ ስትል
ያኔ አልሰማህም ፍፁም አልጠቅምህም
ድፍረት አይሁንና እኔ አልረዳህም፡፡

ምዕራፍ በላይ ፳፻፲፩

@getem
@getem
@getem
1
ሞት

ትላንት ተወኝ
ዛሬም ተወኝ
ነገም ተወኝ
ቆም ብለህ አስበኝ
ተምሬያለው እየኝ
አንተ ስታስበኝ
ላልመለስ ሄድኩኝ
እንደ ሞትክ አሰብኩኝ

Dave A.K

@getem
@getem
ዘረኛ ገጣሚ በሱፍቃድ ዲባባ 2
<unknown>
በየቀነኑ በዘረኝነት ምክንያት ስለሚደርስ ችግር በሀገራችን ስላለው ሁኔታ የሚያስለቅስ ግጥም

#በሱፍቃድ

@Getem 😫😩😩😩😩
@getem 😫😩😩😩😩?


@Yewahpictures ?😰😰😰?

Yewahpictures😩😩😩😩😩
👍1
መሼ ደሞ
(አቤል ምሕረት Barich)
መሸ ደሞ ልትናፍቂኝ
በስስት ሃይቅ ልታጠልቂኝ
መሼ ደሞ
መሼ
መሼ
ምሽት መጣ ፀሃይ ሸሼ
....
በደብዛዛው መብራት ግርጌ....
.
ጎዳናው ላይ
.
ተጣምረው ሳይ
.
ተቃቅፈው ሳይ
ልቤ አንችው ጋር አዝግሞ.....
የት ናት ይላል የኔን ሲሳይ
የት ነሽ?

☞FB አቤል ባርች

@getem
@getem
@gebriel_19
ቀብር ሞት ቀደመ
መኖር ቡቱቶ ተጀቡኖ
በባዶ ዝና ተጀንኖ
በምላስ ዶፍ መኖር ገኖ
በሀብት ነሮ ጠሪያ አህሎ
አፈር ቢሸሽ ካፈር በቅሎ
ድሎት በዝቶ ቢመሰል አለሎ
አይ ሰው ከንቱ
ዛሬን ለነገ መሰዋቱ
ለማያቀው ለመጪው መረታቱ
ትቢያነቱ መርሳት መዘንጋቱ
ለመያስከፍለው ለፍቅር መሰሰቱ
መወቅ መወቅን ከሰወረ
አይናማው ብሌን ከወረ
የሰላም ጠቅሙ ከዋቂ ከተሰወረ
በሰዉኛ ቀመር ትውልድ ነው የከሰረ
የተመረው መክኖ አንገቱን ከደፋ
መሀይ በርትቶ በአንባው ካናፋ
በታሪክ ተቀብረን ድንጋይ ከዘከርን
ዘንድሮ ሞተን አምና ተቀበርን፡፡




ብሌን አሰላ

@getem
@getem
@gebriel_19
///////// #ፍቅር_የሸንፋል_¡ //////

ጥላቻ ፣ በርትቶ፣
#ዘረኝነት 'ሚባል ፣ ቆንጆ ስም አግኝቶ።
ጡንቻውን አፈርጥሞ ፣ እንደ ድልብ በሬ፣
ይንጎማለል ጀመር በ'ያደባባዩ ፣ እዚም እመንደሬ።

ብዙን አሳንሶ ፣ አንድ እያነገሰ፣
ከእኔ ውጭ ወዲያ ፣ ብሎ እያፈረሰ።
በፈርጣማ ጡንቻው ፣ አምሳሉን እረግጦ፣
'እኔ' ና 'የእኔ' ፣ በሚሉ ፈሊጦች ሌላውን ደፍጥጦ።

እንሰማለን ከዛ
ከ'ያቅጣጫው ዜና

ቅስምን የሚሰብር ፣ ፍቅርን የሚያሳዝን፣
የሚያለብስ ፍርሃት ፣ የሚያቆስል ልብን።
ነፍስን የሚ'ያሸብር ፣ ቀኑን የሚያጨልም፣
ባዶ የሚያረጋት ፣ የመኖርን ትርጉም።

እንሰማለን ከዛ

እዚ'ጋ ብጥብጥ ፣ እዛ ሰው አለቀ፣
ይህን የሚያህል ህዝብ ፣ መኖሪያ ለቀቀ።
ኑሮን እየኖረ ፣ 'ካገር ወጦ ያለው የተሞላቀቀ፣
አለሁ ባይ 'ባገሬ ፣ ቀን ውሎ ለመግባት እየተሳቀቀ።
ሁሉም አንድም ሳይቀር ፣ ተዋልዶ ከሁሉም ሲኖር እነዳልነበር፣
በጥላቻ ወኔ ፣ በዘር ጎሳ ስካር፣
ቤተሰብ በትኖ ፣ ውጣ ከሀገሬ ድንበርህን አስምር።

#ጥላቻ ፍቅርን ፣ በዚ በዚ ምክንያ፣
ቁመትም ክብደትም ፣ በደጋፊም በልጦት።

#ፍቅር በአንጻሩ ፣ ጉልበቱ ጠንፍፎ፣
በረሀብ በጥማት ፣ ብርታቱ ተገ'ፎ።
የሃይሉን ተራራ ፣ የማይናድ ግርማው፣
ትንሿ ድማሚት ፣ ጥላቻ ደርምሳው።
ከጎኑ 'ሚቆሙ ፣ የልቤ 'ሚላቸው፣
ትተውት ሄደዋል ፣ ጥላቻ ገዝቷቸው።

እናም ቀኑ ደርሶ ፣ መፋለሚያው ሰዓት፣
አሸዋ ከሆነው፣አእላፍ ከሆነው ፣ #ከጥል ደጋፊ ፊት።
#በፍቅርም በኩል ፣ በጣት 'ሚቆጠሩ ቢሞቱም 'ማይከዱት፣
ነበሩ የቆሙ ፣ እኛ አለን ብለውት።

የጥል ደጋፊዎች ፣ ሞቆ ጭፈራቸው፣
የፍቅርን ሜዳ ፣ አርገው የራሳቸው።
#ፍቅር_ከ_ጥላቻ ፣ ፍልሚያው ተጀምሮ፣
ፍቅር በሃገሩ ፣ እነደ ባዕድ ተቆጥሮ።

ባላወቁ ሰዎች ፣ የፍቅርን መዛል፣
#ፍቅር_ያሸንፋል ፣ በየቦታው ሲባል፣
እንኳንስ ማሸነፍ ፣ መቆምም አቅቶታል።
#ፍቅር_ያሸንፋል_¡

@DannyShy

@getem
@getem
ላንጥፍልሽ ወርቁን
ላንጥፍልሽ ብሩን፤
አልቻልኩትምና ለብቻ ማደሩን፤
(ልዑል ሀይሌ )

@getem
@getem
@lula_al_greeko
አዋቂ እያበጀን ሰነፍ እያበጀን
አለማፈር ነው ወይ እንደዚህ ያስረጀን
(ልዑል ሀይሌ)

@getem
@getem
@gebriel_19
አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል
(ልዑል ሀይሌ)
.
አንድ ሐሙስ ቀርቶታል ይላሉ
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል
ጌታ በመጨረሻው እራት
በትህትና አጥቦኛል
.
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል
.
ጌታዬን በ30 ዲናር ልሸጥ
ተደራድሬ መጥቻለሁ
ግን እንደሚያነፃኝ ስለማምን
እንደሚነሳ ስለማውቅ
ይሁን ስቀሉት ብያለሁ
.
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል!.
.
የሐጢያትን ቀንበር ላወርድ
በስቅላቱ ልነፃ
በስጋ ደሙ ሊያጥበኝ
የአዳምን የዕዳ ደብዳቤ
ቀዶ አዳምን ነፃ ሊያወጣ
የዕዳ ደብዳቤው ክታብ
ከጀርባዬ ላይ አርፎ
ክፉ ልቤ ጌታን ሸጠው
30 ዲናር አትርፎ
.
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል!
.
የትንቢቱ መፈፀሚያ
ጊዜው እንዳይርቃችሁ
የመጨረሻው ሐሙስ ቀን
ዛሬ ጌታዬን ሼጬ
ጌታዬን ሰቅዬ ነው
ተዓምሩን ማሳያችሁ
.
አዎ አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል!
.
ሐጢያቴ ሊደመሰስ
ልታጠብ በአዲስ ህይወት
መድህን ይሆን ዘንድ ሊቸነከር
ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሊሞት
.
ይኸው ሰማዪ ጠቋቁሯል
ጌታ ለመጨረሻው እራት ጠርቶኛል
አንድ ሐሙስ ቀርቶኛል!!
27-07-2010

@getem
@getem
@gebriel_19
እርቃን
-------
ጨረቃውም ቀላ፣ፀሐዩም ጠቆረ
ግዑዝ ባምላኩ ቃል...
እርቃን የመደበቅ፣ሚስጥርን ተማረ
.
ሰውም ሰለጠነ፣መጠቀ በረረ
ነገር ግን እሳቤው፣ከግዑዝ አጠረ
እንኳን የሰው እርቃን…
የራሱን መሸፈን፣ ይሳነው ጀመረ
.
« ሚኪ እንዳለ »

@getem
@getem
ቃል
#ፀሀፈ ብሩህ

የአካሌ ንዝረት
ስሜቴ ተዋቅሮ
ለልሳን ከሳቹ
ከንፈሬ አቀብሎ
ነበር የኔ ቃል
አካልሽን ገንቢ፣ከስሜትሽ አልፎ
ከኔ እኩል ያረገሽ፣ጎደሎሽን ሞልቶ
ነበር የደረስነው
ለቆየው ፍቅራችን
ፍቅርን በገነባ
በቃል ሳይበተን።

@Birukam

@getem
@getem
🙏እለተ ሀሙስ🙏
------------------
የህዝባችን ልቡ በክፍት ስለጓደፈ
የአባቶች ማንነት
በልጅ ልጆች ሀሳብ
ዘቅጦ ስላደፈ
ከዚህ ሁሉ ጥፋት
የወንበሩ አለቃ
እራሱን ለማንጻት
እጁን ከሚታጠብ፤
ጥቂት ወረድ በሎ
የምእመናኑን ልብ
እስከ ስሩ ይጠብ።

ፀጋየ ግርማ እረቲ(ሜሎስ)

@getem
@getem
#ሴይጣን_ሆይ_ዛሬ_ትቃጠላለህ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም የሚሰግዱበት ያመቱ ጁወዓ ነው።
ሄለን ፋንታሁን

ሳሚኝ ሳሚኝ አትበል መሣም እፈራለሁ
የተሣመ ታሞ ተሠቅሎ ስላየሁ



@getem
@getem
@gebriel_19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
...ፍረደን...
ስማኝማ አንድዬ
አራት መቶ ጅራፍ ተቆጥሮ የማያልቅ ስፍር የለሽ በደል
ለከፈልክባት ቀን እንኳን አደረሰህ አይባልም አይደል
የሰማዕታት ሀገር የፃድቃን ከተማ
ፅርሐዓርያም እንዴት ነው በበዓል ዋዜማ
ከዙፋንህ ግርጌ ቄጠማ ጎዝጉዘው እያሸበሸቡ
ሰውና መላእክት በአንድ ሲሰበሰቡ
ከመላእክት ምግብ ፃድቃን ሲመገቡ
ሰማይ ቤት እንዴት ነው የበዓል ድባቡ
ትዝ ይልሀል አይደል ?
አልጋውን አስይዘህ ያ'ዘለልከው ድኩም
አላውቀውም ብሎ የመታህ በኩርኩም
እንዴት ነው መፃጉ ኑሮ እንዴት ይዞታል
ቸርነትህ ደርሶት እርሱም ገነት ገብቷል
ወይስ የሲዖል ፍም እሣት ተስማምቶታል
ኑሮ ከተባለ እኛ አለን እንዳለን
አንተን መስለንና ያንተን አስመስለን
እንደ ኮሶ እንደ ሬት ኑሮ እየመረረን
እኔን ምሰሉ ሚል ቃልህን አክብረን
ሰውን ያክል ክቡር ነፍስ ተሸክመን
ታክሞ የማይድን ስልጡን ከብት አክመን
አድናለሁ ስንል እራሳችን ታመን
ሰርዷችንን ግጦ የጠገበ ኮርማ ዞሮ እየረገጠን
ወርቅ የሰፈርንለት አመድና ትቢያ አፈር እየሰጠን
ኑሮ ከተባለ እኛ አለን እንዳለን
አንተን መሆን ባንችል ያንተን አስመስለን
እናልህ አንድዬ
እንዳይጎርስ ለጉመው እንዳይሄድ ቀይደው
ከቤት እንዳይወጣ በጥዋት ጥመደው
የሚል ህግና ደንብ በዝባዥ አዋጅ ወጥቶ
ተመጥምጦ አለቀ ጉልበታችን ሟሙቶ
በራሳቸው ችሎት
ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ዳኛ ሆነው እየቀጡን
ውኃ ጠማን ስንል ሆምጣጤ እያጠጡን
ከኩንታል ሙሉ ማር ሸክማችን ከበደ
ወዳንተ እንዳንመጣ ጉልበታችን ራደ
እንደ ልባሽ ጋቢ ዋጋችን ቀለለ
እባክህ ቶሎ ና ትክሻችን ዛለ
ልብሳችንን ነክተው ደማቸው ቀጥ ያለ ከሞት የተረፉ
ሀኪም ድሮ ቀረ እያሉ ለፈፉ
በእኛ መስዋዕትነት ከመቅሰፍት የዳኑ
በፈውሳቸው ማግስት እኛ ላይ ጀገኑ
መንግሥት!?
መንግሥትማ አለ እንጅ ስራውን ይሰራል
ዘላለም የመንገሥ መብቱን ያስከብራል
የተቃዋሚውን ጀርባ አጥንት ይሰብራል
በጠብመንጃው አረር የደቀቁ እግሮችን ሆስፒታል ይልካል
እንቶኔና እንትና በፈጠሩት ግጭት እያለ ይሰብካል
ተሰባሪው ታዲያ ሰባሪውን ፈርቶ አዳኙን ይከ'ሳል
የሀኪሞች ስህተት ውጤት ነው እያል አቧራ ያስነሳል
በርግጥ ሰው ይስታል እውነቱ አይካድም
በማካሮ ሽጉጥ መስበሩ ባይከብድም
ለዜና ካልሆነ
የተሰበረ እግር በጥገናው ማግሥት ቆሞ አይራመድም
እናልህ አንድዬ በዚች የጉድ ሀገር
ባልታደለ ዘመን በግም ወቅት ተፈጥረን
አንድ ቀን ከግማሽ ያለምንም ዋጋ ዱቲ ተወጥረን
በእለተ ትንሳኤ ላባችን ገብረን በደማችን ሰክረን
ካሣ' መሉ ፈጅቶ የመጣ ሰካራም እያደነቆረን
ልዝብ ያልከው ቀንበር ሸክሙ ከበደን
ነፃ አውጭ ላክልን ወይ መጥተህ ፍረደን

መታሰቢያነቱ፦ የትንሳኤ በዓልን ከቤተሰብ ተለይታችሁ ሆስፒታል ውስጥ ለምታሳልፉ የጤና ባለሙያዎች በተለይ በአውደ ዓመት ምድር ያለምንም ክፍያ ላብና ደማችሁን ለምትገብሩ ኢንተርን ሀኪሞች ይሁንልኝ ።

ዶ/ር ጌታነህ ካሴ
ዝቋላ ሆስፒታል

በዚሁ አጋጣሚ ለመላው የዚህ ቻናል ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቴ ይድረስልኝ!!!

@getem
@getem
@getem
ስቀለው ስቀለው ደጉን ስው ስቀለው
ግደለው ግደለው በርባንን ግን ማረው
አዳኝነቱንም በክደት ሽፈጡ
ጌታቸውን ትተው በርባንን መረጡ
ያመጻን ጎዳናን ፈትፍተው የበሉ
ለርባና ቢስ አለም ደፍ ቀና እሚሉ
በርባን ወዳድ ትውልድ ይኸው ዛሬም አሉ።


@getem
@getem
@Bebra48