ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
///////// #ፍቅር_የሸንፋል_¡ //////

ጥላቻ ፣ በርትቶ፣
#ዘረኝነት 'ሚባል ፣ ቆንጆ ስም አግኝቶ።
ጡንቻውን አፈርጥሞ ፣ እንደ ድልብ በሬ፣
ይንጎማለል ጀመር በ'ያደባባዩ ፣ እዚም እመንደሬ።

ብዙን አሳንሶ ፣ አንድ እያነገሰ፣
ከእኔ ውጭ ወዲያ ፣ ብሎ እያፈረሰ።
በፈርጣማ ጡንቻው ፣ አምሳሉን እረግጦ፣
'እኔ' ና 'የእኔ' ፣ በሚሉ ፈሊጦች ሌላውን ደፍጥጦ።

እንሰማለን ከዛ
'ያቅጣጫው ዜና

ቅስምን የሚሰብር ፣ ፍቅርን የሚያሳዝን፣
የሚያለብስ ፍርሃት ፣ የሚያቆስል ልብን።
ነፍስን የሚ'ያሸብር ፣ ቀኑን የሚያጨልም፣
ባዶ የሚያረጋት ፣ የመኖርን ትርጉም።

እንሰማለን ከዛ

እዚ'ጋ ብጥብጥ ፣ እዛ ሰው አለቀ፣
ይህን የሚያህል ህዝብ ፣ መኖሪያ ለቀቀ።
ኑሮን እየኖረ ፣ 'ካገር ወጦ ያለው የተሞላቀቀ፣
አለሁ ባይ 'ባገሬ ፣ ቀን ውሎ ለመግባት እየተሳቀቀ።
ሁሉም አንድም ሳይቀር ፣ ተዋልዶ ከሁሉም ሲኖር እነዳልነበር፣
በጥላቻ ወኔ ፣ በዘር ጎሳ ስካር፣
ቤተሰብ በትኖ ፣ ውጣ ከሀገሬ ድንበርህን አስምር።

#ጥላቻ ፍቅርን ፣ በዚ በዚ ምክንያ፣
ቁመትም ክብደትም ፣ በደጋፊም በልጦት።

#ፍቅር በአንጻሩ ፣ ጉልበቱ ጠንፍፎ፣
በረሀብ በጥማት ፣ ብርታቱ ተገ'ፎ።
የሃይሉን ተራራ ፣ የማይናድ ግርማው፣
ትንሿ ድማሚት ፣ ጥላቻ ደርምሳው።
ከጎኑ 'ሚቆሙ ፣ የልቤ 'ሚላቸው፣
ትተውት ሄደዋል ፣ ጥላቻ ገዝቷቸው።

እናም ቀኑ ደርሶ ፣ መፋለሚያው ሰዓት፣
አሸዋ ከሆነው፣አእላፍ ከሆነው ፣ #ከጥል ደጋፊ ፊት።
#በፍቅርም በኩል ፣ በጣት 'ሚቆጠሩ ቢሞቱም 'ማይከዱት፣
ነበሩ የቆሙ ፣ እኛ አለን ብለውት።

የጥል ደጋፊዎች ፣ ሞቆ ጭፈራቸው፣
የፍቅርን ሜዳ ፣ አርገው የራሳቸው።
#ፍቅር_ከ_ጥላቻ ፣ ፍልሚያው ተጀምሮ፣
ፍቅር በሃገሩ ፣ እነደ ባዕድ ተቆጥሮ።

ባላወቁ ሰዎች ፣ የፍቅርን መዛል፣
#ፍቅር_ያሸንፋል ፣ በየቦታው ሲባል፣
እንኳንስ ማሸነፍ ፣ መቆምም አቅቶታል።
#ፍቅር_ያሸንፋል_¡

@DannyShy

@getem
@getem