ከ፦አምባ፦ጔሮ
#ፀሀፈ_ብሩህ
በተለቀመ ጥጥ፣
በሸማኔ ድውር
የሰው እራቁቱ፣
ገላ እንደሚከለል
እኩይ ስብእና፣
የታጨቀ በነውር
የበግ ለምድ ለብሶ፣
ተሰው እንደሚኖር
ማየት ማመን ብለህ፣
አይንህን አትመን
እዪዪን አታብዛ፣
ፊትህ ለሚከወን
ባየኽው አትኮንን፣
አይንህን አስዳኝተህ
የውስጥህን ግለት፣
ማየቱ ተስኖህ
ከእሳቤህ በላይ፣
የሰው ልጅ አናት ላይ
ላንተ ተሰውሮ ፣
ለግዜሩ ከሚታይ
አምባጔሮ አለ፣
ከ–እንባ–እጔሮው ውስጥ
ሰላም የሚነሳ፣
ሰውሮ የከተመ
የማንነቶች ነውጥ።
@getem
@getem
@Birukam
#ፀሀፈ_ብሩህ
በተለቀመ ጥጥ፣
በሸማኔ ድውር
የሰው እራቁቱ፣
ገላ እንደሚከለል
እኩይ ስብእና፣
የታጨቀ በነውር
የበግ ለምድ ለብሶ፣
ተሰው እንደሚኖር
ማየት ማመን ብለህ፣
አይንህን አትመን
እዪዪን አታብዛ፣
ፊትህ ለሚከወን
ባየኽው አትኮንን፣
አይንህን አስዳኝተህ
የውስጥህን ግለት፣
ማየቱ ተስኖህ
ከእሳቤህ በላይ፣
የሰው ልጅ አናት ላይ
ላንተ ተሰውሮ ፣
ለግዜሩ ከሚታይ
አምባጔሮ አለ፣
ከ–እንባ–እጔሮው ውስጥ
ሰላም የሚነሳ፣
ሰውሮ የከተመ
የማንነቶች ነውጥ።
@getem
@getem
@Birukam