ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ተፈላሰፍ አለኝ

📝📝📝

ተመሰጥ ተደመም ተመልከት ተፈጥሮ
እይታህን አጥራ አስተውል በአንክሮ
ተገንጠል ተለየው ናቀው ይህን ዓለም
ቆሞ አንቀላፍቷል በቁሙ በማለም
ጠይቅ ተመራመር ግለጠው መጽሐፉን
አራግፈው መርምረው እየው ብራናውን
የአባቶችን እውቀት ባሕረ ሃሳቡን
ግባና ፈትሸው ቅኔ ማህሌቱን
ጥበብን ፈልጋት እውቀትን አስሳት
ግባ ከመድራሳው እውነትን ፈልጋት


ተነስ ተመራመር ተፈላሰፍ አለኝ
ጥልቅ ብለህ ስመጥ ግባበት አሰኘኝ
የኋላውን እውቀት የዛሬን መነሻ
የነገን አብነት መንገድ መቀየሻ
አንሳው አሞግሰው አይረሳ ከቶ
የፀና ዛፍ የለም ስሩ ተበላሽቶ
አለኝ አስታወሰኝ የህሊናው ደውል
ሊያባንነ ኝ ቢሻ ካንቀላፉ መሃል
ይህንንም ነግረውኝ ጠፉ ተሰወሩ
አነቃነው ብለው ርቀው በረሩ
መች ተረዱኝና....
አውቆ የተኛን ሰው...መሆኑን ነገሩ

🗒🗒🗒

ኪነ ዳን

@getem
@getem
@gebriel_19
ይመስለኛል ልቤ
ያመልክሽ ነበረ
ድንገት"ሰው" ስትሆኚ
ቅያሜው መረረ።
አንቺም ትክክል ነሽ....
ባልተፃፈ ራእይ
ባልተባለ ንግርት
በሚቆጠር ነገ
እፍኝ እድል ዘግኖ
እሷኑ መንዝሮ
መኖር ከተቻለ
ከመላእክት ይልቅ
ሰው መሆን ተሻለ።
(በዚ አላዝንብሽም)
ልቤም እውነት አለው.......
አፍቃሪ ልብና
የፈጣሪ ሚዛን
ይመሳሰላሉ
ከፍጡራን መሀል
ከላባ የቀለለ
ልብ ይፈልጋሉ።
(በዚ አትዘኝብኝ)

ዳኒ.B.

@getem
@getem
@gebriel_19
"ትርጉም የለሽ ፍቅር "
( አምባዬ ጌታነህ )

ሰርክ ትዝ የሚለኝ አንቺን ባሰብኩ ቁጥር፣
በሰው መጣ ፍርሀት የሳምኩሽ ቀን ነበር።
ሰይጣን የኔን እምነት ሊፈታተነው ሲል፣
አንቺን ውብ አድርጎ ፊቴ አመጣሽ ልበል!
መች ጠፋኝ ቀድሞውን አንቺ ነሽ ድክመቴ፣
በአንቺ የምትሀት ውበት፦
ስንቱን የእግዜርን ህግ ያለ ምርጫ ሻርኩት።
አንቺን በልቤ ላይ ያለ ጫና አንግሼ፣
ከነ በድን አካሌ ቤተሰኪያን ደርሼ፣
እስከ ዘጠኝ ፆሜ በዛው አስቀድሼ፣
ወደ ቤት ስመለስ፦
ድንገት በመንገድ ላይ አንቺን ካገኘሁሽ፣
"አንተቃቀፍም"የተባባልነውን በአንዴ ረሳውና ስበር እመጣለሁ በእቅፌ ላስገባሽ።
አንቺን መመኘት ነው ትልቅ ሀጢያት ህመም፣
እውነቱን ልንገርሽ በአሁኑ ሁዳዴ መራብ ነው የኔ ፆም።

▥ 10/07/2011 ▥

@getem
@getem
@gebriel_19
ተላለፉ ሲለን
**

ከመረዋው ውግረት
ከቃጭሉ ዋይታ እኩል ብንሰማም
በአንድ ደውል ድምፅ
ግለ ህሊናችን አንድ ላይ ቢደቃም
ተላለፉ ሲለን
ፊትና ኃላ እንጂ እኩል አንነቃም።

ይስማዕከ ወርቁ
ከ "የወንድ ምጥ" የግጥም መድብል

@getem
@getem
@gebriel_19
ወዳጄ ቤት አከራይን የሚያህል ገጣሚ የለም ስልህ?...ይኸው እትዬ
ሰርጓጇ ቤት እየመቱ ነው..ኳኳኳ!.."ስማ!...ትከፍል እንደሁ
ክፈል...አሻፈረኝ ያልክ እንደሁ ቤቴን ለቀህ ውጣ!!.."...(ርዕስ ነው)
(ልዑል ሀይሌ)
.................................................
ስላንቺ ልገጥም
ሐሳብ ይዤ ነበር ከልቤ ውስጥ ወጥቶ፤
ግን ቤት አከራዬ ኪራይ ሲጠይቁኝ
የቤት ኪራይ በሚል ርዕስ ተተክቶ፤
ጉዞ ጀምሬያለሁ ወደ ሌላ ግጥም፤
ላንቺ ፍቅር ብዬ
የቤት አከራዬን አሳልፌ አልሰጥም፤
.
ይኸውልሽ ዓለሜ!...
የተከራይ ዕዳ የተከራይ ጣጣ፤
በአከራይ ፍቃድ ነው
እንኳንስ ጎጆውን ፍቅረኛ የሚያጣ፤
ስለዚህ አትምጪ
ተይ ልጣሽ ግድየለም፤
አንቺ አትታወቂም
በአከራዬ ዓለም፤
.
በአከራዬ ዓለም!..
ክፈል የሚለው ነው
ረዥም ስንኛቸው፤
ተይ ራቂኝ ዓለሜ
ይምሩኝ እንደሆን አንቺን ልክፈላቸው፤
.
አውቃለሁ ውድ ነሽ..
እንኳን በወር ኪራይ በነፍስ ማትሸጪ፤
ግን እያንኳኩ ነው
የማደርገው ጠፋኝ በቃ ቤቴ አትምጪ፤
.
በቃ ቤቴ አትምጪ!
በቃ ቤቴ አትምጪ!..
ልቤን እሰጥሻለሁ
ከማይደርሱበት ላይ
አርፈሽ ተቀመጪ፤
.
ይኸውልሽ ዓለሜ!!...
እሮሮ ነው መቼም
የሚሰማው ሁሉ የፈጣሪን ጸጋ ሰው ሲያሳድረው፤
ይኸው አከራዬም
አኖርኩህ ይሉኛል በተሠጠኝ አፈር ሌላ አፈር ጭነው፤
መቼም ታውቂዋለሽ
አፈር ነው ኑሯችን አፈር ነው ልብሳችን፤
ግን መች ይረዱናል
ቤት አከራያችን፤
.
የሚያነበንቡት
ክፈል ነው ክፈል ነው ሰርክ እየተነሡ፤
በአከራዬ ድርሰት
ሰው ያንሣል ከኪሡ፤
.
እናም እኔም አለሁ
እያደር እያደር ኪሴ እየበለጠኝ፤
አንቺን ልሸጥሽ ነው
ኑሮ ይሁዳ ነው አሳልፎ ሰጠኝ፤
.
እናም!...
ስላንቺ ልገጥም
ሐሳብ ይዤ ነበር ከልቤ ውስጥ ወጥቶ፤
ግን ቤት አከራዬ ኪራይ ሲጠይቁኝ
የቤት ኪራይ በሚል ርዕስ ተተክቶ፤
ጉዞ ጀምሬያለሁ ወደ ሌላ ግጥም፤
ላንቺ ፍቅር ብዬ
የቤት አከራዬን አሳልፌ አልሰጥም፤

፳፯-፯-፳፻፲፩ ዓ.ም.
ከለሊቱ ፭:፴ ሰዓት

@getem
@getem
@getem
#የኔ ዓለም
(ማዶ)

ሰማዩ አለቅጥ - አጎንብሼም ቀርቦኝ
ምድሩም ላ'ሳቤ - ተሰብስቤም ጠቦኝ
እንደዚህ አንሼ
እንዲህ አጎንብሼ
ከ'ርጅናዬም ብሼ
ቀና ማለት ከብዶኝ - መሬት ፥ መሬት ስቃኝ
የማስተዋል ልምሻ - ዘውትር እየደቃኝ
በነበርኩኝ ጊዜ - አንቺ ብቅ ብለሽ
ሰ...ፊ መሬት ሆነሽ - ጥልቅ ሰማይ ሰቅለሽ
አዲስ ዓለም ሰርተሽ - ስላ'ረግሽኝ ቀና
( ያው ብዙ አይደለሽ-)
ግራና ቀኝ ቁሜ - አንዴ ሹመት ላፅና ...
( በእቅፍሽ ስሆን -- )
እስትንፋስሽ ንፋስ - ውበትሽ ዳመና !

ፍርድ እና እርድ
( አበረ አያሌው )

@getem
@getem
@getem
#ሽር---ሸረሪቷ

አንጀቷን ---
የተቋጨውን ከእትብቷ
ወተቷን ---
የተሾመውን ከግቷ
ወለላዋን ---
የተሰራውን በደሟ
ቅርሷን ---
ያኖረችውን በስሟ
አወጣችው ! - እያማጠች
እንደ ፈትል - እያደራች
እንደ ጅማት - እየላገች
እሷ ---
ቤተሰሪዋ ...
ብቸኛዋ ...
ኗሪዋ ...
ድምፅ የላትም ---
አትሰማም
ኮቴዋ እንኳን ---
አይጣራም
ዝም - ሽው
ሽክርክርክር ...
አቅታዋን ገትታ
መዞር
በዝምታ በጸትታ ---
መሽከርከር
ያለ ተራዳ ---
ድንኳን ማቆም
ያለ ካስማ ---
ቱሻ ማገም
ትንፋሽ የለ ---
ወይ ኮሽታ
ጣሪያ ማድራት ---
በዝምታ በጸትታ
ወራጀ የለ ---
ባለ ማገር
በጸጥታ ---
ትንፋሽ መስበር ...
ጣሪያ ሠርታ ---
መሽከርከር
ግድግዳ ሠርታ ---
ሳትወጥር
ሽር - ሸረሪቷ ---
ኃያል ጥበቧን ሰጥታ
አጀብ ዘመኗን ፈጅታ ---
ሽር --- ሸረሪቷ
ላንዲት መዓልት ቆይታ
አዲስ ቤቷን ሰርታ
ሽር --- ሸረሪቷ ---
ሁሉን ነገር ረስታ ...

ሚያዚያ ---- 1977
የማለዳ ስንቅ
(አበራ ለማ)

@getem
@getem
ይድረስ......
ንጉሱም እንዳይከሰስ
ከሀሳብ እጅጉን ርቆ
ሰማዩም እንዳይታረስ
ከጠፈር ባንድ ሸምቆ።
* * * * * *
ይህ ምስኪን
ሆድ የባሰው ህዝብ
የሚላስ ሚቀመስ ያጣው
ስምክን በየአድባሩ ጥግ
ሰርክ ከሚያሳቅለው
አቤቱ ፈጣሪያችን ሆይ
ንጉሱን ባትችል እንኳ
ሰማዩን ትንሽ ዝቅ አርገው።
ዳኒ.B

@getem
@getem
# የመሸባት……..
ትላንት ዛሬን ወልዶ
ዛሬም ነገን ናፍቆ
እየተያያዙ ሲጉአዙ ሲጉአዙ
ሲሄዱ ሲነጉዱ
ቆሜ አሳልፌአቸው
…………………………….
ቁጭ ብዬ ሳያቸው
ይተባበራሉ ይከባበራሉ
ሰኞ ከማክሰኞ
አሮብም ካሙስ ጋር
አብረው ይሄዳሉ
ይፍጣጠራሉ ይወላለዳሉ
እነሱም እንደ ሰው
ያድጋሉ ይሞታሉ
###################
ይህንን የምልህ ምለፈልፍብህ
ልሰብክህ አይደለም ጊዜን ላስተምርህ
እኔው ተገርሜ ተደንቄ እኮ ነው
አንተን ላማክርህ ያኔን ላስታውስህ
*
*
*
አስታወስከው አይደል ያኔ ያልኩትን ጊዜ
ያበዛው ስህተቴን ያስቃኘኝ ትካዜን
የፍቅሬን መግለጫ ፊደል ምመርጥልህ
ኢሜል ምልክልህ
በ ቀን አስር ጊዜ በ ስልክ ማወራህ
ላግኝህ እያልኩኝ የምጨቀጭቅህ
አስታወስከው አይደል…….
የረፍትህን ጊዜ
ያቺን ቅድስት ሀሙስ ብዬ የሰየምኳትን
በናፍቆት በጉጉት ሁሌ ምቆጥራትን
ነገ እኮ ሀሙስ ነው እያልኩኝ ለሁሉም የማወራላትን
###############################
ታድያ…………………………………………………..
###############################
ለማንስ ላካፍለው ይህንን ስህተቴን
ለማንስ ላውርሰው ይህን ነጩን ጸጉሬን
የተጨማደደው ያረጀውን ፊቴን
ሸካራውን እጄን
ፍለጋ ያደከመው የጠቆረው እግሬን

ላንተ!
ለልጆችህ !
ወይንስ ለራሴው!
በ ቤዛዊት ከበደ

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
የፋኖ ፍቅር

ሰይፍ ከሰይፍ እየተፋጨ ፣
ሕይወት ባረር እጅ እየተዳጨ ፣
ሞት በጥይት አፍ ሰክሮ እያፏጨ ፣
ጨበጣ ውጊያ ቀውጢ ሲጀመር ፣
ጉንፋን ይዞኛል ያልሽኝን ነገር
ላንቺ እየሰጋው ሳስበው ነበር ፡፡


ኑረዲን ኢሳ

@getem
@getem
@getem
አተላው ይደፋ !

የዘረኝነት ጉሽ ፣
. . . . . . ያሰከረው ትውልድ ፤
አንጎሉ እንደዞረ ፤
አንጀቱ እንዳረረ ፤
. . . . . . ቀኑን ከሚገፋ ፤
ጋኑን አለቅልቆ ፣ አተላውን ይድፋ ፡፡

ዶ / ር በድሉ ዋቅጅራ

@getem
@getem
@getem
*ህመም ፩***
በአንዲት ትንሽ ቅፅበት
በትንሽ መንደር ውሥጥ
ዙሪያየን ሥቃኘው
ይህ ነው የሚታየኝ.....
ሢጠጡ ያደሩ የጀዘቡ ነፍሶች
የተበታተኑ የቢራ ጠርሙሶች
ከበሩ ፊት ለፊት....
ሀገር የገነቡ ድንበር ያሥከበሩ
ጊዜ የጣላቸው ሠው ያላነሣቸው
ንፋሥ ላይ ተቀምጠው የሚራቡ ፊቶች
.....ትንሽ ዝቅ ብሎ...
ሁለት ልጅ ያዘለች
ከጡአት እሥከ ማታ ላፍታ ያላረፈች
የተጎሣቆለች ቆሎ ምትሸጥ እናት
ምንገድ ዳር ላይ ውላ ምንገድ የምታድር
..........................ማረፊያ የሌላት
ከዚህ አለፍ ብሎ...
ሽቶ ተርከፍክፈው ድሀ ተፀይፈው
የሚጉአዙ ጥንዶች..
ከነሡ ከፍ ብሎ
አየር ላይ ሚበሩ ጥንብ አንሣ ጭልፊቶች
..
ዱላ የጨበጠ ጋንጃ መቶ አዳሪ
ከቅርብ እርቀት ላይ..
እንዳላየ የሚያልፍ ሠላም አሥከባሪ
..
የተበታተኑ መፈክር የያዙ በጭሥ የታፈኑ
ሥራ አጥ ወጣቶች...
ከነሡ ፊት ለፊት...
ጥይት የታጠቁ እልፍ ወታደሮች
ከዚህ ሁሉ ጀርባ...
ግርማ የሌላቸው የፈረሡ ግንቦች

/ኅይሌ፩/

@getem
@getem
@getem
አዙሪት
❖❖❖❖❖

እጅ ተጠላልፎ በአዙሪት ጨዋታ
ተብሎ አይጠየቅም ማነው የሚረ-ታ
አሸናፊ የለ አልያ ተሸናፊ
አንዱ ከለቀቀ አይኖረም ተራፊ
ሚዛኑን ጠባቂ ለአዙሪቱ ቋሚ
ፍቅር አይደለ ወይ ማገርና አግዳሚ?

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሀገር እንደዚ ናት በሀሳቦች ትብታብ
ስትዞር ምትዳክር ሰርክ እምትጋልብ
ታሪክ ሚዘውራት ትውልድ የሚያዞራት
ዙረቷ እማይቆም ጥበብ እሚያጥላተ

ውድነህ ተሾመ
2011

@getem
@getem
@getem
*አንዴ ባይከፈል*
"""""""""፠""""""'''"''

ደርሶ ዛሬ ጠየኩ የትናቱ 'ያለ
በከፈልኩ ኖሮኝ ጠይቄው ከማለ!
ያለመድኩት ዱቤ ትላንት በሠጠውት
ካቲካላ ፣ አረቄ ቢተወኝ በተውኩት!


@getem
@getem
@getem

@Johny_Debx ገጣሚ
#አዬ_ሙሴ_ግሪክ

አንድ ግሪክ ነበር አሉ ከጠላት በፊት
አራት ኪሎ ሰፈር መጠጥ ምግብ ቤት
ከፍቶ የሚነግድ በጣም የታወቀ
መኳንንቱ ሳይቀር እየተሰረቀ
ጓዳው ተለይቶ ጉዱ እንዳይወጣ
እቤቱ የሚውል ሲበላ ሲጠጣ !

ከእለታት አንድ ቀን በሁዳዴ ቀን
ደንበኛው የሆነ አንድ መኮንን
ከለመዱት ጓዳ ተሰርቀው ገቡና
ሲበሉ ሲጠጡ ሲያወሩ ዋሉና
ሊወጡ ሲነሱ እንዲህ አሉት ሙሴን

"ሙሴ ልብ አድርግ በፃም ቀን መግደፌን
ኀላ እንዳትናገር ለማንም ቢሆን !
ትልቅ ሰው ነኝና ክርስቲያን አማራ
አገር ጉድ ይለኛል ስሜን ብትጠራ !"

ግሪኩም መለሰ " ጌታዬ ምን ቆርጦኝ
እርሶ ብቻ አይደሉም አደራ ያሉኝ !

ደጃዝማች ታፈሰ ባላምበራስ ግርማ
ቀኛዝማች አደራ እነራስ ይማማ
መኳንንቱ ሁሉ በጦም የሚበላ
አደራ ብሎኛል ከበላ በኃላ ፤
ስለዚህ ግዴለም አያስቡ ፍጹም
በኔ ይሁንብዎ ማንም አይሰማውም !"

አለና ሲጨርስ ሰውየው ደንግጠው
እንዲህ አሉ ይባላል ሲወጡ ተናደው

"አዬ ሙሴ ግሪክ ወራዳ ገገት
ምስጢር መያዙ ነው አሁን ባንተ ቤት !"

1951 አ.ም
አዲስ አበባ
የመስከረም ጮራ
#አሰፋ_ገ/ማርያም ተሰማ

@getem
@getem
@getem
#ርእስ_አልባ
(ሀሳቡን እንደተረዳችሁት ርእስ ስጡልኝ 🙏 በፍቅር ጋበዝኳቹ)

በልብ ማህደር ባለው ክቡር ዙፋን
ከመለኮት ፀጋ የተቸረ ፍቅርን
መዋደድ 'ሚሰጠንን አፍልሶ ጥላቻን
በልባችን መንበር አንግሰን ካኖርን

ፍቅር #በልብ #ቃል #እስትንፋስ ዘርቶ
ህያው ያደርገናል በበረከት መልቶ
ግና እስትንፋስ የዘራ
በበረከት የተመላ የአፍቃሪ ልቡ
የ'ራስ ስሜት ብቻ ከሆነ ቀለቡ
ከ'ኔነት ጎጆ ወቶ እኛነት ቀዬ ካልገባ
የፍቅር ትርጉሙ ሆኗል የተዛባ......

እናማ ጃል ስማኝ
ከልብህ አድምጠኝ

የኦሪቱን ክዳን የአዲሱም መሰረት
የመለኮት ባህሪ ቃል የተገለጠበት
የተሸመነበት የጦቢያነት ጥለት
ድርና ማግ አድርጎ ዘላለም ሚያኖር
ትርጉሙ ተዛብቶ በታሪክ እንዳይቀር

ዘሩ ተጥሎ ፍሬን እንድናይ
እኔን እንተውና እኛ እንበል በአንድላይ
ከመለኮት ፀጋ እንድንሆን ተካፋይ
እርሱ እንኳን ሲናገር ፈጣሪ ሀያሉ
እንፍጠር ነው እንጂ ልፍጠር
አልነበረም ቃሉ።
#መኳስ

@getem
@getem
@getem
ስላልሺኝ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ተወኝ አልሺኝ ተውኩሽ
እንዳደገ ህጻን የእናት ጡት ወተት
በግድ እንዳስተዉት
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እርሳኝ አልሽኝ ረሳሁሽ
ከነመፈጠርሽ ማስታውሰው የለም
ባደጋ እንደመጣ የጭንቅላት ህመም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጥላኝ እንኳ ብትይ
ነፍሴን የሚገድል ጠላት እንደመጥላት
ከቃልሽ ላልወጣ ጠላሻለሁ መጥላት
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሚወደኝ ቢኖር ትዛዜን ይፈጽም
በፍቅር መጽሐፍ የፍቅር አምላክ እንዲል
ቃልሽ ትዛዜ ነው ያልሺው ይፈፀማል
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሌላ ፈልግ ብትይ ሌላ ፍቅር ጀመርሁ
አትሆነኝም ላልሺው ምትሆነኝ አገኘሁ
ዞርበል ባልሺኝ ማግስት ሀገር ለቅቄአለሁ
ላይኔ የጠላሁሽ
ስላልሺኝ ነው እንጂ እኔ አፈቅርሻለሁ
ፍቅር ማለት ለኔ የተፈቃሪን ቃል ትዛዙን ማክበር ነው
መጽሐፉ እንደሚለው።
06/02/11

@getem
@getem
@getem
🔥1
#የደርግ ዘመን
#የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ -- ኢትዮጵያ ቅደሚ
በህብረሰባዊነት -- አብቢ ለምልሚ !

ቃል ኪዳን ገብተዋል -- ጀግኖች ልጆችሽ
ወንዞች ተራሮችሽ -- ድንግል መሬትሽ
ለኢትዮጵያ አንድነት -- ለነፃነትሽ
መስዋህት ሊሆኑ -- ለክብር ለዝናሽ !

ተራመጅ ወደፊት -- በጥበብ ጎዳና
ታጠቂ ለስራ -- ላገር ብልፅግና !

የጀግኖች እናት ነሽ -- በልጆችሽ ኩሪ
ጠላቶችሽ ይጥፉ -- ለዘላለም ኑሪ !

መስከረም 1 ቀን 1968 ዓ.ም
አዲስ አበባ

@getem
@getem
@getem
///ፀሎትህን መልስ///

ክምር ገንዘብ ይዞ
በምቾት ደንዝዞ
ከኪሱ ሳያወጣ
አንዲት ዲናር ሳንቲም የገንዘብ ጠብታ
እባክህ አንድዬ ላጡት አንተ ድረስ
ይላል ተንበርክኮ እየተለመነ
ፀሎቱን መመለስ እራሱ እየቻለ


ግጥም:ምህረት

@getem
@getem
@getem
የደርግ ዘመን መዝሙር
#ሰንደቅ አላማ ሲወርድ

ወዛደር ገበሬ ---- ህፃን አዛውንት
መለዮ ለባሹ ---- ተራማጅ ወጣት
ቃልኪዳን አለበት -- የቆየ ከጥንት
ለሰንደቅ አላማው -- ሊሰዋ ሊሞት፤

ለፍትህ ለእኩልነት -- ለሰብአዊ መብት
ለሰላም ለፍቅር -- ለሀገር እድገት
ለኢትዮጵያ ነፃነት -- ለልጆቿ ክብር
ሰንደቅ አላማችን -- ዘላለም ትኑር ፤

መስከረም 1 ቀን 1968 ዓ.ም
#አሰፋ ገ/ማርያም ተሰማ

@getem
@getem
@getem