ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ይፍታ

መላ ያጣ ላጤ የላጤ ደንቆሮ
ውሉ የጠፋበት የመላ ቋጠሮ
ድመቱን አልጋው ላይ በገመድ ጠፍሮ
አይጥ ያሳድዳል ሊገላት አባሮ
ላ'ይጥ ዱላ ይዞ እቃ ከሚመታ
ስራዋን ትስራበት ድመቲቱን ይፍታ ፡፡

ከ የአገጭ ጢሞች መድብል
(በለው ገበየው)

@getem
@getem
@gebriel_19
ሃሎ የበግ አምላክ

ፋሲካ ደረሰ ፣
በግ ሁሉ አለቀሰ ፣
ሕዝቡ ይስለም ብሎ ፣
ለአንድ አላህ ከሰሰ ፡፡

አረፋ ደረሰ ፣
በግ ሁሉ አለቀሰ ፣
ሕዝብ ይጠመቅ ብሎ ፣
ለአንድ እግዜር ከሰሰ ፡፡

እንግዲህ ...
ፋሲካ እያለፈ ፣
አረፋ እየመጣ ፣
በደም ግብር ሰበብ ፣
በግ እሩሁን ካጣ ፣
ሠው እየታረደ ፣
በግ ነጣ እንዲወጣ ፣
ሃሎ የበግ አምላክ ...
የበግ በዓል አምጣ !!


ከ ዒሻራ መድብል
( ኑረዲን ኢሳ )

ማንኛውንም እንዲለቀቅላችሁ ምትፈልጉትን ግጥም ላኩልን!
@gebriel_19

@getem
@getem
ገንዘብ ግን የማነው??

ሁለት ሀሳብ ሆኜ ብዕሬን አነሳው
ጥያቄ ልጠይቅ እየተሰናዳው
ገንዘብ የእግዚአብሔር ወይስ የሴጣን ነው
የሚለው ጥያቄ ውስጤ ተመላልሶ
ሰላም እየነሳኝ ከአይምሮዬ ደርሶ
ብዙ ጊዜ አስቤ መፍትሄ መጣልኝ
መልሱን ላድማጭ ብዬ ይሄን ግጥም ፃፍኩኝ

          ገንዘብ ግን የማነው??
ገንዘብ የሴጣን ነው ብለው እያወሩኝ
ገንዘብ ስጠኝ ብዬ ፈጣሪን ለመንኩኝ
የሴጣን ነው እያሉ ፈጣሪን መለመን ስህተት ሆነብኝ
ግን ቆም ብዬ አሰብኩ እኔም ግራ ገብቶኝ
ገንዘብ ግን የሴጣን እንዴት ሆነ ብዬ አንድ ሰው ጠየኩኝ
   እሱም አንደዚህ አለኝ
ሠርተህ ያመጣኸው የልፋትህ ገንዘብ በላብህ የመጣ
አንተን ተገዢ አርጎ አይምሮህን ወርሶ ካመጣብህ ጣጣ
ለሰው ማሰብ ትተህ ለራስህም ሳትሆን
ጨካኝ ህሊና ቢስ አይምሮ የለሽ ስትሆን
ገንዘብ ሞልቶህ ሣለ ሰላም ካልተሰማህ
የሴጣን ገንዘብ ነው አይጠቅምህም ይቅርብህ
ብሎ መለሰልኝ የጠየኩት ሰው
ያለኝን ሰምቼ ሄድኩ አመስግኜው
ግን ከሄድኩበት መለስ አርጎ ጠራኝ
አንድ ነገር አለ ሳልነግርህ የቀረኝ
አለኝና ጠርቶ ወሬውን ቀጠለ
ገንዘብ የእግዚአብሔር የሚሆንበትም አንድ አጋጣሚ አለ
ሰርተህ ያመጣኸው የልፋትህ ገንዘብ በላብህ የመጣ
አንተን አለቃ አርጎ እሡ ባርያህ ሆኖ ከችግር ካወጣህ
ከራስህም አልፎ ለሰው ማሰብ ስትችል
አይቶ እንዳላየ ሰው ማለፍ ሳትችል
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ ካረከው
እሱን ነገር ለምን የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው
አለኝና ሄደ ምክሩን ጨርሶ
ግራ ያጋባኝን ጥያቄ መልሶ
ከዛም እኔ ብልጡ ያለኝን ሰምቼ
እግዜሩን እንዲ አልኩት እጆቼን ዘርግቼ
ያንተን ገንዘብ ስጠኝ መፍትሔ እንዲሆነኝ
ሰው ልርዳበትና ሰው ይደሰትብኝ::
                                      
                                               ★★★ F8 ★★★

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
Ethiopia: አርቲስት አለማየሁ ታደሰ ስለ ኢትዮጵያዊያን አንድነት እንባ እያነቀዉ ሲናገር 16k
Andafta
አርቲስት #አለማየሁ_ታደሰ ስለ ኢትዮጵያዊያን አንድነት እንባ እያነቀዉ ሲናገር

ግጥም ብቻ
🕥 10:36
💾 1.3 MB

@getem
@getem
@gebriel_19
//ማስተካከያ ፍርድ//

ባለ አንድ ጥፍር ንጉስ ፣ ግፍ እያዘነበ ፣ ሕዝብ ስላስነባ ፣
እግዜር ለንጉሱ ፣ ሲፎክት ይኖር ዘንድ ፣ እዥ እና እከክ ጀባ ፤
ሕዝቡም ለንጉሱ እጅግ ስላዘነ ፣
ፍርድ ሊያስተካክል እንዲህ ሲል በየነ ፦
" ከንቱ ነፍሱ ላትድን ፣ ባንድ ጥፍር ታካ ፣
አሁንም አሁንም ፣ ከንቱ እየነካካ ፣
እጁ መርዝ ሆኖበት ፣ ገላው እንዳይተላ ፣
አንድ ጥፍሩ ትጣል - ከጣቱ ተነቅላ ፡፡"

ከ ዒሻራ መድብል
( ኑረዲን ኢሳ )

@getem
@getem
@gebriel_19
#ድንቄም_ፃድቅ

ክብሩን ጥብያ ጥሎ ፤ በጎሳ ቀረርቶ
ከዘር ይማግጣል ፤ፍፁም ፍቅር ፈርቶ
ማ-መንዘር ሀገር ላይ ፤ ያ ሁሉ ተረስቶ
መ-መንዘር ፅድቅ ሆነ ፤በዝርዝር ተኮርቶ!

ውድነህ ተሾመ
16/06/2011

@getem
@getem
@Gebriel_19
Forwarded from SPACE COMPUTER
Forwarded from SPACE COMPUTER
🔥🔥ደረሰ🔥🔥 👍👍
በጉጉት የተጠበቀው አነጋጋሪ ቴአትር
የባህር ወጥ
አዲስ ቴአትር ለ እይታ የሚበቃበት ቀን መጋቢት 30/2011 ።
ድርሰትና ዝግጅት እሱባለው የኔነህ አልጣህ
በኤር ኦር የቴአትር ፕሮዳክሽን የቀረበ

መጋቢት 30/2011 ከ11:00 ሰአት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል !!!

ዘመን ተሻጋሪ ሀሳቦች በድንቅ የመድረክ ዝግጅት ተከሽነው
ፍቅርንና የሀገር አንድነትን ለማጽናት የሚከፈለውን ሀያል ተጋድሎ የሚያስቃኝ
ድንቅ የመድረክ ቴአትር

የባህር ወጥ
ጊዜ የገለጠው ክስተት
የማለዳ ኮኮቡ የትወናው ፈርጥ ካሳሁን ቦጋለ ድንቅ የትወና አሻራውን ያተመበት ዘመን ተሻጋሪ ቴአትር

ሺዎች ሊያዩት ጓጉተዋል እርስዎስ ?

ግሩም አስፋው(ኩሲ) ፣ አቤኔዜር አለማየሁ፣ ማቲዎስ ሽፈራው (ሉሉ) ፣ አሸናፊ ሀ/ማሪያም፣ኤልሻዳይ ሚፍታህ ፣ ብሩክ ሀብታሙ ተውነውበታል !!!
ኤር ኦር የቴአትር ፕሮዳክሽን

መጋቢት 30 ሰኞ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት
እንዳያመልጥዎ !!!!!

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ኡደት
""""""

ፈጣሪ ሸመነ
አንድ ሁለት እያለ ምድርን አሳመረ
ህይወትን አደለ ሁሉንም ፈጠረ
ነፍስን ከስጋ ጋር በፍቅር አቆራኘ
ለስጋ በምድር ምግብን አናኘ።
(ሰውም ይሄን ሲያገኝ)
ለእውነት መኖር ትቶ ለሆዱ አደረ
ጥጋብን ወደደ ስለ ሰው ችላ አለ
የከሲታዎች ሞት
በአንድ ቦርጭ ውስጥ ሆነ
(እንዲ ነዋ ቅሉ)
የሰው ልጅ ከእንስሳ በሀሳብ ቢልቅም
ሆዳም ሰው ሆድ እንጂ ፍቅርን አያቅም
ደፍ ደፏን ያስባል በሀሳብ አይመጥቅም
እሩቅ.... አያስብም!

*
ፈጣሪ ቀረፀ
ተፈጥሮ ላይ ጀጋኝ ሞትን አሰረፀ
በሞቱት መተኪያ ህይወትን አነፀ
በሞት ነፍስን አዛኝ ባደረጋት አፍታ
ሀዘንን አሳ'ጥቶ ሰጣት ለደስታ።
(ሰውም ይሄን ሲያገኝ)
ደስታው ቅጥ አጣና
ለስሜቱ ኖሮ ይሰፈር ጀመረ በፈጣሪ ቁና
ልኩን መያዝ ትቶ እግዜር አስከፋና
ይከተል ጀመረ የሲኦልን ዳና!

(እንዲ ነዋ ቅሉ)
የተደሰተ ሰው ልቡ ጮቤ ይረግጣል
የረጋችን ሰማይ
እግሩን አንፈራጦ አሻቅቦ ይመታል
በደስታው ሲሰክር ፈጣሪን ይረሳል
ፈጣሪን ሲረሳ
ከኔ በላይ ጌታ እያለ ይፎክራል።

*

ፈጣሪ ጠረበ
የሰውን ባህሪ ሁሉን አነበበ
ለሰው ነፍስ ማደሻ ተክልን ተከለ
በዚም አላበቃም አእዋፍን ፈጠረ
(ፈጣሪ ጠረበ)
የሰውን ባህሪ ሁሉን አነበበ
ትንሽ እንዲፈራ አውሬን አሰፈረ
ትንሽ እንዲጀግን ብልጠትን አደለ።
(ሰውም ይቺን ሲያገኝ)
በኖረው ብልጠት ላይ ጭካኔን ዘራበት
ፍቅርን ሰላም ትቶ ፀብ አበቀለበት
ብልጠቱ በዛና ግፍ ደራረበበት
ሚዛን ተዛባና ፍርድን አጓደላት

(እንዲህ ነዋ ቅሉ)
በግ በጅልነቱ ተገፍቶ እየኖረ
የፍየል ብልጥነት
ከግራ አዋላት ምንም አልጠቀመ
ምላሷም አልበጃት ጩኸት ብቻ ሆነ!

***
ፈጣሪ ጠረበ....አነፀ....ገነባ
የተፈጥሮን ኡደት ከነጋ ከጠባ
አንድ ሁለት ብሎ ፈካ እንደአበባ

(ግን ይቺን ሲያገኙ)
አንዳንድ ያልታደሉ
የፈጣሪ ፍጥረት ተፈጣሪ ሆኑ
በእግዜር ታለፉና በሰው ተፈጠሩ

(እንዲያ ነዋ ቅሉ)

በፈጣሪ ማሳ ሰው ክፉ ማብቀሉ
ረግጦ የገዛን ቆሞ መሸለሙ
ጭካኔ ያለው ሰው በሰው መታበሉ
አረም እና እህል አንድ ላይ መብቀሉ

(እንዲያ ነዋ ቅሉ...እንዲያ ነዋ ቅሉ)

አብርሃም

@getem
@getem
@gebriel_19
የተሠበረ የራቁት ፍቅር

#Johny_Debx
"""""""""፠"""""""""፠"""""""""
ስኖር የወለድኩት ሣልኖር ያልደረስኩት
ሳብ አድርጌ ጎተት መች ወጣው አየሁት
ሳምግ ስመግ ቢለኝ?
.......ኧረ ወደላይ ነው~
.......የራቁት ሩቅ ነው!

መውደድ የት መሀላው በጸሎት ለዋለ፣
በገዜ ዕርምታ ቆይ ልሂድ ና ልምጣ ዕየማለ
ደስታ ተራራ ነው ግን ደረስክ ከስሩ፣
ና ውጣ ይለኛል 'ስደርስ' ለሹሩሩ !

ፍቅር የደገሠው'
ለችግር የዳረው;
ሀሳብ ዕሷን ማየት፡
ረጅም አለንጋ የተረረ መሬት፡፡
ግና?
ግርፊያው መች ተጠላ ተኩሱ ወደታች
ጠመንጃ ወዳጅ.............. ተፈቃሪ ነች !
ታዲያ ~
ወዲያ~

ከዚህ በላይ ፍቅር
ከዚህ በላይ ችግር
ኧረ ዕንዴት ይረሳል ፣ ኧረ የት ይገኛል!
ራቅ ራቅ ስል ጅራፍ ይጠራኛል'
የራቁት ዕሩቅ ነው አጥብቀኝ ይለኛል!

@getem
@getem
@getem
****መንገደኛ******

በሀሳብ አገልግል ምኞቱን ሠንቆ
በተስፋ ጎዳና ተራውን ጠብቆ
የአለም መንገደኛ
አቀበት ይወጣል፤ቁልቁሉን ይወርዳል
ጀንበሯ ሳትጠልቅ ካሠበው ለመድረስ
ከህይወት ማዕድ ላይ ድርሻው ሊቋደስ
ሁሉም ሰው ይሄዳል ይጓዛል ይፈልሳል ........
ግና ከዚ ሁሉ የአለም መንገደኛ
ተግቶም የሚጓዘው ሌት ተቀን ሳይተኛ
ቀርፋፋውም ቢሆን ሌት ተቀን ሚተኛ
ከዚ ሁሉ ተጓዥ ደራሽ አንድም የለም
ከመጣበት አፈር ተመላሽ ነው ሁሉም።።።።፨
Zola

@getem
@getem
@gebriel_19
አተላው ይደፋ !

የዘረኝነት ጉሽ ፣
. . . . . . ያሰከረው ትውልድ ፤
አንጎሉ እንደዞረ ፤
አንጀቱ እንዳረረ ፤
. . . . . . ቀኑን ከሚገፋ ፤
ጋኑን አለቅልቆ ፣ አተላውን ይድፋ ፡፡

ዶ / ር በድሉ ዋቅጅራ
@getem
@getem
@Yeaseratfere
" ከስዕሉ ጀርባ "
( በአምባዬ ጌታነህ )
ለመክሊቱ መቅድም አይኑ እያማተረ፣
አንዴ መምህሩን አንዴ ተማሪውን እየቀያየረ ፣
በምትሀት እጆቹ ቁጭ አርጎ እያኖረ፣
ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ፦
ስዕል ብቻ ሚስል አንድ ልጅ ነበረ።
ከእለታት ባንድ ቀን መምህሩ ሲዞር "ደብተርህን "ሲለው፤
ደብተሩን አሳየው።
የስዕል ደብተሩን የሰጠኝ ነው መስሎት፣
መምህሩ ደንግጦ
"ሌላ ደብተር" አለው፣
ሌላ ደብተር ሰጠው፣
ይህንም ቢገልጠው፣
ስዕል ብቻ ሆኖ እሱ ያፃፈውን ኖት ማየት ናፈቀው።
....
ወደ በሩ በኩል እጁን እየጠቆመ "ውጣ ከዚህ "አለው።
ልጁን አስወጥቶ ደብተሩ ላይ ባሉ ስዕል አፈጠጠ፤

<ስዕል ፩>

ሀገር የሚረከብ ሀገርን የሚቀርፅ
ትውልድን ለማነፅ
ደፋ ቀና የሚል ከጠመኔው ጋራ የተመሳሰለ፣
ኑሮ ያንገላታው ትጉህ መምህር አለ።

<ስዕል፪>

የመምህሩን መኖር
ከመጤፍ ሳይቆጥር
ስልክ ሚጎረጉር
ፀጉሩን በጣቶቹ እያፍተለተለ፣
አልፎ አልፎ መምህሩን ቀና ብሎ እያየ ከሱ ጋራ መስሎ ከእሱ ጋ የሌለ፣
የአርሴናልን ማሊያ የለበሰ ወጣት አንድ ተማሪ አለ።

<ስዕል ፫>

በተደፋ ኩሏ የተንሸዋረረች፣
ያለ እረፍት ከንፈሯን እያሸራመጠች፣
ተገላልጣ ለብሳ ሳትታይ የቀረች፣
በስተመጨረሻ ተስፋ የቆረጠች፣
የምትቁነጠነጥ አንዲት ሴት ልጅ አለች።

<ስዕል፬>

መምህሩ ሚለውን ከአፉ እየነጠቀ እየተከተለ፣
በደብተሩ ሚያስቀር ትጉህ ተማሪ አለ።

<ስዕል ፭>

የመምህሩን መውጫ ስአት የናፈቁ፣
ቁራጭ ወረቀት ላይ በተፃፃፏቸው ቃላት የሚስቁ፤
በወንበሩ አሻግረው እግርና እግራቸውን እያነባበሩ፣
ፍቅር ሚጀምሩ፣
በብርድ የሞቃቸው እሳት ልጅ ነበሩ።

<ስዕል ፮>

በዛ በኩል ደግሞ፣
ሁሉንም ተማሪ እያየ በአርምሞ፣
በድርጊቶቻቸው ከልቡ ተገርሞ፣
" ልሳላቸው ብሎ እየሳለ ሳለ "
ድንገት መምህሩ አይቶት ወደ እሱ መጣና፣
" ስዕል ከምትስል ለምን አትማርም
በኋላ ሳትማር ለወላጅ ለሀገር ከምትሆን ሸክም?
ብትከታተለኝ ሳይሻል አይቀርም፣"
የሚል መምህርና የተማሪው ምስል
በስዕሉ ይታያል።

ከዛም መምህሩ
ይህን ሁሉ ስዕል ተመለከተና፣
"ያለ መክሊቱ ነው የሚማረው?" ብሎ ከልቡ አዘነና፣
የስዕል ስድስትን- መምህር ተግባር ወስዶ፣
" ና ግባ" አለው ልጁን የጥል ግምቡን ንዶ።
ይህን ሁሉ ምናብ በስዕል መስሎ በስንኝ ሚሰድር፣
ከስዕሉ ጀርባ ሳይ ገጣሚ ነበር።

09/06/2011ለሊት 10:24

@getem
@getem
@gebriel_19
ነገ ቅዳሜ 6 ሰአት በመዘጋጃ ቴያትር ቤት "ሰው መሆን "የፊልምና የቴያትር ብሮዳክሽን የሚያቀርበውን የኪነ-ጥበብ ዝግጂት ትታደሙ ዘንድ በአክብሮት ጠርተነወታል

!!!በእለቱ የሚቀርብት ስራወች!!! ---------------------------------------
ቴያትር በሰው መሆን
ድስኩር በመጋቢ ሀድስ እሽት አለማየሁ
ግጥም በገጣሚ በሀብታሙ ያለው
ወግ በተዋናይና ደራሲ ፍቃዱ ከበደ
ወግ በሰው መሆን በረድኤት ተስፋየ
እድሁም በተጋባዥ እንግዳ ደራሲና ገጣሚ አያልነህ ሙላት ሌሎችም ስራወች ተውበን ለመቅረብ ዝግጂታችንን ጨርሰናል። እናተስ???

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
አባት´ማ

እነሱ ካንተ እኩል ወንድ መባላቸው
እነሱ ካንተ እኩል ስም መሰጠታቸው
ለኔ ከዚያም በላይ ለእኔ ከአባት በላይ
አሁንም ላውራልህ ወጥቼ አደባባይ
ባይበላም ባይጠጣም ባይገባ ከቤት
ከደጃፍ ቁጭ ሲል ደስ ይላል አባት
አሁን ነው የገባኝ እንዲያ የሚሉት ተረት
እረ ለመሆኑ .. ለእነሱ ወንድ ብሎ ስም ያወጣላቸው
ከአንተ ከአባቴ እኩል ያረጋቸው

እናም የኔ ቆንጆ እናማ የእኔ ክብር
ሞተሀል ተብሎ ስገኝ በአንተ ቀብር
አላመንኩም ነበር
ግን ....ግን....
አሳመነኝ ጊዜ አሳመነኝ አመት
ካንተ ተለይቼ ብቻዬን ኖርኩበት
ካንተ መለየቱ አንድንም ትልቅ ቅዠት
አንድም ትልቅ እውነት
አባት ማለት ስሙ ለአንተ ቢያንስብም
የወንድነት ልኩ አባት ስለሆነ
አባዬ ስላልኩህ አንተም አልከፋህም

ላላገኝህ ሄደህ ዘመናት አለፉ
ቀናትና ሰከንድ በፍጥነት ከነ ፉ
ከህልሜ ባንኜ ህልም ባደረኩት
ቅዠቴንም ትቼ እውነት ባስመሰልኩት
ያንተን አለመኖር መኖር ከተባለ
እንደው በለወጥኩት

እኔ ግን ያመኛል
ወንዶች የተባሉት ካንተ እኩል ሲጠሩ
በለምለም ሜዳ ላይ ገለባ እየዘሩ
እናማ
ወልዶ ማሳደጉ ወንድ ሆኖ መፈጠር
የአባን አባትነት አያክልም ነበር

እናም የኔ አባት እናም የኔ ቀለም
በስጋ ባትኖር ብትርቅ ከዚህ አለም
ከትዝታችን ላይ የረ ሳሁት የለም

አባት ማለት ለእኔ ስኖር በዘመኔ
፻(100)አለቃው ይትቤ
የአንገት ማህተቤ
የ የ ቀን ክታቤ
ለዛሬው ማንነት መ ሰረት የሰጠኝ
ለእኔ እሱ ነው አባት በዚህ ምድር ስገኝ።

(ነፃነት ይትባረክ)

@getem
@getem
@gebriel_19
​አትላስ የግሪኩ፣ አትላስ መለኮቱ፣ ምድርን ስላዘለ
ሲዘከር ጉብዝናው፣ ሲወደስ መጠሪየው፣ ፅኑ እየተባለ።
የኔ ስስ ትከሻ ምን ተብሎ ይጠራ
ተሸክሞ ሚኖር ምድርን፣ ከአትላስ ጋራ ?

(በእውቀቱ ሰዩም )

@getem
@getem
@paappii
ሃሎ የበግ አምላክ

ፋሲካ ደረሰ ፣
በግ ሁሉ አለቀሰ ፣
ሕዝቡ ይስለም ብሎ ፣
ለአንድ አላህ ከሰሰ ፡፡

አረፋ ደረሰ ፣
በግ ሁሉ አለቀሰ ፣
ሕዝብ ይጠመቅ ብሎ ፣
ለአንድ እግዜር ከሰሰ ፡፡

እንግዲህ ...
ፋሲካ እያለፈ ፣
አረፋ እየመጣ ፣
በደም ግብር ሰበብ ፣
በግ እሩሁን ካጣ ፣
ሠው እየታረደ ፣
በግ ነጣ እንዲወጣ ፣
ሃሎ የበግ አምላክ ...
የበግ በዓል አምጣ !!


ከ ዒሻራ መድብል
( ኑረዲን ኢሳ )

@getem
@getem
🔥1
አትሄድም ብዬ

አትኤድም ብዬ ፣
ጎጆዬን ላሰፋ ፤
ግርግዳ ስገፋ ፤
ጥሪት ላጠራቅም ፤
ጥሬ ስቆረጥም ፤

አትሄድም ብዬ ፣
የብቻ ጎጆዬን ሰው ልመጂ ስላት ፤
ቡናው ሳያከትም ፤
ካፊያው ሳያባራ ፤
... ከአጠገቤ አጣኃት ፤

በል ተከተል ልቤ ፦
ማግኘት ነበር ጣሩ ፣ ማጣት መች ይደንቃል ፤
እንኳን በጅ ያልያዙት ፣ ጥሬ ካፍ ይወድቃል ፡፡

የወይራ ስር ፀሎት
( ዶ / ር በድሉ ዋቅጅራ )

@getem
@getem
@getem