ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አዬ_ሙሴ_ግሪክ

አንድ ግሪክ ነበር አሉ ከጠላት በፊት
አራት ኪሎ ሰፈር መጠጥ ምግብ ቤት
ከፍቶ የሚነግድ በጣም የታወቀ
መኳንንቱ ሳይቀር እየተሰረቀ
ጓዳው ተለይቶ ጉዱ እንዳይወጣ
እቤቱ የሚውል ሲበላ ሲጠጣ !

ከእለታት አንድ ቀን በሁዳዴ ቀን
ደንበኛው የሆነ አንድ መኮንን
ከለመዱት ጓዳ ተሰርቀው ገቡና
ሲበሉ ሲጠጡ ሲያወሩ ዋሉና
ሊወጡ ሲነሱ እንዲህ አሉት ሙሴን

"ሙሴ ልብ አድርግ በፃም ቀን መግደፌን
ኀላ እንዳትናገር ለማንም ቢሆን !
ትልቅ ሰው ነኝና ክርስቲያን አማራ
አገር ጉድ ይለኛል ስሜን ብትጠራ !"

ግሪኩም መለሰ " ጌታዬ ምን ቆርጦኝ
እርሶ ብቻ አይደሉም አደራ ያሉኝ !

ደጃዝማች ታፈሰ ባላምበራስ ግርማ
ቀኛዝማች አደራ እነራስ ይማማ
መኳንንቱ ሁሉ በጦም የሚበላ
አደራ ብሎኛል ከበላ በኃላ ፤
ስለዚህ ግዴለም አያስቡ ፍጹም
በኔ ይሁንብዎ ማንም አይሰማውም !"

አለና ሲጨርስ ሰውየው ደንግጠው
እንዲህ አሉ ይባላል ሲወጡ ተናደው

"አዬ ሙሴ ግሪክ ወራዳ ገገት
ምስጢር መያዙ ነው አሁን ባንተ ቤት !"

1951 አ.ም
አዲስ አበባ
የመስከረም ጮራ
#አሰፋ_ገ/ማርያም ተሰማ

@getem
@getem
@getem
የደርግ ዘመን መዝሙር
#ሰንደቅ አላማ ሲወርድ

ወዛደር ገበሬ ---- ህፃን አዛውንት
መለዮ ለባሹ ---- ተራማጅ ወጣት
ቃልኪዳን አለበት -- የቆየ ከጥንት
ለሰንደቅ አላማው -- ሊሰዋ ሊሞት፤

ለፍትህ ለእኩልነት -- ለሰብአዊ መብት
ለሰላም ለፍቅር -- ለሀገር እድገት
ለኢትዮጵያ ነፃነት -- ለልጆቿ ክብር
ሰንደቅ አላማችን -- ዘላለም ትኑር ፤

መስከረም 1 ቀን 1968 ዓ.ም
#አሰፋ /ማርያም ተሰማ

@getem
@getem
@getem