ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ጥሩ ሰው መርጫ፣ ጓደኛ እሚሆነኝ
ፈልጌ ለማግኛት ፣ በምርመራ ላይ ነኝ።

@getem
@getem
@Gebriel_19
"ነይ እንበስብስ"
.
# _ዳዊት_ንጉሡ
.
ይኸው ደሞ መጣሁ!
.
የዝናም ውስጥ ተጓዥ
መሸሻ የሌለው፥ይጠጋበት ስፍራ
ይራመዳል እንጂ
ጸሐያ እስክት 'ሠርቅ'፥ወጀቡ እስኪያባራ
ኃላ አያፈገፍግም
መጨቅየትን አይሸሽ!..መነከር አይፈራ!
.
ለሙሾ ስጠበቅ
አመስጋኝ ምላሴ፥ቅኔ 'እየተቀኜ'
ይኸው ደሞ መጣሁ!
ከጽልመት ብተዪኝ፥የሌሊት ወፍ ሆኜ
.
ይኸው ደሞ ፈራሁ
ዘር ከአፈር ሲጥሉት፥'ፈርቶ' እንደሚነቃ
በመገፋቴ ይልቅ
ከትናንቱ ይባስ፥ልወድሽ ነው በቃ!
.
ዘራፍ!
.
እስቲ ደሞ ግፊኝ
ልበስብስ..ልዘፈቅ...ልብሽ እስኪቀና
ወድቄ ልነሳ
ተዋግቶ ነው እንጂ
ሸሽቶ አይሞትም ጀግና
.
ዘራፍ..!
.
ተመስገን ነው እኛስ!
የተገኘንበት ላይነሳን አፈር
በሟች ቆሞ መሄድ
ገዳይ ነው 'ሚሸበር
.
ከጭቃ መብቀልን
ሞቶ መነሳትን፥ከፍጡር ተውሼ
ከጣልሺኝ ቦታ ላይ
ከጭላንጭል ብርሃን
ከአፈሩ ርጥበት፥'ፈራሁኝ' በስብሼ
.
ይመስገን ስብራት!
.
ካሰበው እስኪደርስ
ያልተንገዳገደ..ማነው ያልወደቀ?..
በመዶሻም አይደል
በመመታት አይደል፥ምስማር የጠበቀ?
.
ይመስገን አምላክሽ!
.
አፈር ያልነፈገኝ
የተገፋሁ እኔን፥ከጭንጫ ያልጣለ
ከውድቀትም ውድቀት
ከሞትም ሞት አለ
.
ይመስገን!
ይመስገን...ይመስገነው እጅሽ!
ይኸው ደሞ ፈራሁ፥ይመስገነው ጭቃ
ደግሞ እነሳለሁ
ደግሞ እመጣለሁ፥ተስፋዬን ጥበቃ
.
መምጣቴ አይግረምሽ!
ያዝላል መንገዱ፥ካልተደጋገፉ
በብቻነት ጉዞ፥ስንዝር ላትራመጅ
እግር ማድከም ትርፉ
.
ነይልኝ አልልም!
ስሜቴን ተረድተሽ፥ልብሽን ሳታውቂ
መጎዳቴን አይተሽ
ፍቅርሽን መጽውተሽ፥በሃዘንሽ ልጸድቂ
ነይልኝ አልልም!
በአማራጭ እጦት፥ምርጫሽን ልትወጂ
መሰንበቻ ልሆን
ይሻል የመጣ 'ለት፥ጥለሺኝ ልትሄጂ
.
(ይሄዱታል እንጂ
ቆመው ቢጠብቁት..አይጓዝም መንገድ
በእንፉቅቅ ጉዞ ነው
ወድቆ በመነሳት...መሄድ የሚለመድ)
.
.
ነይልኝ በህማም
በጌቴ ሰማኔ.....ነይ በጎልጎታ
ኩራትሽን ሰብረሽ
መስቀሌን ተጋርተሽ.....ወድቀሽ ከከፍታ

@getem
@getem
@paappii
👍2
አፋልጉኝ
።።።።።።
#AbaynehTegegne
ኮፍያዬ ከላይ፣
………………ከታች ከረቫቴ፣
ሱሪና ጫማዬ…
………………ሸሚዝና ኮቴ፣
ቦታቸውን ይዘው፣
………………ደምቆልኝ ውበቴ፣
ሰው የመሆኛዬ፣
………………ጠፋ ጭንቅላቴ።

@getem
@getem
@gebriel_19
///ሰማይን///

ሰው አፍቅሬ ሰው ሲከዳኝ
ንፋስ ስከተል ሲሰወርብኝ
የኔ ያልኩት ተራራ የወደድኩት ደን
ሲሰጥ ለቆራጭ የሌላ ሲሆን
ስወድ
ስካድ
ስወድ
ስካድ
ስወድ
ስካድ
የሞትኩለት ገድሎኝ ሲሄድ
ሁሉም ከፍቶ ሁሉም ሲክድ
መካድን ካድኩና አንድ ዘዴ ዘየድኩ
ትቶኝ ማይሸሸውን ሰማይን አፈቀርኩ።

እስጢፋኖስ ተስፋየ
2011 woldia university

@getem
@getem
@gebriel_19
ይቅር በል (ዳኒ ከአርባምንጭ)
--------------

ከቶ እንዳትመጻደቅ!!
ባንተ ሲሆን ድንገት, አንተ ስትጠየቅ
ሊከብድ እንደሚችል ቀድሞዉኑ ጠብቅ
ከከበደህ ደግሞ ምትለዉን አታዉቅ
ስለዚህ ተጠንቀቅ
ማለት ያለብህን አስቀድመህ እወቅ
.
.
.
ወጥነኸዉ ሳይሆን
ሳታስበዉ ጭራሽ
ወይ ተጠያቂ ልትሆን
ወይ ይቅርታህን አድራሽ
ባንዱ ትገኛለህ
ከሆንክ ስጋ ለባሽ!!!
.
.
.
ይቅርባዩ መምህር
እራሱ ሲያስተምር
ሰባት ጊዜ ሳይሆን ሰባሰባቴ እንድንምር
አስቦ ይሆናል እኛ #እንድንማር
.
.
.
ምንም ሆኖ ቢሆን ምንም እንዳልሆነ
ረስቶት ይቅር ብሎ ደግሞ ካልኮነነ
በቃ አዉቆበታል እሱ ነዉ ይቅር-ባይ
አምላክ የሚምረዉ ኃጢአቱ ሚሰረይ
------------------------------

Jul. 6, 2013...

@getem
@getem
@gebriel_19
🎉1
///የማይቻል አንድ ነገር///

እዉነት - ቤት ስትሰራ
ዉሸት - ላግዝ ካለች፣
ምስማር ካቀበለች፣
ቤቱም አልተሰራ
እዉነትም አልኖረች።

#ጌትነት_እንየው

@getem
@getem
@gebriel_19
🇪🇹 ወገን ለወገን የክተት ጥሪ 🇪🇹
📯ዓዋጅ❗️ 📯ዓዋጅ❗️ 📯ዓዋጅ❗️

በጉጉት ስንጠብቀው የነበረ ነውና ሁላችሁም #SHARE በማድረግ ለወገን ጥሪ የበኩላችሁን ተወጡ።

ይሄ የክተት ዓዋጅ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ከመገንባት በላይ ነው ። እኔ መቼም በጓደኞቼ አላፍርም። በጭራሽ።

ኢትዮጵያን እወዳለሁና ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትል ኢትዮጵያዊ የሆንክ በሙሉ። ከወደ አዲስ አበባ የምሥራች የሆነ ዜና መጥቷልና #ሀሀሀ ብለህ ስማ ተብለሃል። በደቡብ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ ረሃብ ለሚሰቃዩት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እንደርስላቸው ዘንድ በጉዞ ዓደዋዎቹ #ያሬድ_ሹመቴና በጓደኛው #መሐመድ_ካሳ አማካኝነት የቁሳቁስና የእህል እርዳታ ለተጎጂዎቹ ለማድረስ ተወስኗል እና ተዘጋጁ ተብላችኋል።

ካለሁበት ከራየን ወንዝ ዳር ሆኜ በዛሬው ዕለት ከወንድሜ ያሬድ ሹመቴ ጋር በእርዳታ አሰባሰቡና አሰጣጡ ላይ በሰፊው ተነጋግረናል። ከያሬዶና ከመሐመድ ጋር በሊቢያ ለታረዱት ክርስቲያኖች እርዳታ በማሰባሰብ ተጎጂዎችን በማጽናናት የቆየ ልምድም አለን። እናም ወገን ከእነ ያሬዶ ጋር የተነጋገርንበትንም ጉዳይ ለእኔ የፌስ ቡክ ጓደኞቼ ለሆናችሁ ለእናንተ እነግር ዘንድም ከወንድሜ መሐመድ ጋርም ወስነናል። ዝግጁ ናችሁ?

ወደህ ነው ዝግጁ የምትሆነው። በግድህ ነው እንጂ። አሁን ሁሉም ሰው ባለበት ይዘጋጅ። እርዳታው የሚሰበሰበው ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 21 በመሐል አዲስ አበባ በሚገኝ ሥፍራ ነው። ቦታው አሁን #የማይገለጸው ሰዉ ከነገ ጀምሮ እርዳታውን ይዞ እንዳይመጣ ነው። እርዳታው ከሚጠበቀው በላይ ከሆነ ደግሞም ይሆናል ለሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ህይወት ማቆያ ይሆናል ማለት ነው። አስቸኳይ እርዳታ ታላቅ ዘመቻ። ተዘጋጁ።

መንግሥት መኪና በማቅረብ፣ የእርዳታ መሰብሰቢያውን ቦታ በማዘጋጀት ፣ የተሰበሰበውንም ዕርዳታ አጅቦ ተጎጂዎቹ ያሉበት ቦታ ድረስ ለማድረስ ፈቃደኝነቱን ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱንም አሳውቋል። ወዶ ነው።

አሁን ከእናንተ ገንዘብ አይፈለግም። በገንዘብ የሚታማም፣ የሚነካካም አይኖርም። የባንክ አካውንትም አይከፈትም። የሚፈለገው ዕቃ ብቻ ነው። ምግቦች፣ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ አልባሳት ከእናንተ ይጠበቃል።

🥞የማይበላሹ_ምግቦች
•ስንዴ
•ምስር
•ፓስታ
•መኮረኒ
•ሩዝ
•ፉርኖ ዱቄት
•ዘይት
•ሴሪፋም /ፋፋ/
•ብስኩት /ጋቤጣ/

🗑የንጽህና_ቁሳቁሶች
•ሳሙና
•ኦሞ
•ሳኒታይዘር
•የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

👖አልባሳት
•ብርድ ልብስ
•ነጠላ ጫማ (ብቻ)
•የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን) አዘጋጁ ተብላችኋል።

አስተባባሪዎቹ የጊዞ ዓደዋ መስራቾቹ ቅድሚያ ለሰብዓዊት ቡድን ጊዜያዊ አስተባባሪዎችና የቡድኑ ተወካዮች የሆኑት ያሬድ ሹመቴና መሐመድ ካሳ።

⚠️ማስታወሻ ⚠️

📍 የእርዳታ መሰብሰቢያውን ቦታ ከመጋቢት 16 ሁለት ቀን በፊት መጋቢት 14 በይፋ እናሳውቃለን። እስከዚያው ድረስ ግን ሁላችንም በዕድር፣ በመሥሪያ ቤት፣ በቤተሰብ፣ በመኅበር፣ በየሠፈራችሁ እያሰባሰባችሁ። በማዳበሪያ፣ በማዳበሪያ እየከተታችሁ ጠብቁ። በውጭ የምትኖሩም ኢትዮጵያውያን በቤተሰብ በኩል ገንዘብ እያስላካችሁ የፈለጋችሁትን ዕቃ እየገዛችሁ አዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ከእኛ በላይ ለእኛ የሚደርስልን የለም።

📍በረሃብ ለተጠቁት ለጌዲኦ ህዝብ የምንደርስበት ዕድል ተዘጋጅቷልና ወገኔ በያለህበት ተዘጋጅተህ ጠብቅ። ተመስገን አምላኬ ሆይ ይህን የምሥራች ያሰማኸኝ አምላክ ክበር ተመስገንልኝ።

መጋቢት 6/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።

#ምንጭ:- Zemedkun Bekele Facebook Page

📍 ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ፁፉን እንዳነበባችሁት ነው፡፡ ወገኖቻችን እጅግ ያሳዝናሉ፡፡ አብዛኞቻችን ምናልባት የምንበላው ፣ የምንለብሰው አላጣን ይሆናል፤ ነገር ግን እዚህ እኛ ባይሞላልን እንኳን ሳይጎልብን ውለን እናድራለን፡፡ በሌላ በኩል ግን የገዛ እህት ወንድሞቻችን በዚህ ዘመን በእራብ እያለቁ ነው፡፡ ህፃናት መቦረቅ ቀርቶ አፋቸውን መክፈት እያቃታቸው ነው፡፡ አረጋዊያን በርሀብ ደርቀው እየሞቱ ነው፡፡

📍እናም እላችኀለው ቢያንስ ቢያንስ የአንድ ቀን ሻይ ፣ ካርድ ፣ ቢራ ፣ ጫት ይቅርብንና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡ የግድ ማዳበሪያ ሙሉ አዋጡ አይደለም። ኤኔ 1 ኪሎ ፍርኖ ዱቄት ባዋጣ አንተ አንድ እሽግ ፓስታ ብታመጣ አንቺ ደሞ አንድ ኪሎ ምስር ብታመጪ ሁለት ወይም ሶስት ሰውን ለአነድ ቀን በህይወት ማቆየት ይቻላል፡፡ ስንበዛ ደሞ አስቡት፡፡ ስለዚህ ትንሽ ነው ብላችሁ ሳትጨናነቁ ከ10 ብር ሳሙና ጀምራችሁ እናዋጣ፡፡

ከጎናችን የሆናቹ ኢትዮጵያኖች

🙏ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ ይበቃል🙏
እኔ ጠላሻለሁ
______
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
እኔ ጠላሻለሁ፣
እንደ ጫማ ሽታ
ልክ እንደ በሽታ
ጌታ በባሪያው ላይ እንደ ሚበረታ
እኔ ጠላሻለሁ፣
እንደ ረጅም መንገድ
ላብታም እንደ መስገድ
ከጠጡ በሗላ እንደ መንገዳገድ
እኔ ጠላሻለሁ፣
ገንዘብ እንደ ማጣት
ዳገት እንደ መውጣት
ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት
እኔ ጠላሻለሁ፣
ልክ እንደ መልከስከስ
እምነት እንደ ማርከስ
ማስቲካ እያኘኩ ምላስ እንደ መንከስ
እኔ ጠላሻለሁ...(ወዘተ)...
አሁን ግኔ ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል
ጠላሁሽ ያበዛው ወድጄሽ ነው መሰል!

@getem
@getem
@paappii
👍1
ፈላጊ_ነፍስ

# አሌክስ_ይህ
.
ከግዙፍ ዋርካ ላይ
ነፋስ እንደጣላት ~ ትንሽዬ ቅጠል
ይህ ነው ችግር ማለት
በሰዎች ተከቦ ~ ከሰዎች መነጠል
.
በዚህ በዘመኔ ...
ዝቅ በሚልበት ~ ዝምታ ሚዛኑ
በሚገመትበት ~ "መፅሃፍ በሽፋኑ ..."
.
ከዳንኪረኞች ጋር
መደለቅ እየቻልሽ
እስኪሰማሽ ድረስ ~ የድምፅሽ ማሚቶ
ተክዘሻል ኣሉ
ታስቢያለሽ ኣሉ
የዝምታ ባህር ~ ነፍስሽ ላይ ተኝቶ
...
ታስቢያለሽ ኣሉ !
.
ወዲህ ደግሞ ...
ርሃብሽን ላይቆርጠው ~ የማዕድሽ ዕንጀራ
በሚቀዱልሽ ወይን ~ ጥምሽ ላያባራ
"ምን ጎደለ" እያሉ ~ ሰዎች ያደክሙሻል
ያጣውን የሚያውቀው
ልብሽ ሌላ ይሻል።
.
ሌላ !


@getem
@getem
@paappii
👍1
ሰው መጣ.....ሰው ሄደ


ያይኔ የልቤ ጉጥ የዘላለም ፍቅሬ
ሰው ያየናል እዚህ ፈርቻለሁ ዛሬ
እንዲህ ተሸጉጬ በአንተ ክንድ ላይ
አባዬ ያየኝ እንደሁ አይኖርም ገላጋይ

ብዬ እያካፈልኩት ጭንቀቴን ከሆዴ
ጥላ ባየሁ ቁጥር ከእቅፉ እወጣለሁ
አወይ ልጅነቴ

ሰው መጣ ሰው ሄደ
ምንም ሳናወራ በመጨነቅ ብቻ
አንዴ እጁን ሲሰቅል አንዴ እጁን ሲያወርድ
ሰአቴ ደረሰ የመሰናበቻ
ሳልጠግበው ሳይጠግበኝ ናፍቆቴ ሳይወጣ
ሌላ የቀን ቀጠሮ ላንድ አይነት ቆይታ፡፡

ያኔ በልጅነት ባፍላነት እድሜያችን
ሰው መጣ ሰው ሄደ ነበር ስጋታችን

አመታት አለፉ ጊዜውም ነጎደ
በሰው መጣ ጭንቀት ሀሳብ ተወገደ
በትዳር ትስስር ነፃነት ታወጀ

ነገር ግን

የሰው መጣ ጭንቀት ቆይቶ ቆይቶ...
ጊዜውን ጠብቆ በር ላይ አድብቶ
እንደገና መጣ በራችን አንኳክቶ

ዐይኖችህ ከዐይኖቼ እንዳልተራራቡ
እንዳልተቃቀፍን ጠብቀን ሲዞሩ
መተቃቀፍ ጀመርን ሰው ሲኖር ከበሩ፡፡


ንፁህ ግርማ

@getem
@getem
ንጉስ ይከሰስ(ልዑል ሀይሌ)

ነገሩ ነው እንጂ...
ንጉስ ይከሰሳል
በችሎቱ ፍርጃ
ወንበር ይወረሳል
በውርሻው ክፍፍል
እግሩ ባይሰበር
ለከሳሹ ካሳስ
ወንበር ደግ ነበር
..
.
ነገሩ ነው እንጂ...
ሰማይ ይታረሳል
በገበሬ ዕንባ
በበሬ ልመና
ፈጣሪ ይደርሳል.
.
የታረሰው ሰማይ
ጥሩ ፍሬ አፍርቶ
በዓለም ህዝብ ላይ
ሰላም ፍቅርን ዘርቶ
ሁሉን ሆኖ እንድናይ
ንጉሱ ይከሰስ
ሰማዩም ይታረስ
ለውርስ ከመጋጨት
ተስማምተን እንንገስ
.
ሰላም ፍቅር ጤና
ካሳ ይከፈለን
ለዓለሙ ገዢ
ዛሬም እንጮሃለን
.
ሰላም!
ፍቅር!!


@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
መምህር ወምስክር
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በረዶው ቀለጠ . . .!
ምድር ሰውነት ላይ
ነፍስ አቀጠቀጠ፤
ጥውልግ ገላ ሁሉ
አምሮ ተገለጠ።
-
አበባን አየሽ ወይ?
ሕይወትን አየሽ ወይ?!
(ያበበ አበባና ሕይወት ምስስሉ፣
ከረገፉ ወዲያ እንደአዲስ መብቀሉ፤
መፍካትና መክሰም፥መክሰምና መፍካት
የፍጥረት አመሉ።)
-
ይሰማሻል ወይ ድምፅ . . .?
ይሰማሻል ወይ ድምፅ?!
ከሩ . . .ቅ የሚመጣ
የወንዝ ዜማ ወረብ፣
ግኡዝ አካል ያልነው
'ዮም ፍሥሓ ኮነ'
(ቀኑ ደስታ ሆነ)እያለ ሲደረብ።
ልብ ብለሽዋል ወይ . . .?
ልብ ብለሻል ወይ?!
ከመፀው ወፍ ዘሮች
ወርዶ ሲ-ን-ቆ-ረ-ቆ-ር
የቀን ደስታ ልሳን፣
ጥዩፍ ትላንትናን . . .
ባዲስ ቀን ቀይሮ
ነበርን ሲያስረሳን።
ልብ ብለሽዋል ወይ??
-
አስተውይ እንግዲህ . . .
አጣጥሚ በደንብ
የዘመንን ድግስ፥የወቅቶችን ዝክር፣
ከሰው ልጆች ይልቅ
መምህር ይሆናል . . .!
የተፈጥሮ ምክር፥ለፍቅርም ምስክር።

@getem
@getem
@paappii

በቃሉ ሙሉ ይማነው
Audio
ድንቅ ስብስብ
አባካችሁ አበርቱል🙏🙏

ዜማ አራራይ የሙዚቃ ቡድን
ድንቅ ሙዚቃ በ ያሬድ ጥበቡ
ዘፋኝ ማስተዋል እያዩ
@zemararay
@zemararay
@zemararay
//አንዳንዴ //

ሲከፋኝ:~
ድንገት አስቀይሟት ወይም እሷ አጥፍታ
የሞቀውን ፍቅር የሳቁን ቤት ትታ
አሳየኝ አንድዬ ከባሏ ተፋታ

እያልኩኝ ልፀልይ ድንገት አስብና
ሀዘን ያጠላበት መልክሽን አይና
ተወው በቃ አምላኬ ምልጃዬን መልሰው
የኔን ልብ ትተህ የሷን እንባ አብሰው
እያለኩ ፀሎቴን ቀለብሰዋለው

ምክንያቱም ያኔ
አብረን በሰፋነው በለበስነው ሸማ
አፍሽ ከአፌ ላይ ጨዋታ እየቀማ
ያሳለፍነው ጊዜ ቀጭኑ ትውስታ
ካንቺ ባይነጥለኝ ሆኖብኝ ትዝታ
ያለጊዜ ወድጄ በጊዜ ባጣሽም
ክፉ አርገሻል ብዬ
አንቺን አልወቅስሽም

ይሄ ሁሉ ሀተታ ይሄ ሁሉ ወሬ
አንድ እውነት ልነግርሽ አስቤ ነው ዛሬ
የእስካሁኑ ይብቃ የያበጠው ይፈንዳ
አንቺንም አላሳቅ እኔም አልጎዳ

በሰፊው አደባባይ ብዙ ህዝብ ካለው
እንዲህ ይነበባል ምስጢሬን ብሰቅለው
ለሺህ የስሜቴ ጎርፍ ገላጭ ቃሉ አንድ ነው
"ባልነግርሽ ነው እንጂ ዛሬም ወድሻለው"

((ምንያህል ጥላሁን))
አዶኒስ
@getem
@getem
@gebriel_19
ታምር አያልቅበት

ከጠላት ከደመኛዬ
በገጠመኝ ቢገጥም - የጉዟችን አቅጣጫ
የጎሪጥ እየተያየን
ያይጥ ና የድመት - የሌባ ፖሊስ ፍጥጫ
ኃላ ና ፊት ተፈራርተን - በጎንዮሽ ግርመማ
ጉዟችንን ሳንጨርስ
ብርሃን ተለወጠብን - ተደፋብን ጨለማ ::

በፍርሃት ተውጠን - ስንርድ ስንደናቀፍ
ተጣጥለን ለማለፍ - ለትግል ብንተቃቀፍ
የሚተናኮል አውሬ - ግብግባችንን ዓይቶ
ለሆዱ ቢፈልገንም - አለፈን ሳይበላን ፈርቶ

ምንም ቢፈጠር በሕይወት - በጎነው ማለት ለበጎ
እግዜር ታምር ይሰራል - እንዳንጠፋ ፈልጎ ፡፡

የአስራትፍሬ ይበልጣል ( ሮሪሳ )
ታህሳስ 26 / 2011 ዓ ም መቂ

@getem
@getem
@gebriel_19
# ሩብ_ጉዳይ
በሰለሞን ሳህሌ
ነብሴን ከነብስሽ አጣምረሽ ዓለም ጥግ ላይ ያኖርሽው
ሩብ ጉዳይ የሳምሽኝ ልጅ ጥበቡን ከየት ተማርሽው?

እውነት እውነት

ከንፈርሽ እጅግ ልዩ ነው የሜንት ጠረን ታድሏል
ሰሞኑን የሳምሽው ጉንጬ አየር ማስገባት ጀምሯል።
በሩብሽ እንዲህ የሆነው የጉንጬ ከንፈር ጥጉ
በሙሉ ቢሆን ኖሮማ ልቤና ነፍሴ ተማክረው እኔን ጥለውኝ ባረጉ።

እውነት እውነት

ለካንስ የመሳም ጥበብ እጅጉን እጅግ ተራቋል
በሜንት ጠረን ታጅቦ በሩብ ጉዳይ ልብ ይሰልባል
እኔ ምልሽ?
ይሄ የምሄድበት ጎዳና ጠረኑን በሜንት የናኘው
ንፋሱንም ልክ እንደኔ ሩብ ጉዳይ ስመሽው ነው?

እውነት እውነት

የምጠጣው የእግዜር ውሃ ጣዕም መልኩ ተቀይሯል
ግድ የለሽም አትደብቂኝ ውሃውንም ስመሽዋል?
ከሳሙስ አይቀር እንዲህ ነው ለስለስ አርጎ ሸረፍ አርጎ
መዓዛ ጠረን ደባልቆ በከንፈር አብሾ ልኮ
እንዲህ ነችኔ ሩብ ጉዳይ ወፈፍ አረገኝ እኮ
እናልሽ ከሳምሽኝ በኋላ ለሩብ ጉዳይ እጅ ሰጠው
ሠዓቱ ሙሉ ሆኖ እንኳን ሩብ ጉዳይ ነው እላለው

እውነት እውነት

ከመስታወቱ ፊት ቆሜ ከውስጡ እኔን እያየው
መተት አርጋብኝ ይሆን እያልኩ እጠይቃለው
የጉንጬን የከንፈሬን ጥግ በእጆቼ ዳብሳለው
የዳበስኩትን እጄን ሩብ ጉዳይ ስመዋለው
ወይ ጣጣዬ ወይ መከራ
ግድ የለሽም ልለምንሽ ግድ የለሽም ተለመኚኝ
አንድ ያጣላል ወዳጄ ሆይ ሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ።

#መልስ ከጥያቄ ለሰለሞን ሳህለ #ከኤሽታ

እንኳን ንዑስ ሆነ
ከግማሽ ዝቅ አለ
እሰይ እሩብ ሆነ ከንኡስ ከፍ ያለ፤
የከንፈርን ሾርኔ የሽሙጥ የቻለ።
ጥበበ ስሞሽን ከልብ እየሳለ
አይነኬ ዝልፈት በምናብ ካኖረ
# ፀጋዬን አውጥቼ የውስጥ ፍኖቴን ቅኔ ካናገረ
እንኳን እሩብ ሆነ ከግማሽ ያነሰ
ንዑስ ላይሆን ወርዶ ቁልቁል ያልተማሰ
አልቦ ላይሆን ሞልቶ ከልብ ያልደረሰ፤
እንዲሞላ ተስፋ እንዳይጎልም ስጋት
የጨረፍታ ስሞሽ የእሩብ ጉዳይ ጥለት
አይገቡ ልኬትን በግጥም ያሰረ
እሩብ ጉዳይ ብሎ ቅኔ ካዘረፈ፤
ከንፈሯ ምን ይሁን በኪሎ ያረፈ?

@getem
@getem
@gebriel_19
👍3
የሰማውን ይዞ ፤
ያየውን ጠምዝዞ ፤
ሁሉም በየጎራው ፤
ፊደል እየሻረ ፉከራ እያበዛ ፤
ጃሂል ልታይ አለ ፣
ተሸከሙኝ አለ ፤
ልክ እንደ ወሳንሳ ፤ ልክ እንደጂናዛ ።
ጃሂል ከምሸከም ፤
ድንጋይ ከምሸከም ፤ ትክሻየ አውጥቼ ፤
ኪታቤ ጋር ልዋል ፥
ዛሬም በስተርጅና፤ አንገቴን ደፍቼ ፤
የከተበ ሲሽር ፤
ይኸው ስንት ዘመን ፤ አይተዋል አይኖቼ ።
በዚህች በኛ ቀየ ፤
ጃሂል በየሜዳው ፤
ልርገጣችሁ ብሎ ፤ ስለሚደነፋ ፤
ይማረን እያለ ፤
ቀለሜው በሙሉ ፤ ቀለም ላይ ተደፋ! !!!!

@getem
@getem
@paappii

Mengistu zegeye
👍1
በዕውቀቱ ስዩም

//ከተመኙ ላይቀር//

ከተመኙ ላይቀር ወንዝነት መመኘት....
ሀገርን ሳይለቁ ሌላ ሀገር መገኘት.....::

@getem
@getem
@gebriel_19
# ሃገረ_ኢትዮጵ
°
በታላቁ መፅሃፍ ፥ ታሪኩ የሰፈረ
እዮብ ሰው አይደለም ፥ በምድር የኖረ።
°
"እዮብ" የተባለች
ምስኪን ሀገሬ ነች፤
ልጆች ሞተውባት
ገላዋ ተልቶባት
አመድ ላይ የተኛች።
°
በእምነት ተንበርክካ ፥ እጆቿን ዘርግታ
ምህረት የምትለምን ፥ ከሠራዊት ጌታ።
ወዳጅ ዘመዶቿ ፥ ሰድበሽው ሙች ሲሏት
"ሰጠ! -- ነሳ!" ብላ ፥ የምትኖር በፅናት።
~~~~~~~~~//~~~~~~~~~
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@gebriel_19
ዘፈንና ሙሾ ተዳቅለው ነው አሉ
አንቺን የፈጠሩ፥
ላ'ቤት የቸኮሉ
አንዳቸው ሲጠሩ፤
እስኪ ቆይ ይግረመኝ
እነሱ ተዳቅለው
አንቺን ካበቀሉ፥
በ'ኔ ትብስ ፍጭት
እኛን ሲበቀሉ፤
መካሪ እንዳቶኚ
ተቆጭ አስታራቂ፥
ልቅሶሽ ወዴት ጠፋ
እዝጎን አሟሟቂ?
*
ሳቂ ግዴለኝም
ዘፈንሽ አይንጠፍ፥
ከውብ ጥርሶችሽ ላይ
ዘንዶ ከሚለጠፍ፤
*
ሳቂ ግድ የለሽም!
ካንቺ ወዲያ ላንቺ
ስላንቺ ሊያውቅ የሻ
ሥርሽን አጠና፥
ከህልቀትሽ ቀድሞ
ዘርሽ ላይ አቀና፤
አባትሽ ሙሾ ነው አፈር የዘገነ፥
እናትሽም ዘፈን
እዚህ እዛ ፈሶ የተበታተነ፤
ከዘፈን ተወልደሽ በሙሾ እንድታልቂ፥
ተጽፎ ነው መሰል
በዘመናት መሀል በስተት ማትስቂ!
*
አንቺዬ!?
ሳቂ ግዴለሽም የጥርሶችሽ ስድር
ሰርክ ይተራመሱ፥
አልቅሽ እባክሽን ዘለላ እምባወችሽ
አፈሩን ሲያርሱ፤
አዲስ ታሪክ በቅሎ
ቡቃያ ከወጣ
ፍሬ አናጣም እኛ፥
አይጨክንምና
ከላይ ያለ ዳኛ።
*
ሳቂ ግድ-የለሽም
ደግሞ አልቅሽ ነፍርቂ፥
ሞላ ብለሽ ዘለሽ ከደጁ እንዳ'ርቂ።
ለምን ካልሽ?
*
ሳቅሽ ምሥጋና ነው
ልቅሶሽ የልመና፥
ከእግዜር ስትጣዪ አንች የለሽምና::

@getem
@getem
@paappii

Mitu yimer