ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
# ሩብ_ጉዳይ
በሰለሞን ሳህሌ
ነብሴን ከነብስሽ አጣምረሽ ዓለም ጥግ ላይ ያኖርሽው
ሩብ ጉዳይ የሳምሽኝ ልጅ ጥበቡን ከየት ተማርሽው?

እውነት እውነት

ከንፈርሽ እጅግ ልዩ ነው የሜንት ጠረን ታድሏል
ሰሞኑን የሳምሽው ጉንጬ አየር ማስገባት ጀምሯል።
በሩብሽ እንዲህ የሆነው የጉንጬ ከንፈር ጥጉ
በሙሉ ቢሆን ኖሮማ ልቤና ነፍሴ ተማክረው እኔን ጥለውኝ ባረጉ።

እውነት እውነት

ለካንስ የመሳም ጥበብ እጅጉን እጅግ ተራቋል
በሜንት ጠረን ታጅቦ በሩብ ጉዳይ ልብ ይሰልባል
እኔ ምልሽ?
ይሄ የምሄድበት ጎዳና ጠረኑን በሜንት የናኘው
ንፋሱንም ልክ እንደኔ ሩብ ጉዳይ ስመሽው ነው?

እውነት እውነት

የምጠጣው የእግዜር ውሃ ጣዕም መልኩ ተቀይሯል
ግድ የለሽም አትደብቂኝ ውሃውንም ስመሽዋል?
ከሳሙስ አይቀር እንዲህ ነው ለስለስ አርጎ ሸረፍ አርጎ
መዓዛ ጠረን ደባልቆ በከንፈር አብሾ ልኮ
እንዲህ ነችኔ ሩብ ጉዳይ ወፈፍ አረገኝ እኮ
እናልሽ ከሳምሽኝ በኋላ ለሩብ ጉዳይ እጅ ሰጠው
ሠዓቱ ሙሉ ሆኖ እንኳን ሩብ ጉዳይ ነው እላለው

እውነት እውነት

ከመስታወቱ ፊት ቆሜ ከውስጡ እኔን እያየው
መተት አርጋብኝ ይሆን እያልኩ እጠይቃለው
የጉንጬን የከንፈሬን ጥግ በእጆቼ ዳብሳለው
የዳበስኩትን እጄን ሩብ ጉዳይ ስመዋለው
ወይ ጣጣዬ ወይ መከራ
ግድ የለሽም ልለምንሽ ግድ የለሽም ተለመኚኝ
አንድ ያጣላል ወዳጄ ሆይ ሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ።

#መልስ ከጥያቄ ለሰለሞን ሳህለ #ከኤሽታ

እንኳን ንዑስ ሆነ
ከግማሽ ዝቅ አለ
እሰይ እሩብ ሆነ ከንኡስ ከፍ ያለ፤
የከንፈርን ሾርኔ የሽሙጥ የቻለ።
ጥበበ ስሞሽን ከልብ እየሳለ
አይነኬ ዝልፈት በምናብ ካኖረ
# ፀጋዬን አውጥቼ የውስጥ ፍኖቴን ቅኔ ካናገረ
እንኳን እሩብ ሆነ ከግማሽ ያነሰ
ንዑስ ላይሆን ወርዶ ቁልቁል ያልተማሰ
አልቦ ላይሆን ሞልቶ ከልብ ያልደረሰ፤
እንዲሞላ ተስፋ እንዳይጎልም ስጋት
የጨረፍታ ስሞሽ የእሩብ ጉዳይ ጥለት
አይገቡ ልኬትን በግጥም ያሰረ
እሩብ ጉዳይ ብሎ ቅኔ ካዘረፈ፤
ከንፈሯ ምን ይሁን በኪሎ ያረፈ?

@getem
@getem
@gebriel_19
👍3