#ቫለንታይን_ለምኔ
፧
በቫላንታይን ስም
ቀይ ለባሽ ሁላ፣
እስኪ ታሪኩን
ይመርምር ከኋላ፣
በርግጥ ቀይ
ልብሱንስ ይልበሰው፣
ለዛ ለዓድዋ ፋኖ
ህይወት ለከፈለው፣
ላሁኑ ነፃነት
ደሙን ላፈሰሰው፣
በየካቲት ወር
ዝክር እንዲሆነው፣
እንጂ ቫለንታይን
መች የሱ ሆነና፣
ይልቅ ቀዩን ለብሶ
ያስታውስ ያንን ጀግና!!
፨
#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
፧
በቫላንታይን ስም
ቀይ ለባሽ ሁላ፣
እስኪ ታሪኩን
ይመርምር ከኋላ፣
በርግጥ ቀይ
ልብሱንስ ይልበሰው፣
ለዛ ለዓድዋ ፋኖ
ህይወት ለከፈለው፣
ላሁኑ ነፃነት
ደሙን ላፈሰሰው፣
በየካቲት ወር
ዝክር እንዲሆነው፣
እንጂ ቫለንታይን
መች የሱ ሆነና፣
ይልቅ ቀዩን ለብሶ
ያስታውስ ያንን ጀግና!!
፨
#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
ቫላንታይን ደይ ወ ሲሩሁ!
(ፉአድ ኸይረዲን)
"የኮሰሰ ፍቅር…
ዘመናት ተሻግሮ በአንድ ቀን ፀደቀ?
በፍቅር ቀን ውሎ…
እውነተኛ ፍቅር ልቦች ስር ዘለቀ?
ብዬ የጠየቅኩሽ አይደለም በዋዛ
ፍቅር ያልገባው ልጅ ቃላት እያዋዛ
"እሞትልሻለሁ፣ እሆናለሁ ቤዛ"
እያለ ሲሞግት … ውሸቱን ሲነዛ
መርህ ያልተበጀለት ገረመኝ ሞራሉ፣
ለካስ… አሀ አሀ… ወዲህ ነው ጠለሉ፣
ለአንድ ቀን ፌሽታቸው በዓል ነው እያሉ፣
በቫላንታይን ደይ … ሰው እያታለሉ፣
ፆታ እየሰለሉ፣
ወዳጅ የመሰሉ፣
በታመመ መንፈስ፣ ሰርክ እየደለሉ፣
ቀያይ የለበሱ … በቁም የቀለሉ፣
እንጭጭ ማንነቶች፣ ሰላቢዎች አሉ።
በቫላንታይን እለት…
"እሆናለሁ ቤዛ" ያለላት በአምና ፣
ዘንድሮ ሌላ ናት፣ ልክ እንደ ካቻምና፣
ጊዜ ሲቀያየር አሮጌው ቀን ወድቆ፣
እሱም ይቀይራል አመቱን ጠብቆ!
መጪውን ጠብቁት…
ልክ እንደ ዘንድሮ አንዷን አሸብርቆ፣
"እሆናለሁ ቤዛ" …
በሚለው ፉገራ ማንነቷን ሰርቆ፣
ይተዋታል ንቆ።
@getem
@getem
@qteloch
(ፉአድ ኸይረዲን)
"የኮሰሰ ፍቅር…
ዘመናት ተሻግሮ በአንድ ቀን ፀደቀ?
በፍቅር ቀን ውሎ…
እውነተኛ ፍቅር ልቦች ስር ዘለቀ?
ብዬ የጠየቅኩሽ አይደለም በዋዛ
ፍቅር ያልገባው ልጅ ቃላት እያዋዛ
"እሞትልሻለሁ፣ እሆናለሁ ቤዛ"
እያለ ሲሞግት … ውሸቱን ሲነዛ
መርህ ያልተበጀለት ገረመኝ ሞራሉ፣
ለካስ… አሀ አሀ… ወዲህ ነው ጠለሉ፣
ለአንድ ቀን ፌሽታቸው በዓል ነው እያሉ፣
በቫላንታይን ደይ … ሰው እያታለሉ፣
ፆታ እየሰለሉ፣
ወዳጅ የመሰሉ፣
በታመመ መንፈስ፣ ሰርክ እየደለሉ፣
ቀያይ የለበሱ … በቁም የቀለሉ፣
እንጭጭ ማንነቶች፣ ሰላቢዎች አሉ።
በቫላንታይን እለት…
"እሆናለሁ ቤዛ" ያለላት በአምና ፣
ዘንድሮ ሌላ ናት፣ ልክ እንደ ካቻምና፣
ጊዜ ሲቀያየር አሮጌው ቀን ወድቆ፣
እሱም ይቀይራል አመቱን ጠብቆ!
መጪውን ጠብቁት…
ልክ እንደ ዘንድሮ አንዷን አሸብርቆ፣
"እሆናለሁ ቤዛ" …
በሚለው ፉገራ ማንነቷን ሰርቆ፣
ይተዋታል ንቆ።
@getem
@getem
@qteloch
👍1
ግጥም ብቻ 📘
ቃል ልግባልሽ #anu📝 አፈቅርሻለሁ ልል ቀናትን አልመርጥም ወደድኩሽ ለማለት ሰበብ አልፈልግም በእያንዳዷ ሰከንድ በሁሉም ደቂቃ ፀሀይም ባትወጣ ባትደምቅም ጨረቃ ሰማዩ እንኳን ቢናድ ኮከቦች ቢረግፉ ጥላቻ አግዝፈው ፍቅርን ቢፀየፉ ቀናት ቢሰየሙ ስም ቢወጣላቸው የፍቅር ባይባል መጠርያ ስማቸው አንቺ ከለሽልኝ ለኔ የፍቅር ናቸው በእያንዳንዷ ሰከንድ ፍቅሬን ብነግርልሽ ጨርሶ አይቻልም እኔ አንቺን ልገልፅሽ…
ተቃራኒ መልስ 📝yami fo anu
አፈቅርሻለሁ አትበል ቀናት አትመርጥም
ጠላሁሽም በል ሰበብ አትፈልግም
በያንዳንዷ ሰከንድ በሁሉም ደቂቃ
ፀሀይም ትውጣ ትደማምቅ ጨረቃ
ሰማይም አይናድ ከዋክብት አይርገፉ
ፍቅርን አግዝፈው ጥላቻ ይፀየፉ
ቀናት አይሰየሙ ስም አይውጣላቸው
መለያያ ይሁን መጠርያ ስማቸው
አንተ የለህ ለኔ ተቃራኒ ናቸው
የፍቅር ቀን ብሎ አለም የሰየመው
በቃልኪዳን ብዛት ያልተንበሸበሸው
ያላማሩ ጥንዶች በቀይ ቢደምቁም
ፍቅር በልባቸው ብዙ ቢሰንቁም
እንደኔ አደሉም
ስለኔና አንተ ምኑንም አያቁም
ምንም አይወክሉም
ምንም አይመስሉንም
ምንም ምንም ምንም
ሁሉም ተቃራኒ ጥቁር በ ነጭ ነው
ትተኸኝ መሄድህን
መናቅ መተውህን
መረሳቴን ነው ማስታውሰው
ፍቅርህን ስትጽፍ ብትከትብ ልትነግኝ
የረሳኸው ልቤ መርሳትን ነው ሚቀኝ
🙇♀🙇♀🙇♀
@getem
@getem
@gebriel_19
አፈቅርሻለሁ አትበል ቀናት አትመርጥም
ጠላሁሽም በል ሰበብ አትፈልግም
በያንዳንዷ ሰከንድ በሁሉም ደቂቃ
ፀሀይም ትውጣ ትደማምቅ ጨረቃ
ሰማይም አይናድ ከዋክብት አይርገፉ
ፍቅርን አግዝፈው ጥላቻ ይፀየፉ
ቀናት አይሰየሙ ስም አይውጣላቸው
መለያያ ይሁን መጠርያ ስማቸው
አንተ የለህ ለኔ ተቃራኒ ናቸው
የፍቅር ቀን ብሎ አለም የሰየመው
በቃልኪዳን ብዛት ያልተንበሸበሸው
ያላማሩ ጥንዶች በቀይ ቢደምቁም
ፍቅር በልባቸው ብዙ ቢሰንቁም
እንደኔ አደሉም
ስለኔና አንተ ምኑንም አያቁም
ምንም አይወክሉም
ምንም አይመስሉንም
ምንም ምንም ምንም
ሁሉም ተቃራኒ ጥቁር በ ነጭ ነው
ትተኸኝ መሄድህን
መናቅ መተውህን
መረሳቴን ነው ማስታውሰው
ፍቅርህን ስትጽፍ ብትከትብ ልትነግኝ
የረሳኸው ልቤ መርሳትን ነው ሚቀኝ
🙇♀🙇♀🙇♀
@getem
@getem
@gebriel_19
❤1
ተማጥኖ ለገመድ
(ልዑል ሀይሌ)
እንፈራገጣለሁ
ያሰረኝን ገመድ ታግዬ ለመፍታት፤
የማሠሪያ ዕጣ ነው
በነፃነቱ ልክ
እስረኛዋን ነፍሴን ነፃ የሚያወጣት፤
.
ነፃ ውጣ ገመዱ!
አትገደብ በኔ በገላዬ ልኬት፤
የኔ ስቃይ አይሁን
ያንተ ጥጋት ስኬት፤.
.
የውልህ ገመዴ!...
ኑሮን እወቅበት ክንድህን አበርታ፤
ስንት ልብስ መሰለህ
ታጥቦ ሚጠብቀው ከላይህ ሊሰጣ፤
ስንት ስጋ አለልህ
ቋንጣነትን ብሎ አንተን የሚማጠን፤
ሂድ መከታ ሁነው
እስራቴን ለቅቀህ
ጀግን በፍጥረትህ በመክሊትህ መጠን፤
.
የውልህ ገመዴ!...
አትያዘኝ ጨምድደህ አትፍቀድ እስራት፤
አሳሪውን ትተህ
ውስጥህን አድምጠው ፍርቱናህን ኑራት፤
.
ገመድ ሆይ ልቀቀኝ!!
አታብዛው ጭንቀቴን ነፃ ሁን ተፈታ፤
አንተም እስረኛ ነህ
ዕድሜህን ከፈጀህ
ለአሳሪው ትዕዛዝ ገላህ ከተረታ፤
ነፃ ሁን ገመዴ!!..
፯-፮-፳፻፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@lula_al_greeko
(ልዑል ሀይሌ)
እንፈራገጣለሁ
ያሰረኝን ገመድ ታግዬ ለመፍታት፤
የማሠሪያ ዕጣ ነው
በነፃነቱ ልክ
እስረኛዋን ነፍሴን ነፃ የሚያወጣት፤
.
ነፃ ውጣ ገመዱ!
አትገደብ በኔ በገላዬ ልኬት፤
የኔ ስቃይ አይሁን
ያንተ ጥጋት ስኬት፤.
.
የውልህ ገመዴ!...
ኑሮን እወቅበት ክንድህን አበርታ፤
ስንት ልብስ መሰለህ
ታጥቦ ሚጠብቀው ከላይህ ሊሰጣ፤
ስንት ስጋ አለልህ
ቋንጣነትን ብሎ አንተን የሚማጠን፤
ሂድ መከታ ሁነው
እስራቴን ለቅቀህ
ጀግን በፍጥረትህ በመክሊትህ መጠን፤
.
የውልህ ገመዴ!...
አትያዘኝ ጨምድደህ አትፍቀድ እስራት፤
አሳሪውን ትተህ
ውስጥህን አድምጠው ፍርቱናህን ኑራት፤
.
ገመድ ሆይ ልቀቀኝ!!
አታብዛው ጭንቀቴን ነፃ ሁን ተፈታ፤
አንተም እስረኛ ነህ
ዕድሜህን ከፈጀህ
ለአሳሪው ትዕዛዝ ገላህ ከተረታ፤
ነፃ ሁን ገመዴ!!..
፯-፮-፳፻፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@lula_al_greeko
የመስኩ ላይ ቁርሾ! !!!
ሲጀምሩ ፤
ሁለቱም ቆርኬዎች ፤
አብረው ከኖሩበት ፤
ከሚያምረው መስክ ዳር ፤
እየጋጡ ነበር ፤
ከጨፌው ማሳ ላይ ፤ እየፈነደቁ ፤
ድንገት ሳይታሰብ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ወዳጅ ዘመድ መስለው ፤ ወደዚያ ዘለቁ ።
ቆርኬዎቹ ዘንተው ፤
ሳር ከሚግጡበት ፤
ደረሱ ተኩላዎች ፤ እየተፋነኑ ፤
ውሃ በሞላው አፍ ፤
የጨፌውን ማማር ፤
የጋጮቹን ገላ ፤ እያስተነተኑ ፤
የተኩላ መንጎች ፤
እንኳን በስጋቸው ፤
በተቆላለፈው ፣ በቀንዳቸው ቀኑ ።
ቆርኬዎቹ ጠግበው ፤ እስኪፈነጥዙ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ሳሩ ላይ ዋሉበት እየተሟዘዙ ።
ጀመሩ ቆርኬዎች ፤
በጥጋብ ጀመሩ ቀጠሉ ማስካካት ፤
ተኩላ ተናቃ ፤
በጨዋታ መሃል ሸር ለማስገባት ።
እንደዚህ አላቸው ተኩላ አባ ሴራ ፤
ከአያት ቅም አያቶች ታሪክ ስናጣራ ፤
አለቃ ሚሆነው የቆርኬዎች አውራ ፤
ታግሎ የጣለ ነው ፤
ተፋልሞ ሚገዛ ከገጠሙት ጋራ ።
ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጠቅልሎ ፤
በቀንዱ ጀመረው ፤
ካንደኛው ትከሻ አንዱ ቆርኬ ዘሎ ።
ተኩላ ዳር ቆማ ፤
በጭብጨባ በአጀብ ፤
በል በለው ትላለች ፤ በክፋት አንደበት ፤
ጀግና ማለት በኛ ፤
የጫካው አርበኛ ፤ የሚዘመርለት ፋኖ እየተባለ ፤
ቀንድን በቀንድ ይዞ ፤
አንገቱን ጠምዝዞ መሬት ላይ የጣለ።
በግብግብ መሃል ፤
ገራገር ቆርኬዎች ፤
የተኩላን ፊሽካ ፤ ሰምተው ተናነቁ ፤
ቀንዳቸው ተጣልፎ ፤
ሁለቱም ሜዳው ላይ ዘፍ ብለው ወደቁ ።
በተጠለፈ ቀንድ ፤ በተገመደ አንገት ፤ ወድቀው ተጋጠሙ ፤
ራስ በራሳቸው በጀመሩት ትግል ማንም ሳያሸንፍ ሁለቱም ደከሙ ፤
በተኩላ ተንኮል አብሮ አደግ ቆርኬዎች ሞትን ተሸለሙ ።
ይህን ያየ ቆርኬ ፤
የወንድሞቹ ሞት ፤ በተኩላዎች ሴራ መሆኑን ተረድቶ ፤
ከሞቱበት ሳር ላይ ፤
ካለው ትልቅ ዛፍ ላይ ፤
እንዲህ ብሎ ጻፈ ብእሩን አውጥቶ ።
ሰፊ መስክ ሳለ ፤
ሰፊ ጨፌ ሳለ ፤ በዚህ በመንደሩ ፤
ያንዲት እናት ልጆች ፤
አንተ ወግድልኝ
እኔ ነኝ አለቃ ፤
እኔ ነኝ ባለ ሹም በሚሉት አምቡላ ስለተሳከሩ ፤
ሞሰቡ ሳይቸግር ፤
እኔ በሚል እሳት ፤ ተበላልተው ቀሩ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
ሲጀምሩ ፤
ሁለቱም ቆርኬዎች ፤
አብረው ከኖሩበት ፤
ከሚያምረው መስክ ዳር ፤
እየጋጡ ነበር ፤
ከጨፌው ማሳ ላይ ፤ እየፈነደቁ ፤
ድንገት ሳይታሰብ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ወዳጅ ዘመድ መስለው ፤ ወደዚያ ዘለቁ ።
ቆርኬዎቹ ዘንተው ፤
ሳር ከሚግጡበት ፤
ደረሱ ተኩላዎች ፤ እየተፋነኑ ፤
ውሃ በሞላው አፍ ፤
የጨፌውን ማማር ፤
የጋጮቹን ገላ ፤ እያስተነተኑ ፤
የተኩላ መንጎች ፤
እንኳን በስጋቸው ፤
በተቆላለፈው ፣ በቀንዳቸው ቀኑ ።
ቆርኬዎቹ ጠግበው ፤ እስኪፈነጥዙ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ሳሩ ላይ ዋሉበት እየተሟዘዙ ።
ጀመሩ ቆርኬዎች ፤
በጥጋብ ጀመሩ ቀጠሉ ማስካካት ፤
ተኩላ ተናቃ ፤
በጨዋታ መሃል ሸር ለማስገባት ።
እንደዚህ አላቸው ተኩላ አባ ሴራ ፤
ከአያት ቅም አያቶች ታሪክ ስናጣራ ፤
አለቃ ሚሆነው የቆርኬዎች አውራ ፤
ታግሎ የጣለ ነው ፤
ተፋልሞ ሚገዛ ከገጠሙት ጋራ ።
ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጠቅልሎ ፤
በቀንዱ ጀመረው ፤
ካንደኛው ትከሻ አንዱ ቆርኬ ዘሎ ።
ተኩላ ዳር ቆማ ፤
በጭብጨባ በአጀብ ፤
በል በለው ትላለች ፤ በክፋት አንደበት ፤
ጀግና ማለት በኛ ፤
የጫካው አርበኛ ፤ የሚዘመርለት ፋኖ እየተባለ ፤
ቀንድን በቀንድ ይዞ ፤
አንገቱን ጠምዝዞ መሬት ላይ የጣለ።
በግብግብ መሃል ፤
ገራገር ቆርኬዎች ፤
የተኩላን ፊሽካ ፤ ሰምተው ተናነቁ ፤
ቀንዳቸው ተጣልፎ ፤
ሁለቱም ሜዳው ላይ ዘፍ ብለው ወደቁ ።
በተጠለፈ ቀንድ ፤ በተገመደ አንገት ፤ ወድቀው ተጋጠሙ ፤
ራስ በራሳቸው በጀመሩት ትግል ማንም ሳያሸንፍ ሁለቱም ደከሙ ፤
በተኩላ ተንኮል አብሮ አደግ ቆርኬዎች ሞትን ተሸለሙ ።
ይህን ያየ ቆርኬ ፤
የወንድሞቹ ሞት ፤ በተኩላዎች ሴራ መሆኑን ተረድቶ ፤
ከሞቱበት ሳር ላይ ፤
ካለው ትልቅ ዛፍ ላይ ፤
እንዲህ ብሎ ጻፈ ብእሩን አውጥቶ ።
ሰፊ መስክ ሳለ ፤
ሰፊ ጨፌ ሳለ ፤ በዚህ በመንደሩ ፤
ያንዲት እናት ልጆች ፤
አንተ ወግድልኝ
እኔ ነኝ አለቃ ፤
እኔ ነኝ ባለ ሹም በሚሉት አምቡላ ስለተሳከሩ ፤
ሞሰቡ ሳይቸግር ፤
እኔ በሚል እሳት ፤ ተበላልተው ቀሩ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
፤ ሲጋራ
መጀመሪያ ክበክ
ከሁሉ አብልጠህ
በጅህ ሸፍነሀት
ነፋስ እንዳይነካት
ብርድ እንዳያጠቃት
ከለኮስክ በኋላ
ካነደድክ በኋላ
እሳቱን አጥፍተህ ክብሪት ወደ ኋላ
አንዴ ስትናፍቅህ አፍህ ውስጥ ስከታት
አስሬ ስስማት ስታገላብጣት
አንዴ ስታስጠላህ ካፍህ ስታርቃት
ግና የኋላ የኋላ በስተመጨረሻ
ከእግርህ በታች የዋለች ልክ አንደ ቆሻሻ
ዮናስ ምትኩ
2008
@getem
@getem
@gebriel_19
መጀመሪያ ክበክ
ከሁሉ አብልጠህ
በጅህ ሸፍነሀት
ነፋስ እንዳይነካት
ብርድ እንዳያጠቃት
ከለኮስክ በኋላ
ካነደድክ በኋላ
እሳቱን አጥፍተህ ክብሪት ወደ ኋላ
አንዴ ስትናፍቅህ አፍህ ውስጥ ስከታት
አስሬ ስስማት ስታገላብጣት
አንዴ ስታስጠላህ ካፍህ ስታርቃት
ግና የኋላ የኋላ በስተመጨረሻ
ከእግርህ በታች የዋለች ልክ አንደ ቆሻሻ
ዮናስ ምትኩ
2008
@getem
@getem
@gebriel_19
*ፍቅር ነው የራበኝ*(ሳሙኤል አዳነ)
*
ደህና ነኝ እንዳልል
ደህንነቴ ጠፍቷል ፣
እሞኛል እንዳልል
ይሄው ፊቴ ፈክቷል ።
ሰው ሲያየኝ ጤነኛ ፣
ውስጤ በሽተኛ ፣
ቆይ ምን ብየ ላውራ
ሰሚ ሰው አግኝቼ ፣
በልቤ ጠራ ውስጥ
የትኛውን ትቼ ፣
*
አይቶ በሚፈርድ
ጆሮ ጠቢ ምላስ በሞላበት ሀገር ፣
ለየትኛው ሰሚ
ለየትኛው ሀኪም ህመሜን ልናገር ።
ከማንነት በላይ ፣
ከምንነት በላይ ፣
ምን ቃል ሊተነፈስ ?
በሽፋን መለኪያ
ምን እውነት ሊታፈስ ?
*
ፍቅር ነው የራበኝ..
እሱ ነው ያመመኝ ..
የሀገሬ መሬት ሰው እያካሰሰ ፣
ሰው እያናከሰ፣
የሀገሬ ቋንቋ
ዘር እያስቆጠረ ፣
ክልል እያጠረ ፣
ያዳም የ አብራክ ክፋይ
ሰውነት ቀረና ፣
በጎሳ በብሄር
ታጥሮ ህልውና ፣
በሽብር አይምሮ
ሀገር ይታመሳል ።
ለማይጠቅም አለም
ንጹህ ደም ይፈሳል ።
ክብር የ ሰው ስጋ
በግፍ ይቆረሳል ።
አፍ አየቀደመ
የህሊና ደወል
መሰማት ተስኖት ፣
የአምላክ ቃል ይፈርሳል ።
*
ይሔው ነው ህመሜ
የእድሜያችን ጣሪያ
ሰማኒያ ላይሞላ ፣
በሳር በቅጠሉ
ባፈር ስንባላ ፣
እኔ ነኝ የኔ ነው ፣
ማንነቴ እንትን ነው ፣
የሚል እድር ፈላ ።
በሉ እስኪ ንገሩኝ
ማንነት ምንድን ነው?
ምንነት የቱ ነው ?
*
ሰው ከመባል ወዲያ
ምን ትርጉም ተገኝቶ ?
ከአምላክ ፍጡር ውጭ
ምን ጠላት መጥቶ ?
*
ምንድን ነው ነገሩ ፣
ዝንትአለም መናከስ
ደምበር እያጠሩ ፣
በመግባቢያ ቋንቋ
በትውልድ ቀየ ዘር እየቆጠሩ ፣
ምንድን ነው ?ዘር መቁጠር
ዘር ማሳለይ እንጅ
ሰው ላይ ምን ያደርጋል ፣
ማን በሀሩር ደርቆ
ማን በዝናብ ያድጋል?
*
አመሉ ነው እንጅ ፣
ሞኝነት ነው እንጅ፣
ጥንትም ተፈጥሮውን
ሰው በአምላክ ካመነ፣
ማን ሀባሻን መርጦ
ማን ፈረንጅ ሆነ ?
ከግዜሩ ሆኖ አንጅ
ፍጥረት የተሰጠ ፣
ይሁንልኝ ብሎ
ማን ፆታ መረጠ ።
*
ከአፈር ተፈጥሮ
አፈር የሚሆን ሰው ፣
ከአፈር ጋር ታግሎ
አፈር የሚቆርሰው ፣
ምነው? ይሄ ትውልድ
ከራስ የዘለለ ማስተዋል አነሰው ።
*
ይገርማል ...
በማለዳ ፀሀይ
በምሽት ከዋክብት ቀን እየተዋጀ፣
ህዝቤ አንደጎበጠ
ቅን ሆኖ ቀን ሳያይ ሰማኒያውን ፈጀ ።
ፍቅር ነው የራበኝ ...........
*
03/02/2011
2:00pm
አ.አ
@getem
@getem
@gebriel_19
*
ደህና ነኝ እንዳልል
ደህንነቴ ጠፍቷል ፣
እሞኛል እንዳልል
ይሄው ፊቴ ፈክቷል ።
ሰው ሲያየኝ ጤነኛ ፣
ውስጤ በሽተኛ ፣
ቆይ ምን ብየ ላውራ
ሰሚ ሰው አግኝቼ ፣
በልቤ ጠራ ውስጥ
የትኛውን ትቼ ፣
*
አይቶ በሚፈርድ
ጆሮ ጠቢ ምላስ በሞላበት ሀገር ፣
ለየትኛው ሰሚ
ለየትኛው ሀኪም ህመሜን ልናገር ።
ከማንነት በላይ ፣
ከምንነት በላይ ፣
ምን ቃል ሊተነፈስ ?
በሽፋን መለኪያ
ምን እውነት ሊታፈስ ?
*
ፍቅር ነው የራበኝ..
እሱ ነው ያመመኝ ..
የሀገሬ መሬት ሰው እያካሰሰ ፣
ሰው እያናከሰ፣
የሀገሬ ቋንቋ
ዘር እያስቆጠረ ፣
ክልል እያጠረ ፣
ያዳም የ አብራክ ክፋይ
ሰውነት ቀረና ፣
በጎሳ በብሄር
ታጥሮ ህልውና ፣
በሽብር አይምሮ
ሀገር ይታመሳል ።
ለማይጠቅም አለም
ንጹህ ደም ይፈሳል ።
ክብር የ ሰው ስጋ
በግፍ ይቆረሳል ።
አፍ አየቀደመ
የህሊና ደወል
መሰማት ተስኖት ፣
የአምላክ ቃል ይፈርሳል ።
*
ይሔው ነው ህመሜ
የእድሜያችን ጣሪያ
ሰማኒያ ላይሞላ ፣
በሳር በቅጠሉ
ባፈር ስንባላ ፣
እኔ ነኝ የኔ ነው ፣
ማንነቴ እንትን ነው ፣
የሚል እድር ፈላ ።
በሉ እስኪ ንገሩኝ
ማንነት ምንድን ነው?
ምንነት የቱ ነው ?
*
ሰው ከመባል ወዲያ
ምን ትርጉም ተገኝቶ ?
ከአምላክ ፍጡር ውጭ
ምን ጠላት መጥቶ ?
*
ምንድን ነው ነገሩ ፣
ዝንትአለም መናከስ
ደምበር እያጠሩ ፣
በመግባቢያ ቋንቋ
በትውልድ ቀየ ዘር እየቆጠሩ ፣
ምንድን ነው ?ዘር መቁጠር
ዘር ማሳለይ እንጅ
ሰው ላይ ምን ያደርጋል ፣
ማን በሀሩር ደርቆ
ማን በዝናብ ያድጋል?
*
አመሉ ነው እንጅ ፣
ሞኝነት ነው እንጅ፣
ጥንትም ተፈጥሮውን
ሰው በአምላክ ካመነ፣
ማን ሀባሻን መርጦ
ማን ፈረንጅ ሆነ ?
ከግዜሩ ሆኖ አንጅ
ፍጥረት የተሰጠ ፣
ይሁንልኝ ብሎ
ማን ፆታ መረጠ ።
*
ከአፈር ተፈጥሮ
አፈር የሚሆን ሰው ፣
ከአፈር ጋር ታግሎ
አፈር የሚቆርሰው ፣
ምነው? ይሄ ትውልድ
ከራስ የዘለለ ማስተዋል አነሰው ።
*
ይገርማል ...
በማለዳ ፀሀይ
በምሽት ከዋክብት ቀን እየተዋጀ፣
ህዝቤ አንደጎበጠ
ቅን ሆኖ ቀን ሳያይ ሰማኒያውን ፈጀ ።
ፍቅር ነው የራበኝ ...........
*
03/02/2011
2:00pm
አ.አ
@getem
@getem
@gebriel_19
ከጭቃ የነበረው ወርቅ
________________
የውስጥ ማንነቱ በውጪ ታምቆ
በተጨራመተ ልብሱ ውበቱን ደብቆ
የዋህ ብልህነቱን በመልኩ ሸፍኖ
ቢገለል ከነዛህ እንደ ርካሽ ሆኖ
ወርቅነቱን ትቶ አመጣጡን ሆነ
እንደ ጭቃ ወርዶ ከፍ ሊል ወሰነ
ጥር 23/2011
በምንቴ/የአብስራ
@getem
@getem
@gebriel_19
________________
የውስጥ ማንነቱ በውጪ ታምቆ
በተጨራመተ ልብሱ ውበቱን ደብቆ
የዋህ ብልህነቱን በመልኩ ሸፍኖ
ቢገለል ከነዛህ እንደ ርካሽ ሆኖ
ወርቅነቱን ትቶ አመጣጡን ሆነ
እንደ ጭቃ ወርዶ ከፍ ሊል ወሰነ
ጥር 23/2011
በምንቴ/የአብስራ
@getem
@getem
@gebriel_19
አይገባም ወይ ክብር
መልካም እየሰራ ታሪክ እየሰማ
አድዋ ለደረሰ በእግሩ ተጉዞ
ይወጣ የለም ወይ
ስንት አይነት ተራራ ባዶ ታሪክ ይዞ።
(ሀና ሀይሉ)
ክብር እኛነትን ላኖሩ ላከበሩን ላስከበሩን አባቶች
ክብር ለአድዋ ተጓዦች
ምንጭ @hanahailu
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@getem
@getem
መልካም እየሰራ ታሪክ እየሰማ
አድዋ ለደረሰ በእግሩ ተጉዞ
ይወጣ የለም ወይ
ስንት አይነት ተራራ ባዶ ታሪክ ይዞ።
(ሀና ሀይሉ)
ክብር እኛነትን ላኖሩ ላከበሩን ላስከበሩን አባቶች
ክብር ለአድዋ ተጓዦች
ምንጭ @hanahailu
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@getem
@getem
ቃታዬ
የወደደሽ ሁሉ
በተራበ አፈ-ሙዝ ተታኩሶ እያለቀ፤
ቃታ እንደምን ልሳብ
ልቤ ባንቺ ፍቅር ነገ እየናፈቀ፤
.
ስጋውን ባታቆስል
አንቺን እያሰበ በሚጋራኝ ጠላት፤
ድምፅ አልባ ሆና'ንጂ
ተስፋ 'ምትመግበኝ
ክፉ ቀን ማለፊያ ትዕግስቴ ቃታ ናት፤
፰-፮-፳፻፲፩ ዓ.ም.
(ልዑል ሀይሌ)
@getem
@getem
@gebriel_19
የወደደሽ ሁሉ
በተራበ አፈ-ሙዝ ተታኩሶ እያለቀ፤
ቃታ እንደምን ልሳብ
ልቤ ባንቺ ፍቅር ነገ እየናፈቀ፤
.
ስጋውን ባታቆስል
አንቺን እያሰበ በሚጋራኝ ጠላት፤
ድምፅ አልባ ሆና'ንጂ
ተስፋ 'ምትመግበኝ
ክፉ ቀን ማለፊያ ትዕግስቴ ቃታ ናት፤
፰-፮-፳፻፲፩ ዓ.ም.
(ልዑል ሀይሌ)
@getem
@getem
@gebriel_19
ቅዳሜና ደሴ!!!!!
በአረብ ገንዳ ሪጋ፤ በላይኛው ጦሳ፤
ደሴ ሸሞንሟኒት፤ ደሴ ደንገላሳ፤
ቅዳሜና ደሴ፤ ሸጋና ሳቢሳ፤
ይች የዳውዶ ልጅ፤
ዛሬም ሰበር ሰካ፤ አደረጋትሳ፤
ከርቤና ሉባንጃ፤ እጣን አጫጭሳ፤
አህሪቡ ትላለች፤ ፍቅር ራት ምሳ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
የኔዋ!! ሸጋ ቅዳሜ ትሁንላቹ!!!💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
በአረብ ገንዳ ሪጋ፤ በላይኛው ጦሳ፤
ደሴ ሸሞንሟኒት፤ ደሴ ደንገላሳ፤
ቅዳሜና ደሴ፤ ሸጋና ሳቢሳ፤
ይች የዳውዶ ልጅ፤
ዛሬም ሰበር ሰካ፤ አደረጋትሳ፤
ከርቤና ሉባንጃ፤ እጣን አጫጭሳ፤
አህሪቡ ትላለች፤ ፍቅር ራት ምሳ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
የኔዋ!! ሸጋ ቅዳሜ ትሁንላቹ!!!💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
<አራዥ ፡አጉራሽ>
የሀገር ልጅ በሀገር ወድቀቆ
ወጥቶ የሚያየው ሰው እርቆ
አንድ የሰው ሰው የእናት አንጀት
ክብሩን ጥሎ የወገኑን ጎጆ ዳሱን ሊሰራለት
ሲል በምሽት ደፋ ቀና
እኔ ያንተ ነኝ በሚል ቃና
ወንድምህ ነኝ በሚል ዜማ
ወገንህ ነኝ በሚል አርማ
እንኳን ሆንኩ አልኩ ከዚች አፈር
ሺ ሰው አለኝ በኔ ኑሮ በኔ ገላ የማያፍር፡፡
✍...አብርሀም <ልጅ ኤቢ>
@getem
@getem
@artbekiyechalal
"🇪🇹ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር🇪🇹"
የሀገር ልጅ በሀገር ወድቀቆ
ወጥቶ የሚያየው ሰው እርቆ
አንድ የሰው ሰው የእናት አንጀት
ክብሩን ጥሎ የወገኑን ጎጆ ዳሱን ሊሰራለት
ሲል በምሽት ደፋ ቀና
እኔ ያንተ ነኝ በሚል ቃና
ወንድምህ ነኝ በሚል ዜማ
ወገንህ ነኝ በሚል አርማ
እንኳን ሆንኩ አልኩ ከዚች አፈር
ሺ ሰው አለኝ በኔ ኑሮ በኔ ገላ የማያፍር፡፡
✍...አብርሀም <ልጅ ኤቢ>
@getem
@getem
@artbekiyechalal
"🇪🇹ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር🇪🇹"
በሳምንቱ መጨረሻ በለተ ቅዳሜ ፤
በል ቶሎ ናልኝ ፤ አልጠግበውም እና ከንፈርህን ስሜ ።
አና እልሀለሁ
ብዙ ቀን አለፈኝ ፤
ባጉል መሽኮር መሜ ።
እቅፍ አርገኝ እስኪ ፤
ይተወኝ እንደሆን አንተን ተሳልሜ ።
ሉባንጃ እና ብርጉድ፤ አጥነዋለሁ ቤቴን ፤
ባሪቲ እና ከርቤ ያልጋዬን መናገሻ አውጄ ጓዳዬን ።
እጠብቅሀለሁ ነግረኸኛልና
እንደምትወደኝ ፤
ሳትደብቅ ውስጥህን
እንደምታፈቅረኝ ።
ምን እንጠብቃለን ከጉያህ አስገባኝ፤
ያ መጥፎ አባዜ
አንተን ባየሁ ጊዜ ካላሽኮረመመኝ ።
#Yami
@getem
@getem
@gebriel_19
በል ቶሎ ናልኝ ፤ አልጠግበውም እና ከንፈርህን ስሜ ።
አና እልሀለሁ
ብዙ ቀን አለፈኝ ፤
ባጉል መሽኮር መሜ ።
እቅፍ አርገኝ እስኪ ፤
ይተወኝ እንደሆን አንተን ተሳልሜ ።
ሉባንጃ እና ብርጉድ፤ አጥነዋለሁ ቤቴን ፤
ባሪቲ እና ከርቤ ያልጋዬን መናገሻ አውጄ ጓዳዬን ።
እጠብቅሀለሁ ነግረኸኛልና
እንደምትወደኝ ፤
ሳትደብቅ ውስጥህን
እንደምታፈቅረኝ ።
ምን እንጠብቃለን ከጉያህ አስገባኝ፤
ያ መጥፎ አባዜ
አንተን ባየሁ ጊዜ ካላሽኮረመመኝ ።
#Yami
@getem
@getem
@gebriel_19
የፍቅር መግለጫ
ከእወድሀለሁ ሌላ፣
ከአፈቅርሀለሁ ሌላ፣
ምን አለ ቢመጣ ምን አለ ቢፈጠር፣
ለፍቅሬ ማሳያ እገልፅበት ነበር።
እውነት ነው የምልህ ፣
እወድሀለሁ ስልህ፣
ፍቅርህን ሚተካ አምሳያ ሚሆነው፣
ፈልጌ አስፈልጌ........
ቃላት ስላጣሁ ነው።
ኪያ ብዬህ ነበር የኔ በመሆንህ፣
ስሞች መርጫለሁ ፍቅሬ እንዲገባህ፣
ግን... ግን.. .....
ለመጠሪያ እንጂ ከቶ አልቻሉም ፍቅሬን ሊገልፁልህ።
ለሰርክ አዲስ ፍቅርህ
ሁሌም ለሚዋበው፣
ቃል እስኪገኝ ድረስ
እንዲሁ ልበልህ በቃ እወድሀለው
በቃ አፈቅርሀለው።
9-6-11ቅዳሜ
( ፅዮን )
@getem
@getem
@gebriel_19
ከእወድሀለሁ ሌላ፣
ከአፈቅርሀለሁ ሌላ፣
ምን አለ ቢመጣ ምን አለ ቢፈጠር፣
ለፍቅሬ ማሳያ እገልፅበት ነበር።
እውነት ነው የምልህ ፣
እወድሀለሁ ስልህ፣
ፍቅርህን ሚተካ አምሳያ ሚሆነው፣
ፈልጌ አስፈልጌ........
ቃላት ስላጣሁ ነው።
ኪያ ብዬህ ነበር የኔ በመሆንህ፣
ስሞች መርጫለሁ ፍቅሬ እንዲገባህ፣
ግን... ግን.. .....
ለመጠሪያ እንጂ ከቶ አልቻሉም ፍቅሬን ሊገልፁልህ።
ለሰርክ አዲስ ፍቅርህ
ሁሌም ለሚዋበው፣
ቃል እስኪገኝ ድረስ
እንዲሁ ልበልህ በቃ እወድሀለው
በቃ አፈቅርሀለው።
9-6-11ቅዳሜ
( ፅዮን )
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
/// ስሜን ማን አወጣው ///
ብሩኬ(የወይን ፍሬ)
_ _ ___
ስምን መላዕክት ያወጣዋል አሉ
የሀገሬ ሰዎች ምስጋናን ሲያድሉ
ብለው ያስተማሩን ከወሬ ተነስተው
ባህሪን ተረድተው ገፅታንም ቃኝተው
እውነት እንደሚሉት መላዕክት ካወጣው
ስሜን ቅዱስ ብሎ ስለምን ሰየመው
የሰው ላብ ስጠጣ ስሜንም አልፋቀው
ስቃይ ህመማቸው ደስታ ሲሆንብኝ
ምርቅዝ ቁስላቸው አያመኝ አይሰማኝ
እናም የሀገሬ ሰዎች እናንተው ፍረዱት
ስብሀት ተብሎ ፈጣሪን ካልፈራ
አደፍርስ ተብሎ ፈጣሪን ከፈራ
የውብ ዳር ተብሎ የቀፋፋ ዳር ከተሆነ
ጫን ያለው ተብሎ የማይጫን ከሆነ
ስም አውጪው መላዕክት አምታታው ባልሆነ።
ግንቦት 11-2010 ዓ.ም
ቅዳሜ ቀን 9:08
@getem
@getem
@gebriel_19
ብሩኬ(የወይን ፍሬ)
_ _ ___
ስምን መላዕክት ያወጣዋል አሉ
የሀገሬ ሰዎች ምስጋናን ሲያድሉ
ብለው ያስተማሩን ከወሬ ተነስተው
ባህሪን ተረድተው ገፅታንም ቃኝተው
እውነት እንደሚሉት መላዕክት ካወጣው
ስሜን ቅዱስ ብሎ ስለምን ሰየመው
የሰው ላብ ስጠጣ ስሜንም አልፋቀው
ስቃይ ህመማቸው ደስታ ሲሆንብኝ
ምርቅዝ ቁስላቸው አያመኝ አይሰማኝ
እናም የሀገሬ ሰዎች እናንተው ፍረዱት
ስብሀት ተብሎ ፈጣሪን ካልፈራ
አደፍርስ ተብሎ ፈጣሪን ከፈራ
የውብ ዳር ተብሎ የቀፋፋ ዳር ከተሆነ
ጫን ያለው ተብሎ የማይጫን ከሆነ
ስም አውጪው መላዕክት አምታታው ባልሆነ።
ግንቦት 11-2010 ዓ.ም
ቅዳሜ ቀን 9:08
@getem
@getem
@gebriel_19
የነጻ አውጭ ታሪክ¡¡¡¡¡¡
እነዚያ ውርጋጦች ፤
የዛሬ ስንት አመት ፤
ከሙት መጽሃፍ ላይ ፤
በተገኘ ፊደል ፤ በአቢዮት ተጠምቀው ፤
ሰባራ ጠበንጃ ፤
ሰባራ ህልም ጋር ፤ ከቅዠት ጋር ታጥቀው ፤
ነጻ እንድናወጣሽ፤
እሽ በይ ሃራይ በይ፤
እያሉ ሰበኳት ፤አደይን ጨቅጭቀው ።
ሰምታ ማታውቀውን ፤
አይታ ማታውቀውን ፤
መከራሽ መኣት ነው ብለው ዘረዘሩ፤
አታውቂውም እንጅ ፤
በደልሽ ብዙ ነው ብለው ተናገሩ ፤
ከስብከታቸው ጋር ፤
የአዞ ልቅሷቸውን ፤ እንደጉድ አዘሩ ።
የነገሯት ነገር ፤
ከምታውቀው እውነት ፤ ሃቁ ተጣርሶባት ፤
ስትል ፈራ ተባ ፤ግራ እንደተጋባት ፤
ልጆችሽን አምጭ ፤ ብለው ነዘነዟት ፤
ያው እንደፈራችው ፤
ነጻነቱም ቀረ፤ ልጆቿም ሞቱባት ፤
እንደ በላይ ገዳይ ፤
ለሙት ማስታወሻ ፤
የገደላቸውን ጠበንጃ አስታጠቋት ።
ነጻነት በማያውቅ ፤
በነጻ አውጭ መንደር ፤
ትውልድ የሞተለት፤ ነጻነት ባይመጣም ፤
ከነ መፈክሩ ፤
የወደቀ ክላሽ ፤ ተሸካሚ አያጣም ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
እነዚያ ውርጋጦች ፤
የዛሬ ስንት አመት ፤
ከሙት መጽሃፍ ላይ ፤
በተገኘ ፊደል ፤ በአቢዮት ተጠምቀው ፤
ሰባራ ጠበንጃ ፤
ሰባራ ህልም ጋር ፤ ከቅዠት ጋር ታጥቀው ፤
ነጻ እንድናወጣሽ፤
እሽ በይ ሃራይ በይ፤
እያሉ ሰበኳት ፤አደይን ጨቅጭቀው ።
ሰምታ ማታውቀውን ፤
አይታ ማታውቀውን ፤
መከራሽ መኣት ነው ብለው ዘረዘሩ፤
አታውቂውም እንጅ ፤
በደልሽ ብዙ ነው ብለው ተናገሩ ፤
ከስብከታቸው ጋር ፤
የአዞ ልቅሷቸውን ፤ እንደጉድ አዘሩ ።
የነገሯት ነገር ፤
ከምታውቀው እውነት ፤ ሃቁ ተጣርሶባት ፤
ስትል ፈራ ተባ ፤ግራ እንደተጋባት ፤
ልጆችሽን አምጭ ፤ ብለው ነዘነዟት ፤
ያው እንደፈራችው ፤
ነጻነቱም ቀረ፤ ልጆቿም ሞቱባት ፤
እንደ በላይ ገዳይ ፤
ለሙት ማስታወሻ ፤
የገደላቸውን ጠበንጃ አስታጠቋት ።
ነጻነት በማያውቅ ፤
በነጻ አውጭ መንደር ፤
ትውልድ የሞተለት፤ ነጻነት ባይመጣም ፤
ከነ መፈክሩ ፤
የወደቀ ክላሽ ፤ ተሸካሚ አያጣም ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
ስድ ፎቶዎችሽ
ከፌስብክ መስኮት ላይ
ተለጠፉ አሉ
ያዪት ወንዶች ሁሉ
በምናብ ሊዳሩሽ
ፎቶሽን ባውራ ጣት
like ያረጋሉ።
.ተፈጥሮን አድናቂ
ሁሉም ይመስላሉ
.
. እኔ ግን ገልጣለው
የ post አልበምሽን
ተመስጬ አያለው
ገልጣለው ገልጣለው
ደሞ ባንንና
ምን ነካት እላለው
.
.
ዝሞ በል! ፋራ እያለ
ሲጋጨኝ ስሜቴ
ደሞ ያባንነኛል
ከጨዋ እኔነቴ።
.
ደግሜ ገልጣለው
ባለጌ ፎቶሽን
ጡትሽን ጠግቤ
ስፈልግ ጭንሽን።
ጡትሽም ሲጣራ
ጭንሽም ሲጣራ
ቂ' 'ም ሲጣራ
ዳሌሽም ሲጣራ
የት አባቱ ይሂድ
ቦቅቧቃ ወንድነቴ
ተጨነቀ ፈራ!
አዬ ካሜራ man
ወይ selfie እራቁት
ከእርቃን አልበም ውስጥ
ለካ እንዲ ከባድ ነው
ሰው ፈልጎ ማግኘት
ለካ እንዲህ ከባድ ነው
ራስ ፈልጎ ማግኘት
.
አምላከኛ ጭቃ
በፎቶ እያማረ
ሴቱ ጨርቁን ጣለ
ወንዱ ደጅ አደረ
.
.
ወይ ሶሻል ሚድያ
አዬ ቴክኖሎጂ
ቀን ሰርቶ የደከመው
ይረፍበት እንጂ
.
.
ሀበሻ ስለጡኑ
ፈረንጅ የቀደመ
ቁጭ ብሎ ያነጋል
ገላ እየተመኘ
እርቃን እየሳመ።
ሀበሺት ዘመናይ
ካለም የዘመነች
ለነፃ ገበያ
ገላ ታቀርባለች
በselfie ካሜራ
ፎቶ ትነሳለች።
comment ክፈሏት
like ክፈሏት
የፌስቡክ ዋጋዋን
የተተመነላት።
.
.
.
እንቺም ምርት አቅርቢ
ሰልፊውን ቀጭ አርጊው
በ like ሚተመን
በ comment ሚተመን
facebook ገበያ ነው።
ዮ 20/03/11
@getem
@getem
@gebriel_19
ከፌስብክ መስኮት ላይ
ተለጠፉ አሉ
ያዪት ወንዶች ሁሉ
በምናብ ሊዳሩሽ
ፎቶሽን ባውራ ጣት
like ያረጋሉ።
.ተፈጥሮን አድናቂ
ሁሉም ይመስላሉ
.
. እኔ ግን ገልጣለው
የ post አልበምሽን
ተመስጬ አያለው
ገልጣለው ገልጣለው
ደሞ ባንንና
ምን ነካት እላለው
.
.
ዝሞ በል! ፋራ እያለ
ሲጋጨኝ ስሜቴ
ደሞ ያባንነኛል
ከጨዋ እኔነቴ።
.
ደግሜ ገልጣለው
ባለጌ ፎቶሽን
ጡትሽን ጠግቤ
ስፈልግ ጭንሽን።
ጡትሽም ሲጣራ
ጭንሽም ሲጣራ
ቂ' 'ም ሲጣራ
ዳሌሽም ሲጣራ
የት አባቱ ይሂድ
ቦቅቧቃ ወንድነቴ
ተጨነቀ ፈራ!
አዬ ካሜራ man
ወይ selfie እራቁት
ከእርቃን አልበም ውስጥ
ለካ እንዲ ከባድ ነው
ሰው ፈልጎ ማግኘት
ለካ እንዲህ ከባድ ነው
ራስ ፈልጎ ማግኘት
.
አምላከኛ ጭቃ
በፎቶ እያማረ
ሴቱ ጨርቁን ጣለ
ወንዱ ደጅ አደረ
.
.
ወይ ሶሻል ሚድያ
አዬ ቴክኖሎጂ
ቀን ሰርቶ የደከመው
ይረፍበት እንጂ
.
.
ሀበሻ ስለጡኑ
ፈረንጅ የቀደመ
ቁጭ ብሎ ያነጋል
ገላ እየተመኘ
እርቃን እየሳመ።
ሀበሺት ዘመናይ
ካለም የዘመነች
ለነፃ ገበያ
ገላ ታቀርባለች
በselfie ካሜራ
ፎቶ ትነሳለች።
comment ክፈሏት
like ክፈሏት
የፌስቡክ ዋጋዋን
የተተመነላት።
.
.
.
እንቺም ምርት አቅርቢ
ሰልፊውን ቀጭ አርጊው
በ like ሚተመን
በ comment ሚተመን
facebook ገበያ ነው።
ዮ 20/03/11
@getem
@getem
@gebriel_19