አዲስ አድማስ !!
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!! የመደመርና የፍቅር የኪነ ጥበብ ምሽት!!
ነገ#💚
ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም በብሔራዊ ቴያትር ከቀኑ 11 ሰዓት እስከ ምሽት 2 ሰዓት በመደመር፣በይቅርታ፣በአንድነት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ግጥሞች፣ወጎች፣ዲስኩሮች፣........ይቀርቡበታል!
የስነፅሁፍ አቅራቢዎች
* ገጣሚ ነብይ መኮንን
*ገጣሚና የሥነልሳን ምሁር ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
*ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ
*የፍልስፍና ምሁር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
*ሰዓሊ፣ቀረፂ ገጣሚ በቀለ መኮንን ❤️
*ደራሲና ሀያሲ አለማየሁ ገላጋይ
*ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ
የመድረኩ አጋፋሪ:- ተዋናይና፣ገጣሚ ፈለቀ አበበ
የምትችሉ ሰዎች ይህን ከባድ ሚዛን የሆኑ የጥበብ ሰዎች የሚገማቸሩበት የኪነጥበብ ምሽት ብትታደሙ እና በብዙ አትርፋቹ ብትመለሱ ምኞቴ ነው......
በጣም የምወደው በተለይ ደሞ በአንድ ድንቅ ግጥሙ ያስደመመኝን #በቀለ መኮንን ( ቼ በለው ) በሚለው ግጥሙ ያወኩትን ሰው ለማየት ጎጉቻለው እናም እታደማለሁኝ ......እናተም እንዳትቀሩ.....!!
---------------------------
ቼ በለው
ሕይወት ጎዳናው ገፁ ሲለወጥ
በጭነት ታክቶ ጀርባው ሲመለጥ
የእንቅፋት አፅሙ ቋጥኙ ሲገጥ
ሸክም ዘንቦበት ትቢያው ሲላቁጥ
ሲሆን ድጥ በድጥ
ሾህ ጭቃ ቅይጥ
ልብህ አይደንግጥ፡፡
በምኞት ቅዠት በስጋት ርዶ
አይፍረስ ግንቡ ወኔህ ተንዶ
ከቆመው ቆመህ ከንፈር ከመምጠጥ
በተስፋ ፈረስ በልጓም ሸምጥጥ፡፡
አያረጅ የለም አይለዋወጥ
ነገን ተማምነህ በመጓዝ ቁረጥ...
ከሩቅ አልመህ ቅርብ አትርመጥመጥ
ሰግተህ ከምትቆይ ስትጋልብ ፍረጥ፡፡
ሰዓሊ ቀራፂ፡ በቀለ መኮንን
ሰላም እደሩልኝ!!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!! የመደመርና የፍቅር የኪነ ጥበብ ምሽት!!
ነገ#💚
ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም በብሔራዊ ቴያትር ከቀኑ 11 ሰዓት እስከ ምሽት 2 ሰዓት በመደመር፣በይቅርታ፣በአንድነት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ግጥሞች፣ወጎች፣ዲስኩሮች፣........ይቀርቡበታል!
የስነፅሁፍ አቅራቢዎች
* ገጣሚ ነብይ መኮንን
*ገጣሚና የሥነልሳን ምሁር ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
*ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ
*የፍልስፍና ምሁር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
*ሰዓሊ፣ቀረፂ ገጣሚ በቀለ መኮንን ❤️
*ደራሲና ሀያሲ አለማየሁ ገላጋይ
*ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ
የመድረኩ አጋፋሪ:- ተዋናይና፣ገጣሚ ፈለቀ አበበ
የምትችሉ ሰዎች ይህን ከባድ ሚዛን የሆኑ የጥበብ ሰዎች የሚገማቸሩበት የኪነጥበብ ምሽት ብትታደሙ እና በብዙ አትርፋቹ ብትመለሱ ምኞቴ ነው......
በጣም የምወደው በተለይ ደሞ በአንድ ድንቅ ግጥሙ ያስደመመኝን #በቀለ መኮንን ( ቼ በለው ) በሚለው ግጥሙ ያወኩትን ሰው ለማየት ጎጉቻለው እናም እታደማለሁኝ ......እናተም እንዳትቀሩ.....!!
---------------------------
ቼ በለው
ሕይወት ጎዳናው ገፁ ሲለወጥ
በጭነት ታክቶ ጀርባው ሲመለጥ
የእንቅፋት አፅሙ ቋጥኙ ሲገጥ
ሸክም ዘንቦበት ትቢያው ሲላቁጥ
ሲሆን ድጥ በድጥ
ሾህ ጭቃ ቅይጥ
ልብህ አይደንግጥ፡፡
በምኞት ቅዠት በስጋት ርዶ
አይፍረስ ግንቡ ወኔህ ተንዶ
ከቆመው ቆመህ ከንፈር ከመምጠጥ
በተስፋ ፈረስ በልጓም ሸምጥጥ፡፡
አያረጅ የለም አይለዋወጥ
ነገን ተማምነህ በመጓዝ ቁረጥ...
ከሩቅ አልመህ ቅርብ አትርመጥመጥ
ሰግተህ ከምትቆይ ስትጋልብ ፍረጥ፡፡
ሰዓሊ ቀራፂ፡ በቀለ መኮንን
ሰላም እደሩልኝ!!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
እጠብቅሀለሁ!!!!
ልክ እንደ ጤዛዋ
ጠዋት እንዳየሁዋት፣
ማታ እንደማልደግማት፣
እንደስዋ ሆነብኝ ያንተ ህይወት።
ለራሥህ ሳትኖር እኛን እኛን እያልክ፣
ነገን በእኛ ላይ ተስፋ እያደረክ፣
ሩቅ ተመኝተህ ቅርብ ግን አደርክ።
አባትነት ረቂቅ ትርጉሙ ብዙ ነው፣
ቀርቦ ላላየው በደንብ የማይገባው።
እውነት ግን አልፈሀል???
ከምር ተኝተሀል????
እኔ ግን አላምንም ያለህ ይመስለኛል፣
ድምፅህ በጆሮዬ በደንብ ይሰማኛል።
"አቤት" ብዬሀለሁ መልስ እየጠበኩ ነው፣
"እህ"ብዬ ልሥማህ ምን ልትለኝ ነው።
.
.
.
.
ጠበኩህ ጠበኩህ አሁንም ጠበኩህ..
መልሥ ግን የለም ዝም ፀጥ ብለሀል፣
እውነት ነው እንዴ ከምር ተኝተሀል????
አይመስለኝም እኔ ቀልድ ጀምረሀል፣
ቀልድ ቢሆን እንኩዋን ይህ ባንተ ያስጠላል።
ስለዚህ ተነሳ ድምፅህን አሰማኝ፣
መልስ እየጠበኩ ነው ባክህ ተናገረኝ።
.
.
.
ዝምታህ ያስፈራል በጣም ይጨንቃል፣
አልነሳም ብለህ በዛው ተኝተሀል።
ተመችቶሀል ወይ ሀገሩስ እንዴት ነው፣
መቼም ጥሩ ቢሆን ነው ከኛ ያስበለጥከው።
እኔ ግን......
እኔ ግን እጠብቅሀለሁ ሞትህ ቀልድ
ስለሆነ፣
ትመለሳለህ ብሎ ልቤ ስላመነ።
የሆነ ሩቅ ቦታ ለፊልድ እንደወጣህ፣
በውል ባላቀውም ዳግም መምጫህን፣
እጠብቅሀለሁ ልቤን እያሞኘሁ፣
በር በርህን በአይኔ እየቃኘሁ።።።።
19-5-2011
ገጣሚ ፅዮን ተፈራ
@getem
@getem
@gebriel_19
ልክ እንደ ጤዛዋ
ጠዋት እንዳየሁዋት፣
ማታ እንደማልደግማት፣
እንደስዋ ሆነብኝ ያንተ ህይወት።
ለራሥህ ሳትኖር እኛን እኛን እያልክ፣
ነገን በእኛ ላይ ተስፋ እያደረክ፣
ሩቅ ተመኝተህ ቅርብ ግን አደርክ።
አባትነት ረቂቅ ትርጉሙ ብዙ ነው፣
ቀርቦ ላላየው በደንብ የማይገባው።
እውነት ግን አልፈሀል???
ከምር ተኝተሀል????
እኔ ግን አላምንም ያለህ ይመስለኛል፣
ድምፅህ በጆሮዬ በደንብ ይሰማኛል።
"አቤት" ብዬሀለሁ መልስ እየጠበኩ ነው፣
"እህ"ብዬ ልሥማህ ምን ልትለኝ ነው።
.
.
.
.
ጠበኩህ ጠበኩህ አሁንም ጠበኩህ..
መልሥ ግን የለም ዝም ፀጥ ብለሀል፣
እውነት ነው እንዴ ከምር ተኝተሀል????
አይመስለኝም እኔ ቀልድ ጀምረሀል፣
ቀልድ ቢሆን እንኩዋን ይህ ባንተ ያስጠላል።
ስለዚህ ተነሳ ድምፅህን አሰማኝ፣
መልስ እየጠበኩ ነው ባክህ ተናገረኝ።
.
.
.
ዝምታህ ያስፈራል በጣም ይጨንቃል፣
አልነሳም ብለህ በዛው ተኝተሀል።
ተመችቶሀል ወይ ሀገሩስ እንዴት ነው፣
መቼም ጥሩ ቢሆን ነው ከኛ ያስበለጥከው።
እኔ ግን......
እኔ ግን እጠብቅሀለሁ ሞትህ ቀልድ
ስለሆነ፣
ትመለሳለህ ብሎ ልቤ ስላመነ።
የሆነ ሩቅ ቦታ ለፊልድ እንደወጣህ፣
በውል ባላቀውም ዳግም መምጫህን፣
እጠብቅሀለሁ ልቤን እያሞኘሁ፣
በር በርህን በአይኔ እየቃኘሁ።።።።
19-5-2011
ገጣሚ ፅዮን ተፈራ
@getem
@getem
@gebriel_19
^^^^^^ሰላም ነህ አትበይኝ^^^^^^
=====================
ሰላምታሽ ካፍሽ ቃል ሰላም እያለ ሲወጣ!
ከከንፈሮችሽ መንቀሳቀስ ልቤን እያስደነገጠ ሲወርድ ሲወጣ! ተይ ተይ ውዴ ሰላም አትበይኝ!
የድሮ ትዝብቴን ያመጣው መሰለኝ!
ከሚገርምሽ ውዴ የፍቅርሽ ነበልባል እየመጣ በህልሜ!
ይሄዳል ከሚዞረው አካል ሰውነቴ ደሜ!
ተይ ሰላም አትበይኝ
ትዝ ይልሻል ውዴ የፍቅራች ጣዕም
ቤት አይበቃም ነበር!
አሁን ግን ወደ ወትሮ በታሪክ ሆኖ
በቀረ ግዜ ነበር!
አውቃለው መመለስ ባይችሉም በነዚያ ቀናቶች!
አሁን ግን አልፈዋል በሄደው ለሊቶች!
እና ምልሽ ውዴ
በፍቅርሽ አጥምቀሽ ከሄድሽ በኅላ!
ዛሬ ግን መተሽ ሰላም ነህ ስትይኝ ዞርኩኝ ወደኅላ!
ያኔ ድሮ ድሮ ፍቅር መስጠት ነው ብለሽ አልነበረ!
ታድያ ምነው የዛሬን ግዜ እንደዛ እንዳልነበረ!
እና ምልሽ
ሰላም ነህ ስትይኝ እንዴት ነኝ ልበልሽ!
እንደዚው ነኝ ብቃ አንቺ ግን እንዴት ነሽ!
💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️️
@getem
@imperial_2001
@imperial_2001
=====================
ሰላምታሽ ካፍሽ ቃል ሰላም እያለ ሲወጣ!
ከከንፈሮችሽ መንቀሳቀስ ልቤን እያስደነገጠ ሲወርድ ሲወጣ! ተይ ተይ ውዴ ሰላም አትበይኝ!
የድሮ ትዝብቴን ያመጣው መሰለኝ!
ከሚገርምሽ ውዴ የፍቅርሽ ነበልባል እየመጣ በህልሜ!
ይሄዳል ከሚዞረው አካል ሰውነቴ ደሜ!
ተይ ሰላም አትበይኝ
ትዝ ይልሻል ውዴ የፍቅራች ጣዕም
ቤት አይበቃም ነበር!
አሁን ግን ወደ ወትሮ በታሪክ ሆኖ
በቀረ ግዜ ነበር!
አውቃለው መመለስ ባይችሉም በነዚያ ቀናቶች!
አሁን ግን አልፈዋል በሄደው ለሊቶች!
እና ምልሽ ውዴ
በፍቅርሽ አጥምቀሽ ከሄድሽ በኅላ!
ዛሬ ግን መተሽ ሰላም ነህ ስትይኝ ዞርኩኝ ወደኅላ!
ያኔ ድሮ ድሮ ፍቅር መስጠት ነው ብለሽ አልነበረ!
ታድያ ምነው የዛሬን ግዜ እንደዛ እንዳልነበረ!
እና ምልሽ
ሰላም ነህ ስትይኝ እንዴት ነኝ ልበልሽ!
እንደዚው ነኝ ብቃ አንቺ ግን እንዴት ነሽ!
💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️️
@getem
@imperial_2001
@imperial_2001
ጣይቱ ነደደች!!!!!!!!
ብርሃን ዘ ኢትዮጲያ፣የሴት ዘመናይ፣
ጣይቱ መለኛ፣ ጣይቱ ጠሀይ።
ያበሻ ባለሟል፣ ያድዋ ዘማች፣
ጣይቱ ነደደች፣ ዛሬም አበራች።
ለምን ያገሬ ሰው፣ እንዲህ ይሸበራል፣
ጠሀይ ማንደድ እንጅ፣መቼ ይቃጠላል።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
ብርሃን ዘ ኢትዮጲያ፣የሴት ዘመናይ፣
ጣይቱ መለኛ፣ ጣይቱ ጠሀይ።
ያበሻ ባለሟል፣ ያድዋ ዘማች፣
ጣይቱ ነደደች፣ ዛሬም አበራች።
ለምን ያገሬ ሰው፣ እንዲህ ይሸበራል፣
ጠሀይ ማንደድ እንጅ፣መቼ ይቃጠላል።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
👍1
~~~ፍለጋ~~~(ሳሙኤል አዳነ)
ከቆምኩበት መሬት
ወደታች ወርጄ ፣
ከማላውቀው ሀገር
ሩቅ መንገድ ሄጄ ፣
ጆሮየ እየሰማ
ብዙ እየተናገርኩ ፣
መጽሀፍ እያነበብኩ ፣
በቅዠት አለም ውስጥ
ፍለጋየ አልቀረ ፣
እንቅልፍ ያጣሁበት
ዘመን ተቆጠረ ።
አንች እውነት የት አለሽ ?
ዱካሽ ወዴት አለ ?
ምነው ለፈለገሽ
ፍርድሽ ተጓደለ።
09/12/2010
3፡30pm
ሸንኮራ
@getem
@getem
@gebriel_19
ከቆምኩበት መሬት
ወደታች ወርጄ ፣
ከማላውቀው ሀገር
ሩቅ መንገድ ሄጄ ፣
ጆሮየ እየሰማ
ብዙ እየተናገርኩ ፣
መጽሀፍ እያነበብኩ ፣
በቅዠት አለም ውስጥ
ፍለጋየ አልቀረ ፣
እንቅልፍ ያጣሁበት
ዘመን ተቆጠረ ።
አንች እውነት የት አለሽ ?
ዱካሽ ወዴት አለ ?
ምነው ለፈለገሽ
ፍርድሽ ተጓደለ።
09/12/2010
3፡30pm
ሸንኮራ
@getem
@getem
@gebriel_19
👍2
ባቲ ገበያው ዳር ፤
በቀርሳ ብርቱካን ፤
በገርፋ መንደሪን ፤ ተጨምቃ ያደገች ፤
በአውሳ ልጆች ጊሌ ፤
ከጀግና ጋር ውላ ፤ ጀግና ጋር ያደረች ፤
አሳ ባራ ጊቴ ፤
አውቶብስ የሚቴ ፤
በሚል ሃያል ዜማ የተሽሞነሞነች
ባቲ ገበያው ዳር ፤
እንደ ጆፌ ጥላ ፤ ዋርካ የነበረች ፤
ሁሉ የሚዋያት ፤
የባቲ ከራማ አንዲት ሴት ነበረች ።
ሰኞ ገበያው ቀን ፤
ባቲ መቃኛው ላይ ፤
ካለችው ግራር ስር ፤ ጨፌዋን ጎዝጉዛ ፤
ከአፋር ልጆች ወተት ፤
ከአርጎባ ልጅ ቅቤ ፤
ከአሰብ ልጆች ፍቅር ፤ መውደድ የምትገዛ ።
ከገራገር ጥርሷ ፤
ከታማኝ ከንፈሯ ፤
ከረጠበው ቀልቧ ፤
ከቃሏ በስተቀር ፤
የምትከፍለው ገንዘብ ፤ሽልንግ ያልነበራት ፤
ባቴየ መሆኗን ፤
ስንቱ በአሻጋሪ በሩቅ እየለያት ፤
መቼም በአማኑ ቀን ፤
መውደዷን እያየ ፤
አገር ሙሉ ፍቅር ፤ ስንቱ ነየተላት ።
ገንዘብ የማይገዛው ፤
ባውንድ የማይተካው ፤
ሃገር ሙሉ ፍቅር ፤
እንደ ዋርካ ጥላ ፤ ሰብስባ ያደረች ፤
ፈልጉልኝ እስቲ ፤
ባቲ አጣሪ ገንዳ ፤ አንዲት ሴት ነበረች ።
ኧረ ባቲ ባቲ ፤
ባቲ አጣሪ ገንዳ ፣ ቀርሳ ታቹን ቡርቃ ፣
ንግግሯ አዱርስ ነው ፤
እንደ አበጋር እጣን ፤
ቡልቅልቅ እያለ ላገር የሚበቃ ፤
ስንቱን መንገደኛ ፤
ፍዝ አርጋ አስቀረችው ፤
በከዳሚ ጥርሷ ፤ ከም ከም ብላ ስቃ ።
ባቲና ሸጋ ልጅ ፤
ሸጋና በረሃ ፤በምን ተዋወቁ ፤
ሲወደዱ ጊዜ ፤
በፍቅር አስክረው ፤
ሃቅል እየነሱ ፤ ልብስ እያስወለቁ ።
ከበረሃው ግርጌ ፤
ከወበቁ መሃል ፤ የቆሞምኩት በእርጋታ ፤
በንዳዱ መሃል ፤
የምንጎማለለው ልቤ ሳይረታ ፤
ጉልበቴ የጠናው፤
በቀርሳ ልጅ ሳቅ ነው፤ በባቲ ጨዋታ ።
በዚያ ግለት ጠሃይ ፤
በዚያ ወፍራም ነፋስ ፤
በዚያ ደረቅ ወጀብ ፤ በረሃ በዋጠው ፤
ሃየ በል እያልኩኝ የምሸራገጠው ፤
አይደለም በቅስሜ በገዛ ጉልበቴ ፤
ተዘይሬልሽ ነው ፤
ስትይኝ አህሪቡ ስትይኝ በሞቴ ።
ባቲ ገበያው ላይ ፤
ወሎ መጀን ብሎ ፤ አበጋር ተጣራ ፤
ሁሉም አሚን አለ ፤
ወሎ ድብልቁ ፤ የሁሉም እንጀራ ።
ከእንጀራው መሃከል ፤ እንጎቻ ደርሳኝ ፤
እኔም በተራየ ፤
ወሎ መጀን ብየ እሷን ጎረስኩኝ ።
የግጦሽ ሳርና ፤ የወሎ መሬት ፤
አፈሩ ብዙ ነው፤ የተሰራበት ፤
የኛ እንጅ ቅብቅቡ የኔ ማይሉት ፤
ባንተው መጀን ብላኝ ፤
ሁለት ጋሻ መሬት ለሷም ደረሳት ።
ከጥውልግ ጉንጨ ላይ ፤
ደረቅ ከንፈሬ ላይ ፤
በባቲ ብርቱካን ፤
በቀርሳ መንደሪን ፤ ሳልሳም ቀርቼ ጦም አድሬ ቢሆን ፤
የምወድሽዋ ፤
ጠሃይዋም አትበርድም ፤ባቴ ባቲም አይሆን ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
በቀርሳ ብርቱካን ፤
በገርፋ መንደሪን ፤ ተጨምቃ ያደገች ፤
በአውሳ ልጆች ጊሌ ፤
ከጀግና ጋር ውላ ፤ ጀግና ጋር ያደረች ፤
አሳ ባራ ጊቴ ፤
አውቶብስ የሚቴ ፤
በሚል ሃያል ዜማ የተሽሞነሞነች
ባቲ ገበያው ዳር ፤
እንደ ጆፌ ጥላ ፤ ዋርካ የነበረች ፤
ሁሉ የሚዋያት ፤
የባቲ ከራማ አንዲት ሴት ነበረች ።
ሰኞ ገበያው ቀን ፤
ባቲ መቃኛው ላይ ፤
ካለችው ግራር ስር ፤ ጨፌዋን ጎዝጉዛ ፤
ከአፋር ልጆች ወተት ፤
ከአርጎባ ልጅ ቅቤ ፤
ከአሰብ ልጆች ፍቅር ፤ መውደድ የምትገዛ ።
ከገራገር ጥርሷ ፤
ከታማኝ ከንፈሯ ፤
ከረጠበው ቀልቧ ፤
ከቃሏ በስተቀር ፤
የምትከፍለው ገንዘብ ፤ሽልንግ ያልነበራት ፤
ባቴየ መሆኗን ፤
ስንቱ በአሻጋሪ በሩቅ እየለያት ፤
መቼም በአማኑ ቀን ፤
መውደዷን እያየ ፤
አገር ሙሉ ፍቅር ፤ ስንቱ ነየተላት ።
ገንዘብ የማይገዛው ፤
ባውንድ የማይተካው ፤
ሃገር ሙሉ ፍቅር ፤
እንደ ዋርካ ጥላ ፤ ሰብስባ ያደረች ፤
ፈልጉልኝ እስቲ ፤
ባቲ አጣሪ ገንዳ ፤ አንዲት ሴት ነበረች ።
ኧረ ባቲ ባቲ ፤
ባቲ አጣሪ ገንዳ ፣ ቀርሳ ታቹን ቡርቃ ፣
ንግግሯ አዱርስ ነው ፤
እንደ አበጋር እጣን ፤
ቡልቅልቅ እያለ ላገር የሚበቃ ፤
ስንቱን መንገደኛ ፤
ፍዝ አርጋ አስቀረችው ፤
በከዳሚ ጥርሷ ፤ ከም ከም ብላ ስቃ ።
ባቲና ሸጋ ልጅ ፤
ሸጋና በረሃ ፤በምን ተዋወቁ ፤
ሲወደዱ ጊዜ ፤
በፍቅር አስክረው ፤
ሃቅል እየነሱ ፤ ልብስ እያስወለቁ ።
ከበረሃው ግርጌ ፤
ከወበቁ መሃል ፤ የቆሞምኩት በእርጋታ ፤
በንዳዱ መሃል ፤
የምንጎማለለው ልቤ ሳይረታ ፤
ጉልበቴ የጠናው፤
በቀርሳ ልጅ ሳቅ ነው፤ በባቲ ጨዋታ ።
በዚያ ግለት ጠሃይ ፤
በዚያ ወፍራም ነፋስ ፤
በዚያ ደረቅ ወጀብ ፤ በረሃ በዋጠው ፤
ሃየ በል እያልኩኝ የምሸራገጠው ፤
አይደለም በቅስሜ በገዛ ጉልበቴ ፤
ተዘይሬልሽ ነው ፤
ስትይኝ አህሪቡ ስትይኝ በሞቴ ።
ባቲ ገበያው ላይ ፤
ወሎ መጀን ብሎ ፤ አበጋር ተጣራ ፤
ሁሉም አሚን አለ ፤
ወሎ ድብልቁ ፤ የሁሉም እንጀራ ።
ከእንጀራው መሃከል ፤ እንጎቻ ደርሳኝ ፤
እኔም በተራየ ፤
ወሎ መጀን ብየ እሷን ጎረስኩኝ ።
የግጦሽ ሳርና ፤ የወሎ መሬት ፤
አፈሩ ብዙ ነው፤ የተሰራበት ፤
የኛ እንጅ ቅብቅቡ የኔ ማይሉት ፤
ባንተው መጀን ብላኝ ፤
ሁለት ጋሻ መሬት ለሷም ደረሳት ።
ከጥውልግ ጉንጨ ላይ ፤
ደረቅ ከንፈሬ ላይ ፤
በባቲ ብርቱካን ፤
በቀርሳ መንደሪን ፤ ሳልሳም ቀርቼ ጦም አድሬ ቢሆን ፤
የምወድሽዋ ፤
ጠሃይዋም አትበርድም ፤ባቴ ባቲም አይሆን ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
#ስቅታ
ስቅ ባለኝ ቁጥር ውዴ ደስ ይለኛል
ስሜን እያነሳህ ምታወራ ይመስለኛል
አነሳኝ እያልኩኝ ልቤን የማሞኘው
አረሳኝም ብዬ በማሰቤ እኮ ነው
እንጂማ ውዴ...
ትዝ እንዳላልኩህ ቀድሞንስ መች አጣሁት
ያፈቅረኛል ብዬ ፍቅሬን አታለልኩት
መረሳቴን ባይወድ ልቤ ቅር ቢለው ነው
ስቅ ባለኝ ቁጥር የሚለኝ እሱ ነው
እሱ ነው ...እሱ ነው....
ስምሽን ያነሳው ቢወድስ እኮ ነው
ይለኛል ይህ ልቤ....
መረሳቱን መርሳት እጅጉን ቢከብደው።
5-6-2011
#ፅዮን_ተፈራ
@getem
@getem
@gebriel_19
ስቅ ባለኝ ቁጥር ውዴ ደስ ይለኛል
ስሜን እያነሳህ ምታወራ ይመስለኛል
አነሳኝ እያልኩኝ ልቤን የማሞኘው
አረሳኝም ብዬ በማሰቤ እኮ ነው
እንጂማ ውዴ...
ትዝ እንዳላልኩህ ቀድሞንስ መች አጣሁት
ያፈቅረኛል ብዬ ፍቅሬን አታለልኩት
መረሳቴን ባይወድ ልቤ ቅር ቢለው ነው
ስቅ ባለኝ ቁጥር የሚለኝ እሱ ነው
እሱ ነው ...እሱ ነው....
ስምሽን ያነሳው ቢወድስ እኮ ነው
ይለኛል ይህ ልቤ....
መረሳቱን መርሳት እጅጉን ቢከብደው።
5-6-2011
#ፅዮን_ተፈራ
@getem
@getem
@gebriel_19
((በላይ በቀለ ወያ))
ባለፈ አመት ክረምት ፣ ዛሬ አይታረስም
ጀግኖች አይጠሩም ፣ በፈሪዎች ስም፡፡
ጎጥ እና ዘር ማንዘር...
ዛሬ ላይ ቀምቶህ፣ የነፃነትን ጣም
ታሪክ መስራት እንጂ...
ታሪክን በማጉደፍ ፣ ነፃ ባይወጣም
ባርነት ላይ ሆኖ ፣
ነፃነቱን ሚያከብር ፣ ያስቀኛል በጣም!
የጀግና ልጅ ከሆንክ...
አደዋ ከምትል ፣
ዘረኝነትህን ድል አርገህ አትወጣም?
በጠ*ም!
።።።
አደዋ የሰው ድል።
@getem
@getem
@gebriel_19
ባለፈ አመት ክረምት ፣ ዛሬ አይታረስም
ጀግኖች አይጠሩም ፣ በፈሪዎች ስም፡፡
ጎጥ እና ዘር ማንዘር...
ዛሬ ላይ ቀምቶህ፣ የነፃነትን ጣም
ታሪክ መስራት እንጂ...
ታሪክን በማጉደፍ ፣ ነፃ ባይወጣም
ባርነት ላይ ሆኖ ፣
ነፃነቱን ሚያከብር ፣ ያስቀኛል በጣም!
የጀግና ልጅ ከሆንክ...
አደዋ ከምትል ፣
ዘረኝነትህን ድል አርገህ አትወጣም?
በጠ*ም!
።።።
አደዋ የሰው ድል።
@getem
@getem
@gebriel_19
*ቫላንታይንስ ደይ *(ሳሙኤል አዳነ)
ፍቅር ነው...
ስትስቂ አሳስቄሽ፣
ስትሄጅ ናፍቄሽ፣
ስትመጭ መርቄሽ፣
ስትከፊ ደግም የአይኖችሽ እንባ
በልቤ እየገባ፡እኔም አነባለሁ፤
በአንች መታመም ታማሚ እሆናለሁ፡፡
ታሪክ ነው ፣
ድምፅሽን ሣልሰማ ልቤ እየጨነቀው፤
የሞባይል ካርዴ ባንች ነው የሚያልቀው።
አንችን ስወድሽ ቀን ፡እኔን ስለተውኩኝ፤
ጊዜህን ብትይኝ፡ሁሉን ነገር ትቼ ካንችጋራ ሆንኩኝ
ታሪክ ነው፣
አንች ሪሞት ሆነሽ፡እኔ ደሞ ቻናል፤
play pause ስትይኝ ፡የስንቱ መዝናኛ ሚዲያ ሆነናል።
ደሞ ከሰሞኑ...
ሚዲያ የሚሉት መረጃ ማይርቀው፣
የፍቅረኛሞች ቀን ብሎ እያከበረ ልቤን አስጨነቀዉ።
እህህ...
valantines day በእኔው እይታ፤
የሞኞች ዕብደት ነው፤የሞኞች ጨዋታ፤
አድማጭ የሌለበት የስብሰባ ቦታ ።
ለምን ብትይ...
ዛሬ የፍቅር ቀን ነገ የጥላቻ፣
ፍቅርና ውሸት ቀን ቆጠራ ብቻ።
እውነቱን ልንገርሽ፣
ፍቅር በባህሪው ቀን ቆጠራ አያውቅም።
አበባ እያሳየ የሰው ልብ አይሠርቅም።
ዛሬ እያስደሰተ ነገ አያስለቅስም።
እሡን ተይውና
ይሄውልሽ ፍቅሬ
አንች ብጠይኝም እኔ ወድሻለሁ፣
መልሰሽ ከመጣሽ፤
በልቤ ዙፍን ላይ
አስቀምጥሻለሁ።
ቦታ አገኘሁ ብሎ
መጤ ሳያርፍበት፣
ንግስናሽን ይዘሽ
ነይና ተኝበት።
እንደዛ ከሆነ፡፤
ፍቅራችን አይሎ
እውነት እንሆናለን፣
እኔ ባሪያ ሆኘ አንች ደግሞ ንግስት
valantines day ሁሌ እናከብራለን።
*
27/07/08
8:00pm
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
@getem
@getem
@gebriel_19
ፍቅር ነው...
ስትስቂ አሳስቄሽ፣
ስትሄጅ ናፍቄሽ፣
ስትመጭ መርቄሽ፣
ስትከፊ ደግም የአይኖችሽ እንባ
በልቤ እየገባ፡እኔም አነባለሁ፤
በአንች መታመም ታማሚ እሆናለሁ፡፡
ታሪክ ነው ፣
ድምፅሽን ሣልሰማ ልቤ እየጨነቀው፤
የሞባይል ካርዴ ባንች ነው የሚያልቀው።
አንችን ስወድሽ ቀን ፡እኔን ስለተውኩኝ፤
ጊዜህን ብትይኝ፡ሁሉን ነገር ትቼ ካንችጋራ ሆንኩኝ
ታሪክ ነው፣
አንች ሪሞት ሆነሽ፡እኔ ደሞ ቻናል፤
play pause ስትይኝ ፡የስንቱ መዝናኛ ሚዲያ ሆነናል።
ደሞ ከሰሞኑ...
ሚዲያ የሚሉት መረጃ ማይርቀው፣
የፍቅረኛሞች ቀን ብሎ እያከበረ ልቤን አስጨነቀዉ።
እህህ...
valantines day በእኔው እይታ፤
የሞኞች ዕብደት ነው፤የሞኞች ጨዋታ፤
አድማጭ የሌለበት የስብሰባ ቦታ ።
ለምን ብትይ...
ዛሬ የፍቅር ቀን ነገ የጥላቻ፣
ፍቅርና ውሸት ቀን ቆጠራ ብቻ።
እውነቱን ልንገርሽ፣
ፍቅር በባህሪው ቀን ቆጠራ አያውቅም።
አበባ እያሳየ የሰው ልብ አይሠርቅም።
ዛሬ እያስደሰተ ነገ አያስለቅስም።
እሡን ተይውና
ይሄውልሽ ፍቅሬ
አንች ብጠይኝም እኔ ወድሻለሁ፣
መልሰሽ ከመጣሽ፤
በልቤ ዙፍን ላይ
አስቀምጥሻለሁ።
ቦታ አገኘሁ ብሎ
መጤ ሳያርፍበት፣
ንግስናሽን ይዘሽ
ነይና ተኝበት።
እንደዛ ከሆነ፡፤
ፍቅራችን አይሎ
እውነት እንሆናለን፣
እኔ ባሪያ ሆኘ አንች ደግሞ ንግስት
valantines day ሁሌ እናከብራለን።
*
27/07/08
8:00pm
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
@getem
@getem
@gebriel_19
እንኳን አንች ሸጋ፤ የተወለድሽበት ፤
ያን የራያ ግልድም ፤
የፈረንጅ አገር ሰው ፤ ለብሶ ዘነጠበት።
እንኳንስ ላይ ዞባል፤ ታቹን ካላኮርማ፤
ፈረንጅም ዘለቀ ፤
በሸዋየ ቦልጋ ፤በዋጃ ከተማ ፤
ሃየ በል እያለ ፤ ስበር ላለይ ጉማ ።
የትፍትፏ ጥለት ክሩ ቡራቡሬ ፤
ንገሯት ፈረንጇን ፤
እንግሊዝ መናገር ፤ አይችልም ከንፈሬ ፤
ባለ አምስት ጥማድ ፤ ሞጃ ነኝ ባገሬ ፤
ባል የላትም እንደሁ ፤ ጭኔ ላይ ትደልደል እንደምንሽሬ ።
መገን ፈረንጅዋ ፤ አይሳሳም በቤቱ ፤
ኮበሌው ሰላሳ ፣ ሶስት መቶ ነው ሴቱ፤
እንደው ከቶ ጓዴ ፤
በእነዚህ ተከቦ ይነጋል ወይ ሌቱ !???
የኔ አገር መድሃኒት ስሙ ጥቁረ በላ ፤
ምን ይለኛል ዛሬ ከቀዩስ ብበላ ።
ንገሯት ፈረንጅን በምታናግሯት ፤
ቀይነት ነው እንጅ መልክ የለሽም በሏት ፤
አዳ ምናለበት ደገፍገፍ አድርጌ ዛሬን ባጠይማት ።
ማይ ማዩ ቢለበስ ቢደረብ እርቦሽ ፤
አደመቀው እንጅ ሸገነ ገላሽ ፤
ምን ልብሱን ብለብሽው ፤
እንደ ማሬ ጉግሳ ፤
ስበርን አይጠግን ቂጣ ነው ገላሽ ፤
ይልቅ ፈረንጅዋ፤
ቀይ ሰው ክፍሌ ነው ፤
መወክል ይሆናል ፤ ከጎኔ ላርግሽ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
ያን የራያ ግልድም ፤
የፈረንጅ አገር ሰው ፤ ለብሶ ዘነጠበት።
እንኳንስ ላይ ዞባል፤ ታቹን ካላኮርማ፤
ፈረንጅም ዘለቀ ፤
በሸዋየ ቦልጋ ፤በዋጃ ከተማ ፤
ሃየ በል እያለ ፤ ስበር ላለይ ጉማ ።
የትፍትፏ ጥለት ክሩ ቡራቡሬ ፤
ንገሯት ፈረንጇን ፤
እንግሊዝ መናገር ፤ አይችልም ከንፈሬ ፤
ባለ አምስት ጥማድ ፤ ሞጃ ነኝ ባገሬ ፤
ባል የላትም እንደሁ ፤ ጭኔ ላይ ትደልደል እንደምንሽሬ ።
መገን ፈረንጅዋ ፤ አይሳሳም በቤቱ ፤
ኮበሌው ሰላሳ ፣ ሶስት መቶ ነው ሴቱ፤
እንደው ከቶ ጓዴ ፤
በእነዚህ ተከቦ ይነጋል ወይ ሌቱ !???
የኔ አገር መድሃኒት ስሙ ጥቁረ በላ ፤
ምን ይለኛል ዛሬ ከቀዩስ ብበላ ።
ንገሯት ፈረንጅን በምታናግሯት ፤
ቀይነት ነው እንጅ መልክ የለሽም በሏት ፤
አዳ ምናለበት ደገፍገፍ አድርጌ ዛሬን ባጠይማት ።
ማይ ማዩ ቢለበስ ቢደረብ እርቦሽ ፤
አደመቀው እንጅ ሸገነ ገላሽ ፤
ምን ልብሱን ብለብሽው ፤
እንደ ማሬ ጉግሳ ፤
ስበርን አይጠግን ቂጣ ነው ገላሽ ፤
ይልቅ ፈረንጅዋ፤
ቀይ ሰው ክፍሌ ነው ፤
መወክል ይሆናል ፤ ከጎኔ ላርግሽ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
👍1
ንባበ-ሰማይ(ልዑል ሀይሌ)
የርምጃዬ ስድር
ሸንጎ እየገተረኝ፤
በተራመድሁት ልክ
ጥላ እያባረረኝ፤
.
በሮጥኩት ፍጥነት ልክ
ለፍርድ እየታጨው፤
እንዴት እግሬን ልመን
ደረስኩ ደረስኩ ስል ከህልሜ እየተጋጨው፤
.
ይወቀስ የኔ 'ግር
ጠልፎ ሚጥል ራሱን በገዛ አካሄዱ፤
እርምጃ እያመነ
ለመሽቀዳደም ሲል ይጠፋል መንገዱ፤
.
መሬት መሬት መርቶ
በአፅም ላይ ተራምዶ የማይማር መሪ፤
እግር ነው መሠሪ!፤
.
የመንገድ አይደለም
የተጓዥነት ልክ የመድረሻ ዕጣ፤
ቆመው ይደረሳል
በእግር ተተክቶ ጭንቅላት ከመጣ፤
.
ጉዞ ከጀመሩ
ከእግር አስቀድመው ጭንቅላትን መርጠው፤
መድረሻ ቅርብ ነው ያዩታል አሻግረው
ሰማይ ላይ አንጋጥጠው፤
.
አንገት እያቀና
በቅን ፀሎት ምልጃ
ኑሮ እየሰደረ፤
እግርስ ጭንቅላት
ከሰማይ አቅርቦ
በፈጣሪ ፍቃድ ነፍስን ያሳደረ፤
.
እናም ስማ 'ኔ ሆይ!
.
መድረሻህን አይተህ
ለምትነሳት ህልም ለምትነቃት ንጋት፤
መፍቻህን ከሰማይ አንጋጥጠህ ፈልጋት፤
.
መፍቻዋ ከሰማይ
ስትመጣ እንዳትጠፋ፤
ዓይንህን አትንቀል በፀሎትህ ግፋ!፤
.
ግፋ!
.
ልፋ!
.
ፀልይ!...ለምን! እሻ!፤
ከምድር አትፈልገው
ሰማይ መንበር ለምን ያንተን መጨረሻ!፤
.
የመንገድ አይደለም
የተጓዥነት ልክ የመድረሻ ዕጣ፤
ቆመው ይደረሳል
በእግር ተተክቶ ጭንቅላት ከመጣ፤
.
እናም!...ቀና በል!
፳፯-፭-፳፻፲፩ ዓ.ም.
ከምሽቱ 5:12
@getem
@getem
@gebriel_19
የርምጃዬ ስድር
ሸንጎ እየገተረኝ፤
በተራመድሁት ልክ
ጥላ እያባረረኝ፤
.
በሮጥኩት ፍጥነት ልክ
ለፍርድ እየታጨው፤
እንዴት እግሬን ልመን
ደረስኩ ደረስኩ ስል ከህልሜ እየተጋጨው፤
.
ይወቀስ የኔ 'ግር
ጠልፎ ሚጥል ራሱን በገዛ አካሄዱ፤
እርምጃ እያመነ
ለመሽቀዳደም ሲል ይጠፋል መንገዱ፤
.
መሬት መሬት መርቶ
በአፅም ላይ ተራምዶ የማይማር መሪ፤
እግር ነው መሠሪ!፤
.
የመንገድ አይደለም
የተጓዥነት ልክ የመድረሻ ዕጣ፤
ቆመው ይደረሳል
በእግር ተተክቶ ጭንቅላት ከመጣ፤
.
ጉዞ ከጀመሩ
ከእግር አስቀድመው ጭንቅላትን መርጠው፤
መድረሻ ቅርብ ነው ያዩታል አሻግረው
ሰማይ ላይ አንጋጥጠው፤
.
አንገት እያቀና
በቅን ፀሎት ምልጃ
ኑሮ እየሰደረ፤
እግርስ ጭንቅላት
ከሰማይ አቅርቦ
በፈጣሪ ፍቃድ ነፍስን ያሳደረ፤
.
እናም ስማ 'ኔ ሆይ!
.
መድረሻህን አይተህ
ለምትነሳት ህልም ለምትነቃት ንጋት፤
መፍቻህን ከሰማይ አንጋጥጠህ ፈልጋት፤
.
መፍቻዋ ከሰማይ
ስትመጣ እንዳትጠፋ፤
ዓይንህን አትንቀል በፀሎትህ ግፋ!፤
.
ግፋ!
.
ልፋ!
.
ፀልይ!...ለምን! እሻ!፤
ከምድር አትፈልገው
ሰማይ መንበር ለምን ያንተን መጨረሻ!፤
.
የመንገድ አይደለም
የተጓዥነት ልክ የመድረሻ ዕጣ፤
ቆመው ይደረሳል
በእግር ተተክቶ ጭንቅላት ከመጣ፤
.
እናም!...ቀና በል!
፳፯-፭-፳፻፲፩ ዓ.ም.
ከምሽቱ 5:12
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ለቫላንታይን ቀን አክባሪ ሴቶች የተገጠመ ግጥም።
======"============================ ባል
አታይም ( ባላታይም)!!! VS Valantine!!!!!
ካምና ከዘንድሮ፣ ታገባለች ሲሉ፣
እናቷ በምኞት፣ጠላ እየዘለሉ፣
አባቷም በምኞት፣ፍሪዳ እየጣሉ፣
አንድኛውን ጎበዝ፣ ባንዱ እያናጠሩ፣
ይኸው ስንት ዘመን፣
እሷም አላገባች፣ እነሱም አልዳሩ።
በስንት ሺህ ፓሪ ፣ሺህ ጎበዝ ሲስማት፣
አንዱ ያዝኩኝ ብሎ፣ሌላው ሲቀበላት፣
ከንፈር ሳሚው በዝቶ፣ ፈልቶ በሽቅድድም፣
እንደነካት ቀረ፣
አምና የሳመችው፣ዘንድሮን ላይደግም።
ሁሌም ባመት ባመት፣አዲስ ነው ድግሷ፣
ባለተራ ወዳጅ፣ ቀይ ጃኖ አልብሳ፣
እሷ ምን አለባት፣
ለተራበው ቀልቧ፣ጌት ዳውን ነው ምሷ፣
ይኸው በአመት በአመት፣
ቫላንታይን እንጅ፣ባል አታይም እሷ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ቃል መፍቻ፤፤፤ """""ምስ""""ማለት የሱስ ማስታገሻ ፣
የአመል ማብረጃ ማለት ነው።
@balmbaras
@getem
@getem
======"============================ ባል
አታይም ( ባላታይም)!!! VS Valantine!!!!!
ካምና ከዘንድሮ፣ ታገባለች ሲሉ፣
እናቷ በምኞት፣ጠላ እየዘለሉ፣
አባቷም በምኞት፣ፍሪዳ እየጣሉ፣
አንድኛውን ጎበዝ፣ ባንዱ እያናጠሩ፣
ይኸው ስንት ዘመን፣
እሷም አላገባች፣ እነሱም አልዳሩ።
በስንት ሺህ ፓሪ ፣ሺህ ጎበዝ ሲስማት፣
አንዱ ያዝኩኝ ብሎ፣ሌላው ሲቀበላት፣
ከንፈር ሳሚው በዝቶ፣ ፈልቶ በሽቅድድም፣
እንደነካት ቀረ፣
አምና የሳመችው፣ዘንድሮን ላይደግም።
ሁሌም ባመት ባመት፣አዲስ ነው ድግሷ፣
ባለተራ ወዳጅ፣ ቀይ ጃኖ አልብሳ፣
እሷ ምን አለባት፣
ለተራበው ቀልቧ፣ጌት ዳውን ነው ምሷ፣
ይኸው በአመት በአመት፣
ቫላንታይን እንጅ፣ባል አታይም እሷ።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤️
ቃል መፍቻ፤፤፤ """""ምስ""""ማለት የሱስ ማስታገሻ ፣
የአመል ማብረጃ ማለት ነው።
@balmbaras
@getem
@getem
****እኛ****
አባ ይናገሩ
የኛ ጀግና አያቶች
እንደምን አድርገው
ነብስ እየገበሩ
ድንበር አስከብረው
በገዛ እጥንታቸው
ሀገር እንዳጠሩ?
-አርበኛው አባታችን-
ልጄ እንዴት ልናገር?
ያ ታሪክ የሚያምረው
በፍቅራችን ቋንቋ
በልባችን ጆሮ
ብናደምጠው ነበር!
አያት ደም አፍሶ አባት አውርሷቸው
መሬት ላጣላቸው ለወንድምማማቾች
መስመር አበጅተው መኖር ለጀመሩ
............የአንድ ሀገር ህዝቦች
ልባቸው ተስቦ ዘር እየቆጠሩ
መሬት እያሰሉ ችግር ለደመሩ
ክብሯ ሳይነካ ክብሯን ከደፈሩ
የጠላትን ቀመር ለራስ ሲቀምሩ
እንዴትስ ይጥማል
እንደምን ይነገር
ጀግነት ሲወራ ጀግነት ሲነገር
የድል ታሪክ ሲባል አድዋ ሚከበር
ሀገሩን የሚወድ ተከባብሮ ሚኖር
ትውልድ ቢኖር ነበር!
ሀና ሀይሉ
የካቲት 2011ዓ.ም
ክብር መከበረን ለሰጡን ላስከበሩን ጀግኖቻችን!
ፎቶ ዳዊት ጥበቡ
@getem
@getem
@HanaHailu
አባ ይናገሩ
የኛ ጀግና አያቶች
እንደምን አድርገው
ነብስ እየገበሩ
ድንበር አስከብረው
በገዛ እጥንታቸው
ሀገር እንዳጠሩ?
-አርበኛው አባታችን-
ልጄ እንዴት ልናገር?
ያ ታሪክ የሚያምረው
በፍቅራችን ቋንቋ
በልባችን ጆሮ
ብናደምጠው ነበር!
አያት ደም አፍሶ አባት አውርሷቸው
መሬት ላጣላቸው ለወንድምማማቾች
መስመር አበጅተው መኖር ለጀመሩ
............የአንድ ሀገር ህዝቦች
ልባቸው ተስቦ ዘር እየቆጠሩ
መሬት እያሰሉ ችግር ለደመሩ
ክብሯ ሳይነካ ክብሯን ከደፈሩ
የጠላትን ቀመር ለራስ ሲቀምሩ
እንዴትስ ይጥማል
እንደምን ይነገር
ጀግነት ሲወራ ጀግነት ሲነገር
የድል ታሪክ ሲባል አድዋ ሚከበር
ሀገሩን የሚወድ ተከባብሮ ሚኖር
ትውልድ ቢኖር ነበር!
ሀና ሀይሉ
የካቲት 2011ዓ.ም
ክብር መከበረን ለሰጡን ላስከበሩን ጀግኖቻችን!
ፎቶ ዳዊት ጥበቡ
@getem
@getem
@HanaHailu
ቄስ ቫላንቲኖ ሆይ……
እንዴት ሰንብተዋል ኑሮዎት እንዴት ነዉ
ይሄዉ ተገናኘን መሰንበት ደግ ነዉ
እኔ ብቻየን ነኝ ዛሬም ልክ እንዳምናዉ
የክህደት ባንዴራ ሕይወታችን መሀል
ከፍ ብሎ ሲሰቀል
ጥንድ መሆን ሕመም ብቻነት ይበጃል
የኔን ነገር ተዉት ይቅር አይነሳ
ግን እንደዉ ግንሳ….
የባለፈዉ ለታ የቫላንቲኖ ቀን
ህዝቤ ያረገዉን መቸም አይረሱትም
ከሰሜን ደቡብ ጫፍ ከምራብ ምስራቅም
ተፋቀርን ያሉ ጥንዶች ባደባባይ
ቀይ አበባ ይዘዉ…
ቀይ ወይን ተጎንጭተዉ…
ጓዳ ጎዳናዉን በቀይ አስሸብርቀዉ
ቀይ ጠረጴዛ ቀይ ስጋጃ ላይ
በጥንዶች ተሞልቶ ዓለም ቀልቶ ሲታይ
እዉነት እንዳይመስሎት ቄስ ቫላንቲኖ ሆይ
እዉነት እዉነት እዉነት
ዓለም ቀልቶ አይደለም ቀንቶ ነዉ እዉነቱ
እሽ አሁን የት አሉ አምና የቀሉቱ?
ቀንተዉ ነዉ በሰዉ ቀይ አበባ ይዘዉ
ሲሉ ሰምታን ሰምተዉ ያለ ሀቁ ናዉዘዉ
ሲነጋ የጠፉት ቀዩን ካርድ መዝዘዉ
በእዉነት ቫላንቲኖ
እርስዎ ደክመዋል እርስዎ ለፍተዋል
ለፍቅረኞች ሲሉ ሕይወት ሰዉተዋል
ግና ባደባባይ እዩኝ ያለ ፍቅር
እዩኝ ያለ ሕይወት
መሰረት ከሌለዉ
በረከት ከሌለዉ ንፋስ ሽዉ ያለ ለት
ፍጻሜዉ ቀይ ነዉ ቢጫም አይገባበት
ቫላንቲኖ አባቴ….
ግዜዉ ተለዉጧል ዘመን ለዛዉ ከፍቷል
ታሪክ ተቀይሯል
በእርግጥ በእርሶ ዘመን
ንጉሥ ወጣቶቹን እንዳይጋቡ አዝዟል
ይህም ክፉ ትዛዝ እርሶን አስከፍቷል
አሁን በኛ ግዜ
ወጣቱ ይጋባል ግን ወድያዉ ይፋታል
ለምን?
የተሸበረ ልብ የፈራ ሰዉነት
ትዳርን አይደለም የራሰንም ሕይወት
መሸከም ይፈራል
በእዉነት ቫላንቲኖ አለም ተሸብሯል
ቀይ ሲያይ…. ሹፌሩ ይቆማል
ቀይ ሲያይ….ኳሰኛዉ ይወጣል
ቀይ ሲያይ….ቀይ ሲያይ
የከፋዉ ሀገሬዉ ልቡ ይሸበራል
ባክዎን አባቴ
ባክዎን አባቴ
የሚቀጥለዉን ዳግመኛ ሲመጡ
ቀይ አበባ ጥለዉ…
እንደ ኖህ እርግብ ከሳር ከቀንበጡ
አረንጓዴ ቅጠል ጨፌ ይዘዉ ይምጡ
((( ሰለሞን ሳህለ ))
@getem
@getem
@getem
እንዴት ሰንብተዋል ኑሮዎት እንዴት ነዉ
ይሄዉ ተገናኘን መሰንበት ደግ ነዉ
እኔ ብቻየን ነኝ ዛሬም ልክ እንዳምናዉ
የክህደት ባንዴራ ሕይወታችን መሀል
ከፍ ብሎ ሲሰቀል
ጥንድ መሆን ሕመም ብቻነት ይበጃል
የኔን ነገር ተዉት ይቅር አይነሳ
ግን እንደዉ ግንሳ….
የባለፈዉ ለታ የቫላንቲኖ ቀን
ህዝቤ ያረገዉን መቸም አይረሱትም
ከሰሜን ደቡብ ጫፍ ከምራብ ምስራቅም
ተፋቀርን ያሉ ጥንዶች ባደባባይ
ቀይ አበባ ይዘዉ…
ቀይ ወይን ተጎንጭተዉ…
ጓዳ ጎዳናዉን በቀይ አስሸብርቀዉ
ቀይ ጠረጴዛ ቀይ ስጋጃ ላይ
በጥንዶች ተሞልቶ ዓለም ቀልቶ ሲታይ
እዉነት እንዳይመስሎት ቄስ ቫላንቲኖ ሆይ
እዉነት እዉነት እዉነት
ዓለም ቀልቶ አይደለም ቀንቶ ነዉ እዉነቱ
እሽ አሁን የት አሉ አምና የቀሉቱ?
ቀንተዉ ነዉ በሰዉ ቀይ አበባ ይዘዉ
ሲሉ ሰምታን ሰምተዉ ያለ ሀቁ ናዉዘዉ
ሲነጋ የጠፉት ቀዩን ካርድ መዝዘዉ
በእዉነት ቫላንቲኖ
እርስዎ ደክመዋል እርስዎ ለፍተዋል
ለፍቅረኞች ሲሉ ሕይወት ሰዉተዋል
ግና ባደባባይ እዩኝ ያለ ፍቅር
እዩኝ ያለ ሕይወት
መሰረት ከሌለዉ
በረከት ከሌለዉ ንፋስ ሽዉ ያለ ለት
ፍጻሜዉ ቀይ ነዉ ቢጫም አይገባበት
ቫላንቲኖ አባቴ….
ግዜዉ ተለዉጧል ዘመን ለዛዉ ከፍቷል
ታሪክ ተቀይሯል
በእርግጥ በእርሶ ዘመን
ንጉሥ ወጣቶቹን እንዳይጋቡ አዝዟል
ይህም ክፉ ትዛዝ እርሶን አስከፍቷል
አሁን በኛ ግዜ
ወጣቱ ይጋባል ግን ወድያዉ ይፋታል
ለምን?
የተሸበረ ልብ የፈራ ሰዉነት
ትዳርን አይደለም የራሰንም ሕይወት
መሸከም ይፈራል
በእዉነት ቫላንቲኖ አለም ተሸብሯል
ቀይ ሲያይ…. ሹፌሩ ይቆማል
ቀይ ሲያይ….ኳሰኛዉ ይወጣል
ቀይ ሲያይ….ቀይ ሲያይ
የከፋዉ ሀገሬዉ ልቡ ይሸበራል
ባክዎን አባቴ
ባክዎን አባቴ
የሚቀጥለዉን ዳግመኛ ሲመጡ
ቀይ አበባ ጥለዉ…
እንደ ኖህ እርግብ ከሳር ከቀንበጡ
አረንጓዴ ቅጠል ጨፌ ይዘዉ ይምጡ
((( ሰለሞን ሳህለ ))
@getem
@getem
@getem
👍1
#አንዳንዴ...
፧
አንዳንዴ...
እንዲህ ያደርገኛል...
ጀንበር በወጣችበት
ቀን ይጨልምብኛል፣
ሰውን ማየት...
ጠልቼ ያነጫንጨኛል፣
ትኩሳቴ ግሎ
ሳያመኝ.......ያመኛል፣
አንዳንዴም...
እንዲህ እሆናለሁ...
አጫዋች ፍለጋ
ባ'ይኔ እቃብዛለሁ፣
በወይን ስካር ውስጥ
ሳቅ....እናፍቃለሁ፣
የኑሮ ሸክም ላቀል
ማሰብ...አቆማለሁ፣
አንዳንድ...
ጊዜ ደግሞ...
ሐሳቤ...
መጪውን አልሞ፣
ተስፋ ያሳየኛል
ከፊቴ......አቁሞ፣
ይኸው እስከዛሬ...
ባ'ንዳንድ አጋጣሚ
ሰውን.....እጠላለሁ፣
ባ'ንዳንድ አጋጣሚ
ሰው.....እናፍቃለሁ፣
ባ'ንዳንዴዎች ውዬ
አምሽቼ...አድራለሁ፣
ባ'ያሌው በብዙ...
አንዳንዴዎች ተስፋ፣
ዛሬን እኖራለሁ...
አንዳንድ ቀን ስገፋ !!!
፨
#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
፧
አንዳንዴ...
እንዲህ ያደርገኛል...
ጀንበር በወጣችበት
ቀን ይጨልምብኛል፣
ሰውን ማየት...
ጠልቼ ያነጫንጨኛል፣
ትኩሳቴ ግሎ
ሳያመኝ.......ያመኛል፣
አንዳንዴም...
እንዲህ እሆናለሁ...
አጫዋች ፍለጋ
ባ'ይኔ እቃብዛለሁ፣
በወይን ስካር ውስጥ
ሳቅ....እናፍቃለሁ፣
የኑሮ ሸክም ላቀል
ማሰብ...አቆማለሁ፣
አንዳንድ...
ጊዜ ደግሞ...
ሐሳቤ...
መጪውን አልሞ፣
ተስፋ ያሳየኛል
ከፊቴ......አቁሞ፣
ይኸው እስከዛሬ...
ባ'ንዳንድ አጋጣሚ
ሰውን.....እጠላለሁ፣
ባ'ንዳንድ አጋጣሚ
ሰው.....እናፍቃለሁ፣
ባ'ንዳንዴዎች ውዬ
አምሽቼ...አድራለሁ፣
ባ'ያሌው በብዙ...
አንዳንዴዎች ተስፋ፣
ዛሬን እኖራለሁ...
አንዳንድ ቀን ስገፋ !!!
፨
#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
ቃል ልግባልሽ #anu📝
አፈቅርሻለሁ ልል ቀናትን አልመርጥም
ወደድኩሽ ለማለት ሰበብ አልፈልግም
በእያንዳዷ ሰከንድ በሁሉም ደቂቃ
ፀሀይም ባትወጣ ባትደምቅም ጨረቃ
ሰማዩ እንኳን ቢናድ ኮከቦች ቢረግፉ
ጥላቻ አግዝፈው ፍቅርን ቢፀየፉ
ቀናት ቢሰየሙ ስም ቢወጣላቸው
የፍቅር ባይባል መጠርያ ስማቸው
አንቺ ከለሽልኝ ለኔ የፍቅር ናቸው
በእያንዳንዷ ሰከንድ ፍቅሬን ብነግርልሽ
ጨርሶ አይቻልም እኔ አንቺን ልገልፅሽ
የፍቅር ቀን ብሎ አለም በሰየመው
በቃልኪዳን ብዛት በተንበሸበሸው
ባማሩ ጥንዶች ፊት በቀይ በደመቁ
ፍቅርን በልባቸው ብዙ በሰነቁ
ከፊታቸው ቆሜ ውዴ ቃል ልግባልሽ
ከምገልፀው በላይ እኔ እንደማፈቅርሽ
@getem
@getem
@gebriel_19
አፈቅርሻለሁ ልል ቀናትን አልመርጥም
ወደድኩሽ ለማለት ሰበብ አልፈልግም
በእያንዳዷ ሰከንድ በሁሉም ደቂቃ
ፀሀይም ባትወጣ ባትደምቅም ጨረቃ
ሰማዩ እንኳን ቢናድ ኮከቦች ቢረግፉ
ጥላቻ አግዝፈው ፍቅርን ቢፀየፉ
ቀናት ቢሰየሙ ስም ቢወጣላቸው
የፍቅር ባይባል መጠርያ ስማቸው
አንቺ ከለሽልኝ ለኔ የፍቅር ናቸው
በእያንዳንዷ ሰከንድ ፍቅሬን ብነግርልሽ
ጨርሶ አይቻልም እኔ አንቺን ልገልፅሽ
የፍቅር ቀን ብሎ አለም በሰየመው
በቃልኪዳን ብዛት በተንበሸበሸው
ባማሩ ጥንዶች ፊት በቀይ በደመቁ
ፍቅርን በልባቸው ብዙ በሰነቁ
ከፊታቸው ቆሜ ውዴ ቃል ልግባልሽ
ከምገልፀው በላይ እኔ እንደማፈቅርሽ
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1