ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የልደትሽ_መርዶ

ለራሱ ሲል...
ይመጣል ልደትሽ፣
ዘመናትን ቆጥሮ
እርጅናን ሊያበስርሽ፣
ምን አስቸኮለሽ
ይዘግይ ምን አለበት፣
የምትኖሪው እድሜ
ያልፋል...እንደ ዘበት !!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
#ሰሞነኛ_ወሬ

በኛ አገር...
ያንዱ ስም 'ሚወሳ፣
አንድም...
ሲወድቅ ነው...
አለዚያም....ሲነሳ፣
የእስሩም ወሬ
ሳምንትን አይዘልቅም፣
ባ'ንዱ መፈታት ነው
ወሬው...የሚያከትም🤔 !!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@kaleab_1888
#ነፃ_አውጪ

ሰደድ እሳት ሆኖ
ነገር ባገር ላይ ከመጣ፣
ያፈገፈገው ነው
ሌላውን ነፃ የሚያወጣ !!!



#ሀብታሙ_ወዳጅ

@getem
@getem
@gebriel_19
#አንዳንዴ...

አንዳንዴ...
እንዲህ ያደርገኛል...
ጀንበር በወጣችበት
ቀን ይጨልምብኛል፣
ሰውን ማየት...
ጠልቼ ያነጫንጨኛል፣
ትኩሳቴ ግሎ
ሳያመኝ.......ያመኛል፣
አንዳንዴም...
እንዲህ እሆናለሁ...
አጫዋች ፍለጋ
ባ'ይኔ እቃብዛለሁ፣
በወይን ስካር ውስጥ
ሳቅ....እናፍቃለሁ፣
የኑሮ ሸክም ላቀል
ማሰብ...አቆማለሁ፣
አንዳንድ...
ጊዜ ደግሞ...
ሐሳቤ...
መጪውን አልሞ፣
ተስፋ ያሳየኛል
ከፊቴ......አቁሞ፣
ይኸው እስከዛሬ...
ባ'ንዳንድ አጋጣሚ
ሰውን.....እጠላለሁ፣
ባ'ንዳንድ አጋጣሚ
ሰው.....እናፍቃለሁ፣
ባ'ንዳንዴዎች ውዬ
አምሽቼ...አድራለሁ፣
ባ'ያሌው በብዙ...
አንዳንዴዎች ተስፋ፣
ዛሬን እኖራለሁ...
አንዳንድ ቀን ስገፋ !!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
#ቫለንታይን_ለምኔ

በቫላንታይን ስም
ቀይ ለባሽ ሁላ፣
እስኪ ታሪኩን
ይመርምር ከኋላ፣
በርግጥ ቀይ
ልብሱንስ ይልበሰው፣
ለዛ ለዓድዋ ፋኖ
ህይወት ለከፈለው፣
ላሁኑ ነፃነት
ደሙን ላፈሰሰው፣
በየካቲት ወር
ዝክር እንዲሆነው፣
እንጂ ቫለንታይን
መች የሱ ሆነና፣
ይልቅ ቀዩን ለብሶ
ያስታውስ ያንን ጀግና!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
#ስላንቺ...

አይቼ እንዳላየሁ
ሰምቼ እንዳልሰማሁ፣
ማለፌን አትዪ
ሁሉንም...አውቃለሁ፣

ያልሽውን እንዳምን
ያወቅኩትን አትካጅኝ፣
እናልሽ...
ፍቅሬ ሆይ!
"እንዲህ ነኝ" አትበይኝ!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
አላፊው...
እንዳላየ አይቶ እያለፈኝ፣
አላልፍ ያለው...
ቀን ነው ... እኔን የደቆሰኝ !!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem