*እግዜር ለሐበሻ የፃፈው ደብዳቤ*
(በላይ በቀለ ወያ)
እንዴት ነህ ሐበሻ - ምድርህስ እንዴት ነው?
እመጣለሁ ብዬህ
ከቀጠርሁህ ቦታ - ጠፋህብኝ ምነው?
እኔማ ይኸውልህ
ለእልፍ አእላፍ መላእክት - ትእዛዜን ሰጥቼ
ከቀጠርኩህ ቦታ - ላገኝህ መጥቼ
ተመልሼ ሄድሁኝ
ሐበሻ መሚመስል - አንድ ሀበሻ አጥቼ።
እንደውም እንደውም
"ሌሎችን ለመሆን - ቀን ተሌት ሚለፋ
ለሌሎች ታሪክ ሲል - ታሪኩ የጠፋ
ሐበሻ ምድር
ታሪክ ማውራት እንጅ - ታሪክ መስራት ቀወ።"
እያሉ የሚያሙህ
የመላእክትን ቃል - ሰምቼ ነበረ።
እኔ ምልህ ሐበሻ
እውነት እንደሚያሙት
በሐበሻ ምድር ላይ - ታሪክ መስራት ቀርቷል?
አክሱም ላሊበላ
ዛሬም ይናገራል - ዛሬም ይተረታል?
እንደውም ልንገርህ
አውቆ ጠያቂ ነኝ! ሐበሻነት ጠፍቷል።
ድሮ እኮ ሐበሻ
የዳዊትን ወንጭፍ - ጠይቆኝ አያውቅም
"ዘራፍ " ሲል ይገላል - ከፎከረ አይለቅም
ድሮኮ ለሐበሻ
ለእልፍ አ'ላፍ ጎልያድ - ከቶ አይጨነቅም።
ድሮኮ ሐበሻ
ለሚኖርበት ቤት - አያውቅም ተጨንቆ
"ኤሎሄ " በማለት
ቤት እንድጥልለት - አያውቅም ጠይቆ
ድሮኮ ሐበሻ
ቤት ከስራ ኋላ
ጥሎ ነው ሚሄደው - ለእንቦሳ ለቆ።
ድሮኮ ሀበሻ
ሙሴ በትርህን - አውሰኝ አይልም - ባህር ለመሻገር
ከሌሎች የሚሻል
አለው የራሱ ምድር - አለው የራሱ ሀገር።
የሆነው ሆነና
ምድርህ እንደምነው?
እመጣለው ብዬህ
ከቀጠርሁህ ቦታ - ጠፋህብኝ ምነው?
እኔማ ይኸውልህ
ለእልፍ አእላፍ መላእክት - ትእዛዝ ሰጥቼ
ከቀጠርኩህ ቦታ - ላገኝህ መጥቼ
ተመልሼ ሄድሁኝ
ሐበሻ የሚመስል - አንድ ሀበሻ አጥቼ
"እንቅልፍ እና ሴት" ከተሰኘው መድብል የተወሰደ ገፅ፦69 - 70 )
#ገፅ
@getem
@getem
@gebriel_19
(በላይ በቀለ ወያ)
እንዴት ነህ ሐበሻ - ምድርህስ እንዴት ነው?
እመጣለሁ ብዬህ
ከቀጠርሁህ ቦታ - ጠፋህብኝ ምነው?
እኔማ ይኸውልህ
ለእልፍ አእላፍ መላእክት - ትእዛዜን ሰጥቼ
ከቀጠርኩህ ቦታ - ላገኝህ መጥቼ
ተመልሼ ሄድሁኝ
ሐበሻ መሚመስል - አንድ ሀበሻ አጥቼ።
እንደውም እንደውም
"ሌሎችን ለመሆን - ቀን ተሌት ሚለፋ
ለሌሎች ታሪክ ሲል - ታሪኩ የጠፋ
ሐበሻ ምድር
ታሪክ ማውራት እንጅ - ታሪክ መስራት ቀወ።"
እያሉ የሚያሙህ
የመላእክትን ቃል - ሰምቼ ነበረ።
እኔ ምልህ ሐበሻ
እውነት እንደሚያሙት
በሐበሻ ምድር ላይ - ታሪክ መስራት ቀርቷል?
አክሱም ላሊበላ
ዛሬም ይናገራል - ዛሬም ይተረታል?
እንደውም ልንገርህ
አውቆ ጠያቂ ነኝ! ሐበሻነት ጠፍቷል።
ድሮ እኮ ሐበሻ
የዳዊትን ወንጭፍ - ጠይቆኝ አያውቅም
"ዘራፍ " ሲል ይገላል - ከፎከረ አይለቅም
ድሮኮ ለሐበሻ
ለእልፍ አ'ላፍ ጎልያድ - ከቶ አይጨነቅም።
ድሮኮ ሐበሻ
ለሚኖርበት ቤት - አያውቅም ተጨንቆ
"ኤሎሄ " በማለት
ቤት እንድጥልለት - አያውቅም ጠይቆ
ድሮኮ ሐበሻ
ቤት ከስራ ኋላ
ጥሎ ነው ሚሄደው - ለእንቦሳ ለቆ።
ድሮኮ ሀበሻ
ሙሴ በትርህን - አውሰኝ አይልም - ባህር ለመሻገር
ከሌሎች የሚሻል
አለው የራሱ ምድር - አለው የራሱ ሀገር።
የሆነው ሆነና
ምድርህ እንደምነው?
እመጣለው ብዬህ
ከቀጠርሁህ ቦታ - ጠፋህብኝ ምነው?
እኔማ ይኸውልህ
ለእልፍ አእላፍ መላእክት - ትእዛዝ ሰጥቼ
ከቀጠርኩህ ቦታ - ላገኝህ መጥቼ
ተመልሼ ሄድሁኝ
ሐበሻ የሚመስል - አንድ ሀበሻ አጥቼ
"እንቅልፍ እና ሴት" ከተሰኘው መድብል የተወሰደ ገፅ፦69 - 70 )
#ገፅ
@getem
@getem
@gebriel_19
*የዘወትር ቁማር*
-
አንቺ የሰዉ ደሴት የዕድሜ ስንቅ ሰሌዳ፣
ገሚሱን አየፃፍሽ ማጥፊያሽ የሚከዳ፣
የጥያቄ ድርሳን መልስ አልባ አኮፋዳ፣
እንደምን ነሽ ህይወት የስጋዬ ባዳ።
-
ህልም እየታቀፉ በባዶ ሆድ ማደር፣
ሀሳብ እየሞቁ-
በተስፋ መለኪያ እልፍ ጊዜ መስከር፣
ዳግም መንገዳገድ ለመነሳት መዉደቅ፣
ክንድን አበርትቶ ለመዳን መንፏቀቅ።
-
ግብርሽ በመሆኑ ያንከራትተናል፣
ሳትመልሺዉ ልናልፍ ዘዉትር ይጠበናል።
-
(ናርዶስ-ካሳሁን)
@getem
@getem
@gebriel_19
-
አንቺ የሰዉ ደሴት የዕድሜ ስንቅ ሰሌዳ፣
ገሚሱን አየፃፍሽ ማጥፊያሽ የሚከዳ፣
የጥያቄ ድርሳን መልስ አልባ አኮፋዳ፣
እንደምን ነሽ ህይወት የስጋዬ ባዳ።
-
ህልም እየታቀፉ በባዶ ሆድ ማደር፣
ሀሳብ እየሞቁ-
በተስፋ መለኪያ እልፍ ጊዜ መስከር፣
ዳግም መንገዳገድ ለመነሳት መዉደቅ፣
ክንድን አበርትቶ ለመዳን መንፏቀቅ።
-
ግብርሽ በመሆኑ ያንከራትተናል፣
ሳትመልሺዉ ልናልፍ ዘዉትር ይጠበናል።
-
(ናርዶስ-ካሳሁን)
@getem
@getem
@gebriel_19
ማነሽ(ባታ አልሜ)
ማነሽ
አዎ ማነሽ
የልቤን በር ምታንኳኪ
በግዞቴ ምትማርኪ
እኮ ማነሽ?
ከከበረ መንበሬ ላይ ደርሰሽ በጦር ምትነካኪ
እኔ እንደሆን
ጎዶሎ ነኝ የማይሞላ
ከእናቴ ውጪ ለሴት መዳፍ እማልደላ
ፍቅር ሲቀርበኝ የምሸሽ ስቀርበው ፊቱን አዟሪ
ለተጎዱት አፅናኝ ጌታ ላፈቀሩት አማካሪ
እኔ እንደሆን
ተፈጥሮ ባያል ያሰረኝ
ብቸኝነት የማረከኝ
የውሸት መውደድ እምያመኝ
ማስመሰል ሞት እሚመስለኝ
ተስፋ ታቅፎ አዳሪ
ስሜት በድሎ ነዋሪ
ያልኖርኩበተን ትዝታ ስቃኝ እምውል በሀሳቤ
መመኘትን እምመኘው በሗሊት
ፈረስ ጋልቤ
እኔ እንደሆን
ተወዶ ዝምታ
አፍቅሮ ዝምታ
ተደብቆ ናፍቆት ነው የኔ ስጦታ
እናም ማነሽ
እኮ ማነሽ??
ባስከበርኩት ድንበሬ ላይ
ልዕልት መሆን እምያምርሽ
ባቀናዋት ባህሬ ላይ
መዋኘቱ እሚከጅልሽ
በጠፋሁላት ሀገሬ ንግስትነት ሚናፍቅሽ
እናም ማነሽ ካደመጥሽኝ
በልቤ ሀገር ሴት አትነግስም
መልኳ ቢሆን የማክዳ
ድንግልናዋም አይከበር ሳባዊነቷም አይፀዳ
እናም ማነሽ
አዎ ማነሽ
ከቀረብኩሽ እንድትርቂ
አንደበቱ በተዘጋ በዲዳ ፍቅር እንዳትወድቂ
አዎ ማነሽ
የደንቆሮን ምክር ስሚ
ጨለማን ለመረጠ ሰው ብርሀን መስጠት አታልሚ
አዎ ማነሽ
መታሠብያነቱ ለኔው
@getem
@getem
@gebriel_19
ማነሽ
አዎ ማነሽ
የልቤን በር ምታንኳኪ
በግዞቴ ምትማርኪ
እኮ ማነሽ?
ከከበረ መንበሬ ላይ ደርሰሽ በጦር ምትነካኪ
እኔ እንደሆን
ጎዶሎ ነኝ የማይሞላ
ከእናቴ ውጪ ለሴት መዳፍ እማልደላ
ፍቅር ሲቀርበኝ የምሸሽ ስቀርበው ፊቱን አዟሪ
ለተጎዱት አፅናኝ ጌታ ላፈቀሩት አማካሪ
እኔ እንደሆን
ተፈጥሮ ባያል ያሰረኝ
ብቸኝነት የማረከኝ
የውሸት መውደድ እምያመኝ
ማስመሰል ሞት እሚመስለኝ
ተስፋ ታቅፎ አዳሪ
ስሜት በድሎ ነዋሪ
ያልኖርኩበተን ትዝታ ስቃኝ እምውል በሀሳቤ
መመኘትን እምመኘው በሗሊት
ፈረስ ጋልቤ
እኔ እንደሆን
ተወዶ ዝምታ
አፍቅሮ ዝምታ
ተደብቆ ናፍቆት ነው የኔ ስጦታ
እናም ማነሽ
እኮ ማነሽ??
ባስከበርኩት ድንበሬ ላይ
ልዕልት መሆን እምያምርሽ
ባቀናዋት ባህሬ ላይ
መዋኘቱ እሚከጅልሽ
በጠፋሁላት ሀገሬ ንግስትነት ሚናፍቅሽ
እናም ማነሽ ካደመጥሽኝ
በልቤ ሀገር ሴት አትነግስም
መልኳ ቢሆን የማክዳ
ድንግልናዋም አይከበር ሳባዊነቷም አይፀዳ
እናም ማነሽ
አዎ ማነሽ
ከቀረብኩሽ እንድትርቂ
አንደበቱ በተዘጋ በዲዳ ፍቅር እንዳትወድቂ
አዎ ማነሽ
የደንቆሮን ምክር ስሚ
ጨለማን ለመረጠ ሰው ብርሀን መስጠት አታልሚ
አዎ ማነሽ
መታሠብያነቱ ለኔው
@getem
@getem
@gebriel_19
<ጥጊያ>
ደክሞኛል አትቀስቅሱኝ
አሞኛል አታቁስሉኝ
ከማልችለው ጋር አታጋፋኝ
ልኑር ጥጌን ይዤ
የትካዜ ካብ በትሬን ተመርኩዤ፡፡
✍....አብርሀም
@getem
@getem
@artbekiyechalal
ደክሞኛል አትቀስቅሱኝ
አሞኛል አታቁስሉኝ
ከማልችለው ጋር አታጋፋኝ
ልኑር ጥጌን ይዤ
የትካዜ ካብ በትሬን ተመርኩዤ፡፡
✍....አብርሀም
@getem
@getem
@artbekiyechalal
የካቲት 12 ግን ታስቦ መዋሉ ብቻ በቂው ነው ትላላችሁ???
አስተያየታቹን ከነ ምክንያታቹ ብታደርሱን ደስ ደስ ይለናል....
ክብር ለሰማዕታት !!💚💛❤
@balmbaras
@Gebriel_19
አስተያየታቹን ከነ ምክንያታቹ ብታደርሱን ደስ ደስ ይለናል....
ክብር ለሰማዕታት !!💚💛❤
@balmbaras
@Gebriel_19
#የፈረሱ_መልኮች
( ኤፍሬም ስዩም )
ከዘመናት ኋላ
ድንገት ባጋጣሚ አንድ ቀን ያየኋት
እሷን እያሰብኩኝ
በበራቸው በኩል ትላንትና አለፍኩኝ።
ገረመኝ
ደነቀ…
ለካ . .
ስፍራቸውን ለቀው
ቤተሰቡ ሁሉ ከዚያ ቦታ ጠፍቷል
ኮረብታው ላይ ያለው መኖሪያቸው ግና…
ግድግዳና ጣሪያ አጥሩ ፈራርሶ ወለሉ ይታያል
እኔ በበኩሌ… ከዚህ የበለጠ ላወራ ምችለው
አንድም ቃል የለኝም
ፈርሶ ለማየው ቤት አራት ኪሎ ላለው
ሁኔታው…
ክፍት የእንጨት አጥር
ትንሽ ገደድ ያለ… ልሙጥ ቆርቆሮ በር
መላ ቅጥ የሌለው
ለቅሶና ሙዚቃው የማይለይ ሰፈር
ነበር …
ግን…
ፈገግታ የሞላው
በቤቱ ጥበት ልክ… ደስታ የማያጣው
ግድግዳውን የሚያልፍ ሃዘን የወረረው
ላ'መት በዓልና
ላ'መት በዓል ዋዜማ ብቸኛ ቀናቸው
እፎይ የሚሉበት
ህፃናት ተጫውተው
ጠግበው የሚያድሩበት አዋቂዎች በልተው
ሰፈር…
እዚያ ነበር።
አሁን ግን የለችም
ውበቷ ተረስቶ የገባችበትን አንድም የሚያውቅ የለም
የትገባ - ያ - ውበት
የትገባ- ያ - ቁመት
ሲያስጨንቅ የኖረው ወንዱን ሁሉ ባምሮት
ተስፋ የነበረው ለመንደሯ ጭንቀት።
እልፍ መአት ወንዶች በበሯ አልፈዋል
ባይተኟትም እንኳ
አይኗን አይተው ብቻ እድሜ ቀጥለዋል
ግና…
ያሳዝናል…
እድሜ የጠገቡ ጉልበተኛ ወንዶች ቤቷን አፍርሰዋል
እንኳን ቤቷ ፈርሶ
አንድ ቀን ስታኮርፍ እድሜ እንደምትቀንስ መች ይገባቸዋል።
ድንገት ባጋጣሚ
አንድ ቀኑን ያየኋት እሷን እያሰብኩኝ
ከዘመኋላ
በበራቸው በኩል ትላንትና አለፍኩኝ
ገረመኝ
ደነቀኝ
ለካ…
ስፍራቸውን ለቀው
ቤተሰቡ ሁሉ ከዚያ ቦታ ሄዷል
ኮረብታው ላይ ያለው መኖሪያቸው ግና…
ግድግዳና ጣሪያው አጥሩ ፈራርሶ ወለሉ ይታያል
እኔ … በበኩሌ…
ከዚህ የበለጠ ልናገር የምሻው
አንድም ቃል የለኝም ፈርሶ ለማየው ቤት . . አራት ኪሎ ላለው
ልደታ ላይ ላለው
ሰንጋ ተራ ላለው
የትም ሰፈር ላለው።
ስለሷ ግን ላውራ
ውበት ጠፍቶ እዳይቀር ከግድግዳው ጋራ
በእርግጥም መንደሯ
ተስፋው የሞተላበት
ጦር የወደቀበት
በተራ ወታደር የተረታ ንጉሥ የሚመስል አይነት።
ሞቱን የሚጠብቅ
ታስሮ የሚማቅቅ
መሞት አለመሞት የኑሮ ትንቅንቅ
እሷ መንደር መሃል ይታያል ይሄ ሃቅ።
የፈረሱ መልኮች
የገጠጡ ገፆች … የወየቡ እጆች … ያፈጠጡ አይኖች
የጠቆሩ ቀዮች
ወዝ አልባ ጥቁሮች
ቆዳውን የበላ እረዣዥም አጥንት
ብዙዎች የሞሉበት
ሞልተው ሚሞቱበት
ከሕይወት ተፋተው በተስፋ እጦት ምክንያት።
ሕዝቡ ሚደርበው
ነጠላና ጋቢው
ሀዘን የሸመነው ጨለማ ብርድልብስ
ግራ ጎረቤቷ ህፃን የሚያለቅስ
እናቱን የሞተች በዐዋላጅ እጦት።
የቀኝ ጎረቤቷ እናት ምታቃስት
ሴት ልጇ ያበደች የምታስታምማት።
እወዲያ ጥግ ላይ…
ቤት አልባ- ጎልማሳ
በረሃቡ ምክንያት. . አካሉ የከሳ
ከዘመና በፊት…
በሺህ ዘጠኝ መቶ . . ዘጠና ሁለት ዓመት
ሁለት ዓይኑን ያጣ …በወንድሞቹ ቀስት…
ወዲህ ከትቦው ጎን
ያገሩ ቆሻሻ በሚያልፍበት በኩል
መምጫው ያልታወቀ… አንድ ትንሽ ህፃን…
እድሜው የሚመጥን አስር ዓመት ያህል
የሰውና የከብት ቆሻሻ ካለበት
ትቦ- ጎንሚተኛ
በልጅነት እድሜ የሌሉት ወላጆች
በልጅነት ዕድሜው የሽማግሌ አይኖች
ችግር የሰራበት…
ትንሽ ግንባሩ ላይ አንድ ሺህ መስመሮች
መንተራሻው ድንጋይ ፍራሹ ኮረኮንች
በጀርባዋ በኩል
ሰባት የወለደ አባት የሚያነክስ
ሰባቱን ልጆቹን ድንጋይ ፈልጦ ሚያጎርስ
ሰባቱን ልጆቹን. . ለምኖ የሚያለብስ።
ከፊቷ ትንሽ ሱቅ
ሃሊማና ከድር
ሁለት ባለትዳር… የሰፈሩ ህይወት. . የሰፈሩ አለኝታ
በጭልፋ የሚሸጡ የሃምሳ ሳንቲም ፓስታ
ይህን የሚመስሉ ብዙዎች የሞሉበት
በቁም የሚያለቅሱ ብዙዎች የሞቱበት
የፈረሱ መልኮች. . የሕይወት ግምጃ ቤት።
ነበረ…
ዛሬ ፈርሶ ማየው
መንደሯን የሞላው
የሚገርመው ግና?…
መሶብ ሙሉ ስቃይ . . እንስራ ሙሉ እምባ
የሆነው ይህ ቦታ
የመንገድኛውን. . ዓይን. . የመንገደኛውን. . ልብ ባዘን እያጓጓ
እሷ ግን ነበረች ቀይ ፅጌረዳ የእሾህ ማል አበባ
እናም በዚያ ሰፈር
እናም በዚያ መንደር
የርሷ መኖር ብቻ ለሰፈሩ ሰዎች ሳቅ ይፈጥር ነበር
ተስፋ ይሰጥ ነበር
ጥጋብ ይሆን ነበር
*
ባለማወቅ እንጅ
ጤዛውን ለማበስ
ፅጌውን መቀንጠስ… ማስተዋል ቢመስለን
ባለማወቅ እንጂ…
ላንድ ዝግባ ሲባል
እልፍ አበባ መቁረጥ እልፍ አበባ መጣል
ማስተዋል ቢመስለን
ባለማወቅ ነው እንጅ
ያለማወቅ እውቀት ስልጣኔ መስሎን
ልማት ነው እያልን የሙጥኝ ስላልን
እንጂ…
ብናውቀው ኖሮማ ውበት ቅርስ እንዲሆን…
ብናውቀው ኖሮማ. .
በህይወት ግምጃ ቤት.. ተጥሎ የሚኖር ተምሳሌት እንደሆን
ብናውቀው ኑሮማ
በውበት ብናምርን ቅርስን ብናከብር
ያን ያህል ጨክኖ ይህን የርሷን መንደር
ይህን የእርሷን ሰፈር
ማን ያፈርሰው ነበር።…
ዛሬ…
በዚያ መንደር
ከልጅት መኖሪያ ፍርስራሽ ጣውላ ስር
ከቤተ-መንግስቱ አረንጓዴ ሰፈር
ክፉ ጠረንይዞ ነፋስ ይጓዝ ነበር።
(ኑ፦ግድግዳ እናፍርስ ከተሰኘው መድብል የተወሰደ ገፅ፦84 - 88)
#ገፅ
@getem
@getem
@gebriel_19
( ኤፍሬም ስዩም )
ከዘመናት ኋላ
ድንገት ባጋጣሚ አንድ ቀን ያየኋት
እሷን እያሰብኩኝ
በበራቸው በኩል ትላንትና አለፍኩኝ።
ገረመኝ
ደነቀ…
ለካ . .
ስፍራቸውን ለቀው
ቤተሰቡ ሁሉ ከዚያ ቦታ ጠፍቷል
ኮረብታው ላይ ያለው መኖሪያቸው ግና…
ግድግዳና ጣሪያ አጥሩ ፈራርሶ ወለሉ ይታያል
እኔ በበኩሌ… ከዚህ የበለጠ ላወራ ምችለው
አንድም ቃል የለኝም
ፈርሶ ለማየው ቤት አራት ኪሎ ላለው
ሁኔታው…
ክፍት የእንጨት አጥር
ትንሽ ገደድ ያለ… ልሙጥ ቆርቆሮ በር
መላ ቅጥ የሌለው
ለቅሶና ሙዚቃው የማይለይ ሰፈር
ነበር …
ግን…
ፈገግታ የሞላው
በቤቱ ጥበት ልክ… ደስታ የማያጣው
ግድግዳውን የሚያልፍ ሃዘን የወረረው
ላ'መት በዓልና
ላ'መት በዓል ዋዜማ ብቸኛ ቀናቸው
እፎይ የሚሉበት
ህፃናት ተጫውተው
ጠግበው የሚያድሩበት አዋቂዎች በልተው
ሰፈር…
እዚያ ነበር።
አሁን ግን የለችም
ውበቷ ተረስቶ የገባችበትን አንድም የሚያውቅ የለም
የትገባ - ያ - ውበት
የትገባ- ያ - ቁመት
ሲያስጨንቅ የኖረው ወንዱን ሁሉ ባምሮት
ተስፋ የነበረው ለመንደሯ ጭንቀት።
እልፍ መአት ወንዶች በበሯ አልፈዋል
ባይተኟትም እንኳ
አይኗን አይተው ብቻ እድሜ ቀጥለዋል
ግና…
ያሳዝናል…
እድሜ የጠገቡ ጉልበተኛ ወንዶች ቤቷን አፍርሰዋል
እንኳን ቤቷ ፈርሶ
አንድ ቀን ስታኮርፍ እድሜ እንደምትቀንስ መች ይገባቸዋል።
ድንገት ባጋጣሚ
አንድ ቀኑን ያየኋት እሷን እያሰብኩኝ
ከዘመኋላ
በበራቸው በኩል ትላንትና አለፍኩኝ
ገረመኝ
ደነቀኝ
ለካ…
ስፍራቸውን ለቀው
ቤተሰቡ ሁሉ ከዚያ ቦታ ሄዷል
ኮረብታው ላይ ያለው መኖሪያቸው ግና…
ግድግዳና ጣሪያው አጥሩ ፈራርሶ ወለሉ ይታያል
እኔ … በበኩሌ…
ከዚህ የበለጠ ልናገር የምሻው
አንድም ቃል የለኝም ፈርሶ ለማየው ቤት . . አራት ኪሎ ላለው
ልደታ ላይ ላለው
ሰንጋ ተራ ላለው
የትም ሰፈር ላለው።
ስለሷ ግን ላውራ
ውበት ጠፍቶ እዳይቀር ከግድግዳው ጋራ
በእርግጥም መንደሯ
ተስፋው የሞተላበት
ጦር የወደቀበት
በተራ ወታደር የተረታ ንጉሥ የሚመስል አይነት።
ሞቱን የሚጠብቅ
ታስሮ የሚማቅቅ
መሞት አለመሞት የኑሮ ትንቅንቅ
እሷ መንደር መሃል ይታያል ይሄ ሃቅ።
የፈረሱ መልኮች
የገጠጡ ገፆች … የወየቡ እጆች … ያፈጠጡ አይኖች
የጠቆሩ ቀዮች
ወዝ አልባ ጥቁሮች
ቆዳውን የበላ እረዣዥም አጥንት
ብዙዎች የሞሉበት
ሞልተው ሚሞቱበት
ከሕይወት ተፋተው በተስፋ እጦት ምክንያት።
ሕዝቡ ሚደርበው
ነጠላና ጋቢው
ሀዘን የሸመነው ጨለማ ብርድልብስ
ግራ ጎረቤቷ ህፃን የሚያለቅስ
እናቱን የሞተች በዐዋላጅ እጦት።
የቀኝ ጎረቤቷ እናት ምታቃስት
ሴት ልጇ ያበደች የምታስታምማት።
እወዲያ ጥግ ላይ…
ቤት አልባ- ጎልማሳ
በረሃቡ ምክንያት. . አካሉ የከሳ
ከዘመና በፊት…
በሺህ ዘጠኝ መቶ . . ዘጠና ሁለት ዓመት
ሁለት ዓይኑን ያጣ …በወንድሞቹ ቀስት…
ወዲህ ከትቦው ጎን
ያገሩ ቆሻሻ በሚያልፍበት በኩል
መምጫው ያልታወቀ… አንድ ትንሽ ህፃን…
እድሜው የሚመጥን አስር ዓመት ያህል
የሰውና የከብት ቆሻሻ ካለበት
ትቦ- ጎንሚተኛ
በልጅነት እድሜ የሌሉት ወላጆች
በልጅነት ዕድሜው የሽማግሌ አይኖች
ችግር የሰራበት…
ትንሽ ግንባሩ ላይ አንድ ሺህ መስመሮች
መንተራሻው ድንጋይ ፍራሹ ኮረኮንች
በጀርባዋ በኩል
ሰባት የወለደ አባት የሚያነክስ
ሰባቱን ልጆቹን ድንጋይ ፈልጦ ሚያጎርስ
ሰባቱን ልጆቹን. . ለምኖ የሚያለብስ።
ከፊቷ ትንሽ ሱቅ
ሃሊማና ከድር
ሁለት ባለትዳር… የሰፈሩ ህይወት. . የሰፈሩ አለኝታ
በጭልፋ የሚሸጡ የሃምሳ ሳንቲም ፓስታ
ይህን የሚመስሉ ብዙዎች የሞሉበት
በቁም የሚያለቅሱ ብዙዎች የሞቱበት
የፈረሱ መልኮች. . የሕይወት ግምጃ ቤት።
ነበረ…
ዛሬ ፈርሶ ማየው
መንደሯን የሞላው
የሚገርመው ግና?…
መሶብ ሙሉ ስቃይ . . እንስራ ሙሉ እምባ
የሆነው ይህ ቦታ
የመንገድኛውን. . ዓይን. . የመንገደኛውን. . ልብ ባዘን እያጓጓ
እሷ ግን ነበረች ቀይ ፅጌረዳ የእሾህ ማል አበባ
እናም በዚያ ሰፈር
እናም በዚያ መንደር
የርሷ መኖር ብቻ ለሰፈሩ ሰዎች ሳቅ ይፈጥር ነበር
ተስፋ ይሰጥ ነበር
ጥጋብ ይሆን ነበር
*
ባለማወቅ እንጅ
ጤዛውን ለማበስ
ፅጌውን መቀንጠስ… ማስተዋል ቢመስለን
ባለማወቅ እንጂ…
ላንድ ዝግባ ሲባል
እልፍ አበባ መቁረጥ እልፍ አበባ መጣል
ማስተዋል ቢመስለን
ባለማወቅ ነው እንጅ
ያለማወቅ እውቀት ስልጣኔ መስሎን
ልማት ነው እያልን የሙጥኝ ስላልን
እንጂ…
ብናውቀው ኖሮማ ውበት ቅርስ እንዲሆን…
ብናውቀው ኖሮማ. .
በህይወት ግምጃ ቤት.. ተጥሎ የሚኖር ተምሳሌት እንደሆን
ብናውቀው ኑሮማ
በውበት ብናምርን ቅርስን ብናከብር
ያን ያህል ጨክኖ ይህን የርሷን መንደር
ይህን የእርሷን ሰፈር
ማን ያፈርሰው ነበር።…
ዛሬ…
በዚያ መንደር
ከልጅት መኖሪያ ፍርስራሽ ጣውላ ስር
ከቤተ-መንግስቱ አረንጓዴ ሰፈር
ክፉ ጠረንይዞ ነፋስ ይጓዝ ነበር።
(ኑ፦ግድግዳ እናፍርስ ከተሰኘው መድብል የተወሰደ ገፅ፦84 - 88)
#ገፅ
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ቅዱስ ቁርባን
ወይ ንሰሀ
የቄስ ፍትሃት
ጠበል ውሃ
የመውደዴን ክፉ መንፈስ
አይንቀለው ከላይሽ ላይ
ከጀንበር ሀጥያን መደዳ
በፍቅሬ ሠይጥነሽ ሳላይ
#Yonatan
@getem
@getem
@gebriel_19
ወይ ንሰሀ
የቄስ ፍትሃት
ጠበል ውሃ
የመውደዴን ክፉ መንፈስ
አይንቀለው ከላይሽ ላይ
ከጀንበር ሀጥያን መደዳ
በፍቅሬ ሠይጥነሽ ሳላይ
#Yonatan
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
የኢዮር ቅርንጫፍ፥ የኤረር ተቀጥላ
የሚዘረጋልሽ፥
ዘንባባ እንደጨረር፥ ግራር እንደጥላ
ብስራት
ምድረ ገነት፥
የብርኅን ስነት
የእጽዋት ኪነት
እውን የማይመስል፥ ጥበባዊ ግነት...
ብስራት
የዝምታ ጅረት
የጸጥታ ኩሬ...
እንደፃድቅ ጸሎት፥ እንደ ፆሙ ፍሬ
ለልጅ ልጅ የሚትተርፍ፥ የርጋታ ኑባሬ
ብስራት የከተማ መናኝ
ጩኸትን ባርምሞ ኮናኝ
ድርቀትን ጨለማን ገዛች
"የረጋ ወተት"ን ተራች
ጥድፊያ ግፊያ ላይ ዘባች
ብሥራት
ብሥራተ ገብርዔል... የከተማ መናኝ
ብርኅን ተዘከሪኝ
ለምለም ተዘከሪኝ
እፎይ ተዘከሪኝ፥ ለደጃፍሽ ለማኝ።
#Rediet_aseffa fb
@getem
@getem
@gebriel_19
የሚዘረጋልሽ፥
ዘንባባ እንደጨረር፥ ግራር እንደጥላ
ብስራት
ምድረ ገነት፥
የብርኅን ስነት
የእጽዋት ኪነት
እውን የማይመስል፥ ጥበባዊ ግነት...
ብስራት
የዝምታ ጅረት
የጸጥታ ኩሬ...
እንደፃድቅ ጸሎት፥ እንደ ፆሙ ፍሬ
ለልጅ ልጅ የሚትተርፍ፥ የርጋታ ኑባሬ
ብስራት የከተማ መናኝ
ጩኸትን ባርምሞ ኮናኝ
ድርቀትን ጨለማን ገዛች
"የረጋ ወተት"ን ተራች
ጥድፊያ ግፊያ ላይ ዘባች
ብሥራት
ብሥራተ ገብርዔል... የከተማ መናኝ
ብርኅን ተዘከሪኝ
ለምለም ተዘከሪኝ
እፎይ ተዘከሪኝ፥ ለደጃፍሽ ለማኝ።
#Rediet_aseffa fb
@getem
@getem
@gebriel_19
::ምንኛ ታድሏል የሰነፍ አዕምሮ
እንኳን መማር ቀርቶ ፊደል ሳያጠና
ሁሉንም ያወቀ ይመስለዋልና
አሁን የት ይገኛል ቢፈልጉ ዞሮ
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ
#ከበደ_ሚካኤል
@getem
@getem
@kaleab_1888
እንኳን መማር ቀርቶ ፊደል ሳያጠና
ሁሉንም ያወቀ ይመስለዋልና
አሁን የት ይገኛል ቢፈልጉ ዞሮ
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ
#ከበደ_ሚካኤል
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
ሴሰኛ ስንኞች
ተረከዘ-ሎሚ የትርንጎ ባት'
እንደጪሰኛ አንጀት የረዘመ አንገት'
ካንቺ ጋር አድሬ ነገ ጠዋት ልሙት'
ላፈር አይደለም ወይ የተፈጠርኩት'
ምን ያለ' ከንቱ ነው
እንደው ምን ዓይነቱ፤
ካንቺ ጋር ካደረ
መኖርን ሚጠግብ
ሚናፍቀው ሞቱ።
ምን ሎሚ ተረከዝ
ምን የረዘመ አንገት
ቢኖራትም እንኳ፤
ምንስ ትርንጎ ባት
ቢኖራትም እንኳ፤
ሲያዩት የሚያስደስት
የውብ ሴት ልጅ ገላ፤
ሁልጊዜ እየኝ እንጂ
አያስመኝም ሞትን
አይሸኝ ወደሌላ።
እናማ ሴቲቱ
ካንቺ ጋራ አድሮ እንደው በነጋታው
ከተመኘው ሞቱን፤
አንቺ ሊያሞኝሽ ነው
ሴሰኛ እኮ እንዲህ ነው
እስኪያሳልፍ ሌቱን።
ምን ያለው ከንቱ ነው
እንደው ምን ዓይነቱ፤
ካንቺ ጋር ካደረ እንደው በነጋታው
መኖርን ሚጠግብ
ሚናፍቀው ሞቱ።
ከጭንሽ በገባ እንደው በነጋታው ሞቱን የሚመኝ ሰው፤
ሞቶም ቢሆን እንኳ
የመቃብር ስፍራሽ
ከእርሱ ጋር ቢደርሰው፤
ሞተሽ አግኝቶሽም
ካንቺ ልደርና ነገ ልሙት ይላል
ሞቱም አይመልሰው።
ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@San2w)
8/6/2011 WOLDIA UNIVERSITY
@getem
@getem
@Gebriel_19
ተረከዘ-ሎሚ የትርንጎ ባት'
እንደጪሰኛ አንጀት የረዘመ አንገት'
ካንቺ ጋር አድሬ ነገ ጠዋት ልሙት'
ላፈር አይደለም ወይ የተፈጠርኩት'
ምን ያለ' ከንቱ ነው
እንደው ምን ዓይነቱ፤
ካንቺ ጋር ካደረ
መኖርን ሚጠግብ
ሚናፍቀው ሞቱ።
ምን ሎሚ ተረከዝ
ምን የረዘመ አንገት
ቢኖራትም እንኳ፤
ምንስ ትርንጎ ባት
ቢኖራትም እንኳ፤
ሲያዩት የሚያስደስት
የውብ ሴት ልጅ ገላ፤
ሁልጊዜ እየኝ እንጂ
አያስመኝም ሞትን
አይሸኝ ወደሌላ።
እናማ ሴቲቱ
ካንቺ ጋራ አድሮ እንደው በነጋታው
ከተመኘው ሞቱን፤
አንቺ ሊያሞኝሽ ነው
ሴሰኛ እኮ እንዲህ ነው
እስኪያሳልፍ ሌቱን።
ምን ያለው ከንቱ ነው
እንደው ምን ዓይነቱ፤
ካንቺ ጋር ካደረ እንደው በነጋታው
መኖርን ሚጠግብ
ሚናፍቀው ሞቱ።
ከጭንሽ በገባ እንደው በነጋታው ሞቱን የሚመኝ ሰው፤
ሞቶም ቢሆን እንኳ
የመቃብር ስፍራሽ
ከእርሱ ጋር ቢደርሰው፤
ሞተሽ አግኝቶሽም
ካንቺ ልደርና ነገ ልሙት ይላል
ሞቱም አይመልሰው።
ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@San2w)
8/6/2011 WOLDIA UNIVERSITY
@getem
@getem
@Gebriel_19
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቀንዲል Digital Magazine 01.pdf
7.5 MB
የፍለጋ ህመም
( ኤፍሬም ስዩም )
እኒህ ገጣሚያን
እኒህ ደራሲያን
እኒህ ሰዓሊያን…
ሶስቱ አማልክቶች
ረዳት ፈጣሮች
ሦስቴ ይስታሉ
ሦስቴ ይክዳሉ…
፩
ሃሳቡ ሳይመጣ እንፃፍ ይላሉ
፪
ሃሳቡ እንዲመጣ ሃሳብ ያስባሉ
፫
ሃሳቡ ሲመጣ ሃሳብ ይመርጣሉ
ትተው ይነሳሉ።
0
( ኑ፦ ግድግዳ እናፍርስ ከተሰኘው መድብል የበወሰደ ገፅ፦52 )
ምንጭ #ገፅ
@getem
@getem
@gebriel_19
( ኤፍሬም ስዩም )
እኒህ ገጣሚያን
እኒህ ደራሲያን
እኒህ ሰዓሊያን…
ሶስቱ አማልክቶች
ረዳት ፈጣሮች
ሦስቴ ይስታሉ
ሦስቴ ይክዳሉ…
፩
ሃሳቡ ሳይመጣ እንፃፍ ይላሉ
፪
ሃሳቡ እንዲመጣ ሃሳብ ያስባሉ
፫
ሃሳቡ ሲመጣ ሃሳብ ይመርጣሉ
ትተው ይነሳሉ።
0
( ኑ፦ ግድግዳ እናፍርስ ከተሰኘው መድብል የበወሰደ ገፅ፦52 )
ምንጭ #ገፅ
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ያያቴ ጦርና ፣ ያንቺ ፍቅር
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ስንት ታሪክ ፅፎ
ይዤው የምታይኝ ፣ ያያቴ ጦር እኮ
ሰንደቅ ደፋሪውን
ያንን ነጫጭባ ፣ አሳፍሮ ልኮ
ወይም ደሞ ማርኮ
••••
[ሀገሬን ያቀናው •••
••••••••እሱ ነበር እኮ]
ይሄን ጀብዱ ነበር
እስከዛሬ ድረስ
ብቻዬን ለራሴ ፣ ስነገረው የማውቀው
ታሪክ ሚሉት ወኔ
ሀገሬን የሚያህል ፣ ኩራት ያስታጠቀው
••••••
ልብሽ የማያቀው
ክብርሽ የማያቀው
ይሄ የኔን ታሪክ
ጥላቻ ሚሉት ግንብ ፣ ከገነባሽበት
የዘመተሽ ልቤ
ፍቅርን ላይዋጋ ፣ ከተደበቅሽበት
ለጀግና ውድቀቱ
ድልን ለማጣቱ ፣ አንቺም አለሽበት
ካዲያ አንቺ ካለሽ
ይሄ ሁላ ገድል ፣
ባለበት ታሪክ ላይ
••••የሀገሬ አድዋ ድሉ አያረካም
ፍቅርሽ ለረታው ሰው
መቶ አመት የሞላው
••••ያ ያያቴ ጦር ፣ ስለት አያስመካም
እናም
:
ጀግና የዘመተው
ማለዳ ሚወጣው ፣ የድል አጥቢያ ጀንበር
ፍቅር ሚሉት ፀሀይ
ለመውጣት ተስኖት ፣ ሲጨላልም ነበር
ውጊያው ከባድ ነበር
••••ከዛ ልብሽ ጋራ
ውጊያው ከባድ ነበር
•••• ከፈሪ ሰዉ ጋራ
ፍልሚያ አለው መከራ!
ፍልሚያ አለው መከራ
••••••
[ነገር ግን አደራ]
ስንት ዘመን ሙሉ ሀገሩን ላቀናው
•••••ጀግንነት ለቀናው
ላያቴ ጦር ብለሽ
መሬቱ ላይ ምለሽ
•••በልብሽ መሬት ላይ ፣ እንዋጋ በይኝ
ቀና ስሜት ታጥቀሽ
•••ፍቅር ያነገበ ፣ ጦረኛሽን ቻይኝ
ቻይኝ ጦረኛሽን
ልዋጋው ልብሽን
ልክ እንደ አያቴ ጦር ፣ ድል እንደሚሰራው
ከድል ውጊያ ማግስት
ክብርን ተሸልሞ
እራሱ አያቴ ላይ ፣ ደፍሮ እንደሚኮራው
ማርኮ እንደሚራራው
እንደ እሱ ለመሆን ፣ ነበር የኔ ወኔ
ነገር ግን ባዶ ነው ፣ ምንም የለም ለኔ
[ምንም የለም ለኔ]
ስማረክ ብቻ ነው
ስትረቺኝ ያየሁሽ ፣ ልብ ባለው አይኔ
:
የፍቅር ምርኮኛ
@getem
@getem
@gebriel_19
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ስንት ታሪክ ፅፎ
ይዤው የምታይኝ ፣ ያያቴ ጦር እኮ
ሰንደቅ ደፋሪውን
ያንን ነጫጭባ ፣ አሳፍሮ ልኮ
ወይም ደሞ ማርኮ
••••
[ሀገሬን ያቀናው •••
••••••••እሱ ነበር እኮ]
ይሄን ጀብዱ ነበር
እስከዛሬ ድረስ
ብቻዬን ለራሴ ፣ ስነገረው የማውቀው
ታሪክ ሚሉት ወኔ
ሀገሬን የሚያህል ፣ ኩራት ያስታጠቀው
••••••
ልብሽ የማያቀው
ክብርሽ የማያቀው
ይሄ የኔን ታሪክ
ጥላቻ ሚሉት ግንብ ፣ ከገነባሽበት
የዘመተሽ ልቤ
ፍቅርን ላይዋጋ ፣ ከተደበቅሽበት
ለጀግና ውድቀቱ
ድልን ለማጣቱ ፣ አንቺም አለሽበት
ካዲያ አንቺ ካለሽ
ይሄ ሁላ ገድል ፣
ባለበት ታሪክ ላይ
••••የሀገሬ አድዋ ድሉ አያረካም
ፍቅርሽ ለረታው ሰው
መቶ አመት የሞላው
••••ያ ያያቴ ጦር ፣ ስለት አያስመካም
እናም
:
ጀግና የዘመተው
ማለዳ ሚወጣው ፣ የድል አጥቢያ ጀንበር
ፍቅር ሚሉት ፀሀይ
ለመውጣት ተስኖት ፣ ሲጨላልም ነበር
ውጊያው ከባድ ነበር
••••ከዛ ልብሽ ጋራ
ውጊያው ከባድ ነበር
•••• ከፈሪ ሰዉ ጋራ
ፍልሚያ አለው መከራ!
ፍልሚያ አለው መከራ
••••••
[ነገር ግን አደራ]
ስንት ዘመን ሙሉ ሀገሩን ላቀናው
•••••ጀግንነት ለቀናው
ላያቴ ጦር ብለሽ
መሬቱ ላይ ምለሽ
•••በልብሽ መሬት ላይ ፣ እንዋጋ በይኝ
ቀና ስሜት ታጥቀሽ
•••ፍቅር ያነገበ ፣ ጦረኛሽን ቻይኝ
ቻይኝ ጦረኛሽን
ልዋጋው ልብሽን
ልክ እንደ አያቴ ጦር ፣ ድል እንደሚሰራው
ከድል ውጊያ ማግስት
ክብርን ተሸልሞ
እራሱ አያቴ ላይ ፣ ደፍሮ እንደሚኮራው
ማርኮ እንደሚራራው
እንደ እሱ ለመሆን ፣ ነበር የኔ ወኔ
ነገር ግን ባዶ ነው ፣ ምንም የለም ለኔ
[ምንም የለም ለኔ]
ስማረክ ብቻ ነው
ስትረቺኝ ያየሁሽ ፣ ልብ ባለው አይኔ
:
የፍቅር ምርኮኛ
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1