በሳምንቱ መጨረሻ በለተ ቅዳሜ ፤
በል ቶሎ ናልኝ ፤ አልጠግበውም እና ከንፈርህን ስሜ ።
አና እልሀለሁ
ብዙ ቀን አለፈኝ ፤
ባጉል መሽኮር መሜ ።
እቅፍ አርገኝ እስኪ ፤
ይተወኝ እንደሆን አንተን ተሳልሜ ።
ሉባንጃ እና ብርጉድ፤ አጥነዋለሁ ቤቴን ፤
ባሪቲ እና ከርቤ ያልጋዬን መናገሻ አውጄ ጓዳዬን ።
እጠብቅሀለሁ ነግረኸኛልና
እንደምትወደኝ ፤
ሳትደብቅ ውስጥህን
እንደምታፈቅረኝ ።
ምን እንጠብቃለን ከጉያህ አስገባኝ፤
ያ መጥፎ አባዜ
አንተን ባየሁ ጊዜ ካላሽኮረመመኝ ።
#Yami
@getem
@getem
@gebriel_19
በል ቶሎ ናልኝ ፤ አልጠግበውም እና ከንፈርህን ስሜ ።
አና እልሀለሁ
ብዙ ቀን አለፈኝ ፤
ባጉል መሽኮር መሜ ።
እቅፍ አርገኝ እስኪ ፤
ይተወኝ እንደሆን አንተን ተሳልሜ ።
ሉባንጃ እና ብርጉድ፤ አጥነዋለሁ ቤቴን ፤
ባሪቲ እና ከርቤ ያልጋዬን መናገሻ አውጄ ጓዳዬን ።
እጠብቅሀለሁ ነግረኸኛልና
እንደምትወደኝ ፤
ሳትደብቅ ውስጥህን
እንደምታፈቅረኝ ።
ምን እንጠብቃለን ከጉያህ አስገባኝ፤
ያ መጥፎ አባዜ
አንተን ባየሁ ጊዜ ካላሽኮረመመኝ ።
#Yami
@getem
@getem
@gebriel_19