ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Forwarded from Mykey
መልካም የጥምቀት በዓል!
.
.
.
@Mykeypictures
#Mykeyምስሎች
@Mykey21
(ገሬ ትዛዙ )
ኑ ሀገር እንስፋ......

"ምድረ ሀበሻ ታሞ ፣ አዕምሮው ተነክቶ
ጥለቱን ገንጥሎ ፣ ሲሻማ ቡትቶ
ጥበቡን በሀራጅ ፣ በእጣ ሲከፋፈል
የኔ ጥበበኞች ...
ኑ ሀገር እንስፋ ፣ ኢትዮጵያን ምትመስል"

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ሎሚ ወሳጅ ጠፋ?????!!!!!!!!!

በሃምሌ ተለክፎ ፤
በነሃሴ አፍቅሮ፤ ህዳር የጠናበት ፤
በጥምቀት ይድናል ፤
የመምሬ ጠበል ፤ ውሃ ሲፈስበት ።
ይብላኝ እንጅ ላንች ፤ እኔስ ግዴለኝም ፥
ጥምቀት ከደረሰ ፤
እታጠበዋለሁ ፍቅርሽ አይገለኝም ።
አምና ጉባላፍቶ ፤ ሎሚ እንኪ ብልሽ ፤
ግንባርሽ ተቆጣኝ ፤ አባጨኝ ፊትሽ፤
ዘንድሮ ሸጎቹ ፤ መጡ ሊነጥቁሽ ።
ሎሚ አልከጅል ብለሽ፤ ስትይ ገባ ወጣ ፤
ከእጅ የሚመነጥቅ፤ ሎሚ መጣጭ መጣ ።
እንካ ሲሉት ሎሚ፤ የተግደረደረ ፤
ዘንድሮም እንዳምናው፤ሎሚ ናፍቆ ቀረ ።
ይብላኝልሽ ላንች ፤ ሎሚየን ለናቅሽው ፤
ወዶ መለመንን ፤ ከእንግዲህ ቅመሽው ።
ተሽሎኛል ዛሬ፤ ከአምናው በጥቂቱ ፤
በጠበል ለቆኛል ፤ የመውደድ ግዝቱ ።
ሎሚ ስጠኝ ያልሽው፤ አለቀብኝ እኔ ፤
የስንት ሰው ሎሚ ፤
መጥምጠሽ አኝከሽ ፤
መሮሽ ስትጥይው ፤ እያየሁሽ ባይኔ ።
እቴ በታቦቱ ፤
እቴ በጥምቀቱ ፤ በአድባሩ በአውጋሩ፤
ያንች ሰፈር ልጆች ፤
ሎሚ አንወስድም ብለው ፤ ሎሚ ናፍቀው ቀሩ ።
አንች ባለ ዱኣ ፤
ቀየው የመረቀሽ ፤ በተራ በተራ ፤
እየው በዚያ ሰፈር ፤
ተከምሮልሻል ፤
ሊወረወርብሽ ፤ የሎሚ ተራራ ።
እመጣለሁ ቆንጂት ማለዳ ቀድሜ ፤
ጠበሉን ሲረጩኝ ፤
ከተፋዘዝኩበት፤ ይገለጣል አይኔ ።
አምና በትፍትፍሽ ዛሬ በአንባርሽ ፤
ሎሚ ስወረውር የገረገረሽ ፤
የወደደ ገላ በቀልብ ያሰረሽ፤
ማለዳ ነይና ፤
ሎሚው እንዲቀናሽ ፤ ጠበሉ ይፍታሽ! !!!

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

መልካም የጥምቀት በዓል!!💚💛❤️

የኔዋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
<<ሃምሳ አለቃ ገብሩ>>
‹አንደኛ ታሪክ›
‹አያድርስ እኮ ነዉ!›› አሉና ተከዙ
ሹል ከዘራቸዉን እየወዘወዙ
‹አያድርስ እኮ ነዉ ብቻ ግን ደረሰ
ሚስቴም ኮበለለች ቤቴም ፈራረሰ››
ይህንን የሚሉት ሃምሳ አለቃ ገብሩ
ጥንት ያላየናቸዉ ዛሬም ያልነበሩ
ምናልባት ወደ ፊት ገና የሚፈጠሩ
የስምንተኛዉ ሺ ደግ ሰዉ ነበሩ
ዛሬ ግን ተክዘዉ ቅሬታን አሰሙ
ለነፍስ አባታቸዉ አለቃ ድማሙ
እስቲ እኔ ምን አልኳት ምንድነዉ በደሌ
ቤቴን አክባሪ ነኝ የትዳሬ ሎሌ
ባያድላት እንጂ ደግ እንዳታወራ
ባሳፋሪ ነገር ስሙ ያልተጠራ
ኧረ እንደኔም የለ ጭምቅ አባወራ
ለሚስቴም ታዛዥ ነኝ ትዳሬን አክባሪ
ቤተሰቤን ወዳድ ጋብቻዬን ፈሪ
ይህ ሐሰት ቢሆን
ይመስክል እገሌ ተመስክር እገሊት
እርግጥ አመሻለዉ እስከ እኩለ ለሊት
ቢሆንም! ቢሆንም! በለዉ ተማረሩ
የስምንተኛዉ ሺ አምሳ አለቃ ገብሩ
የገብሩ ነፍስ አባት አለቃ ድማሙ
‹‹ እሷ እኮ የምትለዉ! ›› ብለዉ ሲቃወሙ
‹‹ የሷ ቅጥፈትማ ምናል ባይነሳ
እንደኔ ማ! ነበር-
ሚስቱን የሚናፍቅ ለሚስቱ እሚሳሳ
ይፈልጉ እንደሆን ዕዉነቱን መረዳት
ማንም የለ እንደኔ ሚስቱን የሚወዳት
እርግጥ ነዉ! እርግጥ ነዉ!
( ከአንድ ሁለት ሴቶች ጋር አድሬ ይሆናል )
ቢሆንም! ቢሆንም! አሉ በቅሬታ
አልጥማቸዉ ብሎ የአለቃ ጨዋታ
አስታራቂዉ አባት አለቃ ድማሙ
የሀምሳ አለቃን ብሶት እንደሰሙ
ነጭ ጭራቸዉን እየወዘወዙ
‹‹ መቼ ይህ ብቻ!›› አሉና ተከዙ
‹‹ መቼ ይህ ብቻ እዉነት ከሆነማ ከሆነ ምናልባት››
ብለዉ ሲቀጥሉ አስታራቂዉ አባት
‹‹ ገብቶኛል ገብቶኛል መች አጣዉት እኔ
ለቤቱ አይጨነቅ ሊሉኝ ነዉ ይሔኔ
እስቲ ያሰላስሉት ይታይዎት አባቴ
እንዴት አልጨነቅ እንዴትስ አላስብ ለትዳር ለቤቴ
ሁሌ ደስ እንዲላት ዉዷ ባለቤቴ
ኧረ እጨነቃለዉ ኑሮዬ እንዲሰምር
( እርግጥ የቤት ወጪ ሰጥቻት አላዉቅም)
ቢሆንም! ቢሆንም!😳 እያሉ ሲያቅማሙ
የገብሩ ነፍስ አባት በጣም ተገረሙ
‹‹ እንዳዉ ይህቺ አአለም መቼ ነዉ የሚያልፍላት
አጠፋዉኝ የሚል ሰዉ የሚበቅልባት
መቼ ይሆን ወቅቱ ›› ብለዉ ሲናገሩ
ዕንባ ቀደማቸዉ ሃምሳ አለቃ ገብሩ
‹‹ ልክ ኖት አባቴ-
ጊዜዉ ተበላሽቷል ያለንበት ዘመን
ይቅርታ ጠይቃኝ ጥፋቷን በማመን
ብንኖር ይሻል ነበር ጭቅጭቅ አቁመን
እና እዉነት ብለዋል ምናል ብተፈራ ጡር
በእኔ ይጨከናል በየዋሁ ፍጡር
ሁሌ መፈንጠዝ ነዉ መጫወት ነዉ መሳቅ
ለራሴ የግዜር በግ ክፋትን የማላቅ
እርግጥ አንዳንድ ቀን!!
(በጩቤ አስደንግጫት አስጩኬያት ይሆናል)
ቢሆንም…. ቢሆንም…😜
ይሔን ጥቃቅኑን ካይምሮዋ አዉጥታ
ምናል ብታመጣዉ መልካሙን ትዝታ
አዎ… …
ያ! የጥንቱ ደግ ደጉ ዘመን
መኝታ ቤት ሆነን በፍቅር ሰመመን
ካልጋ እየገፈተርኩ የምወረዉራት
ግድግዳ እያጋጨዉ የማሽቀነጥራት
ምናል ትዝ ቢላት…
ምናል ብታስታዉስ የጥንቱን መዋደድ
እሷም ከሚከፋት እኔም ከምናደድ
በሉ እንግዲ ሂዱ ይህንን ንገሯት
የዋሁ አባወራ ብቻዉን ነዉ በሏት
በቻዉን ነዉ በሏት
ይህንን ንገሯት
ዛሬም ብቻየን ነኝ አላዉቅም የሷን ግን
ጭር ባለ አልጋ ላይ አድራለዉ ስበግን
እርግጥ አንዳንድ ቀን ሲረዝምብኝ ሌቱ
አብራኝ ትተኛለች ሰራተኛይቱ
ቢሆንም… ቢሆንም...😂😂
© ታገል ሰይፉ (ቀፎዉን አትንኩት)
@getem
@kaleab_1888
👍2
# ሳይቀና_ለገነነው

የቀናው ሲጠፋ
እየገነነ ጎብጦ፣
አቀነቀነልን
ጥበብን ገልብጦ፣
የነቀዘው ሁሉ
ዛሬ ላይ ወዛና፣
አሁን ዘመነልን
ቅን'ቅኑን ፈጀና !!

# ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
"ፍራሹም እሾህ ነው
ብርድልብሱም ውጋት ፤
ምን ላይ ተተኝቶ
ይታለማል ንጋት?"

@paappii
@getem

#Teym Tsigereda
#ማሲንቆ_እና_ብቸኝነት
አቅራቢ ፦ቶፊቅ
ገጣሚ ፦ኤፍሬም ስዩም

@getem
@getem
@McTof
#ንጥረ_ነገር
[ፋሲል ስዩም]

የጡሩምባ ዚመት፤
የጡሩምባ ድምፀት፤
ላድማጩ ነው እንጂ፤
ለነፊው ሲቃ ነው፡፡
እያማጡ ነፍተው፤ባወጡት ቅላጼ፤
ፍጋግ ጥርሶች ማየት ምነኛ፤ደስታ ነው/
(ትርጉም)
ተነፊ እና ነፊ
ጡሩምባ ና ስትንፋስ፤
ሰው እና ጭንቀቱ
አድማጭ እና አድራሽ፤
ዕድሜ "ና" ንፍ ትውልድ
ጉላይ የግርድ ድራሽ፡፡
(ትርጉም ሲጥሉበት)
ግጣም አፍራሽ… ፈራሽ….
ግጥም ፈራሽ …አፍራሽ፡፡
17/03/2011
ዲላ

@getem
@getem
@gebriel_19
ግጥም ብቻ
@getem
@getem
@gebriel_19
#ተረጅልኝ ግጥሜን
………………………………
…………ልክ እኮ ነው ያልሽው፡
ግጥሜ ሀዘንን እንጅ…
ደስታን አይነግርሽም፡
አይኔ አለቀሰ እንጅ…
ጥርሴ ሳቀ አይልሽም፡
መጎዳቴን እንጅ…
ባንች መደሰቴን አያሳውቅሽም፡
፩ነቴን እንጅ…
ሠው እንዳለኝ ጭራሽ…እንድታምኝ አይሻም፡
ግን……አትናደጅብኝ ተረጅልኝ ግጥሜን፡
ቢከብደኝ ጊዜ እንጅ…
ብዕር አስነብቸ…ለመንገር ደስታየን፡
ብፈልግማ ኮ……
የሳቅሁትን ሳይሆን ልስቅ ያሠብኩትን፡
ውስጤ ጭንቁን ትቶ የልቤ ሀሴቱን፡
ቅሬታውን ረስቶ ባንች መደሰቱን፡
ይነግርሽ ነበረ…………
ግን……እባክሽን ውዴ ተረጅልኝ ግጥሜን፡
ከዘመኑ ሠው ጋ…እንባ ከሚያስቀው፡
መሀረብን ነፍጎ…ከንፈር ከሚመጠው፡
ያንተ መውደቅ ለኔ ከሚል መነሻ ነው፡
ሊመደብ አይሻም ሊያጣ ህሊናውን፡
በብእሩ ዕንባ…ሊነግርሽ ደስታውን።

#ተፃፈ_በዳዊት_ሠለሞን


@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ሃምሳ አለቃ ገብሩ (ሁለተኛ ታሪክ) ታገል ሰይፉ (ቀፎዉን አትንኩት)

‹‹ የዛሬዉ ለጉድ ነዉ!›› ብለዉ ተናገሩ
ከነከዘራቸዉ ደጃፍ እንደቆሙ
‹‹ ጥላኝ ማደሯ ነዉ›› ሲሉ ደነገጡ
‹‹ ፈጽሞ አይደረግም!›› መልሰዉ ተቆጡ፡፡
ይህንን በቅናት ሲያስቡ ሃምሳ አለቃ
መጣች አመሻሽ ላይ ነጠላ አዘቅዝቃ
ትንሽ ስላስፈራት ያምሳለቃ ነገር
ገና ሳትጠየቅ ጀመረች መናገር፡፡

‹‹ ይኼዉሎት ዛሬ የደብሬ ባል ሞቶ
ጎረቤቱ ሁሉ ከቤትዋ ተገኝቶ
ሲያጽናናት አምሽቶ ሲያጽናናት እንዲያድር
ተመካክሮ ነበር ተሰብስቦ በእድር
እኔ ግን ሳስበዉ ቁጣዎትን ፈርቼ
ሠፈር ጉድ እያለኝ ሁሉን ነገር ትቼ
መጣሁኝ›› እያለች ብዙ ስታወራ
ያጣድፏት ጀመር በያዙት ከዘራ፡፡

ወዲያዉ ተፈንክታ ብትሆንም ደም በደም
የሀምሳለቃ ገብሩ ንዴት አልበረደም፡፡
በሚስታቸዉ ጩኸት ቤቱ ሲበጠበጥ
ምድጃዉ ተደፍቶ ድስቱ ሲገለበጥ
የቤቱን ሁካታ ከሩቅ ስለሰሙ
የነፍስ አባታቸዉ አለቃ ድማሙ
ከየት መጡ ሳይባል ገቡ እየተከዙ
ነጭ ጭራቸዉን እያወዛወዙ፡፡
ቆም ብለዉ ሲያዩት የሀምሳ አለቃን ጥፋት
የሚስትየዉን ደም የወጡን መደፋት
በጣም አዘኑና ተክዘዉ ሲያበቁ
‹‹ አዬ ያንተ ነገር›› ተደነቁ፡፡

‹‹ ያኔ ከሚስት ጋር ተዉ አስታርቁኝ ሰትል
እንኳን በከዘራ ዝንቧን እሽ ላትል
ምለህም አልነበር ›› ተገረሙ
የገብሩ ነፍስ አባት አለቃ ድማሙ
‹‹ ልክ ኖት አባቴ ሚስቴን አልጠላትም
እንኳን በከዘራ በጣቴ አልነካትም
ብቻ ግን ለከርሞዉ… ለከርሞዉ ምናልባት
ያመሸችዉ ማምሸት ጥፋቷ እንዲገባት
ላስፈራራት እንጂ ከዘራ ማንሳቴ
በሚስቴ መጨከን አይችልም አንጀቴ
ይህንን ጥፋት ብለዉ ባያዉኩኝ ምናል
በርግጥ ግንባሯ ላይ ፈንክቻት ይሆናል
ቢሆንም… ቢሆንም…
የገብሩ ባለቤት ይህን እንደሰማች
‹‹ አይሄሄ!›› በማለት ቁጣዋን አሰማች፡፡

አላስጨረሷትም ሀምሳአለቃ ገብሩ
‹‹ አይስሟት አባቴ! ›› ብለዉ ተናገሩ፡፡
‹‹ አይስሟት አባቴ የሚስቴን ምህኛት
አብሬዉ ካላደርኩ በቻዉን መተኛት
በጣም ያስፈራዋል ልትል ነዉ ይሔኔ
የሷን ከንቱ ቅጥፈት መች አጣዉት እኔ
እኮ እኔ ነኝ ፈሪ ከነፍሴ እምሳሳ
ሀገር ያደነቀኝ ጀግና ነኝ አንበሳ
ኮርያ ዘማች ነኝ ኮንጎም አልቀረዉም
እርግጥ የዉጊያዉ ለት በስፍራዉ የለዉም
ቢሆንም ቢሆንም ሲሉ ለመሟገት
‹‹ ፍከራዉን ተወዉ ገብቶኛል ጠባችሁ
አዳምጨዋለዉ ቆሜ በደጃችሁ
ደብሬን ያህል ወዳጅ ባሉዋ ሲሞትባት
ሲሆን ዉላ ድራ ማጽናናት ሲገባት
እንደ ዕባብ ቀጥቅጠህ ሚስትህን ትገላት
የዛሬን እንተወዉ አንተም አርፈ ተኛ
ዉግዝ ከማርዮስ አትንካት ዳግመኛ››
ብለዉ ገሰፁና እንደልማዳቸዉ
አለቃም ወደቤት ገብሩም ወደአልጋቸዉ

ምሽቱ ወደሌት ሰቀየር ሲለወጥ
በድንገት ሸቷቸዉ ያ! የተደፋ ወጥ
ነገሩን ሲያስቡት ብስጭትጭት አሉና
ኧረ ለመሆኑ ጉድሽ መች ያልቅና
ምንስ ጥንቁቅ ብሆን በሚስቴ እምቀና
ደብሬን ያህል ወዳጅ ባለቤትዋ ሞቶ
ጎረቤቱ ሁሉ በስፍራዉ ተገኝቶ
እያስተዛዘነ እያጽናናት ሲያድር
በተከበርኩበት በኖርኩበት ዕድር
ማን ክፉ እንዲባል ነዉ
ማንን ለማሳጣት የህንን ያሰብሽዉ
ከሰዉ ተነጥለሽ ቤትሽ የገባሽዉ
አሉና ተነሱ ከነከዘራቸዉ
በስስ ካናቴራ በረጅም ቁንጣቸዉ

© ታገል ሰይፉ (ቀፎዉን አትንኩት)

@getem
@getem
@gebreil_19
👍1
ንሰሀ ስንቴ ነዉ?

ጥፋቴን አምኘ ላልሰራው እምላለሁ
ሁለተኛ ብየ ቃልም እገባለሁ
ባሁኑ ጥፋቴ በጣም ተፀፅቼ
ሁለተኛ ላልደግም ቃልኪዳን ገብቼ
ንሰሀ ገባሁኝ ሁሉንም ረስቼ
ግን
ንሰሀ መግባቴ ላንድ ቀን ነበረ
ደግሞ
ዳግም ሰራሁትኝ ኧረ ልቤ አረረ
ደግሞ ተፀፅቼ ንሰሀ ገባሁኝ
ዳግም እንደገና ጥፋትን ሰራሁኜ
እስኪ ፍረዱልኝ እናንተ ሰወቹ
ወገኔ እኮ ናችሁ ምከሩኝ አትሠልቹ
ምከሩኝ ተዉ እንጂ ወዳጅ ለመቸ ነው
እኔስ ግራ ገባኝ ንሰሀ ስንቴ ነው?

ማሂ

@getem
@getem
@gebriel_19
*ንስሀ*
....
ለሀዘኔ ደስታ፤ለበሽታዬ ፈውስ ፣
ካንተ እ'ሻ ነበር መንፈሴን ለማደስ ፣
ገና ከሩቅ ሳይህ ልቤ ይሸበራል
ካ'ጠገቤ ስትሆን ይርዳል አካሌ ፣
ንቄ ትቼው እንጂ ደስ ብሎኝ አይደለም
ትርፍ ሰው መባሌ ፣
ስትርቅ ስመልስህ፣ስትሄድ ሳመጣህ ፣
እኔው በገዛ'ጄ ቅብጠት አስተማርኩህ ፣
ከኔ ምን እንዳጣህ ባይገባኝም ቅሉ ፣
በእጅ የያዙት ወርቅ መዳብ ነዉ እንዲሉ፣
ሌባም ይልሰዋል ዳቦውን ላመሉ ።
ይቺም ዘዴ ሆና በ'ረዳለሁ ሰበብ፣
አመልህ ነው አንተ መግጠም ከአህዛብ..
ነገራችሁ ግራ፤አንተም እሷም ግራ ፣
እንዴት ይመራዋል ደንባራን ደንባራ..?
ፈጣሪ ሲልልኝ በጊዜ ስነቃ ፣
ከህመሜ ዳንኩኝ ካንተ ፍቅር ሲቃ ፣
ግን ውዴ ልምከርህ በል ግባ ንስሀ ፣
ማተብክን በጥሶ፤ወደ ጥልቁ ወስዶ
ሳያሰምጥህ ውሀ ።
11/5/11
ባ/ዳር
ማኅሌት ሞላ.....

@getem
@getem
👍1
(ኪራ የላቀች ልጅ)
ሁለት ገፅ አንብቤ ፣ ሁለት መስመር ፃፍኩኝ
"ቁንፅል" ነህ እያሉ ፣ ሰዎቹም ሳቁብኝ
እኔም እስቃለሁ ......
የኔን ጅምር ይዞ ለመፃፍ ለሚመኝ፡፡
13/8/2010 Ju


""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
(ያወቁትን ሁሉ ለመሆን ፣ ለማድረግ ወይንም ለመምሰል መጣጣር ትርፍ አንጀት ባያስይዝም ትርፍ ነገር ነው፡፡ ሰው ታዲያ ሳይጎድለው ትርፍ ነገርን ለምን ይፈልጋል? ለመሙላት ግን አዕምሮቹ እስከፈቀደ ጫንቃቹ እስከቻለ እግራቹ እሳካልዛለ ድረስ ፈልጉ ሞክሩ)..

@getem
@getem
@gebriel_19
**እከኬ እና እከካቸው(ልዑል ሀይሌ)
ጥፍሬ እደግልኝ
ይህ ገላዬን ቧጥጠው፤
ይሁን ጨክንበት
እከካም ለሚል ሰው
ለእልፍ ተሳዳቢ
አሳልፈህ ስጠው፤
.
ቧጭረው የኔን ገላ
ቧጥጠው የኔን ገላ፤
አላምድልኝ ጎኔን
ሃገር ሲቦጭቀኝ አፈር እንዳልበላ፤
.
ቧጭረኝ!
ቧጭረኝ! ቧጭረኝ!
ቧጭረኝ ቧጭረኝ ጥፍሬ፤
ጠባሳ አኑርልኝ
አላምደኝ ስቃዩን አላምደኝ ችግሬን፤
.
ተወው ለኔ ተወው!..
እከካም ሚለውን
ካፉ እየተቀበልኩ እላለሁ እከካም፤
ከኔም አይደርስብኝ
ጥፍራም ሰው ቢሞላም
ተባይን ሲያሳድድ ቁስል አይለካካም፤
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
....የእኔነት በሽታ....

ነይ ትንሽ እንሁን ፤
ነይ ትንሽ እንቆዝም፤
ነይ ትንሽ እንውረድ፤
ነይ ትንሽ እናዝግም።
ብቻ እንቺ እሺ በይ~ብቻ እንቺ ፍቀጂ፤
ትንሽ ሀሳብ ይዘን፤
እንውረድ፤
ውረጂ።
ትንሽ ዘረኝነት፤
ትንሽ ማፈናቀል፤
ትንሽ ሰው ማባላት፤
ትንሽ ሀሳብ ማብቀል።
ትንሽ ወህኒ-ማውረድ፤
ትንሽ ማተራመስ፤
ሀረር እንዳትቆም፤
ምሰሶውን ማፍረስ።
ብቻ እንቺ እሺ በይ~ብቻ እንቺ ፍቀጂ
ሰው ጤፉ እንሁን ፤
እንውረድ
ውረጂ።
...
ምን አልባት ስንወረድ
መቀመቁ ቀርቦን፣
የሰው እንባ አስውቦን፣
የደሀ እንባ ሞልቶ
መመለሻ ካጣን!
ሀገር አጣች እንጂ
እኛማ....
ምን አጣን????
(እኔ ብቻ ነኝ የሚል ሰው አያናድም)

......ፍቅር ስዩም...

@getem
@getem
@gebriel_19
🤩1
አብለኔ

አብለኔ ሰጥቶኛል አንችን ስጦታዬን
በአይኔ ሳይሽ ብቻ ፍቅርን መጥገብያዬን
አብለኔ ሰጥቶኛል አንችን የኔ ደስታ
ነፍሴ እንድትኖር በፍቅርሽ ተረታ
አብለኔ ሰጥቶኛል አንችን የእኔ ንግስት
በልቤ እነዳኖርሽ እንደ አባቴ እርስት
አብለኔ ሰጥቶኛል አንችን የኔ ፍቅር
ሳስደስትሽ ኖሬ ስደሰት እንድኖር ።

ተፃፈ በእኔ(mame) 12/05/2011

@getem
@getem
@gebriel_19
👍2
ስቀሽ … አበረድሽኝ

ከጥም ቆራጭ ምንጭሽ ፥ ልጠጣ ጎምጅቼ
ላታልልሽ ዝቼ
ጢሜን ተላጭቼ
ጫማዬን አጥድቼ
በሚያሽበለብል ቃል ፥ ምላሴን ገርቼ
ለበአሌ ላርድሽ ፥ ቢላዋየን ስዬ
ሁዳዴን የጦመ ፥ መልካም ሰው መስዬ
እንደ አታላይ ተኩላ
ሊነጥቅ ሊበላ
ለምድ እንደለበሰ ፥ በበጎች መካከል
ሳር መጋጥ ጀምሮ ፥ መንጋውን ለመምሰል
በዚያው እንደቀረ ፥ ከሰርዶ ተዋዶ
ጨዋታ ወግሽን ፥ ዠሮየ ተላምዶ
ፍቅር አልብሰሽኝ
ውሀ ልሰርቅሽ ስል ፥ እርጎ አበድረሽኝ
ነድጄ መጥቼ ፥ ስቀሽ አበረድሽኝ

( ናትናኤል ጌቱ )
@getem
@getem
@gebriel_19
የሴት ጭን ሲነሳ ....
(Gere tizazu)
ቀይ ጭኗ ተከፍቶ መዳፏ አርፎበታል ልብሷን እያሸሸ
ልቤ እንዳልሻፈደ ቅንዝረኛ እቃየ በፍርሀት ሟሸሸ
ድንግል ናት አውቃለሁ ህጓ አልተቀደደም
አንሶላው በራሱ ጠምቶታል የሴት ደም

ሙክት ወንድ አግብታ ፣ የመታረስ አምሮት እያንገበገባት
ሺ አመት ተጎልታ ፣ ሀገሬ ድንግል ናት፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
ሌላው ይቅር እንጂ
ቤተስኪያን ስትሄጂ
ጽድቅን ልትቀጂ
እኔም ተከትየሽ
የሳምሽዉን አጥር
ሳልስመው አላድር
በግንቡ ዲንጋዮች
ባሉት ቀዳዳዎች
ያንቺ ውብ ከንፈሮች
ይቀራሉ ብየ ማሰቡን አልሰለች
ቃኤል

@getem
@getem
@gebriel_19