በክብ ሰፌዳችን
ህብረ ቀለማት ነን
ከአፈር የተቀመምን
በሰማያዊ ጣት
ሰበዝ ተሰብዘን
ስፌት ጥበብ ሆነን
ረቂቅ ምስል ሰርተን
በርሱ የተሰፋን
ሸጋ ቀን!!💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
ህብረ ቀለማት ነን
ከአፈር የተቀመምን
በሰማያዊ ጣት
ሰበዝ ተሰብዘን
ስፌት ጥበብ ሆነን
ረቂቅ ምስል ሰርተን
በርሱ የተሰፋን
ሸጋ ቀን!!💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
የሆነ ሰካራም
...................
.
የሆነ ጠጅ ቤት የሆነ ሰካራም
በወጋችን መሃል አለኝ <<ቤት አልሰራም..!>>
.
ለምን ? ያልሁት ግዜ..!
.
<<አሁን በዚች አገር
የቀለሱት ጎጆ የከለሉት አጥር
መች ይሰነብታል ?
እነ-ዘር አዝማሪ ይመነግሉታል..!>>
---------------
ኑርዬ አያሌው (ሉሲ)
@getem
@kaleab_1888
...................
.
የሆነ ጠጅ ቤት የሆነ ሰካራም
በወጋችን መሃል አለኝ <<ቤት አልሰራም..!>>
.
ለምን ? ያልሁት ግዜ..!
.
<<አሁን በዚች አገር
የቀለሱት ጎጆ የከለሉት አጥር
መች ይሰነብታል ?
እነ-ዘር አዝማሪ ይመነግሉታል..!>>
---------------
ኑርዬ አያሌው (ሉሲ)
@getem
@kaleab_1888
👍1
<<በላይ በቀለ ወያ>>
ከነዚህ ውጪ
ነፃ አውጪ
ህዝቡን ጥሎ ፣ ሸሽቶ ነበር ፣ ወደ ውጪ (ኢመኑኝ ርዕስ ነው)
(ታላቁ ሩስያዊ ፈላስፋ በበወቪስኪ እንደፃፈው)
.
.
እውነት ግን እውነት ግን
ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ፣ ወደ ሀገር የመጣው
ድንገት የለማ ቲም ፣ ነፃ ባያወጣው
ምንድን ነበር እጣው?
።።።
ዛሬ እንደልባቸው
ነፃ አውጪ ነን ብለው ፣ ሀገር ሚቀውጡት
ያኔ የት ነበሩ...
ደርግ ጥሎት ሲሔድ ፣ ደርግ ሆነው የመጡት
ህዝቡን እንደጫማ ፣ ሲያስሩና ሲረግጡት?
የድል አጥቢያ አርበኞች ፣
የት ጠፍተው ነው ያኔ ፣ ዛሬ የሚቀብጡት?
ብዬ አልጠይቅም ፣ ምላሹን ሳላጣው
ነፃ አውጪ ነኝ በሚል...
መጨቆን ነውና ፣ የዚህ ህዝብ እጣው
እስከማውቀው ድረስ
ባለሁበት ሀገር
ነፃ አውጪ ብቻ ነው ፣ ነፃ የሚወጣው!
(እኔ ነፃ አውጪ ሳውቅ
የህዝቡን ደም ሳይሆን
እንደ አጤ ቴዎድሮስ ፣ ሽጉጥ ነው ሚጠጣው
@getem
@getem
@kaleab_1888
ከነዚህ ውጪ
ነፃ አውጪ
ህዝቡን ጥሎ ፣ ሸሽቶ ነበር ፣ ወደ ውጪ (ኢመኑኝ ርዕስ ነው)
(ታላቁ ሩስያዊ ፈላስፋ በበወቪስኪ እንደፃፈው)
.
.
እውነት ግን እውነት ግን
ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ፣ ወደ ሀገር የመጣው
ድንገት የለማ ቲም ፣ ነፃ ባያወጣው
ምንድን ነበር እጣው?
።።።
ዛሬ እንደልባቸው
ነፃ አውጪ ነን ብለው ፣ ሀገር ሚቀውጡት
ያኔ የት ነበሩ...
ደርግ ጥሎት ሲሔድ ፣ ደርግ ሆነው የመጡት
ህዝቡን እንደጫማ ፣ ሲያስሩና ሲረግጡት?
የድል አጥቢያ አርበኞች ፣
የት ጠፍተው ነው ያኔ ፣ ዛሬ የሚቀብጡት?
ብዬ አልጠይቅም ፣ ምላሹን ሳላጣው
ነፃ አውጪ ነኝ በሚል...
መጨቆን ነውና ፣ የዚህ ህዝብ እጣው
እስከማውቀው ድረስ
ባለሁበት ሀገር
ነፃ አውጪ ብቻ ነው ፣ ነፃ የሚወጣው!
(እኔ ነፃ አውጪ ሳውቅ
የህዝቡን ደም ሳይሆን
እንደ አጤ ቴዎድሮስ ፣ ሽጉጥ ነው ሚጠጣው
@getem
@getem
@kaleab_1888
🤩1
"" ወንድሜ ብየ የምጠራው ሰው ሰው የምትሸተኝ መሪ አንተ ብቻ ነህ!!!!"" እያለችው
ይመስለኛል!!!!
ወንድም መከታ ነው፤
ማእረጉ ከሰማይ ከምድሩ ይበልጣል ፤
አለሁልሽ ሲለኝ ፤
እንኳን ልቡናየ አይኔም ይገለጣል ።
የምትለውም ይመስለኛል ።
መልካም ምሽት!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
ይመስለኛል!!!!
ወንድም መከታ ነው፤
ማእረጉ ከሰማይ ከምድሩ ይበልጣል ፤
አለሁልሽ ሲለኝ ፤
እንኳን ልቡናየ አይኔም ይገለጣል ።
የምትለውም ይመስለኛል ።
መልካም ምሽት!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
😁2
ዋሾ_ጨረቃ
፧
ጨረቃ ወሬኛ
ጨረቃ......ወሽካታ፣
ባገሬ ሰማይ ላይ
ባይሆኑ ቀን ወጥታ፣
በፀሃይና ምድር
መሃል ላይ....ሰፋሪ፣
ጨረቃ ዋሾ ናት
ጨረቃ.......አቃጣሪ፣
አደናገረችው
ያገሬን......ሰው ሁሉ፣
ያላየውን አምኖ
እንዲምል...በ "አሉ"!!!
፨
# ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
፧
ጨረቃ ወሬኛ
ጨረቃ......ወሽካታ፣
ባገሬ ሰማይ ላይ
ባይሆኑ ቀን ወጥታ፣
በፀሃይና ምድር
መሃል ላይ....ሰፋሪ፣
ጨረቃ ዋሾ ናት
ጨረቃ.......አቃጣሪ፣
አደናገረችው
ያገሬን......ሰው ሁሉ፣
ያላየውን አምኖ
እንዲምል...በ "አሉ"!!!
፨
# ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
ነብስሽን ሳፈቅራት
.
አውቃለሁ...
ግዜውን ጠብቆ፣
እንደ ጠዋት ጤዛ ውበትሽ ይረግፋል
መልክሽም እንደ ቀለድ፣
ልክ እንደ ደመና በድንገት ይጠፋል
አውቃለሁ
ታውቂያለሽ~ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡
ሁሉም ነገር ይለፍ
ውበትሽም ይርገፍ~እኔ ምን አገባኝ
ከስጋሽ ጋ ሳይሆን፣
ከነብስሽ ጋራ ነው ፍቅር የተጣባኝ፡፡
ስጋማ አፈሩ፣
ቤቱ መቃብሩ~ ገርጅፎ ቢጃጅም
ወድሻለሁ ውዴ ነብስሽ አታረጅም።
አካሉ በለጠ
@getem
@getem
@gebriel_19
.
አውቃለሁ...
ግዜውን ጠብቆ፣
እንደ ጠዋት ጤዛ ውበትሽ ይረግፋል
መልክሽም እንደ ቀለድ፣
ልክ እንደ ደመና በድንገት ይጠፋል
አውቃለሁ
ታውቂያለሽ~ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡
ሁሉም ነገር ይለፍ
ውበትሽም ይርገፍ~እኔ ምን አገባኝ
ከስጋሽ ጋ ሳይሆን፣
ከነብስሽ ጋራ ነው ፍቅር የተጣባኝ፡፡
ስጋማ አፈሩ፣
ቤቱ መቃብሩ~ ገርጅፎ ቢጃጅም
ወድሻለሁ ውዴ ነብስሽ አታረጅም።
አካሉ በለጠ
@getem
@getem
@gebriel_19
👍2
~~~ስንፈተ-ጥምረት~~~(ሳሙኤል አዳነ)
*
ገመድ ነው ምላስሽ
ሁሉን ያነካካል ፣
አለንጋ ነው ጣትሽ
ያልበላውን ያካል ።
*
ወታደር ነው እግርሽ
ጠረፍ ይሰደዳል ፣
ደንበርን ተሻግሮ
ሀገሩን ይከዳል ።
*
ልቅ ነው እይታሽ
አይጠነቀቅም ፣
ከሳሽ ነው ልቦናሽ
የሰው ልክ አያውቅም ።
*
እኔ ሆደ ጠባብ
አንች ልብ አውላቂ ፣
እኔ ለዘብተኛ
አንች ወሬ አዋቂ ።
*
ሳቅሽ ጉራማይሌ
ደስታ አያመጣ ፣
ምኑን ረስቸ
ምን ፈልጌ ልምጣ ።
*
እናም ይቅር በይኝ
አልተገናኘንም ፣
አይደለም ጎረቤት
ሀገር አይዳኘንም ።
*******
14/05/2011
3:00am
አ.አ
@getem
@getem
@gebriel_19
*
ገመድ ነው ምላስሽ
ሁሉን ያነካካል ፣
አለንጋ ነው ጣትሽ
ያልበላውን ያካል ።
*
ወታደር ነው እግርሽ
ጠረፍ ይሰደዳል ፣
ደንበርን ተሻግሮ
ሀገሩን ይከዳል ።
*
ልቅ ነው እይታሽ
አይጠነቀቅም ፣
ከሳሽ ነው ልቦናሽ
የሰው ልክ አያውቅም ።
*
እኔ ሆደ ጠባብ
አንች ልብ አውላቂ ፣
እኔ ለዘብተኛ
አንች ወሬ አዋቂ ።
*
ሳቅሽ ጉራማይሌ
ደስታ አያመጣ ፣
ምኑን ረስቸ
ምን ፈልጌ ልምጣ ።
*
እናም ይቅር በይኝ
አልተገናኘንም ፣
አይደለም ጎረቤት
ሀገር አይዳኘንም ።
*******
14/05/2011
3:00am
አ.አ
@getem
@getem
@gebriel_19
✍✍ ስብራት ✍✍
..............ትላንት ስትወደኝ
ከፍቅር መንበሩ ከአውደ ሲመቱ
በሞቀ ፈገግታ ልቤ መረታቱ
ከአድባሩ ቁሜ መዳፌ ካንተ ጋር
በመፅሐፉ ቃላት በእምነት ስታሰር
.............ትላንት ስትወደኝ
ወጣት አዛውንቱ ህፃናቱ ባንድነት ሲስቁ
ደመኞችም ታርቀው በአንድላይ ደመቁ
በፀሎት በኪዳን ሲለመን ከሀገር
ለእኛ አዲሰጠን ስለፍቅር ነገር
ጨረቃ ደመቀች በኮከብ ተሞላ
ደረቁ በረሀ በውሃ ተብላላ
እንደዚ ሁነን ነው
በአንድ የተዋህድ ነው
በፍቅር ተቃቅፈን ፍቅር የሠራነው
ይኸው ዛሬ ነግቶ እኔ ባንኛለሁ
ከሰፊው አልጋላይ ብቻየን ሁኛለሁ
..........ዛሬ አንተ ስተወኝ
የመፅሃፍ ቃላት ሔደው ተሸሸጉ
ፍቅራቸው ቀንሶ ደመኞች መሸጉ
የፍቅር መንበሩ ልቤ ተሰበረ
የሳቄ ፈገግታ በአርምሞ ታሰረ
ከዛሁሉ ደስታ ከዛሁሉ ፌሽታ
ከልቤ ተቀብሮ ሆነብኝ ትዝታ
.............ዛሬ አንተ ስተወኝ
ወጋገኑ ጠፍቶ ጨለማው አይሏል
እኔ ተቀምጬ ሀገር ህልም ያልማል
ፍቅርህ አኬልዳማ ልቤ እያደማ
ጨረቃ አኮረፈች መሔድክን ስትሠማ
................ዛሬ አንተ ስተወኝ
ቃሉን አልጠራውም አፈቀርኩ እያልኩኝ
በማለዳ አፍቅሬ ሲቆይ እየተውከኝ
ከልቤ ባስገባህ ከህይወቴ ጓዳ
ትዝታን ሰጠኸን ለህሊናዬ እዳ
ፍቅሬን ከዳህና ሆንክብኝ ይሁዳ።
.....................//.................
27/12/2010ዓ.ም
✍✍ጃህፈር✍✍
@getem
@getem
@gebriel_1
..............ትላንት ስትወደኝ
ከፍቅር መንበሩ ከአውደ ሲመቱ
በሞቀ ፈገግታ ልቤ መረታቱ
ከአድባሩ ቁሜ መዳፌ ካንተ ጋር
በመፅሐፉ ቃላት በእምነት ስታሰር
.............ትላንት ስትወደኝ
ወጣት አዛውንቱ ህፃናቱ ባንድነት ሲስቁ
ደመኞችም ታርቀው በአንድላይ ደመቁ
በፀሎት በኪዳን ሲለመን ከሀገር
ለእኛ አዲሰጠን ስለፍቅር ነገር
ጨረቃ ደመቀች በኮከብ ተሞላ
ደረቁ በረሀ በውሃ ተብላላ
እንደዚ ሁነን ነው
በአንድ የተዋህድ ነው
በፍቅር ተቃቅፈን ፍቅር የሠራነው
ይኸው ዛሬ ነግቶ እኔ ባንኛለሁ
ከሰፊው አልጋላይ ብቻየን ሁኛለሁ
..........ዛሬ አንተ ስተወኝ
የመፅሃፍ ቃላት ሔደው ተሸሸጉ
ፍቅራቸው ቀንሶ ደመኞች መሸጉ
የፍቅር መንበሩ ልቤ ተሰበረ
የሳቄ ፈገግታ በአርምሞ ታሰረ
ከዛሁሉ ደስታ ከዛሁሉ ፌሽታ
ከልቤ ተቀብሮ ሆነብኝ ትዝታ
.............ዛሬ አንተ ስተወኝ
ወጋገኑ ጠፍቶ ጨለማው አይሏል
እኔ ተቀምጬ ሀገር ህልም ያልማል
ፍቅርህ አኬልዳማ ልቤ እያደማ
ጨረቃ አኮረፈች መሔድክን ስትሠማ
................ዛሬ አንተ ስተወኝ
ቃሉን አልጠራውም አፈቀርኩ እያልኩኝ
በማለዳ አፍቅሬ ሲቆይ እየተውከኝ
ከልቤ ባስገባህ ከህይወቴ ጓዳ
ትዝታን ሰጠኸን ለህሊናዬ እዳ
ፍቅሬን ከዳህና ሆንክብኝ ይሁዳ።
.....................//.................
27/12/2010ዓ.ም
✍✍ጃህፈር✍✍
@getem
@getem
@gebriel_1
👍1
///ጨረቃ ና ናፍቆት///
እቱ የጥንቲቱ
የጥርስሽ ንጣቱ
የጉንጭሽ ቅላቱ
ውል ይለኛል ዛሬም የገላሽ ሙቀቱ
የእግሮችሽ ኮሽታ
የፍቅርሽ ሹክሹክታ
ያ የሣቅሽ ዜማ የበዛው ክትክታ
ይሠማኛል ዛሬም ናፍቆት ሲበረታ
እቱ የጥንቲቱ
አንቺም ትዝ ካለሽ ካለብሽ ናፍቆቱ
ይህ ነው መዳኒቱ
ባስለመድኩሽ ሰዓት ባለሽበት ቦታ
ቀና በይ ላንድ አፍታ
እኔም ባለሁበት ባስለመድሽኝ ሰዓት
ዓይኖቼን አቅንቼ
ጨረቃን አይቼ ልግባ ተፅናንቼ
አንቺም በዚያች አፍታ
ጨረቃዋን ፈክታ
ካየሻት ተጽናኚ
በይ ቃሌን እመኚ
ምንም ብንራራቅ ካንድ ሰማይ ሥር ነን
ነገ አብረን ለመኖር ታላቅ ተሥፋ አለን
(ሳምሶን መኮንን)
@getem
@getem
@gebriel_19
እቱ የጥንቲቱ
የጥርስሽ ንጣቱ
የጉንጭሽ ቅላቱ
ውል ይለኛል ዛሬም የገላሽ ሙቀቱ
የእግሮችሽ ኮሽታ
የፍቅርሽ ሹክሹክታ
ያ የሣቅሽ ዜማ የበዛው ክትክታ
ይሠማኛል ዛሬም ናፍቆት ሲበረታ
እቱ የጥንቲቱ
አንቺም ትዝ ካለሽ ካለብሽ ናፍቆቱ
ይህ ነው መዳኒቱ
ባስለመድኩሽ ሰዓት ባለሽበት ቦታ
ቀና በይ ላንድ አፍታ
እኔም ባለሁበት ባስለመድሽኝ ሰዓት
ዓይኖቼን አቅንቼ
ጨረቃን አይቼ ልግባ ተፅናንቼ
አንቺም በዚያች አፍታ
ጨረቃዋን ፈክታ
ካየሻት ተጽናኚ
በይ ቃሌን እመኚ
ምንም ብንራራቅ ካንድ ሰማይ ሥር ነን
ነገ አብረን ለመኖር ታላቅ ተሥፋ አለን
(ሳምሶን መኮንን)
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
በላይኛው ቀርሳ፣
በታችኛው አውሳ፣
እየተናጠረች፣
በሽንሽን ቀሚሷ፣
ድረስልኝ ብላ፣ ጁምኣ ልካብኝ፣
እረግ ነገ ደግሞ፣
ባቲ አጣሪ ገንዳ፣ ቀጭን ሀጃ አለብኝ፣
አውሳ በር፣
አግኝቸሽ በነበር!!!
አጣሪ ገንዳ፣
ሙቸልሽ ነበረ፣ በሃድራ ስነዳ።
ገንደድዩ፣
መገን እንሶሱላ፣መገን ቀጠናዩ።
ይኸው ደሞ ዛሬ፣
በቀርሳ ብርቱካን፣ ደብዳቤሽ ተጣፈ፣
ጥርስሽ ውልብ አለኝ፣
እንደትርሙብሌ፣እየተሰለፈ።
አለብኝ ፣
አለብኝ፣
ባቲ ያሉ ጊዜ ፣
ሸጋና ደም ግባት፣ ከተፍ እሚልብኝ።
ቅዳሜ በሸጋ፣
ቅዳሜን በሙና፣
ብቅ ያለች እንደሆን፣ በሃድራው መኪና፣
እንደ አፋር ምንሽር፣አምራ ተሽሞንሙና።
መስፈሪያው ባቲ ነው፣ ዛትና ቁመና።
እንደ ብርቱካኑ፣ እንደ ማር ወለላ፣
ሀቂቃ አይደለም ወይ፣
የጠየመ ከንፈር፣ የመከከ ገላ፣
ቀርሳ ላይ ተጋግሮ፣ ባቲ ላይ ሲበላ።
ዘለቀች ልጅቱ፣
ደሞ ጀማመረች፣
በደመነው ሰማይ፣ ብርድ እያባረረች፣
ሀድራ ተሟሙቃ፣ ቡና እየካደመች፣
እኔን የማይበርደኝ፣ ባቴን ነው እያለች።
ከመንዙማ መሃል፣
መደዱን ጎንጉና፣ ተቀኘችላችሁ፣
" ባቴን ተረከዜን፣ ላኩልኝ ብያችሁ፣
ምነው ባቴን ብቻ፣ታስቀሩታላችሁ። "
ቅዳሜና ናፍቆት፣ ሃድራና ዝየራ፣
እንዴት ይጣፍጣል፣ከባቲዎች ጋራ።
አሳ በራ ጊቴ፣
አውቶብስ የሚቴ፣
ቡርቃ ተረከዜ፣
ሃውሳ መቀነቴ፣
እንደ አጀብ፣ ይቀልጣል ቅዳሜና ባቴ።
ያች የሀድራ ሹፌር፣
ድረስልኝ ብላኝ፣ ልካለች ከባቲ፣
ባቲና ቅዳሜ፣ቅዳሜና አሽኩቲ፣
ሀድራና መቀነት፣ ጀምኣና አርቲ፣
እየጎዘጎዘች፣ ድረሱልኝ ካለች፣
መገን ድረሱላት፣ ሀጃ ታወጣለች፣
ቅዳሜም ይቀልጣል፣ ባቲም ትነዳለች።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!!!
ሸጊቷ ቅዳሜ!!!!!
ዘበናይ ቅዳሜ!!!!!!!!!
ሽሙንሙን ፣
ሽሙንሙን፣
ሽቅርቅር፣
ፍንድቅድቅ፣
ፍልቅልቅ በይልኝ፣
ሳቄ ይቀድመኛል፣
ሰማዩ ሲገለጥ፣ አንች ስትመጭልኝ።
ቅዳሜያችን፣
የቅኔ ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ የእሁድን እረፍት እያሰብን
የምንወዳቸውን መፅሃፍት
የምናነብባት፣ ነፍስያችንን በቅጡ ለማዳመጥ ፋታ
የምንወስድባት፣ ከወዳጅ ዘመድ የምንዘያየርባት ደርባባ
ቀናችን ናት!!!!!
#የኔዋ ቅዳሜ!!💚💛❤
ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንላቹ...ወርቆቼ!!!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
በታችኛው አውሳ፣
እየተናጠረች፣
በሽንሽን ቀሚሷ፣
ድረስልኝ ብላ፣ ጁምኣ ልካብኝ፣
እረግ ነገ ደግሞ፣
ባቲ አጣሪ ገንዳ፣ ቀጭን ሀጃ አለብኝ፣
አውሳ በር፣
አግኝቸሽ በነበር!!!
አጣሪ ገንዳ፣
ሙቸልሽ ነበረ፣ በሃድራ ስነዳ።
ገንደድዩ፣
መገን እንሶሱላ፣መገን ቀጠናዩ።
ይኸው ደሞ ዛሬ፣
በቀርሳ ብርቱካን፣ ደብዳቤሽ ተጣፈ፣
ጥርስሽ ውልብ አለኝ፣
እንደትርሙብሌ፣እየተሰለፈ።
አለብኝ ፣
አለብኝ፣
ባቲ ያሉ ጊዜ ፣
ሸጋና ደም ግባት፣ ከተፍ እሚልብኝ።
ቅዳሜ በሸጋ፣
ቅዳሜን በሙና፣
ብቅ ያለች እንደሆን፣ በሃድራው መኪና፣
እንደ አፋር ምንሽር፣አምራ ተሽሞንሙና።
መስፈሪያው ባቲ ነው፣ ዛትና ቁመና።
እንደ ብርቱካኑ፣ እንደ ማር ወለላ፣
ሀቂቃ አይደለም ወይ፣
የጠየመ ከንፈር፣ የመከከ ገላ፣
ቀርሳ ላይ ተጋግሮ፣ ባቲ ላይ ሲበላ።
ዘለቀች ልጅቱ፣
ደሞ ጀማመረች፣
በደመነው ሰማይ፣ ብርድ እያባረረች፣
ሀድራ ተሟሙቃ፣ ቡና እየካደመች፣
እኔን የማይበርደኝ፣ ባቴን ነው እያለች።
ከመንዙማ መሃል፣
መደዱን ጎንጉና፣ ተቀኘችላችሁ፣
" ባቴን ተረከዜን፣ ላኩልኝ ብያችሁ፣
ምነው ባቴን ብቻ፣ታስቀሩታላችሁ። "
ቅዳሜና ናፍቆት፣ ሃድራና ዝየራ፣
እንዴት ይጣፍጣል፣ከባቲዎች ጋራ።
አሳ በራ ጊቴ፣
አውቶብስ የሚቴ፣
ቡርቃ ተረከዜ፣
ሃውሳ መቀነቴ፣
እንደ አጀብ፣ ይቀልጣል ቅዳሜና ባቴ።
ያች የሀድራ ሹፌር፣
ድረስልኝ ብላኝ፣ ልካለች ከባቲ፣
ባቲና ቅዳሜ፣ቅዳሜና አሽኩቲ፣
ሀድራና መቀነት፣ ጀምኣና አርቲ፣
እየጎዘጎዘች፣ ድረሱልኝ ካለች፣
መገን ድረሱላት፣ ሀጃ ታወጣለች፣
ቅዳሜም ይቀልጣል፣ ባቲም ትነዳለች።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!!!
ሸጊቷ ቅዳሜ!!!!!
ዘበናይ ቅዳሜ!!!!!!!!!
ሽሙንሙን ፣
ሽሙንሙን፣
ሽቅርቅር፣
ፍንድቅድቅ፣
ፍልቅልቅ በይልኝ፣
ሳቄ ይቀድመኛል፣
ሰማዩ ሲገለጥ፣ አንች ስትመጭልኝ።
ቅዳሜያችን፣
የቅኔ ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ የእሁድን እረፍት እያሰብን
የምንወዳቸውን መፅሃፍት
የምናነብባት፣ ነፍስያችንን በቅጡ ለማዳመጥ ፋታ
የምንወስድባት፣ ከወዳጅ ዘመድ የምንዘያየርባት ደርባባ
ቀናችን ናት!!!!!
#የኔዋ ቅዳሜ!!💚💛❤
ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንላቹ...ወርቆቼ!!!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
"እኔ_ደግሞ …."
(አሌክስ አብርሃም)
ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……
፡
እኔ ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።
፡
ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ
፡
እኔ ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።
፡
ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።
፡
ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።
፡
ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ
፡
እኔ ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።
፡
ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።
፡
በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….
፡
እኔ ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።
፡
የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።
፡
እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!
@getem
@getem
@gebriel_19
(አሌክስ አብርሃም)
ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……
፡
እኔ ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።
፡
ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ
፡
እኔ ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።
፡
ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።
፡
ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።
፡
ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ
፡
እኔ ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።
፡
ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።
፡
በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….
፡
እኔ ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።
፡
የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።
፡
እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
<እንትናዬ 1>
.
.
'እንትና'ን ልክሰሰው በፍቅር ፍርድ ቤት ፣
ሆኖልኝ ብረታው ባሸንፈው ድንገት ፣
ምናልባት ያቺ 'ሴት' በጣም የሚወዳት፣
ገንዘቡን ጊዜውን የሚገብርላት ፣
አብራው ባትነሳ ባትሟገትለት፣
አቁሜ ልውቀሰው ላዋርደው እሰው ፊት፣
ሸጦ ሄዷልና የኔነቴን ንብረት ።
በል ቅርብኝ አንተስ ሳምንህ ከድተኸኛል፣
ወዳጄ ነው ስልህ ሳምንህ ከድተኸኛል ፣
የኔን 'ፍቅር' ለሷ አጉዘህ ወስደሀል ።
ለቃሉ ታማኝ ነው ብዬ ሳሞካሽህ
ባንተ ላይ ስመካ፣
ከቃላችን በላይ እጅህን ያሰረህ
'ሀይማኖት' ነው ለካ ፣
ፍቅሬን ገፍተህ ሄደህ፤ይቅር በይኝ ብለህ
ብትመጣ ከደጄ፣
እኔም ልክ እንዳንተ እንዳልቆይህ ፍራ
'ሌላ ሰው' ለምጄ።
.
.
18/5/11
<ማኅሌት ሞላ>
@getem
@getem
.
.
'እንትና'ን ልክሰሰው በፍቅር ፍርድ ቤት ፣
ሆኖልኝ ብረታው ባሸንፈው ድንገት ፣
ምናልባት ያቺ 'ሴት' በጣም የሚወዳት፣
ገንዘቡን ጊዜውን የሚገብርላት ፣
አብራው ባትነሳ ባትሟገትለት፣
አቁሜ ልውቀሰው ላዋርደው እሰው ፊት፣
ሸጦ ሄዷልና የኔነቴን ንብረት ።
በል ቅርብኝ አንተስ ሳምንህ ከድተኸኛል፣
ወዳጄ ነው ስልህ ሳምንህ ከድተኸኛል ፣
የኔን 'ፍቅር' ለሷ አጉዘህ ወስደሀል ።
ለቃሉ ታማኝ ነው ብዬ ሳሞካሽህ
ባንተ ላይ ስመካ፣
ከቃላችን በላይ እጅህን ያሰረህ
'ሀይማኖት' ነው ለካ ፣
ፍቅሬን ገፍተህ ሄደህ፤ይቅር በይኝ ብለህ
ብትመጣ ከደጄ፣
እኔም ልክ እንዳንተ እንዳልቆይህ ፍራ
'ሌላ ሰው' ለምጄ።
.
.
18/5/11
<ማኅሌት ሞላ>
@getem
@getem
።።።ፅኑ እስራት።።።።
ልብህን ማርኬ ብሆን ወንጀለኛ
ፍርድን ይሠጠን ዘንድ ብንሄድ ወደ ዳኛ
እሱም በቅንነት እንዲህ ብሎ ቢፈርድ
የጥፋቴ ቅጣት በጣም እንደሚከብድ
ያውም ፅኑ እስራት የዘላለም ሆኖ
ከልብክ ቢያስገባኝ አሳስሮ አፍኖ
ይሄ መልካም ዳኛ የሚመሠገን ነው።
ነገር ግን ለምኜ አደራ የምለው
ልክ እንደ ጥፋቴ ፍርድን እንዲሠጥ ነው ገመዱ ይጠንክር እንዳይላላ አደራ
ወዴትም እንዳላይ ቀኝም ሆነ ግራ
ጠፍሮ ይሠረኝ ከልብህ ሙሶሶ
እንዳልንገዳገድ ንፋስ ከውጪ ነፍሶ
ልታሠር በልብህ እዛዉ ይሁን ቤቴም
ካንተው ጋር እንዲሆን ሞቴም ዘላለሜም፡፡
...............ሠሊና...........
@getem
@getem
@gebriel_19
ልብህን ማርኬ ብሆን ወንጀለኛ
ፍርድን ይሠጠን ዘንድ ብንሄድ ወደ ዳኛ
እሱም በቅንነት እንዲህ ብሎ ቢፈርድ
የጥፋቴ ቅጣት በጣም እንደሚከብድ
ያውም ፅኑ እስራት የዘላለም ሆኖ
ከልብክ ቢያስገባኝ አሳስሮ አፍኖ
ይሄ መልካም ዳኛ የሚመሠገን ነው።
ነገር ግን ለምኜ አደራ የምለው
ልክ እንደ ጥፋቴ ፍርድን እንዲሠጥ ነው ገመዱ ይጠንክር እንዳይላላ አደራ
ወዴትም እንዳላይ ቀኝም ሆነ ግራ
ጠፍሮ ይሠረኝ ከልብህ ሙሶሶ
እንዳልንገዳገድ ንፋስ ከውጪ ነፍሶ
ልታሠር በልብህ እዛዉ ይሁን ቤቴም
ካንተው ጋር እንዲሆን ሞቴም ዘላለሜም፡፡
...............ሠሊና...........
@getem
@getem
@gebriel_19
# ለበረከት
፧
በሰላቢ ቁና
ሰፍረውልን ቀለብ፣
ጠኔ እንዳልጠበሰን
እያረገ.....ለብ'ለብ፣
ቀን የዞረ 'ለት
እነሱም ተለኩበት፣
የባጀንበት ቀን
ቀምሰው ሊኖሩበት፣
የሰፈሩበት ቁና
ይሁን.....ለበረከት!!!
፨
# ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@kaleab_1888
፧
በሰላቢ ቁና
ሰፍረውልን ቀለብ፣
ጠኔ እንዳልጠበሰን
እያረገ.....ለብ'ለብ፣
ቀን የዞረ 'ለት
እነሱም ተለኩበት፣
የባጀንበት ቀን
ቀምሰው ሊኖሩበት፣
የሰፈሩበት ቁና
ይሁን.....ለበረከት!!!
፨
# ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@kaleab_1888
ከአደዋ ተጓዦች አንዱ....
(ገሬ ትዕዛዙ የላቀች ልጅ)
በዘመናት ማርጀት ያልጃጀውን ታሪክ፣
ስንፈትሽ እያየን ፣ ደሰ አለው ምኒልክ፡፡
ደስ አላት ጣይቱ ፣
ስልጡን ቆራጢቱ፡፡
ገመቹ እና ባንጫ ሀጎስ እና አበበ፣
የሚዘሩት ፍቅር ፣ ሀገር አጣበበ፡፡
"ማርያምን አልምርክም ፣ ወስልተክ ከቀረክ
ለነጭ ሊጥ መልክ ሁላ ፣ ሀገርክን ካስወረርክ"
ብለው እንዳወጁ ፣ ይኼውና ዛሬ
ከጫፍ ጫፍ ፣ ስንተም ስታብብ ሀገሬ
ሀገሬ አልኩ እምዬ...
እርግጥ ምን አለበት ፣ በግብሮ ብኮራ
ወትሮም የነበር ነው ፣ ልጅ በአባት ሲጠራ
በአባት መኩራት ካለ ፣ ልጆቼ እንዳያፍሩ
የተጓዝኩበትን የታሪክ አሰሳ ፣ ቅኔ ያመስጥሩ
እርግጥ ነው እምዬ ኢትዮጵያ እናታችን አንተ ያበጀሀት
በኔ ዘመን ትውልድ ቁልቁል ተገፍታለች
ልትፈርስ እየቃጣት
እነሆ ልጆቼ ...
ታሪኬን ጠይቀው ግብሬን እንዳይለኩት
በውጭ ሀገር ቋንቋ ድቅል ስላረኩት
ከወቀሳ ልድን ፣ አደዋን ደገምኩት
"ለአደዋ ጉዞ
ታሪክን ታርዞ
ፍቅር ተስፋን ይዞ...."
ታሪክ ሰራ ተብሎ ይህን እንዲፅፋት
15/06/2011 at, Ju
@kirubeltizazu
@getem
@getem
(ገሬ ትዕዛዙ የላቀች ልጅ)
በዘመናት ማርጀት ያልጃጀውን ታሪክ፣
ስንፈትሽ እያየን ፣ ደሰ አለው ምኒልክ፡፡
ደስ አላት ጣይቱ ፣
ስልጡን ቆራጢቱ፡፡
ገመቹ እና ባንጫ ሀጎስ እና አበበ፣
የሚዘሩት ፍቅር ፣ ሀገር አጣበበ፡፡
"ማርያምን አልምርክም ፣ ወስልተክ ከቀረክ
ለነጭ ሊጥ መልክ ሁላ ፣ ሀገርክን ካስወረርክ"
ብለው እንዳወጁ ፣ ይኼውና ዛሬ
ከጫፍ ጫፍ ፣ ስንተም ስታብብ ሀገሬ
ሀገሬ አልኩ እምዬ...
እርግጥ ምን አለበት ፣ በግብሮ ብኮራ
ወትሮም የነበር ነው ፣ ልጅ በአባት ሲጠራ
በአባት መኩራት ካለ ፣ ልጆቼ እንዳያፍሩ
የተጓዝኩበትን የታሪክ አሰሳ ፣ ቅኔ ያመስጥሩ
እርግጥ ነው እምዬ ኢትዮጵያ እናታችን አንተ ያበጀሀት
በኔ ዘመን ትውልድ ቁልቁል ተገፍታለች
ልትፈርስ እየቃጣት
እነሆ ልጆቼ ...
ታሪኬን ጠይቀው ግብሬን እንዳይለኩት
በውጭ ሀገር ቋንቋ ድቅል ስላረኩት
ከወቀሳ ልድን ፣ አደዋን ደገምኩት
"ለአደዋ ጉዞ
ታሪክን ታርዞ
ፍቅር ተስፋን ይዞ...."
ታሪክ ሰራ ተብሎ ይህን እንዲፅፋት
15/06/2011 at, Ju
@kirubeltizazu
@getem
@getem
🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂💛💛💛💛
አያረጅም ዘመን አልፎበት ቅን ውበቷ በእውነት ክብር የተረጋጋው ሴትነቷ!!!❤❤
ባንቺ ውስጥ ያለውን የማይታየውንና ዘላለማዊ ውበትሽን እሱን ነው ምወድልሽ.....በጊዜ ብዛት የማይከየረውን ፣ የማይረግፈውን እሱን ነው ምወደው እሱን ነው ማፈቅረው !!!! ተወዳጅዋ !!!
ሁሌም አንቺን ባሰብኩኝ ቁጥር እነዚህ ነገሮች ከልብ ምቶቻችን ባልተናነሰ እንደ ብሔራዊ መዝሙር ከነብስያችን እስከ ሙሉ አካላችን እንደ ውብ የቁርአን ቃሪ ይደጋግሙታል❤️❤️❤️
ሆድዬ ብዙ አፍቃሪዎች አሉሽ ይሁንና እኔ ደግሞ ብቻዬን አፈቅርሻለሁ !!! ሌሎች በቀረብሻቸው ቁጥር የሚያፈቅሩት ራሳቸውን ነው !!! እኔ ግን ብቸኝነትሽን አፈቅረዋለሁ !! ሌሎች ወንዶች የራሳቸውን ያህል እንኳን እድሜ የሌለውን ዉበትሽን ያያሉ እኔ ግን በጊዜ ርዝመት የማይጠፋና በእድሜ አመሻሽ ላይ ሲያዩት የማይጠፋውንና መስታወት እንደ ማያሳይሽ ያለውን የውበትሽን ማርጀት ሳይሆን ዘላለማዊ ውበትሽን አየዋለሁ ብቻዬኔም በአንቺነትሽ ውስጥ የማይታየውን እሱን
አ🎂
ፈ🎂
ቅ🎂🎂
ረ🎂
ዋ🎂
ለ🎂
ሁ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
እንኳን ተወለድሽልኝ .....🎂🎂🎂🎂
! እስከተፈቀደልሽ ጊዜ በደስታ ኑሪልኝ....ዋናው የእድሜ
መብዛቱ ማጠሩ አይደለም በኖርንበት እድሜ የሰራነው ነገር ነው....ማቱሳላ 950 አመት
ኖሮ የሚኖርበትን ድንኳን እራሱ የቀየረ አይመስለኝ ...እንደ ነብዩ መሀመድ 63 እንደ
ክርስቶስ 33 አመት ኖረው አለምን ቀይረው የሄዱ አሉና......እናም ያሰብሽው ነገር ሁሉ እሱ
ፈጣሪ ላንተ ይጠቅምሻል ብሎ የሚያስበውን ይስጥሽ..መቼ..?አሁን!!!!!!
አላህ ከሰጠኝ ጥቂት ምርጥ ሰዎች የመጀመሪያውን ደረጃ የምትይዠው አንዱ አንቺ ነሽ😘.....ጥቂቶቹ እነማን ናቸው ብለሽ ደሞ ጠይቂ አሉሽ😁.....ነው...በእድሜሽ ልክ ሻማ ባበራልሽ እጅግ በጣም ደስ ደስ ባለኝ!!ግን ሻማውን የምታጠፊው ኡፍፍፍፍፍ ብለሽ ሳይሆን
የእሳት አደጋ መኪና ጠርቼ መሆኑን ሳሰበው .....ትቼዋለሁኝል ወጪ ማብዛት ነው!!😁😂😂😂
“አንዳንድ ሰዎች ውብ ናቸው!!
በሚመስሉት ሳይሆን በሚናገሩት።
እንዲያው በማንነታቸውም ጭምር፡፡”
የኔዋ አንቺ ነሽ ❤️❤️❤️
ለእኔ ከሚለው በላይ ...ሆድዬ❤️❤️ የእኔ የልቤ ሰው ነሸ
ወዳጅነትን በመልካምነት ብቻ ስትመዝነው ልኬቱ አንቺ ነሽ
፣ ሰው ከራሱ በላይ ለሌላኛው ወዳጁ ጉዳይ በብዙ
ሲደክም አውቃለሁ ግን ሚስትየው❤️ ያንቺ ግን ከእዚህ ሚዛን ያለፈ
ነው በቃ አንድ ሰው እንደዚህ መልካም
የሆነች ሚስት❤️❤️ ካለው የጀመረውን ይጨርሳል የያዘውን
ያሳካል ፣ የወደደውን ያገኛል
የዱንያ ጀነቴ በብዙ የተሰፈረ ፍቅርሽ መልካምነትሽ
ደግነትሽን ማሰብ ደከመኝ ራሴን እንድፈልግ በእውነት
ስለ እውነት እንድቆም የነገረሽኝን ወርቃማ ምክሮች
ዛሬ ላይ ተዘርተዋል....
በሃይል ፍቅርቅር አደርግሻለሁኝ❤❤❤❤❤❤
ሆድዬ አንቺ እኮ ልዩ ነሽ❤️...ዛሬ አንቺ ብቻ ሳይሆን እኔም የተወለድኩበት ቀን ነው....ያንቺ መወለድ ለኔ ደስታ ሰጥቶኛል ያንቺ መወለድ ለኔ እስትፋንስ የመኖር ጉጉት ሰጥቶኛል.....ያንቺ መወለድ ለኔ ህይወትን ጣፋጭ አድርጓልኛል 🎂🎂😍🎂
የኔዋ😘❤️😘 መልካም ሚስት የዱንያ ጀነት ነች !! አንቺ የኔ ጀነት ❤
ሆድዬ"የፈለግሽውን ልሁንልሽ ስትፈልጊ ዛሬ ለሊት ከሰማይ ላይ ሃምሣ ኮኮብ ለቅሜ፣ጠዋት አንድ የብርሃን ጮራ እበጥስና ፣ ከብርሃን ክር በኮከብ ዶቅ ልዩ ያንገት ሀብል እሰራልሻለሁኝ። ጨረቃዋን ሰርቄ መስታወት እንድትሆንሽ እሰጥሻለው። ሰማዩ ባዶውን ይቅር!!! ጨረቃም ላንቺ ብቻ ታብራ !! ላንቺ ያልሆነ ለማን ሊሆን ይችላል ( ያውም በልደትሽ ቀን )
ሆድዬ ሆድዬ ሆድዬ
የመልአክት ምርኩዜ የለሊት መብራቴ
ስራብ እንጀራዬ ስጠማ ወተቴ
ሳዝን መፅናኛዬ ስደክም ጉልበቴ
( ፍቅር እስከ መቃብር እስታየል😊😍 )
ፍቅር የወፎች ዝማሬ እያደመጡ በአበቦች መሀል የመንሸርሸር ጉዳይ አይደለም። ፍቅር የሞራል ፍልሚያ ነው። በመሸነፍ ሚያሸንፋበት ትግል። ጠንካራ ውብ ስብዕና ያላቸው ብቻ ሚጎናፀፉት የመንፈስ ገፀ በረከት !!! እኛ የዚህ በረከት ተቋዳሽ ነን !!! በማን ..? ባንቺ መወለድ ነዋ የኔዋ ሆድዬ❤️❤️❤️አንቺ እኮ በጭንቅላቴ ውስጥ ተወሽቄ ከመኖር ታድገሽ ወደ አስደሳች የህይወት ምዕራፍ ያሸጋገርሽኝ ፍጡር ነሽ .....በመወለድሽ🎂🎂🎂
በመጨረሻም ሆድዬ .....
ጥላሁንን ሙዘቃን አፈቀረ አነገሰችው
ዳቪንቺ ስዕልን አፈቀረ ያለሱ መጠራት አቆመች
ሞዛርት ሙዚቃን አፈቀረ ያለሱ መጠራት አቆመች....ከፍ ከፍ አደረገችው
ሶቅራጠስ ፍልስፍናን ከምንም በላይ አፈቀራት እሷም መልሳ ከማንም በላይ አፈቀረችው
ሆድዬ እኔ አንቺን አፈቀርኩሽ ከፍ ከፍ አልኩኝ....ነገስኩኝ.....ይሄ እንዴት ሆነ በመወለድሽ.....ደስታ ውስጥህ ነች ይባላል አንቺ ውስጤ ነሽ እላለሁ እኔ....ስለዚህም የኔ ደስታ አንቺ እና አንቺ ነሽ እንኳንም ተወለድሽልኝ!!!!!!
አላህ ይቺን ሴት እንዳፈቅራት ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ !! አላህ የዱንያም አላህ ከሷም እንደሷ የሆኑ ልጆችን ስጠኝ ከሷም ሳሊህ ልጅ ስጠኝ የአኺራ ሚስቴ አድርግልኝ !!! አሜን !!!!❤️❤️❤️
የልደትሽ ቀን ነዉ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
እኔ ካንቺ ጋር ሆኜ ግማሹ እኔ ተኝቷል
የተኛው እኔ በህልሙ ስላንቺ ብቻ ያልማል
አልቀሰቅሰውም ይተኛ ስላንቺ ማለም ደስ ይላል
ስወድሽ ልክ የለኝም ህልሜን ራሱ አዝዘዋለሁ
ስለሷ ብቻ አልም ሌላውን ተወው እለዋለሁ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
ከሳቅ ዓለም ተለይቼ ከግርግር ከቱማታ
ከያንት ያለህ እቁብተኛ ከማያልቀው ሰልፍ ተርታ
ግንባሬን አኮሳትሬ የደበኩትን ፈገግታ
ያስቀመጥኩትን ይመስገን የቆጠብኩትን ሰላምታ
ላንቺ ይሁን ይገባሻል ሌሊት ጠዋት ቀንም ማታ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
ሁሉን ነገር ስመለከት ከደስታ ጋር ደስ ሲለኝ
ምድርን በእግሬ እየረገጥኩ አየሩ ላይ በጄ ስዋኝ
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ…
ከቁርስ ጋር ተጣልቼ ቀዝቃዛ ዉሃ እየጠጣሁ
ስወድሽ ልክ የለኝም ለዚህ ግጥም መዝጊያ አጣሁ
ስወድሽ ቃላት የለኝም ቃላት ደብዛቸው ይጠፋል
ግጥሙ ዝርዉ ይሆናል ዝርው ደግሞ ይገጥማል
እንዳሻው ይሁን ግድ የለም ልቤ ግን አንቺን ይወዳል
የልደትሽ ቀን ነዉ🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂❤️🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂
እጅግ በጣም አፈቅርሻለሁኝ❤️❤️ ይሄን የምለው ሆድዬ...ከዚህ በላይ ቃላት በተጠቀምኩኝ.....ግን ቃላት እንደኛ ስሜት መለጠጥ መስፋት በቻሉ...ለካ ቃላት ለምታፈቅሪው ሰው ልትጠቀሚበት ስትይ ደካሞች ናቸው!!! ብቻ በሃይል አፈቅርሻለሁ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሆድዬ መልካም ልደት !!!!ተወዳጇ🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂
አያረጅም ዘመን አልፎበት ቅን ውበቷ በእውነት ክብር የተረጋጋው ሴትነቷ!!!❤❤
ባንቺ ውስጥ ያለውን የማይታየውንና ዘላለማዊ ውበትሽን እሱን ነው ምወድልሽ.....በጊዜ ብዛት የማይከየረውን ፣ የማይረግፈውን እሱን ነው ምወደው እሱን ነው ማፈቅረው !!!! ተወዳጅዋ !!!
ሁሌም አንቺን ባሰብኩኝ ቁጥር እነዚህ ነገሮች ከልብ ምቶቻችን ባልተናነሰ እንደ ብሔራዊ መዝሙር ከነብስያችን እስከ ሙሉ አካላችን እንደ ውብ የቁርአን ቃሪ ይደጋግሙታል❤️❤️❤️
ሆድዬ ብዙ አፍቃሪዎች አሉሽ ይሁንና እኔ ደግሞ ብቻዬን አፈቅርሻለሁ !!! ሌሎች በቀረብሻቸው ቁጥር የሚያፈቅሩት ራሳቸውን ነው !!! እኔ ግን ብቸኝነትሽን አፈቅረዋለሁ !! ሌሎች ወንዶች የራሳቸውን ያህል እንኳን እድሜ የሌለውን ዉበትሽን ያያሉ እኔ ግን በጊዜ ርዝመት የማይጠፋና በእድሜ አመሻሽ ላይ ሲያዩት የማይጠፋውንና መስታወት እንደ ማያሳይሽ ያለውን የውበትሽን ማርጀት ሳይሆን ዘላለማዊ ውበትሽን አየዋለሁ ብቻዬኔም በአንቺነትሽ ውስጥ የማይታየውን እሱን
አ🎂
ፈ🎂
ቅ🎂🎂
ረ🎂
ዋ🎂
ለ🎂
ሁ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
እንኳን ተወለድሽልኝ .....🎂🎂🎂🎂
! እስከተፈቀደልሽ ጊዜ በደስታ ኑሪልኝ....ዋናው የእድሜ
መብዛቱ ማጠሩ አይደለም በኖርንበት እድሜ የሰራነው ነገር ነው....ማቱሳላ 950 አመት
ኖሮ የሚኖርበትን ድንኳን እራሱ የቀየረ አይመስለኝ ...እንደ ነብዩ መሀመድ 63 እንደ
ክርስቶስ 33 አመት ኖረው አለምን ቀይረው የሄዱ አሉና......እናም ያሰብሽው ነገር ሁሉ እሱ
ፈጣሪ ላንተ ይጠቅምሻል ብሎ የሚያስበውን ይስጥሽ..መቼ..?አሁን!!!!!!
አላህ ከሰጠኝ ጥቂት ምርጥ ሰዎች የመጀመሪያውን ደረጃ የምትይዠው አንዱ አንቺ ነሽ😘.....ጥቂቶቹ እነማን ናቸው ብለሽ ደሞ ጠይቂ አሉሽ😁.....ነው...በእድሜሽ ልክ ሻማ ባበራልሽ እጅግ በጣም ደስ ደስ ባለኝ!!ግን ሻማውን የምታጠፊው ኡፍፍፍፍፍ ብለሽ ሳይሆን
የእሳት አደጋ መኪና ጠርቼ መሆኑን ሳሰበው .....ትቼዋለሁኝል ወጪ ማብዛት ነው!!😁😂😂😂
“አንዳንድ ሰዎች ውብ ናቸው!!
በሚመስሉት ሳይሆን በሚናገሩት።
እንዲያው በማንነታቸውም ጭምር፡፡”
የኔዋ አንቺ ነሽ ❤️❤️❤️
ለእኔ ከሚለው በላይ ...ሆድዬ❤️❤️ የእኔ የልቤ ሰው ነሸ
ወዳጅነትን በመልካምነት ብቻ ስትመዝነው ልኬቱ አንቺ ነሽ
፣ ሰው ከራሱ በላይ ለሌላኛው ወዳጁ ጉዳይ በብዙ
ሲደክም አውቃለሁ ግን ሚስትየው❤️ ያንቺ ግን ከእዚህ ሚዛን ያለፈ
ነው በቃ አንድ ሰው እንደዚህ መልካም
የሆነች ሚስት❤️❤️ ካለው የጀመረውን ይጨርሳል የያዘውን
ያሳካል ፣ የወደደውን ያገኛል
የዱንያ ጀነቴ በብዙ የተሰፈረ ፍቅርሽ መልካምነትሽ
ደግነትሽን ማሰብ ደከመኝ ራሴን እንድፈልግ በእውነት
ስለ እውነት እንድቆም የነገረሽኝን ወርቃማ ምክሮች
ዛሬ ላይ ተዘርተዋል....
በሃይል ፍቅርቅር አደርግሻለሁኝ❤❤❤❤❤❤
ሆድዬ አንቺ እኮ ልዩ ነሽ❤️...ዛሬ አንቺ ብቻ ሳይሆን እኔም የተወለድኩበት ቀን ነው....ያንቺ መወለድ ለኔ ደስታ ሰጥቶኛል ያንቺ መወለድ ለኔ እስትፋንስ የመኖር ጉጉት ሰጥቶኛል.....ያንቺ መወለድ ለኔ ህይወትን ጣፋጭ አድርጓልኛል 🎂🎂😍🎂
የኔዋ😘❤️😘 መልካም ሚስት የዱንያ ጀነት ነች !! አንቺ የኔ ጀነት ❤
ሆድዬ"የፈለግሽውን ልሁንልሽ ስትፈልጊ ዛሬ ለሊት ከሰማይ ላይ ሃምሣ ኮኮብ ለቅሜ፣ጠዋት አንድ የብርሃን ጮራ እበጥስና ፣ ከብርሃን ክር በኮከብ ዶቅ ልዩ ያንገት ሀብል እሰራልሻለሁኝ። ጨረቃዋን ሰርቄ መስታወት እንድትሆንሽ እሰጥሻለው። ሰማዩ ባዶውን ይቅር!!! ጨረቃም ላንቺ ብቻ ታብራ !! ላንቺ ያልሆነ ለማን ሊሆን ይችላል ( ያውም በልደትሽ ቀን )
ሆድዬ ሆድዬ ሆድዬ
የመልአክት ምርኩዜ የለሊት መብራቴ
ስራብ እንጀራዬ ስጠማ ወተቴ
ሳዝን መፅናኛዬ ስደክም ጉልበቴ
( ፍቅር እስከ መቃብር እስታየል😊😍 )
ፍቅር የወፎች ዝማሬ እያደመጡ በአበቦች መሀል የመንሸርሸር ጉዳይ አይደለም። ፍቅር የሞራል ፍልሚያ ነው። በመሸነፍ ሚያሸንፋበት ትግል። ጠንካራ ውብ ስብዕና ያላቸው ብቻ ሚጎናፀፉት የመንፈስ ገፀ በረከት !!! እኛ የዚህ በረከት ተቋዳሽ ነን !!! በማን ..? ባንቺ መወለድ ነዋ የኔዋ ሆድዬ❤️❤️❤️አንቺ እኮ በጭንቅላቴ ውስጥ ተወሽቄ ከመኖር ታድገሽ ወደ አስደሳች የህይወት ምዕራፍ ያሸጋገርሽኝ ፍጡር ነሽ .....በመወለድሽ🎂🎂🎂
በመጨረሻም ሆድዬ .....
ጥላሁንን ሙዘቃን አፈቀረ አነገሰችው
ዳቪንቺ ስዕልን አፈቀረ ያለሱ መጠራት አቆመች
ሞዛርት ሙዚቃን አፈቀረ ያለሱ መጠራት አቆመች....ከፍ ከፍ አደረገችው
ሶቅራጠስ ፍልስፍናን ከምንም በላይ አፈቀራት እሷም መልሳ ከማንም በላይ አፈቀረችው
ሆድዬ እኔ አንቺን አፈቀርኩሽ ከፍ ከፍ አልኩኝ....ነገስኩኝ.....ይሄ እንዴት ሆነ በመወለድሽ.....ደስታ ውስጥህ ነች ይባላል አንቺ ውስጤ ነሽ እላለሁ እኔ....ስለዚህም የኔ ደስታ አንቺ እና አንቺ ነሽ እንኳንም ተወለድሽልኝ!!!!!!
አላህ ይቺን ሴት እንዳፈቅራት ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ !! አላህ የዱንያም አላህ ከሷም እንደሷ የሆኑ ልጆችን ስጠኝ ከሷም ሳሊህ ልጅ ስጠኝ የአኺራ ሚስቴ አድርግልኝ !!! አሜን !!!!❤️❤️❤️
የልደትሽ ቀን ነዉ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
እኔ ካንቺ ጋር ሆኜ ግማሹ እኔ ተኝቷል
የተኛው እኔ በህልሙ ስላንቺ ብቻ ያልማል
አልቀሰቅሰውም ይተኛ ስላንቺ ማለም ደስ ይላል
ስወድሽ ልክ የለኝም ህልሜን ራሱ አዝዘዋለሁ
ስለሷ ብቻ አልም ሌላውን ተወው እለዋለሁ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
ከሳቅ ዓለም ተለይቼ ከግርግር ከቱማታ
ከያንት ያለህ እቁብተኛ ከማያልቀው ሰልፍ ተርታ
ግንባሬን አኮሳትሬ የደበኩትን ፈገግታ
ያስቀመጥኩትን ይመስገን የቆጠብኩትን ሰላምታ
ላንቺ ይሁን ይገባሻል ሌሊት ጠዋት ቀንም ማታ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
ሁሉን ነገር ስመለከት ከደስታ ጋር ደስ ሲለኝ
ምድርን በእግሬ እየረገጥኩ አየሩ ላይ በጄ ስዋኝ
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ…
ከቁርስ ጋር ተጣልቼ ቀዝቃዛ ዉሃ እየጠጣሁ
ስወድሽ ልክ የለኝም ለዚህ ግጥም መዝጊያ አጣሁ
ስወድሽ ቃላት የለኝም ቃላት ደብዛቸው ይጠፋል
ግጥሙ ዝርዉ ይሆናል ዝርው ደግሞ ይገጥማል
እንዳሻው ይሁን ግድ የለም ልቤ ግን አንቺን ይወዳል
የልደትሽ ቀን ነዉ🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂❤️🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂
እጅግ በጣም አፈቅርሻለሁኝ❤️❤️ ይሄን የምለው ሆድዬ...ከዚህ በላይ ቃላት በተጠቀምኩኝ.....ግን ቃላት እንደኛ ስሜት መለጠጥ መስፋት በቻሉ...ለካ ቃላት ለምታፈቅሪው ሰው ልትጠቀሚበት ስትይ ደካሞች ናቸው!!! ብቻ በሃይል አፈቅርሻለሁ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ሆድዬ መልካም ልደት !!!!ተወዳጇ🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂
👍2❤1